Wednesday, November 5, 2025

• ደግሜ ልንገርህ ስማኝማ…!

Jihadis Threat in Ethiopia
"…የትዊተር ዘመቻው ጥሩ ነው። ዓለም ሕዝብ ሆይ እኛ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በጽንፈኛ የወሀቢይ እስላሞች 
መገደላችንን፣ መታረዳችንን፣ መፈናቀላችንን ዕወቁልን ብሎ በተገኘው አጋጣሚ ሁላ መጮሁ፣ ማመልከቱ፣ ምስክር መጥራቱ ጥሩ ነው አልነቅፈውም። በርቱ ነው የምለው።

"…ነገር ግን የገጠመን ጠላት የትዊተር ዘመቻ አያስደነግጠውም። አያስፈራውም፣ መቶ ሺ መግለጫም አያስደነብረውም። ሚልዮን ሆነህ ሰልፍ ብትወጣ እሱ ደንታው አይደለም። 

"…አራጁ ወሀቢያ መንግሥት ሆኗል። የሚደገፈው አንተ ስሙን፣ ድረሱልን በምትላቸው ኃያላን ጭምር ነው። እነርሱ ራሳቸው ስጋት ላይ ናቸው። ጣልያን ሰሞኑን ኢማሙን ከሀገራ ያባረረችው እዚያው ጣልያን ሆኖ ጅሀድ ስላወጀባት ነው። እንግሊዝ ተበብራለች፣ አሜሪካ ኒውዮርክ እየሆነ ያለውን መታዘብ ነው። 

"…ነገርኩህ መጽሐፍ ቅዱስም የሚለው "ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" መዝ 68፥ 31 እንጂ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ አሜሪካ፣ አውሮጳና፣ ራሺያ፣ ቱርክና ቻይና አይልም። ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከውስጥ የተነሣን አራጅም ሆነ ከውጭ የመጣባትን ወራሪ ያደባየችው እጆቿን ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ነው። ዓድዋ እንዴት እንደዘመተች፣ ማንን ይዛ እንደዘመተችም ጠይቅ።

"…እነሱ በሰፊው እየተዘጋጁ ነው። እኛ በሰፊው እያወራን፣ እየተንዶቆዶቅን ነው። እነሱ እንደ ሕፃን በሆነው፣ ባልሆነው እሪሪ ኡኡ ብለው እየጮሁ ወሳኙን ሥልጣን ሁላ ተቆጣጥረው ይዘውታል። ባንኩም ታንኩም በእነርሱ እጅ ነው። 

"…የሀገሪቱ መሪ የአፍ ጴንጤ የልብ የወሀቢይ እስላም ነው። የሀገሪቱ የደህንነት ሚንስትር የስልጤ ወሀቢይ ነው። እነሱ መረጃ አላቸው። ገንዘብ አላቸው። ወታደር፣ ፖሊስ ማዘዝ ይችላሉ። ፍርድቤቱም በእጃቸው ነው። ታንኩንና ባንኩን የሚያዝዝ ኃይል አላቸው። 

"…ዝም ብለው በአንድ ጀንበር ከዚህ አልደረሱም። መሬት ረግጠው ሠርተው፣ ለፍተው ነው። የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜም ዕቅድ አውጥተው ነው። ነገርኩህ በቴሌግራም ጦማር፣ በቲክቶክ ውይይት፣ በትዊተር ዘመቻ አታስቆማቸውም። አታስቆማቸውም አልኩህ አለቀ። 

"…በአንድ ሀገር ውስጥ ኖረህ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ከተሰጠህ፣ ሞትህ፣ መታረድህ፣ መገደል መፈናቀልህ የሚያስደነግጠው መንግሥት ካለ፣ ጥበቃ፣ ከለላ የማይሰጥህ መንግሥት ካለ መፍትሄው አንተው ራስህን አደራጅተህ መንግሥት ለመሆን መፋለም ነው። አለቀ።

"…አንዳንዶች እንዴት እንደራጅ? እንዴት እንታገል? እንዴት እንሰባሰብ? እንዴት? እንዴት? እንዴት የሚል ጥያቄ ያበዛሉ። መልሴ ግን ቀላልና ግልጽ ነው። እንጃባክ? ምናአባክ ዐውቅልሃለሁ። ሲርብህ፣ ሲጠማህ እንዴት ነው የሆድህን ረሃብ የምታስታግሰው? ገዳይህ ሲፎክርብህ እንዴት ነው ከገዳይህ እጅ ላለመውደቅ የምትላላጠው? በሕይወት ለመቆየትና ለመኖር እንዴት ነው የምትደክመው? የምትለፋው? እንጃባክ አልኩህ? ደግሞ እሱንም በአደባባይ እንዲህና እንዲያ ሆነህ ተደራጅ እንድትባል ትፈልጋለህ እንዴ?

"…እንጃባክ አልኩህ። መሬቱ አለ አይደል? መረሻ ወገል፣ ሞፈር ቀንበር፣ በሬም ምርጥ ዘርም አለህ አይደል? ምን ላድርገው በለኝ አሉህ? እንጃባህ? ምንአባህ ዐውቄልህ? ታረሰ፣ ተዘራ፣ ታረመ፣ ተወቃ፣ ጎተራ ገባ፣ ተፈጨ፣ ተቦከ፣ ተጋግሮ ቀረበልህ አይደል? እና እንዴት ላድርገው፣ እንዴት ልብላው ነው ያልከኝ? እንጃባህ? ምንአባክ ዐውቅልሃለሁ። 

"…አንት ሽንታም፣ ቦቅቧቃ ደግሞ ናና ኃጢአታችን በዝቶ፣ ንስሀ እንግባ በለኝ አሉህ። ማንአባህ ንስሀ እንዳትገባ ከለከለህ? ራስህን ቻል? ለፍርሃትህ፣ ለቦቁባቃነትህ፣ ለሽንታምነትህ፣ ለበጭባጫነትህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አትፈልግልኝ። በእግዚአብሔር ስም ፍርሃትህን አትሸሽገው፣ የጦስ ዶሮ አትፈልግ። ንስሀ ግባ ማንአባህ ከለከለህ? ምንኢላል ይሄ። 

"…ወሬም፣ ሰበር ዜናም አያድንህም። ስትሞትም አትበዛም ቁርጥህን ዕወቅ። እሱ አራት ሚስት አግብቶ አርባ ልጅ እየወለደ፣ እየተራባ አንተ አንዷን ሚስትህንና ሁለቱን ልጆችህን ገድሎ ዘርህን አጥፍቶ አትበዛም። ነገርኩህ አትበዛም። እና ምንን እናድርግ አትበለኘወ አልኩህ። እንጃባህ ምን እንደምታደርግ። ከጨነቀህ መላ አታጣም። ካልጨነቀህ የራስህ ጉዳይ አልኩህ። 

"…ኦሮሚያ አሩሲ አርደው፣ ከሞት የተረፈው ሕጻን ዛሬ እግሩን መቆረጡ ተሰምቷል። ትናንትም አንድ ሰው መግደላቸው ተነግሯል። እነሱ አሁን በፕሮፓጋንዳ ይገለብጡሃል። ጠብቅ። በቀደም መግለጫ ሲሰጡ ጥቆማ አድርገው ነበር። ከእኛም ሰው ተገድሎብናል ብለው። ወፍ ግን የለም። አሁን ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወይ ወሎ ላይ እስላም ገድለው ሰማይ ምድሩን ሲደበላልቁት ታያለህ። 

"…ነገርኩህ ሁሌ ሰበር ዜና አዝነናል፣ እንባችን ይቁም፣ ደማችን አይፍሰስ? መንግሥት ሆይ ከወዴት አለህ? ሲኖዶሱ፣ ጳጳሱ ብትል ከመሞት፣ ከመጥፋት የሚታደግህ የለም። መፍትሄው ራስህን አስታጥቀህ በብላሽ ሊገድልህ የሚመጣውን ጥለህ በክብር መውደቅ ብቻ ነው። ራስን መከላከል በመጽሐፍ በመንፈሳዊውም ዓለም፣ በሕገመንግሥቱም የተፈቀደ ነው። ራስን መከላከል በአሜሪካም፣ በእስራኤልም፣ በቱርክም ሆነ  በሳዑዲ አረቢያም በምድር ላይ ባሉ ሀገራት ሁሉ የተፈቀደ ነው። እስራኤልን ተመልከታት። ሌላ ምንም መፍትሄ የለም። ከገዳይ አስገዳዩ አቡነ ሳዊሮስ ምንም ፍትሕ አታገኛትም። ነገርኩህ። ይሄን አልክ ብለህ ደግሞ ተንጫጫብኝ አሉህ!

• ኬሬዳሽ፣ ለደንታህ ነው።

ከዘመድኩን በቀለ ቴሌግራም ገጽ የተገኘ


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment