አንዳች አይነት ህብረት ያስፈልገናል። ይህ ህብረት ዋነኛ ዓለማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኦርቶዶክሳዊያንን ሰቆቃ በተገቢውና በተደራጀ
መልክ መረጃ ማሰራጨት፣ በጽሁፍ በምስልና ድምጽ ሰንዶ ማስቀመጥ፣ ኦርቶዶክሳዊያንን በተለያየ መልኩ Mobilize ማድረግ ሲገባ ይህንን ማቀናጀት የሚያስችል፣ ከተለያየ ሙያ መስክ የተውጣጡ ኦርቶዶክሳዊያን ያሉበት ህብረት ያስፈልጋል።
| አርሲ የደም ምድር! |
መልክ መረጃ ማሰራጨት፣ በጽሁፍ በምስልና ድምጽ ሰንዶ ማስቀመጥ፣ ኦርቶዶክሳዊያንን በተለያየ መልኩ Mobilize ማድረግ ሲገባ ይህንን ማቀናጀት የሚያስችል፣ ከተለያየ ሙያ መስክ የተውጣጡ ኦርቶዶክሳዊያን ያሉበት ህብረት ያስፈልጋል።
አሁን እያደረግን ባለው እንቅስቃሴ የታዘብኩት ለብዙ ሰው Tweeter እና Email Campaign ማድረግ እንኳ ቀላል እንዳልሆነ ነው። የተዘጋጁ ትዊቶችን Copy Paste Complex እየሆነባቸው እንዴት እናድርገው የሚሉ እልፍ ናቸው። አስቀድሜ እንዳልኩት ይህ ህብረት ቢኖር የIT ባለሙያዎች በቅጽበት የሚከተሉትን ዘመናዊ መፍትሄ በመጠቀም የብዙሃኑን ችግር መፍታት ይቻል ነበር። ቀላል የ Campaign Blog/website ሰርተውልን የሚያስፈልጉ ጽሁፎችና ፎቶዎች እዛ ላይ እየተቀመጡ በአንድ "Single Button Click" ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳዊያን Email ወይም Tweet እንዲልኩ የሚያስችል Automated System መዘርጋት ይቻላል።
ይህን በግላችን የIT ባለሙያ ጓደኞቻችንን በአንድ ቀን ሰርተው ዝግጁ ማድረግ እንደሚችሉ ነገረውኛል፤ ነገር ግን እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴችን ''በግል'' ለማድረግ መሞከር ዃላ የግል አመለካከትን በቤተክርስቲያን ጉዳይ እያስታከክን ማስኬድ ሊያመጣ ስለሚችል ነው ህብረት ያስፈልጋል ያልኩት።
የዘመኑ የትግል ዘዴ ቅንጅት፣ ስልታዊ ዕቅድ እና ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀምን ይጠይቃል። ይህን ህብረት በመመሥረት፣ ከግለሰባዊ ጥረት ወጥተን ጠንካራ፣ ውጤታማ እና ዲጂታላይዝድ የሆነ ንቅናቄ መፍጠር እንችላለን!
Mariamawit Henok
No comments:
Post a Comment