Saturday, November 1, 2025

ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ጭፍጭፋ ተጠያቂው ሰው አቶ ኢብራሂም ከድር ለፍርድ መቅረብ አለበት

ግፉዓን ይትመሐፀንዋ ለመንግስተ ሰማያት 😭😭😭
ገዳይም አስገዳይም ኢብራሂም ከድር ነው
አቶ ኢብራሂም ከድር ለፍድ ይቅረብ
በመጀመሪያ በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር እንላለን 🤔
ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንመኛለን 😭
ነገሩ የትናንቱ እንደ አዲስ መሰለን እንጂ ስንቱ ነው በሰማይ በድሮን 
በታች በምድር በታንክ 
በዲሽቃ እየተጨፈጨፈ ያለው?
እየተፈናቀለ ያለው ማነው ብለን ከጠየቅን መንግሥት ነው፤
መንግሥት ሲባል ደግሞ በስም ዝርዝር 
በሻሸመኔ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ እስከ አርሲ በተደረጉት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖችን ከማጽዳት ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች ስማቸው ሲነሳ
ቆይቷል በተለይ በአሁን ሰዓት በአርሲ በተፈጸመው ጭፍጭፋ ክርስቲያኖችን የማጽዳቱን ሥራ በዋናነት ከሚመሩት ሰዎች ሥምሪት ከሚሰጡት ስዎች ግንባር ቀደሙ አቶ ኢብራሂም ከድር ዋነኛው ነው፤ 

በዚህ አካባቢ በርካታ ጊዜ ብዙ ደም ፈሷል፤ ብዙ ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል፤ ተገለዋል፣ ተሰደዋል፣ ተፈናቅለዋል ነገር ግን እስከ አሁንድ ድረስ መንግሥትም ሆነ የትኛውም አካል ችግሩ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ብዙ ሥራ መስራት አልተቻለም ወይም ጉዳዩን ማድበስበስ የተለመደ አሰራር አድርገው እንደቀጠሉ ነው፤ ከሻሸመኔው ጭፍጭፋ ባሻገር በአርሲ ብቻ እስከ ዛሬ ድረስ ከ780 በላይ ክርስቲያኖች በተለያየ እድሜ ክልል ያሉ ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋ፤ እድሜያቸው ከ39 ቀን ጨቅላ እስከ 70 ዓመት አዛውንት ድረስ ተጨፍጭፈዋል፤ ደማቸውም ደመ ክልብ ሆኖ ቀርቷል፤ ይሄንን ለማስቆምም ሆነ ችግሩ እንዲወገድ ማንኛውም የመንግሥት አካላት ኢንተርቪን የማድረግ ሥራ ለመስራት አልተቻለም፤ 

መንግሥት ግን ለምን ?❗️
ግን ለምን እንገደላለን?
ግን ለምን እንሰደዳለን?
ግን ለምን ከርስት እንነቀላለን?
ግን ለምን ከመንግስትም ሆነ ከማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት እንገለላለን?
ግን ለምን እንታሰራለን?
ግን ለምን እንጨፈጨፋለን?
ግን ለምን በእሳት እንቃጠላለን?
ግን ለምን ሐገርን ከእነ ታሪኳ ባቀና ሕዝብ 
ግን ለምን ሐገርን ከእነ ማንነቷ የደም ዋጋን እየከፈለ 
ግን ለምን ታሪክን እየከተበ ባጸና ሕዝብ 
ግን ለምን ባህልን ማንነትን ባስጠበቀ ሕዝብ ላይ ሞት ተፈረደበት?
ጠቀለል ሲል ለዚህ ሁሉ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና አማኞቿ ናቸው ፤ግን ለምን የሞትን ጽዋ ቅመሱ ተብሎ ተፈረደባቸው???❗️
ዛሬ እኮ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ስሟ እንዲታወቅ የሆነችው መከራን እየተቀበሉ ድምፀ አራዊቱን ፀብአ አጋንንቱን ተቋቁመው ድንጋይ ተንተርሰው ጤዛን እየላሱ ሲላቸውም ደግሞ እየተዋጉ ታሪኳን ማንነቷን አስከብረው በኖሩ አማኞቿ ነው።
 In The continent of African countries, the one who never colonized by Europeans is Ethiopia !!!
ብሎ አፍን ሞልቶ ለመናገር እኮ ""Who were the Parties that Played the game???"ብሎ to the beginning መጠየቅ ያሻል እኮ! ለነገሩ ተዉት ማን ይሄን ሳያውቅ ቀረና እውነትን እየቀበሩ መሆኑ ነው እንጂ ።

ኦርቶዶክሳውያን ይገባናል ግን?
 ይህ Mission የማን እንደሆነ???
ከመቼስ ጀምሮ ነው እንዲህ እየሆነ ያለው?
ለቀጣይስ ምን ታቅዶብናል (ምን ታስቦብናል)?
የእነ ማንስ እጅ አለበት?
እነማናቸው የሚገድሉንስ? የሚያሳድዱንስ?
"አይጥ ድመት ሲይዛት አማራጭ ስታጣ መጨረሻ ትፎናጨራለች" ከተባልን እኮ ሰነባበትን ስለዚህ በስልት በስልት አቅማቸውን እናዳክማቸው ፤ Then after...What? በጣም ቀላል ይሆናል ።
ከላይ የሚመራውን የሃይማኖት መሪ አባትና ከታች ያለውን ምዕመን ማጣላት፡
አንድነትን እንዳይኖረው ማድረግ፡
ተልዕኮን ለመፈፀም የሚያመችን የሃይማኖት መሪ የተባለ ግን ያልሆነን መተካት.
ወንድማማችን ማጣላት ትግራይና አማራ ብሎ ፤ምክንያቱም በወንድማማች መሃከል ሌላ ጠላት ቢነሳ ለማጥቃት የሚያመቸው በቅድሚያ ወንድማማችን ማጣላት ማለያየት ነው ፤ Then after..... what???ሁለቱንም ለብቻ ለብቻ አድርጎ ለማጥቃት It so very easy!
 
ይሄ ሴራ ከመች ጀምሮ የመጣ ነው?
ድሮም የነበረ ዓላማ ነው ፤ ግን አሁን በጣም እየተሰራበት ያለ ነው ወደ መሬት ወርዶ apply እየተደረገም ነው ፤ ውጤትም አምጥቶላቸዋል።

“ሁለት ንጹሐን ሲገደሉ አንድ ቆስሏል፣ በቅርቡ የታገቱ ሦስት ሰዎች ገንዘብ ተከፍሎም አልተለቀቁም” - ወረዳ ቤተ ክህነቱ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ የታጣቁ ኃይሎች በንጹሐን ሞትና የአካል ጉዳት ማድረሳቸውንና ጥቃቱ መደጋገሙን ወረዳ ቤተ ክህነቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገረ፡፡

በወረዳው እንዴቶ 01 ቀበሌ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም ምሽት 4 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት “ሁለት ንጹሐን ሲገደሉ አንድ ቆስሏል” ሲሉ ለደህነታቸው ሲባል ስማቸው እንደይገለጽ የጠየቁ የወረዳ ቤተ ክህነቱ አካል ነግረውናል፡፡

“በቅርቡ የታገቱ ሦስት ሰዎች ገንዘብ ተከፍሎም አልተለቀቁም” ሲሉ አክለው፣ ሦስቱ ሰዎች የታገቱት 2017 ዓ.ም ሰኔ መጨረሻ እንደሆነ፣ በነሐሴም ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ሰሞኑን ከተገደሉት መካከል አቶ ከበደ ማሞዬ አንዱ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ “ቤተ ክርስቲኒቱን ለብዙ ዓመታት በፀሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡ የሟች ጎረቤት ወይዘሮ አበሬ ስዩምንም ታጠቂዎቹ 'ቤት አመላክችን' ሲሏት 'እምቢ' ብላ ስትጮህ ነው የገደሏት፤ አብሯት የነበረ የ14 ዓመት ልጇንም መትተዋል” ነው ያሉት፡፡

“ሟቾቹ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ናቸው" ያሉት የቤተ ክህነቱ አካል፣  "በተደጋጋሚ ጊዜ ነው በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ተመሳሳይ አደጋ ሲደርስባቸው፡፡ በቅርብ ጊዜ ራሱ እንዲህ አይነት ድርጊት የተፈጸመባቸው ከአስራዎቹ በላይ ሆነዋል” ብለዋል፡፡

የገዳዮቹን ማንነት ስንጠይቃቸው፣ “የታጠቁ ኃይሎች ብለን ከመግለጽ በስተቀር ምንጩ ከየት ነው? ማነው? ለሚለው ጥያቄ ይሄ ነው ተብሎ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ከየት ነው የሚለው በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

“የተያያዙት ቦታውን ማስለቀቅ ይሁን ህዝቡን መግደል ባይገባንም ሰው የመኖር ተስፋው መንምኖ እየተፈናቀለ ነው” የሚሉት እኝሁ አካል፣ “ከእግዚአብሔር በታች መንግስት ነው ተስፋችን፣ ትኩረት አድርጎ ጥቃቱን ያስቁምልን” በማለት አሳስበዋል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች "ታጣቂዎች ከፈቱት" በሚባል ተኩስ "ንጹሐን ተገደሉ" ተብሎ በተደጋጋሚ የሚነገር ሲሆን፣ ጥቃቱ አሁንም እንልዳልቆመ ተጠቁሟል።

ኦሮሚያ ክልል ! የተፈጸሙ ግድያዎች

➡️ በኦሮሚያ ክልል በዋነኛነት በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ኦነግ ሽኔ " መካከል በሚደረገው የትጥቅ ግጭት ዓውድ ውስጥ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፥ አርሲ እና በሌሎች ዞኖች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች አሳሳቢነታቸው ቀጥሏል፡፡

➡️ ሐምሌ 26/2016 ከአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ 66 ተሳፋሪዎችን የያዘ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በፊቼ እና ገበረ ጉረቻ መሃል ሲደርስ '' ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ታጣቂ ቡድን እገታ ተፈጽሞ 2 ሰዎች ተገድለዋል፤ ቀሪዎቹን አግቶ የወሰደ ሲሆን ለእያንዳንዱ ታጋች መለቀቂያ እስከ 1 ሚሊየን ብር መክፈል እንዳለባቸው ለቤተሰባቸው በማሳሰብ ደጋግመው እየደወሉ ክፍያው በቶሎ ካልተፈጸመ ግድያ እንደሚፈጽሙባቸው ሲያስፈራሩ እንደነበር በወቅቱ ከታጋች ቤተሰቦች ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

➡️ ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፣ አቤ ዶንጎሮ ወረዳ፣ ጨሩ ቀበሌ በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የተገለጸ በተለምዶ " ፋኖ " ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ 22 ሰዎች ተገድለዋል በ4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ 540 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል እንዲሁም በግምት 800 አካባቢ ከብቶች በታጣቂ ቡድኑ ተወስደዋል።

➡️ ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፤ አርሲ ዞን፣ አስኮ ወረዳ፤ ጠለፋ ጨፋ ቀበሌ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች ወደ ቀበሌው ገብተው የቀበሌው አስተዳደር ሲቪል ሠራተኞች እና ከመንግሥት ጋ ርግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠቆሙ ነዋሪዎችን ለይተው በፈጸሙት ጥቃት 3 ሰዎችን ገድለዋል።

➡️ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ሰሜን ሽዋ ዞን፣ አቦቴ ወረዳ፣ ኤጄሬ ከተማ ነዋሪ የሆነ 1 ሰው በመንግሥት ኃይሎች ተገድሏል፡፡

➡️ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙት አመያ፣ ቀርሳ ማሊማ፣ ሰደን ሶዶ እና ቶሌ ወረዳዎች ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ኦነግ ሸኔ / ታጣቂዎች በሐምሌ እና በነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም. ብቻ 14 ሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ ስለመፈጸሙ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

➡️ ነሐሴ 19/2016 ዓ.ም. ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ የ03 ቀበሌ በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የተገለጸ " ፋኖ " ተብሎ የሚጠራው ታጣቂ በተፈጸመባቸው ጥቃት 3 ሰዎች ተገድለዋል::

➡️ መስከረም 25/2017 ዓ.ም. ቄለም ወለጋ ዞን፣ ሳጃ ወለል ወረዳ፣ የላሎ ገለታ ቀበሌ ነዋሪ 2 ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡

➡️ መስከረም 28/2017 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ኢተያ ገምባ ጀቴ፣ ኢላላ እና ጢሮ ኢላላ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች 5 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል፡፡

➡️ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሽዋ ዞን፤ አመያ ኢተያ ገምባ ጀቴ ቀበሌ የመንግሥት ኃይሎች 9 ሰዎችን ገድለዋል፡፡

➡️ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቤጊ ወረዳ፤ የኮበሬ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 1 ሰው ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ኦነግ ሸኔ "ድጋፍ አድርገሃል" በሚል በመንግሥት ኃይሎች ተገድሏል፡፡

➡️ ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቆንዳላ ወረዳ፣ የወንዲ ዶች ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 1 ሰው " ለኦሮሞ ነጻነት ስራዊት/ኦነግ ሸኔ ድጋፍ አድርገሃል" በሚል በመንግሥት ኃይሎች ተገድሏል፡፡

➡️ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በምሥራቅ ሽዋ ዞን፣ ዱግዳ ወረዳ፣ ብርቢሣ እና ጋሌ በተባሉ ቀበሌዎች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግ ሸኔ አባላት 38 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል።

➡️ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም. በምሥራቅ ሽዋ ዞን፣ ዱግዳ ወረዳ፣ መጃ ላሉ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግ ሽኔ አባላት በቀበሌው የሚኖሩ 12 ስዎችን ገድለዋል፡፡

➡️ ኅዳር 19/2017 ዓ.ም. የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ፣ ሶሌሳ ረከታ እና መከና ቀበሌዎች በፈጸሙት ጥቃት 13 ሰዎችን ገድለዋል፡፡

➡️ የካቲት 5/2017 ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ ዋላ ቀበሌ ቦሬ ከተማ አቶ ዛኪር አባኦሊ የተባሉ ሰው በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ይህንን ተከትሎ በተከሰተው ግጭት የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. 293 መኖሪያ ቤቶች፣ 11 የእህል ወፍጮዎችና 7 ትራክተሮች ተቃጥለዋል፡፡ ከቃጠሎ የተረፉ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የምግብ እህሎች እና የቀንድ ከብቶችም የተዘረፉ ሲሆን፤ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ የአማራ ብሔር ተወላጆች ወደ አጎራባች አካባቢዎች ተፈናቅለዋል፡፡

➡️ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም. በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (የፋኖ አባላት) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሽዋ ዞን ግንደበረት ወረዳ ጭረቻ ገቶ ቀበሌ በመግባት በ2 ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል፡፡

➡️ ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት / ኦነግ ሽኔ ወደ ሀሮ ወረዳ ሱጌ ቀበሌ በመግባት 10 ሰዎችን ገድለዋል፡፡ በተመሳሳይ ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ኦነግ ሽኔ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ቀበሌው ዘልቆ በመግባት 3 ሰዎችን ገድለዋል፡፡

➡️  ማንነታቸውን በውል ማወቅ ያልተቻለ የታጠቁ ኃይሎች ግንቦት 1/2017 ዓ.ም. በሰሜን ሽዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ፣ ከወረዳ ዋና ከተማ ጎሀጽዎን ልዩ ስሙ አገምሳ ተብሎ በሚታወቅ ቦታ ወደ ንጋት አካባቢ ወደ ነዋሪዎች ቤት ላይ በመተኮስ ከ8 ሰዎች በላይ ገድለዋል።

➡️ ግንቦት 9/2017 ዓ.ም. በኢሉባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ቤና ቶኮፋ እና ቤና ለመፋ በሚባሉ ቀበሌዎች የመንግሥት ኃይሎች 7 ሰዎችን ገድለዋል።

" የግፍ አገዳደል ነው የተፈጸመው ፤ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ አቃጥለውታል ፤ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች ተፈናቅሏል " - የሟች የቅርብ ሰው

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የሰባት ልጆች አባት ካህን በአሰቃቂ ሁኔታ በ "ሸኔ" በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ግድያው አሰቃቂ መሆኑን፣ ሟች ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከቤታቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ ባለቤታቸውም በተመሳሳይ ከተገደሉ አመት ከስድስት ወራት እንዳስቆጠሩ፣ የ11 ዓመት ልጃቸውም በጥይት ተመትቶ ካህኑ በጥልቅ ሀዘን አንደነበሩ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

አንድ የካህኑ የቅርብ ሰው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ፣ " ካህኑን እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ነው የገደሏቸው " ሲሉ በተሰበረ ልብ ገልጸዋል።

" አካላቸውን አፍሰን ነው ይዘን የመጣነው፤ ሰዎች በቄየው ሄደው ለቃቅመው ግማሽ አስከሬናቸው ግማሽ አካላቸው በሮቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሁድ አርፏል፤ ግማሹን ደግሞ ትላንት ለቃቅመው ነው የቀበሩት። ለመናገርም ይዘገንናል " ሲሉም አክለዋል።

" ካህኑን ' እባካችሁ ቦታውን ለቃችሁ ወደ ከተማው ኑ ብንላቸውም ' ቤተክርስቲያኑን ለቅቄ አልሄድም የሆነው ይሁን ' ብለው ሳይመጡ ቀሩ " ብለው፣ " ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያን ውለው ማታ ሲገቡ ጠላት ቀድሞ ቤታቸውን ምሽግ አድርጎ ጠብቆ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ገደላቸው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሟች ወንድም ደውሎ መከላከያ እንዲደርስ አደረገ፣ ካህኑ ግን ተገድለው ተገኙ፣ የግፍ አገዳደል ነው " ያሉት እኝሁ አካል፣ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ እንዳቃጠሉት፣ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች መፈናቀሉን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል እናት ፓርቲ በሰሞነኛው የአማራ ክልል መቃ የተፈጸመው ግድያ እና በኦሮሚያ አርሲ ስለተፈፀመው ግድያ መግለጫ አውጥቷል።

" ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ልዩ መቃ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት መንገደኛና የእርዳታ ግብአት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በደረሰ ድንገተኛ ተኩስ በርካታ ሹፌሮችና የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ከአካባቢው ምንጮች አረጋግጠናል " ያለው ፓርቲው " በአጠቃላይ በጥቃቱ አንድ መቶ በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከነዚህም ውስጥ አሥራ ስድስት የሚሆኑት ሾፌሮች መኾናቸውን ሰምተናል " ብሏል።

" ሁኔታው ከአእምሮ በላይ ነው፤ ሟቹ ከመብዛቱ የተነሳ አስከሬን በኤክስካቫተር ጭምር ሲነሳ ተመልክተናል ይላሉ እማኞች " ሲል ገልጿል። 

" በሌላ በኩል ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ካህን ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላውቸውን ከአካባቢው ምንጮች ማረጋገጥ ችለናል " ብሏል።

" ያለፉትን 7 ዓመታት ኢትዮጵያ የንጹሃን ደም ጎርፍ ሆናለች ቢባል ከእውነይ የራቀ አይደለም " ያለው ፓርቲው " በተለይ የሃይማኖት አባቶችና ሾፌሮች ግድያ የቀን ተቀን ዜና ነው " ሲል ገልጿል።

" ሞቱንም ከማለባበስ በዘለለ ከእቁብም የሚቆጥረው የለም። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዓይነት ተቋማት እንኳን በየቀኑ የሚፈሰውን የካህናትና ቤተሰባቸውን ደም ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ድምጽ አያሰሙም " ሲል ወቅሷል።

" ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም የየቀኑ መረጃ ጠረጴዛው ላይ ደርሶት እያየ እንዳላየ ሆኗል። ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይሄ ጉዳያቸው አይደለም " ሲል ገልጿል።

" ከተወሰኑ የማኅበራዊ ሚዲያ  ተሳታፊዎች በስተቀር አጠቃላይ ሚዲያው በፍርኃት ተሸብቦ እማኝ አናግሮ ማቅረብ ዳገት ሆኖበታል፡፡ የንጹሓን ደም ግን አሁንም በየቀኑ ይጣራል" ብሏል።

ፓርቲው " ጭፍጨፋውን በጽኑ እናወግዛለን ለሞቱት እረፍተ ነፍስን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ለየአካባቢዎቹ ማኅበረሰብ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን " ሲል ገልጿል።

" ተክሰናል ፤ ሕዝቡ በልዩ ልዩ መንገዶች ደስታዉን እየገለፀ ነዉ " - የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ

ዛሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ " የኢትዮጵያ ዋንጫን " ለወላይታ ዲቻ ይመልሳል ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድንም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ #ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል።

ይህን የፌደሬሽኑን ዉሳኔ ተከትሎ የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች በአደባባይ ደስታቸዉን የገለፁ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላላ ከበደን ጨምሮ የክልሉና የወላይታ ዞን አመራሮች " የእንኳን ደስ ያላችሁ " መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገርናቸው የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ " ዉሳኔዉ በእግር ኳሱ ዘርፍ ተስፋ ሰጪና ለወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ትልቅ ደስታን የፈጠረ ተገቢ ዉሳኔ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ተክሰናል " ያሉት ስራ አስኪያጁ " የዉሳኔዉን አፈጻጸም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በሚያስቀሚጠዉ ዕቅድ መሰረት ተፈፃሚ እናደርጋለን " ብለዋል።

ለ2 ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ 5 የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የፋብሪካው ኃላፊ ተናገሩ።

እኚሁ ኃላፊ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።

" አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው " ብለዋል።

ከተገደሉት መካከል 3ቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ዛሬ ተፈፅሟል።

ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ቀብሩ ዛሬ የተፈፀመ ሲሆን ሌላኛው ከደሴ የመጣው ግለሰብ አስከሬን ወደ ስፍራው ተልኳል ተብሏል።

4ቱ ሠራተኞች በፋብሪካው ውስጥ በትራክተር ኦፕሬተርነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እንደሆኑም ተገልጿል።

ሌላኛው የኤሌክትሪክ ሠራተኛ (ፎርማን) ወጣት ሲሆን በቅርብ የተቀጠረ እና ለአንድ ዓመት ያህል በፋብሪካው አገልግሏል።

አንደ ኃላፊው ገለጻ ከሆነ ግለሰቦቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የአዳር ስር ላይ ምሽቱን አሳልፈው ጥዋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን " ዶዶታ " ከሚባለው ፋብሪካው ከሚገኝበት ስፍራ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል።

ሠራተኞቹን ያገቷቸው ሰዎች ገንዘብ ጠይቀው እንደነበር ? ወይም የጠየቋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ዝርዝሩን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ነገር ግን ፋብሪካው ከአጋቾቹ በኩል ምንም ነገር እንዳልተጠየቀ ገልጸው፣ ወዲያውኑ ለመንግሥት አካል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

ፓሊስም ሠራተኞቹን ለማስለቀቅ እየተከታታለ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው ነገር ግን አስከሬናቸው ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት አካባቢ ተገኝቷል ብለዋል።

ስለ ግድያው እንዴት ? እና ስንት ሰዓት ? ተፈጸመ የሚለውን ባያውቁም ምናልባትም ትናንት ምሽት ተገድለዋል ብለው እንደሚጠረጥሩ የተናገሩት ኃላፊው ሰራተኞቹ መገደላቸውን ሰምተው ወደ አካበቢው ሲሄዱ አስከሬናቸውን አግኝተናል ብለዋል።

በፋብሪካው እንዲህ እገታ ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑን እና እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበርም አስረድተዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

" የግፍ አገዳደል ነው የተፈጸመው ፤ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ አቃጥለውታል ፤ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች ተፈናቅሏል " - የሟች የቅርብ ሰው

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የሰባት ልጆች አባት ካህን በአሰቃቂ ሁኔታ በ "ሸኔ" በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ግድያው አሰቃቂ መሆኑን፣ ሟች ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከቤታቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ ባለቤታቸውም በተመሳሳይ ከተገደሉ አመት ከስድስት ወራት እንዳስቆጠሩ፣ የ11 ዓመት ልጃቸውም በጥይት ተመትቶ ካህኑ በጥልቅ ሀዘን አንደነበሩ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

አንድ የካህኑ የቅርብ ሰው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲናገሩ፣ " ካህኑን እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ነው የገደሏቸው " ሲሉ በተሰበረ ልብ ገልጸዋል።

" አካላቸውን አፍሰን ነው ይዘን የመጣነው፤ ሰዎች በቄየው ሄደው ለቃቅመው ግማሽ አስከሬናቸው ግማሽ አካላቸው በሮቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እሁድ አርፏል፤ ግማሹን ደግሞ ትላንት ለቃቅመው ነው የቀበሩት። ለመናገርም ይዘገንናል " ሲሉም አክለዋል።

" ካህኑን ' እባካችሁ ቦታውን ለቃችሁ ወደ ከተማው ኑ ብንላቸውም ' ቤተክርስቲያኑን ለቅቄ አልሄድም የሆነው ይሁን ' ብለው ሳይመጡ ቀሩ " ብለው፣ " ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ቤተ ክርስቲያን ውለው ማታ ሲገቡ ጠላት ቀድሞ ቤታቸውን ምሽግ አድርጎ ጠብቆ ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ ገደላቸው " ሲሉም ተናግረዋል።

" የሟች ወንድም ደውሎ መከላከያ እንዲደርስ አደረገ፣ ካህኑ ግን ተገድለው ተገኙ፣ የግፍ አገዳደል ነው " ያሉት እኝሁ አካል፣ የሟቹን ወንድም ቤትም ታጣቂዎቹ እንዳቃጠሉት፣ የአካባቢው ነዋሪም ወደ አጎራባች ቦታዎች መፈናቀሉን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል እናት ፓርቲ በሰሞነኛው የአማራ ክልል መቃ የተፈጸመው ግድያ እና በኦሮሚያ አርሲ ስለተፈፀመው ግድያ መግለጫ አውጥቷል።

" ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ዞን ልዩ መቃ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች መካከል በተነሳ ግጭት መንገደኛና የእርዳታ ግብአት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ላይ በደረሰ ድንገተኛ ተኩስ በርካታ ሹፌሮችና የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ከአካባቢው ምንጮች አረጋግጠናል " ያለው ፓርቲው " በአጠቃላይ በጥቃቱ አንድ መቶ በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከነዚህም ውስጥ አሥራ ስድስት የሚሆኑት ሾፌሮች መኾናቸውን ሰምተናል " ብሏል።

" ሁኔታው ከአእምሮ በላይ ነው፤ ሟቹ ከመብዛቱ የተነሳ አስከሬን በኤክስካቫተር ጭምር ሲነሳ ተመልክተናል ይላሉ እማኞች " ሲል ገልጿል። 

" በሌላ በኩል ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት የገደብሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ካህን ቀሲስ ተስፋዬ ረታ ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላውቸውን ከአካባቢው ምንጮች ማረጋገጥ ችለናል " ብሏል።

" ያለፉትን 7 ዓመታት ኢትዮጵያ የንጹሃን ደም ጎርፍ ሆናለች ቢባል ከእውነይ የራቀ አይደለም " ያለው ፓርቲው " በተለይ የሃይማኖት አባቶችና ሾፌሮች ግድያ የቀን ተቀን ዜና ነው " ሲል ገልጿል።

" ሞቱንም ከማለባበስ በዘለለ ከእቁብም የሚቆጥረው የለም። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዓይነት ተቋማት እንኳን በየቀኑ የሚፈሰውን የካህናትና ቤተሰባቸውን ደም ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ድምጽ አያሰሙም " ሲል ወቅሷል።

" ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም የየቀኑ መረጃ ጠረጴዛው ላይ ደርሶት እያየ እንዳላየ ሆኗል። ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይሄ ጉዳያቸው አይደለም " ሲል ገልጿል።

" ከተወሰኑ የማኅበራዊ ሚዲያ  ተሳታፊዎች በስተቀር አጠቃላይ ሚዲያው በፍርኃት ተሸብቦ እማኝ አናግሮ ማቅረብ ዳገት ሆኖበታል፡፡ የንጹሓን ደም ግን አሁንም በየቀኑ ይጣራል" ብሏል።

ፓርቲው " ጭፍጨፋውን በጽኑ እናወግዛለን ለሞቱት እረፍተ ነፍስን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ለየአካባቢዎቹ ማኅበረሰብ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን " ሲል ገልጿል።

#ሺርካ

✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል 

✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ)

✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ)

✦ " እኛ ንፁሃን ላይ ጥቃት አላደረስንም " - የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ለቪኦኤ)

✦ " ባለሞያ መድበን ምርመራ ጀምረናል " - ኢሰመኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ፤ ሺርካ ወረዳ ፤ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሐን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸውን እና የዐይን እማኞችና መልክታቸውን ያደረሱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ #የአካባቢው ነዋሪ የቤተሰባችን አባል በላኩልን መልዕክት ፤ " ህዳር 13 /2016 በግምት ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ እና በታጠቁ ኢ - መደበኛ ሀይሎች በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ ጉና እና ጢጆ ለቡ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ 39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በተመሳሳይ ሰዓት በተፈፀመ በሌላኛው ጥቃት ደግሞ 11 በድምሩ 28 ሰው ሲልፍ ሁለት ህፃናት ደግሞ ቆስለው ህክምና ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል። 

ቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ሐሙስ ህዳር 13 እና ሰኞ ህዳር 17 ቀን በተፈጸመ ጥቃት #36_ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል። 

ከሟቾቹ ገሚሶቹ የሁለት ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በዘገባው ጠቅሷል።

ቃላቸውን የሰጡ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ ፤ " ህዳር 13 ለ 14 አጥቢያ ለቡ በተባለው ቀበሌ ላይ 11 ሰው አንድ ላይ ሰብስበው እነዚህ ታጣቂዎች አንድ ላይ ረሽነዋል። ሶሌ ዲገሉ በተባለው ቀበሌ ደሞ 17 ሰው አስሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ሰብስበው ረሽነዋል። እነዚህ 17ዱ በአንድ ጉድጓድ 11ቱ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የዚህን ሀዘን ሳንጨርስ እንደገና በሦስተኛው ቀን ለቡ በተባለው ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላት 8 ሰዎች ረሽነዋል። እነዚህም በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ነዋሪው አክለው፤ " ከእነዚህ ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር  እናቶች ይገኙበታል" ያሉ ሲሆን " የሦስቱ ቦታ ጥቃቶች በተመሳይ መልኩ ቤት እየገቡ አንድ ቦታ ያሉ ሰዎችን መረሸን ነው። ህጻን የለም አዋቂ የለም ገብተው መረሸን ነው። የአማርኛ ስም ያላቸው፣ የአማራ ስም ያላቸውና የኦርቶዶክስ እምነት አማኝ ላይ ያተኮረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። 

ጥቃቱን ማን እንደፈጸመ የተጠየቁት ነዋሪው " ምንም የሚታወቅ ነገር የለም የታጠቁ ኃይሎች ናቸው እከሌ ልንላቸው አንችልም። " ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ለጥቃቱ መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ አድርገዋል። 

ኃላፊው ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ " በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ፤ ጢጆ ለቡ፤ ሲላ ዋጂ አሸባሪው ሸኔ ንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽሟል። ከ2 ዓመት ህጻንን እስከ አቅመ ደካማ ሴቶችን ላይ አነጣጥሮ እኔ ባለኝ መረጃ የ27 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብለዋል።

አክለውም " ይኼ አሸባሪ ቡድን ባሳለፍነው ሳምንት ቡኖ በደሌ ጨዋቃ ወረዳ ላይ በኢትዮጵያ የጸጥታ አካል በተወሰደበት እርምጃ ብዙ ኃይሉ ሙትና ቁስለጫ በመሆኑ ይሄንን ለመበቀል ብሎ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ይሄንን ጥቃት ፈጽሟል።" ሲሉ ከሰዋል።

በመንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የተባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ታርቢ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ክፍል በሰጡት ምላሽ ውንጀላውን #አስተባብለዋል፡፡

" እኛ ኃይላችን በተባለው አከባቢ #በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው እርምጃ፤ ያጠፋው የሰላማዊ ሰዎች ህይወትም የለም። ከህዳር 14 - 17 ድረስ በሥርዓቱ ኃይል ብዙ ሰው ተገሏል፤ ብዙ ቤትም ተቃጥሏል። ይህም በምስራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ነው የተፈጸመው አዛውንቶችም ተገለዋል። ይህንን ለማድበስበስ ነው ጣታቸውን በእኛ ላይ የሚጠቁሙት " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ግን ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ሲሉ ገልጸውታል።

አስተያየታቸውን የሰጡን የቲክቫህ ቤተሰቦች ፤ " እዚሁ ወረዳ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ግድያ እንደነበረ ቢታወቅም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ታጣቂዎች ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ስለነበር ይህ ሁሉ ሰው ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። የአካባቢው ህዝብም በአካባቢው ለመኖር ዋስትና ስለሌለው አካባቢውን ለቆ ለስደት እየተዳረገ ነው፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ፤ ምሥራቅ አርሲ ዞን ፤ ሽርካ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የኮሚሽኑ የክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል ሲኒየር ዳይሬክተር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር)፣ " መረጃ ደርሶናል እያየነው ነው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

" አሁን ላይ በዝርዝር የምናገረው ነገር የለም። ነገር ግን እኛ ጉዳዮች እንደዚህ በሚደርሱን ሰዓት ጉዳዩን የሚከታተል ባለሙያ እንመድባለን፣ በዚህም ምርመራ እናደርጋለን። ያ ነገር የተጀመረ መሆኑን ነው መናገር የምችለው " ሲሉ ገልጸውልናል።

በአርሲ የደም ምድር እየሆነች ነው፤ 

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment