Thursday, November 20, 2025

በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ውሃቢያ እና ጂሃዲስት ምን ላይ እንዳሉ ያየም የሰማም የለም


ዛሬ ዛሬ በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለው መንግሥትም ሆነ ሕዝቡ በጣም ያልተገነዘበው አንድ ትልቅ አደጋ ለሃገራችንም፣ ለሕዝባችንም ብሎም ለቀጠናው ከፍተኛ የሆነ አደጋ የጋረጠ ነገር ቀስ በቀስ እግር አውጥቶ እየተንሰራፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ ከሁሉም በላይ በሃላፊነት ስሜን የሕዝቦችን ደህንነት እና ሁኔታ መጠበቅ ማስጠበቅ፤ የሕግ የበላይነትን ማስፈን ያለበት መንግሥት ቢሆንም ያንን ሥራውን ለሌሎች አሳልፎ የሰጠበት እና ዋናውን ሥራውን ትቶ ብዙ በማይመለከተው እና ባልበላው ቦታ ላይ ገብቶ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያጫርስ እና እራሱም መሣሪያ ሆኖ አንድን ማኅበረሰብ ለመጨረስ ወይም ቁጥር ለመቀነስ በሚል ብዙ ድካም ሲደክም እና ነገሮችም ሳይሳኩለት እየታየ ነው፤ ከመንግሥትም አካላት ተው የሚለውም ያለ አይመስልም፤ ለነገሩ ብዙዎቹም የመንግሥት አካላት አብረው ተከትለው እንደ ነፋስ መንፈስ እንጂ ቆም ብሎ የሚያስብ የሚያመዛዝን የጠፋበት ዘመን ነው፤ ብዙዎቹ ገና ሙቀት ላይ ናቸው የተለየ የሚንፈላሰስበት መኪና አለው፣ መንግሥት የሚሰጠው የመኖሪያ ቤት አለው፣ ወጪውንም በሙሰኝነት የለመደው ስለሆነ ኑሮውም አይሰማውም፣ ምቾት ላይ ነው ብዙው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉት ሰዎች ከሆኑ ሰዎች እንበላቸው እና፤ ሰዎች ከሆኑ ማለት ነው፤ ብዙዎች እየሆነ ያለውን አያስተውሉም፤ "እኔ ከሞላልኝ፤ . . ." በሚል ብሂል ይመስላል ብዙም አይመለከታቸውም፤ እንደ ኢትዮጵያ የሰው ልጅ በየቀኑ እንደ በግ የሚታረድበት ሃገር ያለ እስከማይመስል ድረስ ዛሬ ዛሬ እማ አምስት አሥር ሰው ሲታረድ ወይም ሲገደል ብዙም ቦታ ሰጥቶ የሚያይ ሰው የለም፤ መንግሥትም የመንግሥትም ሰዎች ብዙም አይመለከታቸውም እስከ መቼ ይሆን?

ነገር ግን ዛሬ ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ገንግኖ እጅክ ከፍተኛ እልቂት እያደረሰ ያለው፤ ነገር ግን ኦርቶዶክሳውያን ላይ ስለሆነ ብዙዎቹ አይመለከታቸውም ፕሮቴስታንቱ አይናገርም አይመለከተውም፤ ሙስሊሙ አይናገርም አይመለከተውም አንዳንዴም ጩኸቴን ቀሙኝ በሚል ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ ፤ "አንዳንድ ሙስሊሞችም አብረው ተገለዋል" በማለት በለበጣ መልኩ መግለጫ ከመጅሊሱ ሲወጣም ተመልክተናል፤ ካቶሊኩም አይናገርም አይመለከተውም፣ ዋቄ ፈታው፣ ጆሃቫው፣ ሌሌውም ማንም አይመለከተውም ምክንያቱም በኢትዮጵያ 60% በላይ የሚሆነው የኦርቶዶክስ አማኝ በመሆኑ የእነሱ ጉዳይ አይደለም፤ አይመለከታቸውም፤ ነገሩ ግን ወዲህ ነው እየመጣ ያለው አደጋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን መላውንም የሃገራችንን እና የቀጠናውን የምሥራቅ አፍሪቃን ቀጠና አደጋ ላይ የሚጥል የወሃቢያ እና ጂሃዲስት አደረጃጀት ነው፤ ከላይ በሚታየው ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው ይሄ አደረጃጀት በኢትዮጵያ ሲደራጅ፣ ሲታጠቅ እና የጦር ካምፕ ከፍቶ ሥልጠና ሲያደርግ የሚመለከተውም ክፍል ምንም አያደርግም፣ ማንም ሰላም ወዳድ ሃይሎችም አይናገሩም ምክንያቱም ዛሬ ላይ ኦርዶኮክሳውያን ላይ ያነሱት ሰይፍ ነገ እያንዳንዱን እንደሚነካ እና አደጋ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፤ በቪዲዮው ላይ እንደምናየው ዋናው አስተባባሪ "ሼህ" ተብየው ሲናገር እንደሰማነው "በሃገራችን ኢስላማዊ ኢትዮጵያ ውስጥ፤ እስላማዊ ሸሪያ እስከምንመሰርት ድረስ" በማለት ይናገራል፤ ስለዚህ ነገ በዚህ ከቀጠለ ማንም ይሁን ማን በመንግሥት ውስጥም ያለህ ይሁን የፕሮቴስታንት ጉልት ለራስህ ስትል ብትነቃ የተሻለ ይመስለናል፤ በዚህ ከቀጠለ በምሥራቅ አፍሪቃ ከነ አልሻባብ፣ ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራም፣ ከአፍጋኒስታኑ ታሊባን፣ ከታይላንዱ ታሚል ታይገር እንዲሁም ከአለም አቀፎቹ አሸባሪዎች አልቃይዳ እና አይሲስ ከሚባሉት አሸባሪዎች ጋር የሚስተካከል ሃይል እየገነባ እንዳለ መመልከት ይቻላል።

ዛሬ የሚመከከታቸው የምንግሥት አካላትም፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የእመነት ተቋማት እንዲሁም መላው ሰላም ወዳድ በሙሉ ሊያወግዘው እና አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደበት ሃገራችን ኢትዮጵያ የደም ምድር መሆኗ የማይቀር ሃቅ ነው፤ በዚያ ጊዜ ደግሞ እንደ አሁኑ ኦሮሞ፣ ትግራይ ወይም ጉራጌ አማራ፣ ከንባታ ጌዶ በሚል ሳይሆን ማንኛውንም የክርስቲያን እሴት የያዘውን እሙሉ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በመግደል ሴቶችን ለአስገዳጅ ጋብቻ እና ብዙ እስላማዊያንን እንዲወልዱ አስገድደው በመድፈር የእስላማዊ ሴክስ ስሌቭ እንደሚያደርጓቸው በብዙ ሃገሮች የታየ ነገር ነው፤ የእኛም ሃገር ከሌሎች የተለየ አይደልም እና ይሄንኑ እንደሚፈጽሙት የሚታወቅ ነው፤ 

ስለዚህ ለራስህ ብለህ ዛሬ ላይ በኦሮዶክሳውያን ደም የምትሳለቅ በሙሉ በተለይ ፕሮቴስታንት የሆናችሁ የሰላም ወዳድ ሃይሎች እንደምትኖሩ እናምናለን፤ ይሄንን ክፉ እና አረመኔ አራዊት ከሃገራችን ተባብረን ማጥፋት ካልቻልን ነገር እንደ ሶሪያ እና እንደ ሊቢያ የእስላማዊ ክንፎች እርስ በእርሳቸው እየተጋደሉ የምንኖርባት የምድር ሲዖል ከመሆኗ በፊት እያንዳንዱ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዓይኑን ሊገልጥ እና አብዝቶ ሊሰራበት የሚገባው እውነታ እና ታሪካዊ ግዴታ ነው፤ አለበለዚያ ግን ነግ በኔ የሚለውን ብሂል ሳይውል ሳያድር እናየዋለን፤ እንሰማለንም፤ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ዓይን ያለው ይመርምር ነው እና ከዚህ በላይ ብዙ ማለት ባይቻልም ግን ዓይን አይቶ ልብ ይፍረድ በማለት ጽሁፋችንን እናጠቃልላለን። 
ቸር ያቆየን 

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment