Monday, November 10, 2025

"ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው አልተገደሉም" የሚለው የነቀሲስ ታጋይ ታደለ መግለጫ የኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንዲቀጥል የተፈቀደበት ደብዳቤ አድርጌ ወስጄያለሁ።

መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ (ግብረ በላው ካህን)

እግዚኦ ለዳኝነት ፤ እነዚህ ካህን ተብለው ነው በምሥራቅ አርሲ ስንት ካህናት አንገታቸው ሲቀላ፣ ከሁለት ዓመት ሕጻን እስከ 70 ዓመት አረጋዊ አባት በአጠቃላይ ወደ 170 የሚጠጉ ክርስቲያኖች የተጨፈጨፉት "ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው ግድያ ነው" አንተም ካህን ትባላለህ፤ እውን ካህን ለመሆኑም በእጅጉ ያጠራጥራል? እረ እንደው ምን ያክል ቢከፍሉህ ነው በእነዚያ ምስኪን ክርስቲያኖች ደም ላይ የተዘባበትከው? እውነት አንተም የንሰሃ ልጆች አሉህ? ቀድሰህ ታቆርባለህ? እግዚኦ ለዳኝነት!!!!! 

ያኛው ቀሲስ ታጋይ የሚባለው አንዴ ለይቶለታል፤ ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለበሰችውን እንኳን ካባ ጥሎ እንደ ፕሮቴስታንታዊውያኑ ሱፍ በከረባት ነው የሚለብሰው፤ ካቶሊክ አይሉት ወይም ሞርመን አይታወቅም፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ሰውዬ እዚህ ቦታ ላይ እንዲነሳ ለምን አታደርግም? በቤተክርስቲያን በጀት ነው በቤተክርስቲያን ላይ ብዙ መከራ እና እንግልት እንዲደርስ እንዲጨምር የሚያደርጉ ቄስ ዳዊት እና ቄስ ታጋይ በኅይማኖት ተቋማት በኩል በመሆን የሙስሊም እና የፕሮቴስታንቶችን አጀንዳ የሚሰሩ መሰሪዎች ቢባሉ ትክክል ነን፤ ቢያንስ ይሄንን ሪፖርት ሲያወጡ በተለያየ ቦታ በሞት እና በሕይወት ሆነው የሚገኙትን ክርስቲያኖች አነጋገረው ቢዘግቡ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ቀድሞውንም ለታዘዙበት እና ለበሉበት እንጂ ለሌላው ግድ እንደሌላቸው በትክክል ያሳዩበት ይሄ ሪፖርት ነው፤ እግዚኦ ለዳኝነት፤ 
እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጣችሁ፤ በቤተ ክርስቲያን እና በሕዝብ ላይ እንደተዘባበታችሁ ፍርዱን አግኙት በእናንተ ላይ የሚመጣው ወደ ቤተሰቦቻችሁ አይተላለፍ፤ በራሳችሁ ይድረስባችሁ ለሆዳችሁ እንዳደራችሁ ሆዳቹ የተራበ የተጠማ የከርሳችሁ አይሙላ፤ፍርዱን ያግኙት በአርቡ 
** የክርስቲያኖችን ፍጅት "ተራ ሞት" አደረጋችሁት።  
** የተጨፈጨፉ ክርስቲያኖች፣ ቁስላቸው ገና ያልጠገገ ቁስለኞች፣ የለፉበት ሰብላቸው አሁን በዚህ ሰዓት እየተዘረፈ ያሉ ገበሬዎች፣ ከሴቶችና ሕጻናት ጋራ ወደ ከተማ የተሰደዱ አማኞች ዕንባቸው አርሲን እያጠበ "በሃይማኖቱ ተለይቶ አደጋ የደረሰበት የለም" አላችሁት።
** በነዚህ ዓመታት እንኳን የፈረሰ መስኪድ፣ ጫፉ የተነካ የሙስሊም ንብረት አለ?
** በየቦታው የሚገነቡት የእምነት ቤቶች የነማን ናቸው? የተዘጋውና ጽላቱ ወደ ከተማ የተሰበሰበው የማን ቤተ እምነት ነው?
** በዚህ ወቅት ከቤቱ የተፈናቀለ የሌላ እምነት ተከታይ አግኝታችኋል?
** ከተማ ከተማውን ከመጓዝ ባሻገር፣ አባ ገዳዎችን፣ ሃዸ ሲንቄዎችን ከማናገር ባሻገር የራሳችንን ካህናትና ምዕመናን ለብቻ አግኝታችኋል? ሰይፍ አንገታቸው ላይ የተሳለ ወገኖች ያለ ፍርሃት እንዲናገሩ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል?
** በዚህ የጥድፊያ "ምርመራ" ኦርቶዶክሱን በሃይማኖትህ ምክንያት አልምትህም ብለን ደሙን ደመ ከንቱ ፣ ሞቱን ሞተ ከለባት ማድረጋችን ሳያንስ ለወደፈቱም ጩኸቱ እንዳይሰማ አፉን ዘግተን አልተመለስንም?
** ምነው ምነው መልአከ ሰላም? የሰማዕታቱ ደም እንደ አቤል ደም ይጣራል፣ ይጮኻል።
=====
** "በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም? አሉ።" (ራእይ 6፥10)


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment