Saturday, November 8, 2025

ገዳያችን ማን ነው?

ወገን ተገደልን ብለን መጮኻችን ብቻውን በቂ አይደለም።ገዳይችንን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል።በአርሲ የኦርቶዶክሳውያንን ዘር

እያጠፋ ያለው  "ኦሮሚያን የኢስላም ሀገር አድርጋታለሁ" የሚለው የጽንፈኛ ወሀቢያ ቡድን ነው። ኦነግ ሸኔ የሚባል  ታጣቂ ቡድን አርሲ ውስጥ የለም።እየመረረንም ቢሆን ይኽን እውነት ተቀብለን  የመዳኛ መንገድ እንፈልግ።እንደ፦ ሊቢያ፣ ሰሜን አፍሪካ፣ቱርክ  ከመጥፋታችን በፊት የምንችለውን እናድርግ።ገዳያችን  ወሀቢያ ነው።አንተ ስማቸውን መጥራት ስለፈራህ እነርሱም አይራሩልህም  የሚቀርልህ መከራም የለም።

16 ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ 9ኙን ገድለው የጣሉባቸው የምስራቅ አርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ አንጎደቼ፣ ጉሬ፣ወሸባ፣ተሬ አሚኛ ቀበሌዎች ዛሬም በርካቶችን አፍነው መውሰዳቸውን መንክር ሚዲያ መዘገቡን አጋርቻለሁ፡፡ 

እኛ በጮህን ቁጥር 'ይውጣላቸው' በሚል እልህ በሚመስል ሁናቴ አፈናውንና ግድያውን በየቀኑ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

እኛስ?

እኛማ ግዳይ የፈጸምን ይመስል ሁለት ቀናት አለቀስን አሁን ረገብ ማለት ጀምረናል፡፡ እንዲያውም የልማት ፎቶና ኒሻን ማጋራት ሁሉ የጀመሩ አሉ፡፡ ሌሎቹም እንቶፈንቷቸው ላይ ናቸው፡፡ ይኸ በጣም ነው የሚያደማው፡፡ 

የዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ ግቡ ቢያንስ ለአጭር ጊዜም ቢሆን አፈናውንና ጭፍጨፋውን በማስቆም፣ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየገደለና እያስገደላቸው ላሉ ምስኪኖች ጥበቃ ያደርግ ዘንድ ጫና ማድረግ ነበር፡፡ መንግሥት እያደረገ ያለው እኮ ተገዳዮችን ትጥቅ አልባ ባደረገ በማግሥቱ ገዳዮችን እየላከ ነው የሚያሳፍናቸው፡፡ ይኸ እኮ በተደጋጋሚ ተነገረ፡፡

አንዳንዶች ሥልጣን የመንጠቅ ሁሉ መስሏቸው ሲጨነቁ ታይተዋል፡፡ 'ዐይን ጨፍኑና እናሙኛችሁ፣ ስንገድላችሁም ድምጽ አታሰሙ' ማለት ካልሆነ ሥልጣን የሚያዘው አስቀድሞ መኖር ሲቻል ነው፡፡ በአጭሩ ፖለቲካና ሥልጣንን የቅንጦት አድርገውታል፡፡ 

በሌላ በኩል አርሲ ላይ ጭፍጨፋውን አስቀጥለው ዐዲስ አበባ ላይ ደግሞ ሚዲያዎችንና አንዳንድ አካላትን ሰብስበው የሚዲያውም ጩኸት ይቆምና በጨለማ ውስጥ መግደላቸውን ይቀጥሉ ዘንድ እያስፈራሩ ናቸው፡፡ እዚህ ስብሰባ ላይ እንደተለመደው የአባ ሳዊሮስ ተልእኮ አስፈጻሚዎችም ተገኝተዋል፡፡

እነሱ ለአንዲትም ደቂቃ ከዓላማቸው ፈቀቅ አላሉም፡፡ እኛ ግን በሁለት ቀናት ዘመቻ ተልእኮ እንደጨረሰና ግቡን እንደመታ ነገሩን አቀዘቀዝነው፡፡ ይኸ ባለበት እና ይኸ ትሬንድ በሚታወቅበት ሁኔታ ይኸ ሥርዓት ከቁም ነገር ቆጥሮ ሊሰማን አይችልም፡፡ በአጭሩ በቁጥር ብዙ ነን፣ ነገሩን ተረድተው ለፍታሜው የሚንታገሉ ደግሞ እምብዛም ናቸው፡፡ 

ይኸ ሥርዓት ጠባያችንን ድብን አድርጎ ስላወቀ ይኸው ግድያውን ለአፍታ እንኳን ሳያቆም በየቀኑ እየገደለና እያሳደደ፣ እያፈነ ቀጥሏል፡፡

 ዘመቻው ዐለማቀፋዊ ተደራሽነት ኖሮት ሥርዓቱ ተገዶ ለገዳይ ሽፋን መስጠቱን ካላቆመ፣ ግድያውን ከአርሲው ውጭ ባሉ እና መግደል በሚችሉባቸው ቦታዎች ሁሉ እያስፋፉት እንደሚሄድ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም፡፡ 

ይኸው ነው፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment