Sunday, November 16, 2025

አርሲ የሰቆቃ ምድር

ወንድማችን ዲያቆን ዮሴፍ ከተማ ና ወንድማችን ጸጋየ ክፍሉ ትናንት #የኦሮሚያ ኦርቶዶክሳውያን ፍጅት በሚል መርሐ ግብር በኢትዮ

ቱንቢ ሚዲያ ካቀረቡት እጅግ ውስጤን የነካኝና ሁሉም ኦርቶዶክሳዊና ባለ አእምሮ ኢትዮጵያዊ ሊሰማው የ
ይገባዋል ብዬ ያመንሁባቸውን ሁለቱን ላቅርብላችሁ፦

፩  እኝህ በፎቶ የምታዩአቸው ካህን ቄስ  አሳልፈው መኩሪያ ይባላሉ።በምሥራቅ አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ መድኅን ዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናቸው።ለትንሳኤ ዋዜማ (2017) ምሸት ውስጣቸው ይረበሽና ልጄን ይገድሉብኛል ብለው በመስጋት ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።ልክ ቤታቸው ሲሄዱ እሳቸው እንደሰጉት አልቀረምና አራጆቹ ልጆቸውን ለመውሰድ ቤቱን ከበዋል። ልጃቸውን አሰመለጡ ራሳቸው ግን ማትረፍ አልቻሉም ታፍነው ተወሰዱ።500ሺ ብር ተጠየቀባቸው።አመለሸጋ ሰው አክባሪ ዝምተኛ  ተናግረው የሚሰሙ ሰው አስታራቂ ሴለሆኑ ማኅበረሰቡ እንደምንም ብሎ ተሯሩጦ 500ሺ ብሩን ያዘጋጃል።አራጆቹ ገንዘቡን ወሰዱ ነገር ግን አልለቀቁአቸውም  ስምንት ወር ሆኖአቸዋል ይኑሩ ይሙቱ አይታወቅም ባለቤታቸው ግን "ካህኔ እንደ ወጣ ቀረ" ብላ በለቅሶ ልትሞት ደርሳለች።ሰው ሰላምታ ሲጠይቃትም የምትመልሰው  መልስ "ካህኔ እንደ ወጣ ቀረ"የሚል ነው።

፪ እዚያው ቄስ አሳልፈው ሲያጉለግሉ ከነበሩበት አቦምሳ መድኅን ዓለም ቤተ ክርስቲያን በማሠራት የሚታወቅ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ባለሀብት አለ። የብልጽግና መንግሥት ያስታጠቃቸው "የኦሮሞ ኢስላማዊ መንግሥት "ታጣቂዎች  በአከባቢው ላይ ያሉት ኦርቶዶክሳውያንን ትጥቅ ያስፈታል።ይኽ ሰው ግን በተደጋጋሚ ትጥቁን እንዲያስረክብ ሰው ቢላክበትም በፍጹም አላስረክብም ይላቸዋል።አንድ ቀን ግን አዘናግተው እንዲህ አደረጉ።ከኦርቶዶክስ ወገን የሆነ  አንድ ሰው በሩቁ ይጠሩትና እንትናን ንገረው ከብቶች ሳብሉን እየበሉበት ነው ፈጥነህ ሂደህ ንገረው ይለታል ።የተላከውም እነርሱ እንዳሉት እውነት መስሎት ለ ባለሀብት ይነግረዋል።ባለሀብቱም እውነት መስሎት መሳሪያውን ጥሎ ባዶ እጁን እየሮጠ ሲሄድ ለካስ አራጆቹ ናቸው።ወዲያውኑ አፍነው ወሰዱት።ይኸው እስካሁን አልተለቀቀም።ለመጻፍም እንኳ ቢሰቀጥጥም ድርጊቱ፦ አልገደሉትም  የራሱን ሥጋ ከአካሉ እየቆረጡ እያበሉት ነው እንደሆነ ነው ከአከባቢው የሚወጡ መረጃዎች የሚያሳዩት። 

እነዚህንና መሰል ሰቆቃዎችን የአባ ያሬድ የግል ንብረት የሆነው የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከትም ሆነ  በእነ ሳዊሮስ የሚመረው ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲነገር  አይፈልጉም።ለምን? የመንግሥታቸውን ገጽታ ያበላሽባቸዋልና።ይኽ ነው በሕዝባችን ላይ እየሆነ ያለው።ገና ያልተሰሙ ብዙ ሰቆቃዎች አሉ። አሁን እኛ ኦርቶዶክሳውያን ከእግዚአብሔርና ከጉልበታችን በቀር ሊታደገን የሚችል እንደሌለ ልንገነዘብ ከኀጢአት ብቻ በቀር መፍትሔ ይሆናል ከእልቂታችን ይታደገናል የምንለውን የትኛውንም የመፍትሔ አቅጣጫ መውሰድ ይኖርብናል።
 ይብቃን!


የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment