Monday, April 30, 2012

ሦስት መቶ ሺህ ተሽጦ ሰባ ሺህ ጉርሻ ያስገኘ…..

ተካ ፍሬሰንበት ከራጉኤል መርካቶ

"የፈራ ይመለስ" ከምን??
የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር የሚያደርጉት ግብግብ ተሳክቶ ፍሬ እያስገኘ ነው፡፡ ምዕመኑም “ከልጆቻችን ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን የቀረበ የለም የምንሰማው እነሱን ነው” ብሎ እየተከተላቸው ነው፡፡ ይኽ በእውነት ትልቅ ለውጥ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት በአዳራሽ ተወስኖ መቅረት የለበትም፡፡ በቅድሚያ እያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት በየአጥቢያው የስብከተ ወንጌሌ አገልግሎት በኮሚቴ ከመሳተፍ ጀምሮ በመማር ማስተማሩ ሒደት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ከጥሎ በአቀማመጥ ቅርብ ለቅርብ የሆኑት ደግሞ ተጋግዘው ቦታቸውን ከአጉራ ዘለል ሰባኪያን ለማጽዳት አንድ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በቅርቡ መናፍቁ አሰግድ በአንድ አጥቢያ ተጋብዟል መባልን የሰሙ ሰ/ተማሪዎች ከሩቅ ቦታ በቶዮታ ቲካፕ መኪና ተጭነው ቀድመው ቦታውን ለማስከበር ሲደርሱ ስለተደወለለት ይመስላል አሰግድ ግን ሳይመጣ ቀርቷል፡፡
ሌላው ሰ/ተማሪዎችና ጉዳዩ የሚያንገበግበን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ልንሰራው የሚገባንን የቤት ሥራ ላቅርብና ተወያዩበት ያላችሁንም መረጃ በሰንበት ት/ቤቶች ኅብረቱ በኩል ሰብስቡት እላለሁ፡፡እነሆ ፍሬ ነገሩ፦

                     

Friday, April 27, 2012

በስዊዲን “አዲስ ቤተ ክርስቲያን" ይከፈታል መባሉን ምዕመናን ተቃወሙ

በስዊዲኗ የስቴክሆልም ከተማ በመጪው እሑድ “ይከፈታል” የተባለ ቤተ ክርስቲያንን አስመልክቶ ምእመናን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የተቃውሟቸውን እና ምክንይቱን ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለሥጋዊ ጥቅምና ለበቀል ብቻ ሲባል ቤተክርስቲያን ”የመክፈት” እንቅስቃሴ፣ በስቶክሆልም ስዊድን
በስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘው የደብረ ሰላም መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን

ውድ አንባቢያን በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ እያልን:- የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የግለሰቦችን ስም እያነሱ ማሳጣት ሳይሆን እያካሄዱት ያሉትን ሥጋዊ እና ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ እኛ የተረዳነውን ያክል ለሌሎች ምእመናን እንዲሁም ለአባቶቻችን ካህናት አሳውቀን በአንድነት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለማስከበር እንድንነሳ መሆኑን እንድትረዱልን በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነን ”ኢትዮጵያ ዛሬ” በሚባል ድረ ገጽ ላይ አንድ ”መንፈሳዊ” ጥሪ መመልከታችን ነው (አወዛጋቢውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ )። ማስታወቂያው ”ታላቅ የምስራች ለሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ለሆናችሁ በሙሉ” በማለት ይጀምራል:: ከዚያም ወደ ዉስጡ ሲገባ የሚነበብዉ ነገር ለህሊና የሚከብድ፤ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነ፤ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት፣ ከዚያም አልፎ የምእመናንን አንድነት የሚንድ እኩይ ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን:: ማስታወቂያው ሲነበብ “... በስቶክሆልም ስዊድን ሶላንቱና ሴንትሩም አካባቢ በዓይነቱ ልዩ የሆነና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና መሠረት የሚመራ፤ በካህናት አባቶች የተመሠረተ፤ ንብረትነቱም ሆነ ባለቤቱ በግልጽ በስቶክሆልም ስዊድን በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ የሆነ ቤተክርስቲያኑ የሚገኝበት የቦታው አቀማመጥ በዓይነ ሕሊናችን ወደ ሀገራችን ታላላቅ የእምነት ገዳማት የሚያስጉዝ በውስጥ አደረጃጀቱ ብቃት ያለዉ... ወዘተ” በማለት ጸሐፊዉ ”በአይነቱ ልዩ የሆነ ቤተክርስቲያን ”እንደሚከፈት” ያትትና በዕለቱ የቅድስት ድንግ ማርያምንየአቡነ ተክለሐይማኖትንና የአቡነ አረጋዊን የቃል ኪዲን ታቦታት አካትቶ የያዘ አዲስ ቤተክርስቲያን የፊታችን ሚያዝያ 21/ 2004 ዓ.ም ወይም እ.ኤ.አ. ኤፕሪሌ 29/ 2012፤ እሁድ በብፁዕ አቡነ ኤያስ ጸሎትና ቡራኬ ተመርቆ ”ይከፈታል” ብሎ ጥሪዉን ያጠናቅቃል::

Tuesday, April 24, 2012

አቡነ ፋኑኤል ለምን ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

  • አቡነ ፋኑኤል በአሜሪካ ለ4 ወራት ሲቀመጡ ምን አጋጠማቸው?
  • በመጡ በ4ኛ ወራቸው ተመለሱ?
  • ዓላማቸውን ከሞላ ጎደል ተሳካላቸው ወይስ?
 ዜናውን በPDF ለማንበብ ይጫኑ
አባ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን የገቡ ቀን

አቡነ ፋኑኤል በወረሃ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መጨረሻ አካባቢ ተሳክቶላቸው (በብዞዎች እንደሚባለው ጉቦ ሰጥተው እንደመጡ ይነገራል) ወደ ዋሽንግተን እና ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኃላ፣ በብዙ ቦታዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ማጣት እንደሚፈልጉት በተለምዶ (እንደ አባ ፋኑኤል አባባል) ገለልተኛ በሚባሉት እንኳን ተቀባይነት ማጣቱ ትንሽ ሳያስከፋቸው የቀረ አይመስለንም የተለያዩ የውስጥ ምንጮች እንደገለጹልን እዚህ ከመጣሁ ስኳሬ ሁሉ ጨመረ እንጂ ምንም ያገኘሁት ነገር የለም ሲሉ እንደተሰሙም ተሰምተዋል። ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ፣ በወቅቱ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አባ አብረሃም እስከሄዱ ድረስ እንኳን እንደ ቤተክርስቲያን አባት ተቀራርበው ቤተክርስቲያኒቱን እንዴት እንጥቀማት ለተጠራንበት ዓላም እንዴት እንሥራ ቀርቶ፣ ጅምር ሥራዎች ካሉ እኔ ልረከቦት ከማለት ይልቅ፥ የአብርሃምን ድንኳን አፍርሼ የኔን እተክላለሁ በሚል ፈሊጥ የነበሩትን ጅምር ሥራዎች ሲያፈርሱ አዳዲስ ሥራዎችን ለመሥራት ሲጣጣሩ የተያበት ጊዜ ነበር፣ ባለፉት 4 ወራቶች እንደእውነቱ ከሆነ ከሠሯቸው ብዙ ልማቶች (ካሉ ማለት ነው፣ ምንም እንደሌለ የታወቀ ቢሆንም) ያጠፏቸው በብዞዎች ጎልተው የሚታዩ ሆነው ተገኝተዋል።

Thursday, April 19, 2012

ታሪክን መጠበቅ የማን ሃላፊነት ነው?

ቦታው ቴክሳስ አማሪሎ ይባላል ከዚህች ከተማ ወደ 70 ማይልስ ርቀት ላይ ግሩም የምትባል ከተማ አለች ይህች ከተማ ልዩ የሚያደርጋት ነገር ቢኖር፣ ከተማዋ ሁኔታ ቅድስና ያገኘችበት ነገር የለም፣ በዓመት ውስጥ ቁጥራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ 
ወደዚህች ቦታ በመንገድም ተጓዦች፣ ለሽርሽር መጪዎች፣ በሥራ ላይ ያሉ፣ ከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎች የሚነዱ ሹፌሮች፣ እንዲሁም ሙሽሮች ከዚህች ቦታ ቅድስና ለማግኘት እና በረከት ለመቀበል ወደዚህች ቦታ ይመጣሉ።ይህች ቦታ እንደማንኛውም
የአሜሪካ ግዛት ከተሞች አንዷ ብትሆንም የተለየ ቅድስናዋን (ስያሜውን) ያገኘችው የዓለም መድኅኒት ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህማመ መስቀሉን የሚያሳዩ የጌታን ስቃዩን፣ ግርፋቱን፣ በሰው ፊት ያለሃጢያቱ ለፍርድ መቅረቡን፣ ንጽይተ ንጹሐን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው የሚያሳዩ ቅርጾች የተሰሩበት ቦታ ነው፥በጣም የሚገርመው የዚህ ቦታ አመሰራረት እንደሚከተለው ነው።

ቦታውን ያሰሩት ሰው አቶ ስቲቭ ቶማስ የሚባሉ የፖምፓ ቴክሳስ ነዋሪ የነበሩ ነዋሪ ናቸው፥ በተለያየ ጊዜ በዚያ አካባቢ የሚያያቸው በጣም ትላልቅ አስነዋሪ  (huge billboards advertising XXX pornography) ፎቶግራች በጣም ያሳዝኗቸው ስለነበር ይሄንን ቦታ መቀየር አለብኝ ብለው የጌታን ኅማመ መስቀል የሚያሳየውን ቅርጽ ለማሰራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ይህንን የሰሙ የቦታው ባለቤት ለሰውየው በስጦታ ሰጥተውት በዚህ ቦታ ላይ በሰሜን አሜሪካ በጣም ከትልቅነቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን
ይህንን ትልቅ መስቀል እና የጌታን ህማማ የሚያሳየውን ቅርጽ በ1995 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሊሰራ ችሏል ቦታውን በአሁን ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ከመላው አሜሪካ እየመጡ ይጎበኙታል፣ ይልቁንም ቅዱስ ቦታ እየተባለም ይጠራል። 
በቅርብ ጊዜ ደግሞ ውርጃን የሚቃወም ሃውልት እንዲሁ በበጎ አድራጊ ተሰርቶ 
ለእይታ በቅቷል።

Monday, April 16, 2012

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን

ትንሣኤ ክርስቶስ 
ትንሣኤ ዘክርስቶስ - የክርስቶስ ትንሳኤ
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡ ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል።
፩ ፥ ፩፦ ሦስት መዓልት እና ሦስት ሌሊት በመቃብር፤


Monday, April 9, 2012

ለቪኦኤ የተናገሩት የዋልድባው አባት በፖሊስ እየታደኑ ነው

·         ያሉበትን ካልጠቆማችኹ በሚል ሦስት ገዳማውያን ታስረው ተፈተዋል::
  • እስሩና ‹አደኑ› የቤተ ሚናስ መነኰሳት በተለይም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ለሚደርስባቸው ልዩ ጫና ግልጽ አመልካች ነው ተብሏል::
  • በ1980 ዓ.ም የገዳሙን ሰሜናዊ ክፍል (በእንስያ ወንዝ) የጦር ካምፕ ለማድረግ የተቃጣው ሙከራ ኅቡኣን አበው ኵናት መወገዱ ተነግሯል::
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 29/2004 ዓ.ም፤ April 7/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የመንግሥት ባለሥልጣናት በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ ከሚያደርሱባቸው ወከባና ማስፈራሪያ እንዲታቀቡ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሦስት የገዳሙ ማኅበር አባላት በፖሊስ ታስረው መፈታታቸው ተሰማ፡፡ መነኰሳቱ ለእስር የተዳረጉት “ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት አባ የት እንዳሉ ተናገሩ” ከሚል የፖሊስ ጥያቄ ጋራ በተያያዘ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ መረጃ ኮማንደር በየነ በሚባል የፀለምት ወረዳ ፖሊስ መጋቢት 23 ቀን 2004 ዓ.ም ከገዳሙ የተወሰዱት ሦስቱም ታሳሪዎች በገዳሙ በዲቁና የሚያገለግሉ ሲሆኑ ከሦስቱ ሁለቱ መናንያን መሆናቸው ተገልጧል፡፡

Friday, April 6, 2012

ከክህነት ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት


ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያሽሩ ምክንያቶች
አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አዲስ ሊቀ ጳጳስ ተሹሞ ተልኳል ከተባለበት ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በችግር ላይ ይገኛል። ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በቃለ ዓዋዲው መሠረት የመረጡትን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አልቀበልም ከማለት አልፈው ካህናቱን በሙሉ ማስፈራራት እና አንዳንዶቹንም “አውግዣለሁ” ማለት ጀምረዋል። ይህም መነሻ ሆኖን “ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች”፣ በደፈናው ከመሬት ተነሥተው “ክህነት ይዣለሁ” ስለሚሉ አቡነ ፋኑኤልን ስለመሳሰሉ ጳጳሳት አስቀድመው በቅዱሳን አበው የተሠራውን ሕግ በተመለከተ ፍትሐ ነገሥቱ የሚለውን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን።


+++
ክህነ መዓረጉ ምጡቅ፣ ምሥጢሩ ረቂቅ ነው፡፡ የሰማያዊው ንጉሥ የእግዚአብሔር ወኪል ከመሆን የበለጠ ሥልጣን የለምና፤ ይህ ሥልጣን በሰማይም በምድርም የሚሠራ ነው፡፡ ስለዚህ ከምድራዊው ሥልጣን የላቀ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ለመቀበል ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች እንደመኖራቸው ሥልጣኑን ያለ አግባብ ሲጠቀሙበት የተገኙ ወይም የክህነት ሥልጣን ከሚፈልገው ሕግና ሥርዓት ውጭ ሆነው የተገኙ ተሿሚዎች ክህነታቸው የሚያዝበት ወይም ከክህነት የሚሻሩበት ቀኖናም ተቀንኑዋል፡፡ ይህ ክታብ ለመጀመሪያ ዜ በ1958 ዓ.ም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በ1995 ዓ.ም በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት የታተመውን ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜውን መሠረት ያደረገ ነው በዚህ ክታብ ላይ ለመዳሰስ የተሞከረው በፍትሕ መንፈሳዊ ካህናት ከሹመታቸው ስለሚሻሩበት ሁኔታ የተገለጸውን ለመጠቆም ነው፡፡

Thursday, April 5, 2012

የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የአቡነ ፋኑኤልን ማስፈራርያ እንደማይቀበሉ አረጋገጡ

  • አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን ፀሐፊ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን “ክህነቱን ይዣለኹ” ያሉበትን ደብዳቤ በተሐድሶዎች ብሎግ ላይ አወጡ፤
  •    ይህ ሥርዓት የሌለው “ሥልጣነ ክህነትን ማገድ” ሊቀ ጳጳሱን ከማስገመት ውጪ ትርጉም የለውም ተብሏል፤

 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት “ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ተመድበው ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ አብያተ ክርስቲያናቱ ያቀረቡትን ጥያቄ ባለመቀበል የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በሚያናጋ መልኩ፤ የፓትርያርኩ ስም በጸሎተ ቅዳሴ እንዳይነሳ በመገፋፋት፤ ሰዎች በፈለጉት መንገድ እንጂ በቃለ ዐዋዲ የሚመራ ቤተ ክርስቲያን እንዳይኖር፤ የካህናትን ክብር የሚያቃልል የቦርድ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን እንዲስፋፋ ጥረት በማድረግ፤ በትልቅ ትጋት ሀገረ ስብከቱን ለዚህ እድገት ያበቁትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ቀርበው ተመድቤ መጥቻለሁ ብለው ኃላፊነትን ከመቀበል ይቅ “የአብርሃምን ድንኳን” አፈርሳለሁ በሚል ስሜታዊ አዋጅ ተነሳስተው ሀገረ ስብከት የሚባል የለም  ብለው በአሜሪካ ድምጽ እስከመናገር” ደርሰዋል ሲሉ  በድጋሚ ወቀሱ። 

ከአንባቢያን አስተያየት

እነዚህን የአንባብያን አስተያየቶች ከአሐቲ ተዋሕዶ የተገኘ አስተያየቶች ናቸው፣ አንባቢያን ቢያዩዋቸው  ይጠቅማሉ ብለን ስለገመትን እንደሚከተለው አቅርበነዋል። መነሻ ጽሁፉ "ጥይት የሌለው ጠመንጃ፥ ስልጣን የሌለው 'ውግዘት' " በሚል ርዕስ በአሐቲ ተዋሕዶ ላይ የቀረበ ጽሁፍ ነው። መልካም ምንባብ
 
Berhanu Melaku said...
ይድረስ ለብጹ ቅዱስ አቡነ ፋኑኤል

ካህናትን ለማስፈራራት ተንሳስተው የጻፉትን ደብዳቤ ቁጥር ሀ\ስ\24\04 በተለያዩ ድረ ገጾች አይች ሕዝብ እንዲያውቀው ለእርስዎ ጥያቄ ላቀርብ ክርስቲያናዊ በሆነ መንፈሳዊ ግዴታ ተገደድኩ።

አይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቁንጮዎች፤ ምነው ቤተክርስቲያኒቱን ካለችበት ፈተና ለማውጣት ብትጥሩ። አሁን ይህ ድርጊት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይጠቅማታል? ምእመናን አባትን በማክበርና በሀዋሳ ልይ የሆንውን ግብግብ ችግር ላለመድገም ብለን ዝም ብንል ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል
እንደተባለው ጳጳሱ እየጮሁ አላስቀምጥ አሉን። ከእንግዲህስ ወዲያ ዝምታው እየከበደን ነው።

ብጹእነትዎ እስኪ የሚከተሉት ጥያቄወች የእርስዎን መምጣት በጉጉት እየጠበቅን ላለነው ለምእመናን ይመልሱልን።

Wednesday, April 4, 2012

አፍ ቢያዝ፥ ዓይን ይናገራል

በኤርሚያስ ኅሩይ
በዕለት ተዕለት ግላዊና ማኅበራዊ ሕይወት የሚያጋጥም ማንኛውንም አጋጣሚ፣ አሳብንና ውሳጣዊ ስሜትን  ደስታንና ኀዘንን ማግኘትና ማጣትን ተስፈኛነትንና ተስፋ ቢስነትን ለሁለተኛና ለሦስተኛ ወገን መግለጥ ማንጸባረቅ ማጋራት ሰውን ከሌሎች ሥጋዊና ደማዊ ፍጥረቶች ልዩ ከሚያደርጉት ሰብአዊ ባሕርዮቹ መካከል አንዱና ምናልባትም የራሱ የሆነ ሥርዓትና መለያ ጠባያት ላሉት የሰው ልጅ ኑሮ ከመብልና ከመጠጥ ቀጥሎ አስፈላጊና ወሳኝ ከሆኑት ሰብአዊ ፍላጎቶች ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዝ የመሠረታዊ ፍላጎቶች ሁሉ ማግኛ ማጣፈጫ ማዋሀጃና ማስፈጸሚያ መሣሪያ ነው።

ሰው በተፈጥሮ የተሰጠውን ልዩ የማሰብ ችሎታ ተጠቅሞ መጥፎም ይሁን ጥሩ በየጊዜው ለዓለማችን እንግዳ የሆኑ ነገሮችን አምጥቷል፤ የአኗኗር ስልቱንና ይዘቱንም በየጊዜው በማሻሻል ተፈጥሮን በሚገባ መጠቀምና የጥንት ሰዎች ይኖሩት ከነበረው አኗኗር እጅግ የተሻለና የተደራጀ ቀላልና ምቹ ኑሮ ለመኖር ችሏል። ማሰብ እስካልተቋረጠ ድረስ በሰው ልጆች አኗኗር የሚታየው መሻሻልና መደላደል አይቋረጥም ፧ በእያንዳንዱ አዲስ ቀን ዓለም የሰው ልጅ አሳብና ዕውቀት ውጤቶች የሆኑ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን እንደ ገጸ በረከት ስትቀበል ትኖራለች።

አምስተኛው የቤተክርስቲያን የስደት ዘመን!

በኤርሚያስ ኅሩይ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዓለማችን ቀደምት ከሚባሉ ጥንታውያት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷና በግምባርቀደምነት ተጠቃሽ መሆኗ ተደጋግሞ የተወሳና ከማንም ያልተሠወረ ሐቅ ነው። ይህች ቤተክርስቲያን ከመንፈሳዊ ተልእኮዋ በተጓዳኝ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንንም ኢትዮጵያውያን ያሰኙ እጅግ ብርቅና ድንቅ የሆኑ እንደ ፀሐይ መመላለስ ያለመቋረጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ ሀገርና ትውልድ የሚያኮሩ መንፈሳውያትና ቁሳውያት ዕሤቶችን ፈጥራ ያስረከበች ጠብቃም ያኖረች ውለታዋ እጅግ የበዛ ቤተክርስቲያን ናት። ኢትዮጵያዊ ፊደል፣ቁጥር፣የቀን መቁጠሪያ፣ስነ  ጽሑፍ፣ግጥም፣ቅኔ፣ዜማ፣ሰንደቅ፣ባህል፣ታሪክ፣ሐውልት፣ደን፣ ወዘተ ዛሬ ኢትዮጵያውያን “የእኛ” “የራሳችን” ብለን የምንመካባቸው ብዙዎች የሌላቸው ሀብታችን ከመመካትም አልፎ ተርፎ ቀላል የማይባል የቱሪዝም ገቢ የሚዛቅባቸው ዕሤቶች ከሌላ ከማንም ሳይሆን ከዚህችው እናት ቤተክርስቲያን ያለ ዋጋ የተገኙ ገጸበረከቶች ናቸው። ይህን ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ አባል ቢሆንም ባይሆንም የሀገሪቱን ታሪክ ያጠና ወይም ምድሪቱን የጐበኘ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሊመሰክረው የሚችለው አሌ የማይባል እውነታ ነው።             

Tuesday, April 3, 2012

ክህነትን በደብዳቤ ማገድ ይቻላል?

ሰሞኑን ከወደ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ብዙ ዜናዎችን ሰምተናል አሁንም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ካህንን በደብዳቤ አግጄሃለው በማለት ሥራቸውን እንደቀጠሉ ነው፣ ይሄን ዜና ስናጠናቅር ድረስ ባለን መረጃ መሰረት አንድ ሰው ከሥልጣነ ክህነቱ ሊሻር የሚችለው በምን በምን ምክንያት እንደሆነ ለማየት እንሞክራለን።
ይህንን በተመለከተ ሕገ ቤተክርስቲያን ምን ይላል:

ፍትህ መንፈሳዊ ምን ይላል፣ ሥልጣነ ክህነትን ስለመሻር:
፪፻፳፬ አምስተኛው ክፍል ከሹመቱ የሚሻርበትን ምክንያት የሚናገር ነው። ይህችውም ተጽፋ መኖርዋን ቁጥሯ በአንቀጸ ኤጲስ ቆጶሳት (ፍት. ፭ ፥ ፻፸፪) የተነገረላት ናት። ሁለመናውም ይህ ነው መማለጃ ሰጥቶ ተሾመ ቄስ ሁሉ ይሻር፥ ወይም በማስፈራራት ወይም በማድላት በተንሎል ወይም መማለጃ እሰጣለሁ ብሎ የተሾመ ይሻር ወይም ሁለት ጊዜ የተሾመ ወይም ሁለት ሚስት ያገባ ወይም ወይም ሕዝቡን ከማስተማር ቸል የሚላቸው የማይረዳቸውም ወይም የኃጢአተተኛውን ንስሐ የማይቀበል ወይም በነገር ሠሪነትና ሐሰትን በመመስከር ያታወቀ የሚታበይ፣ ሕግን አውቆ የማይሠራባት ወይም ዘወትር የሚሰክር፣ ክፉ ሥራንም የሚያዘወት፣ በጎ አለመሥራትን የለመደ፣ ከአበደረው ላይ ትርፍን የሚፈልግ ከዘማዊት ሴት ጋር የተኛ፣ ተያዥ የሆናትም ብትሆን እነዚህን የመሳሰሉትን የሠራ ወይም አለቃው ሳይፈቅድለት ወደ ንጉሥ የሚሄድ ወይም ሰዎች ይፈሩት ዘንድ ማንንም የሚማታ፣ ኮከብ በመቁጠር የሚታመን፣ የጠንቋቶችን ነገር ሥር፣ የሚምሱትንም የሚያምን፣ የመናፍቃንን ጥምቀት የተቀበለ፣ ወይም ቁርባናቸውን የተቀበለ ወይም ከእነርሱ ጋር አብሮ የሚጸልይ ቄስ ይሻር።

ጆሮ አይሰማው ጉድ የለም!

ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ስለ ዋልድባ ገዳማችን ይዞታ እና ከፊታችን የተደቀነውን አደጋ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን ዜና ጨምሮ ስንሰማው ቆይተናል፥ የሚገርመው ግን የኢትዮጵያ ዜና ዘገባ እና በሌላው ዓለም የሚዘገበው ዘገባ በጣም የተለያየ መሆኑ ብዙዎችን ዜጎች ይልቁንም ኦርቶዶክሳዊያኑን ግራ ሳያጋባ የቀረ አይመስለንም። ለዚህም ነው አንድ የዝግጅታችን የዘወትር ታዳሚ አንድ ዜና ከአሜሪካዋ መዲና ከሆነችው ዋሽንግተን የላኩልን፥

ነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው ጥቂት ሳምንት በፊት የቤተክርስቲያኑ ልጆች በአንድነት ተሰባስበው መልስ ቢሰጥም ባይሰጥም ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይረዳል ብለው እንደማንኛውም የሀገሪቱ ዜግነታቸው፣ እንደ ሃይማኖተኛነታቸው ድምጻቸውን ለማሰማት ከ1200 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በዚሁ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ አድርገው እንደነበረ ለሁላችንም የተሰወረ አይደለም፥ በዚህ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ከመላው ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚከገኙ ቤተክርስቲያናት ወጣቶች፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ አረጋዊያን አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ሕጻናት በዚሁ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ተሳትፎ አድርገው እንደነበረ በተለያዩ የዜና መሰራጫዎች ተገንዝበናል፥ ከዚህ በተጨማሪ በጣም ጥቂት ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ካሕናት ተገኝተው ነበር እና ነገሩን ለማጣራት የዚህ ዝግጅት ክፍል በተለያየ መልኩ ሙከራ ስናደርግ ቆይተናል በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለው ቤተክህነት ምንም ተስፋ የምጣልበት እንዳልሆነ በዘገባቸው ተረድተናል፤ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ካህናት አባቶች በተለይ ህይወታቸውን በምንኵስና የሚኖሩ የዋልድባን ጉዳይ ከማናቸውም የህብረተሰቡ ክፍል በተለየ ይቆረቆሩለታል የሚል በተለያዩ የህብረተቡ ክፍሎች ታስቦ ነበር፥ ነገር ግን ያ ሊሆን ያልቻለበት ምክንያት ለሁላችንም እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለሁሉ በላይ ግን ትልቅ የህዝብ ተቃውሞ ያስነሳል ብለን የገመትነውን ለማጣራት በተለያዩ መንገዶች ሞክረን፣ ሁሉም መንገዶች ተመሳሳይ ናቸው፥ ነገሩ እንዲህ ነው።

አቡነ ፋኑኤል
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው የተመደቡት አቡነ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ ትልቅ ተቃውሞ ሲደርስባቸው ቆይቷል ተቃውሞውም እንደቀጠለ ነው፥ አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ብፁዕነታቸው በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ወቅት፣ የብዙዎች ክርስቲያኖች፣ ሀገር ወዳድ ማኅበረሰብ፣ የሀገር ሀብት እና ቅርስ መውደም እና መጥፋት የሚጨንቃቸው በሙሉ የብጹዕነታቸውን መምጣት እና የሰላማዊ ሰልፉ ተካፋይ እንደሚሆኑ ጠብቆ ነበር። ነገር ግን ብጹዕነታቸው ለሃገር፣ ለሃይማኖት፣ ለወገን እና ለቅርሶቻችን መጥፋት ተጨንቀው ድምጻቸውን ሊያሰሙ ከመጡት ኢትዮጵያውያን ጋር መሰለፍ ቀርቶ፣ በዚያው ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ጽፈው "ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት በሙሉ፥ ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፖለቲከኞች ናቸው" ብለው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ጽፈው ማስገባታቸውን ስንሰማ "ጆሮ የማይሰማው ጉድ የለም!" ብለን  ብዙ ሙከራዎችን ለማድረግ ችለናል፣ ይልቁንም ደብዳቤውን ለማግኘት የዝግጅት ክፍላችን ሙከራዎችን እያደረገ ይገኛል፤ እንደደረሰን እናቀርበዋለን።

እናመሰግናለን! ለምታደርጉት ሁሉ

እናመሰግናለን!

(አንድ አድርገን መጋቢት 25 ፤ 2004 ዓ.ም)፤- ከቀናት በፊት በሰላ ድንጋይ አካባቢ የሚገኙ ስድስት አብያተክርስትያናትን የመዘጋት ድባብ እንዳጋጠማቸው መልእክት ቢጤ ትንሽ ጹሁፍ መፃፋችን ይታወቃል ፤ ለእነዚህ አብያተክርስትያናትን ለመርዳት የሚፈልጉ ሰዎች ፤ ከአደጋው ሊታደጓቸውና የጎደላቸውን ንዋየ ቅዱሳትን ለማሟላት ፍቃደኛ ለሆኑ ሰዎች የአስተባባሪዎችን ስልክ ቁጥር ማቀመጣችን ይታወቃል ፤ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ይህ ፅሁፍ ብሎጋችን ላይ ወጥቶ መረጃ የደረሳቸው ምዕመናን ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ጧፍ ፤ እጣን ዘቢብ የረዱ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡ ከሀገረ ጀርመን አንድ ወንድማችን 304 ትልልቁን ጧፍ ፤ 19 ኪሎ አንደኛ ደረጃ እጣን እና 5 ኪሎ ዘቢብ ከቦታው በመደወል በሰዎች አማካኝነት ለአስተባባሪዎቹ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ሲስተር እታገኝሁ 100 ጧፍ 5 ኪሎ አንደኛ ደረጃ እጣን እና 5 ኪሎ ዘቢብ ሰጥታለች ፤ በደብረብርሀን አካባቢ የሚገኙ ምዕመናንም የቻለትን ያህል በመርዳት ለአብያተክርስትያናቱ የሚሆን ንዋየ ቅዱሳትን በማሟላት ለተቸገሩት አብያተ ክርስትያናት በጊዜው በመድረስ ክርስትያናዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል ፤ ከተለያየ ቦታም እርዳታ ተደርጓል ፤

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት)


  • በዋልድባ ጉዳይ የጎንደር ወጣቶች ሊቀ ጳጳሱን አነጋገሩ::

  • በሊቀ ጳጳሱ አቋም ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዟል::
  • በዋልድባ ወጣቶች ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ እንዳይደርሱ በፖሊስ ታግደዋል::
  • የማኅበረ ቅዱሳን አጥኚ ቡድን ነገ ወደ ዋልድባ ያመራል::

 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 24/2004 ዓ.ም፤ April 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች ጥምረትና የጥምቀት በዓል አከባበር ወጣቶች ማኅበራት ጥምረት ኮሚቴዎች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የስድስቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጋራ መነጋገራቸው ተሰማ፡፡