Thursday, February 28, 2013

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያሪክ ኾኑ!!!


የድምፅ ቆጠራው ውጤት ታውቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ አሸናፊ ! ! !
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ - 98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል - 70 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ - 98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ - 39 ድምፅ
photo 4
ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ

Wednesday, February 27, 2013

ቆይታ ከ6ተኛው እጩ ፓትርያርክ ጋር


(አንድ አድርገን የካቲት 20 2005 ዓ.ም)፡- ህዳር 19 1993 ዓ.ም ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ከምኒሊክ መጽሄት ጋር ረዘም ያለ ቆይታ አድርገው ነበር ፤ ለአንድ አድርገን ብሎግ አንባቢዎች ትንሽ መረጃ ቢሆን ዘንድ በማለት መጽሄቱ ላይ የሰፈረውን እንዲህ አድርገን ለናንተ አቅርበነዋል፡፡ትላንት “ቆይታ ከ6ተኛው ፓትርያርክ ጋር” ተብሎ የተጻፈው ቆይታ ከ6ተኛው እጩ ፓትርያርክ ጋር ተብሎ ይስተካከል (ብዙ ቦታ ቀናቶቹ እ.ኤ.አ የተቀመጡ ናቸው)

 • አሁን ያለውን መንግሥት በመቃወም አንደግፍም የሚሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ከቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው ያንን የፖለቲካ ተግባራቸውን ስላካሄዱ ነው ቤተክርስቲያን የተከፋፈለችው፡
 • አንድ ፓትርያርክ ሊቀ ጳጳስም ይሁን ቄስ ፤ ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ አባት የሆነ ሁሉ መመዘን ያለበት በመንፈሳዊ ህይወቱ እና በመንፈሳዊ አቋሙ ነው፡፡
 • “ቤተክርስቲያኒቱ በእውነት የፓለቲካ ፤ የዘር ፤ የቋንቋ መድረክ መሆን የለባትም፡፡
 • እግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ ሆኖ ወደ ህብረትና አንድነታችን አንደምንመለስ ትልቅ ተስፋ ነው ያለኝ፡
 • የአሁኑን ፓትርያርክ በምን ልግለጻቸው? አሁን ለማለት የምችለው በሁለት አይነት መክፈል ይቻላል፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ አለ፡፡ የዘር ጉዳይ አለ፡፡
 • በጎሳና በቋንቋ ተለያይተን ምንም የምናስወግደው ችግር አይኖርም
 • አቡነ መርቆርዮስ ችግር ቢያጋጥም እዛው መንበራቸው ላይ ሆነው መቀበል ነበረባቸው፡፡
 • ከጥንት ጀምሮ ቤተክርስቲያን የአንድነታችን ምልክት ናት፡፡
 • የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ስርዓት መያዝ አለበት፡፡ ሲኖዶስ ጠንካራ ጉልበት እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡ የጳጳሳቱ ክብር መጠበቅ አለበት ፤ የቤተክርስቲያኗ ክብር መጠበቅ አለበት፡፡

ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ራሳቸውን ከዕጩነት አገለሉ!!


 • አስመራጭ ኮሚቴው የብፁዕነታቸውን ውሳኔ ለመራጮች በይፋ ያሳውቅ ይኾን?
 • አብዛኞቹ የብፁዕነታቸው መራጮች ለአቡነ ዮሴፍ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ይገመታል
His Grace Abune Mathewos
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ

መራጮች ስለ አቡነ ዮሴፍ እና አቡነ ማቴዎስ እየተነጋገሩ ነው


 • ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ራሳቸውን ሸሽገዋል
 • የዕጩ ፓትርያሪኮችን የሕይወት ታሪክ የያዘው መጽሔት ለዛሬም አልደረሰም
 • ምርጫው ነገ በ1፡00 ሰዓት መራጮች በሚፈጽሙት ቃለ መሐላ ይጀመራል
 • ፓትርያሪኩ በድምፅ ብልጫ ይመረጣል፤ እኲል ድምፅ ያገኙ አባቶች በዕጣ ይለያሉ
 • የምርጫው ውጤት ነገ ከቀኑ 11፡00 ላይ ይታወቃል
 • ‹‹ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እረኛና ታማኝ አገልጋይ ይኾናል ብዬ የማስበውን አባት ብቻ የምመርጥ መኾኔን በቅድስት ሥላሴ ፊት ማእምረ ኅቡአት በኾነው በኀያሉ በእግዚአብሔር ስም ምያለኹ፡፡ ቃል የገባኹትን ባላደርግ በዚህ ዓለምም ኾነ በሚመጣው ዓለም በታላቁ የፍርድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት እጠየቅበታለኹ፡፡›› /ከባዱ የመራጮች ቃለ መሐላ/Patriarch election vote paper

Tuesday, February 26, 2013

የ5ቱ እጩ ፓትርያርኮች አጭር የሕይወት ታሪክ(MK Website/  PDF ለማንበብ ይጫኑ):-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየም እጩ ፓትርያርኮችን ለመምረጥ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከካህናት፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ከማኅበረ ቅዱሳን፤ እንዲሁም ከምእመናን ጥቆማ እንዲያካሔዱ ተደርጓል፡፡ በተካሔደው ጥቆማ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማውን በግብአትነት በመጠቀም አምስት ሊቃነ ጳጳሳትን በእጩነት በማቅረብ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ከየካቲት 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ውይይት በማካሔድ አምስቱም ሊቃነ ጳጳሳት በእጩነት እንዲቀርቡ አጽድቋል፡፡

ሽማግሌዎች ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አነጋገሩ፤ አስመራጩ መግለጫ ሰጠ

አምስቱ የፓትርያሪክ ተመራጮች

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF)፦ ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት አስምት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።


ከፍተኛ ታቃውሞና የከረረ ተግሳጽ የደረሰባቸውን አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌምን ጨምሮ ሌሎቹ አራት አባቶች የተካተቱበት የአስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማ ለቅ/ሲኖዶስ ቢቀርብም ተጨማሪም ተቀናሽም ሳይደረግበት መጽደቁ ዛሬ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ሐሙስ በሚደረገው ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር የሚያገኘው ተወዳዳሪ ስድስተኛ ፓትርያርክ ተብሎ ይሾማል ማለት ነው።

Monday, February 25, 2013

ታሪክን የኋሊት “ፓትርያርኩን አትምጡ ስንላቸው መጥተው እኛንም በገማ እንቁላል አስደበደቡን” አቡነ ማቲያስ


 • አቡነ ማቲያስ አቀድሳለሁ ነው የምልዎት  እንዲህ አይነቱ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ምን ይጎዳል” አቡነ ጳውሎስ
 • እንደ ፖሊሶቹ ቁጥር ማነስና ጥንቃቄ ጉድለት የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎች  የፈለጉትን ዓይነት ወንጀል በላያችን ላይ ከመፈጸም የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም” አቡነ ማቲያስ በጊዜው የተነሳውን ተቃውሞ  ሲገልፁ
 • “ፓትርያርኩን አጅበን ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስተን ቦልቲሞር ስንደርስ ፤ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረው ተቃዋሚው የፖለቲካ ቡድን ቀፎው እንደተነካበት ንብ በድንገት ወጥቶ ወረረን ፤ በጣም ቀፋፊ የሆነ ስድብ ውርጅብኝ አወረደብን፡፡
 • አቡነ ጳውሎስ ይጎበኙታል የተባለው ሕንጻ ውስጥ ፈንጂ ተቀብሯል ስለተባለ እርሳቸውና ከእሳቸው ጋር ያሉት 9 ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

ያሳዝናል! ያሳዝናል! ያሳዝናል! ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ኹና አታውቅም፤ ይፋረደን፤ ይፋረደን !!


 • ‹‹ቤተ ክርስቲያን ስትጠራኝ እምቢ እላለኹ ወይ ! ! !›› /ብፁዕ አቡነ ማትያስ/
 • ‹‹አጃቢ ነን!›› /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
 • ‹‹እንኳን አይደለም ፕትርክናው ጵጵስናውም ከብዶኛል፤ እኔ እጠፋለኹ›› /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ/
 • ‹‹እኛ መናጆ ተብለን ነው የገባነው፤ የሚመረጠው አባ ማትያስ ነው›› /ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ/
 • ‹‹ነገ በታሪክ የሚጠየቅና የሚወገዝ ሲኖዶስና አባት መኖር የለበትም›› /ብፁዕ አቡነ ገብርኤል/
ከላይ በዋናው ርእስ የተመለከተው÷ ቁጭት እንጂ አቅም ያነሳቸው ንግግሮች የተሰሙት ትላንት፣ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም በፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ለመወያየት የተሰበሰበው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በድምፅ ብልጫ ከማስወሰን በላይ ውል ያለው ግልጽ ውሳኔ ላይ ሳይደርስ ከቀትር በኋላ በተጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡

Saturday, February 23, 2013

ሰበር ዜና – የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ያለስምምነት ተቋጨ

 • ‹‹የሚመረጠውን እያወቅን እኛ መናጆ ነን እንዴ!!›› /አራቱ ዕጩ ፓትርያሪኮች/
 • ስብሰባው ያለስምምነት በተቋጨበት ኹኔታ የኮሚቴው ሕዝብ ግንኙነት ቅ/ሲኖዶሱ የዕጩ ፓትርያሪኮቹን ዝርዝር እንዳጸደቀ አድርገው መግለጫ ሰጥተዋል
አርእስተ ጉዳይ፡-
 • አስመራጭ ኮሚቴው ያቀረባቸው አራት ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸውን ከዕጩነት አገለሉ
 • አስመራጭ ኮሚቴው ለምልአተ ጉባኤው በርካታ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ተስኖት ውሏል
 • ኮሚቴው በአምስቱ ዕጩዎች ላይ የተስማማበትን የውሳኔ ቃለ ጉባኤ ማቅረብ አልቻለም
 • አብዛኞቹ ብፁዓን አባቶች በየሀ/ስብከታቸው የደኅንነት ወከባ እንደተፈጸመ ሪፖርት አድርገዋል
 • መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ከኾነ እጁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲያነሣ በአጽንዖት ተጠይቋል
 • ብፁዕ አቡነ ማትያስን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማድበስበስ ተሞክሯል
 • በኮሚቴው ዋና ጸሐፊ እና በሕዝብ ግንኙነቱ መካከል የከረረ ልዩነት ተፈጥሯል
 • ‹‹የኮሚቴው አካሄድ ሕጉን ሥርዐቱን ካልጠበቀ የማስተካከል የማረም የመጨረሻ ሓላፊነቱ የምርጫው ባለቤት የኾነው ቅ/ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊውን ውሳኔ መስጠት ይችላል፤ እኛ ያልነው ይኾናል፤ ሌላ ነገር አንነጋገር›› /የኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ/
 • ‹‹የሚመረጠውን እያወቅን እኛ መናጆ ነን እንዴ!!›› /አራቱ ዕጩ ፓትርያሪኮች/
 •  ‹‹የሚሾማቸው አካል በቀጥታ በደብዳቤ ይሹማቸው [አቡነ ማትያስን] እንጂ በዚህ ዐይነቱ አካሄድ ላይ ፊርማችንን አስቀምጠን አንመርጥም፡፡›› /ብዙኀኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት/
ዜናው በዝርዝር አቀራረብ ይቀጥላል
 http://haratewahido.wordpress.com/

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

ለዕጩ ፓትርያሪክነት ከተለዩት አባቶች ሁለቱ በዕጩነት መካተታቸውን አልተቀበሉትም

 • አቡነ ማትያስ አሜሪካዊ ዜግነታቸውን የመለሱበትን ሰርቲፊኬት እንዲያቀርቡ ይጠበቃል
 • የእነንቡረ እድ ኤልያስን ጫና አንቀበልም ያሉ መራጮች እንዲቀየሩ እየተደረገ ነው
 • የጨለማው ቡድን በአቅምና በሰው ኀይል ተጠናክሮ በአራራት ሆቴል ዳግም እየተደራጀ ነው
 • የአስመራጭ ኮሚቴው አንዳንድ አባላት በተናጠል ማስፈራሪያ ተደርጎባቸዋል
 • ‹‹በሃይማኖት አክራሪነት ለኦርቶዶክስ የበላይነት ብቻ የሚቆሙ ናቸው፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የመንግሥትን ድጋፍ ያጡበት ምክንያት/
 • ‹‹አዲስ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ተመርጦ ምርጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፍ አለበት፡፡›› /አስተያየት ሰጭዎች/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት የለያቸውን አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ነገ፣ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚሰበሰበው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያቀርባል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው የካቲት 14 ቀን ለይቶና አጣርቶ ከተፈራረመባቸውና በነገው ዕለት ለቅዱስ ሲኖዶሱ ለማቅረብ ካዘጋጃቸው አምስት ዕጩ ፓትርያሪኮች መካከል ሁለቱ ግን በዕጩነት በመካተታቸው እንደማይስማሙ ነው ከወዲሁ እየተነገረ የሚገኘው፡፡ በዕጩነት መካተታቸውን እንደማይቀበሉት የተነገረላቸው ሁለቱ የኮሚቴው ዕጩ ፓትርያሪኮች የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የወላይታና ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ናቸው፡፡

Friday, February 22, 2013

ሰበር ዜና – የኢትዮጵያው ቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ‹‹ዐራተኛው ፓትርያሪክና አብረዋቸው ያሉ አባቶች ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ስሕተቶች ከዛሬ ጀምሮ ‹‹በጽሑፍ፣ በሚዲያና በልዩ ልዩ ጉባኤያት ይፋ አደርጋለኹ፤›› አለ


 • ሕዝቡ በውጭ የሚገኙት አባቶች የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ የማያቋርጥ ተጽዕኖ እንዲያደርግባቸው፣ ለ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ ትብብሩንና ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልእኮ በዓለም ዙሪያ ጎልብቶ እንዲቀጥል የተለመደ ድጋፉንና ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዛሬ፣ የካቲት 14 ቀን ረፋድ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫው÷ በሰሜን አሜሪካ በስደት ባሉት አራተኛው ፓትርያሪክና ሌሎች አባቶች የተቋቋመው ሲኖዶስ አውጥቶታል ለተባለው የሐሰት መግለጫ የተሰጠ አጸፋ መኾኑ በርእሱ ተመልክቷል፡፡
የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች÷ አራተኛው ፓትርያሪክ በቅዱስ ወንጌልና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተደነገገውን በመጣስ የዚህን ዓለም ሹመት ከመንፈሳዊው ሹመት ጋራ አዳብሎ በመሥራት ይከሣቸዋል፤ የፓትርያሪክነቱም ሥልጣን የጨበጡት ‹‹የገዥዎችን ኀይል ተጠቅመው፣ ሲኖዶሱን ተጭነውና መንፈስ ቅዱስን ተጋፍተው ነው፤››  ይላል፡፡ ይህንኑ ሥልጣን በራሳቸው ጥያቄ ማስረከባቸውን የሚያስታውሰው መግለጫው÷ ሲኖዶሱ ጥያቄያቸውን አጥንቶ፣ ቀኖናው የሚለውን ጠብቆ ከሥልጣን ካነሣቸው በኋላ ዐራተኛው የቀድሞው ፓትርያሪክ ‹‹ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓትርያሪክ አይደሉም›› በማለት ውሳኔውን ያብራራል፡፡

ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!


 • ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
 • ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
 • የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
 • ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-
1)  ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ
2)  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3)  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4)  ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
5)  ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

Thursday, February 21, 2013

አስታራቂ ጉባኤው መግለጫ አወጣ

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 13/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 20/2013/ PDF)፦ በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት ላማራቅና ዕርቅ ለማውረድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ አወጣ። የመግለጫው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር ቤትና በውጭው ዓለም የሚገኙ አባቶችን በማስማማት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በዝርዝር ለመግለጽና የዕርቁ ሒደት ምን ይመስል እንደነበር በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ለሚኖሩ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምርን እንዲያውቁት ለመግለጽ ነው” ያለው መግለጫ ዝርዝር ሐሳቦችን አካቷል። ሙሉ ቃሉን ከዚህ በታች ተመልከቱ።በወቅታዊው የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ።
የካቲት12/2005ዓ.ም
Feb 19/2013

የመግለጫው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር ቤትና በውጭው ዓለም የሚገኙ አባቶችን በማስማማት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በዝርዝር ለመግለጽና የዕርቁ ሒደት ምን ይመስል እንደነበር በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ለሚኖሩ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምርን እንዲያውቁት ለመግለጽ ነው።

የውጪውን ጠላት ለመመከት በቅድሚያ የውስጥ ችግሮቻችንን ማስወገድ ይኖርብናል


ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችም” በሚለው መጣጥፍ መነሻነት የተዘጋጀ ….
(ከመልዐከ ብሥራት፣ ቨርጂኒያ/PDF)፦ ጌታቸው ኃይሌ ናቸው ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ።በቅድሚያ ልባዊ ምሥጋናዬና አክብሮቴ ይድረሳቸው፡፡ በዚህ ጽሑፌ የምናገረው በእውነት ለቤተክርስቲያን ለሚጨነቁ ምዕመናንና አገልጋዮች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አንድዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ አሁንም እያለፈች ነው፡፡ እግዚአብሔር አይበለውናምናልባት የከፋው ፈተና ያለው ከፊት ለፊታችን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህም ሰበቡ ችግሮቻችንንበቅጡ ካለመረዳታችንና ከቸልተኝነታችን የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችንችግሮች በተለይ በውጪው ዓለም ምንና ምን ናቸው?

Wednesday, February 20, 2013

ስለ መንበረ ፕትርክናው ዕጩዎች የቅድመ ምርጫ ግምት


 • ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘኢየሩሳሌም ረቡዕ አዲስ አበባ ይገባሉ
 • ካህናት፣ የገዳማትና አድባራት አለቆች ብፁዕነታቸውን እንዲመርጡ እየተወተወቱ ነው
ኀምሳ አራት ዓመት ወደ ኋላ፤ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያሪክ ለኢትዮጵያ የተገኘው ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ዕጨጌ ወጳጳስ ሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም በ116ው የእስክንድርያ ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ በተቀቡ ጊዜ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው ለከፍተኛው ማዕርግ በበቁበት የፓትርያሪክነት ሢመታቸው ወቅት እዚያው ግብጽ ካይሮ ይገኙ በነበሩት ግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ ፊት ካሰሙት ታሪካዊ ንግግር መካከል÷ ‹‹ወደዚህ ወደ ከፍተኛው ማዕርግ ለመድረስ ሲፈቀድልኝ ለግርማዊነትዎ ያለኝን የታማኝነት ቃል ኪዳን በፊትዎ ቆሜ ለማረጋገጥ አጋጣሚ ምክንያት አግኝቻለኹ፤›› የሚለው ይጠቀሳል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ከ1951 – 62 ዓ.ም በፓትርያሪክነት ሲያገለግሉ ቆይተው በተወለዱ በ73 ዓመታቸው ጥቅምት 2 ቀን 1962 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ተቀብረዋል፡፡ ከዚያ ወዲህ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ፓትርያሪክ እየተመራች ኤጲስ ቆጶሳትን ትሾማለች፡፡Hossaena BeArayam

Saturday, February 16, 2013

የጠቋሚዎች መብዛት ለዕጩነትና ለፓትርያሪክነት መመረጥን አያረጋግጥም


 • ለአቡነ ሳሙኤል የተካሄደው የጠቋሚዎች ዘመቻ የኮሚቴውን አባላት አስጨንቋል
 • በቡድን የተሰጡ ጥቆማዎች ተቀባይነት አላገኙም
 • ዕጩዎችን ለመለየት ከምርጫ ሕገ ደንቡ በተጨማሪ አለ የተባለው አሠራር አነጋግሯል
 • ከሀገር ውጭ ስምንት አህጉረ ስብከት መራጭ ተወካዮቻቸውን ይልካሉ ተብሏል
 • ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሚቴው አባላት መካከል ተገኝተዋል
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ፣ የካቲት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ ሁለተኛ ዙር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ከተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ በተለየ አኳኋን በሦስት ዙር ከጋዜጠኞች ለቀረቡት በርካታ ጥያቄዎችም የኮሚቴው አባላት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ሁለተኛ ዙር መግለጫ ሰጠ


አርእስተ ዜና፡-
 • የጸሎተ ምሕላው ሱባኤ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ይቀጥላል
 • ኮሚቴው የለያቸውን ዕጩዎች የካቲት 14 ቀን ለቅ/ሲኖዶስ ያቀርባል
 • ከአንድ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ጥቆማዎች በላይ እንደተሰበሰበ ተገምቷል
 • ጥቆማ ለኮሚቴው በግብአትነት ብቻ የሚያገለግል ነው
 • የጠቋሚ ብዛት ለዕጩነት መመረጥን አያመለክትም፤ አንድ አባት በአንድ ሺሕም ተጠቆመ በአንድ ሰው ያው ጥቆማ ነው፤ ዕጩው የሚለየው በፓትርያሪክ መመዘኛ መስፈርት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ ነው፡፡
 • ምርጫው ዓለማዊ ሳይኾን እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማገልገል የሚካሄድ የቤተ ክርስቲያን ምርጫ በመኾኑ ከምንም ዐይነት ተጽዕኖ የጸዳ ነው ተብሏል
 • ሰባክያነ ወንጌል በዐውደ ምሕረት ካህናትንና ምእመናን ለዕጩ ጥቆማ እንዲቀሰቅሱ በመደረጉ፣ ሚዲያውም በማገዙ በዚህም መሠረት የነቃ ተሳትፎ በመታየቱ ጥቆማው ለአዲስ አበባ ብቻ ነው የተሰጠው የሚለው የተጋነነ ነው
 • ዕጩዎች በሕዝብ ጥያቄና አስተያየት የሚተቹበት የ15 ቀን ጊዜ እንዲታጠፍ የተደረገው ምርጫውና ሢመቱ በጾም ውስጥ እንዳይካሄድ፣ ጊዜውም ተራዝሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለአባት ለተጨማሪ ጊዜ እንዳትቆይ አስመራጭ ኮሚቴው አዘጋጅቶ ለቋሚ ቅ/ሲኖዶስ ባቀረበውና ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ባጸደቀው ልዩ ፕሮፖዛል መሠረት ነው፡፡
 • ትክክለኛው የመራጮች ቁጥር ከ800 በላይ ሊደርስ ይችላል፤ ኮሚቴው በቃለ ጉባኤ ወስኖ በቀጣይ ያስታውቃል፡፡
 • የስድስተኛው ፓትርያሪክ መራጮች ቁጥር ከዚህ ቀደሙ የላቀ እንደኾነ መገለጹ በሦስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ከተሳተፈው 1133 መራጭ አንጻር ጥያቄ ተነሥቶበታል
 • ‹‹ወደ ምርጫው የተገባው ዕርቀ ሰላሙ ተዘግቶ አይደለም፤ እርሱ እንደቀጠለ ነው፡፡››
 • የጋዜጠኞችና የሚዲያ ተቋሞቻቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ሊገታ እንደሚገባው ዐቃቤ መንበሩ አሳስበዋል –‹‹ጋዜጠኞች በሞያቸው ሞጋቾች ቢኾኑም ጠበቃም እንዲኾኑ ያስፈልጋል፡፡›› /ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል/
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
Source: http://haratewahido.wordpress.com/

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Wednesday, February 13, 2013

“በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” (ኤፌ. ፬፥፫)


/ውሉደ አበው ዘተዋሕዶ/
ቤተ ክርስቲያን ከፓትርያርክ ምርጫና ከአንድነት የትኛውን ልታስቀድም ይገባታል? ስለምን?
ክፍል ሁለትና የመጨረሻው
አባቶቻችንን እንዲህ ከፋፍለን እንድናያቸው ያደረግን ሌላ ሳይሆን ለእናት ቤተክርስቲያናችን አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጥ ችግሯ እየሰጡት ያሉት ምላሽ እንደሆነ ግልጽ ነው ብለን እናምናለን፡፡ሰው ያልበላውን ቢያኩለት እንዴት መፍትሔ ሊሆነው ይችላል? እንዲያውም ያልበላውን ያከኩ ጊዜ ሌላ ሕማም ወይም ስቃይ ጨመሩለት እንጂ እንዴት መድኃኒቱ ይሆናል? እግሩ ቆስሎ ሐኪም ቤት የሄደን ሰው እጁን ቢዳስሱለት ምን ይበጀዋል? ወይስ ዐይኑን ለታመመ ወገቡን ቢያክሙት ምን ይጠቅመዋል? ይህንን ጌታችን በወንጌል እንዲህ ሲል ገልጦታል። አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ሉቃ ፲፩፥፲፩። የሚያስፈልገው ሌላ የተሰጠው ሌላ። መፍትሔው ሌላ በመፍትሔነት የቀረበው ደግሞ ሌላ። ዓሣ መፍትሔው ሲሆን የሚሰጠው እባብ ከሆነ ሰጪውስ ሰጪ ነውን?
ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ያዘነችበት የተጎዳችበት ዋና ጉዳይ እያለ እርሱን ሁለተኛ ወይም መጨረሻ አድርጎ በመመልከት ቤተ ክርስቲያን እፎይታ ልታገኝ አትችልም። ዓሣ ስትጠይቅ እንዴት እባብ እንሰጣታለን? ባጎረሰች እንዴት ትነከሳለች። ለመሆኑ ለወቅታዊው የቤተ ክርስያን ችግር ትክክለኛው መፍትሔ የቱ ነበር? ምንም እንኳ ሂደቱ ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ነው ለማለት ባይቻልም ከላይ እንደገለጽነው የአባቶቻችን ልዩነት ጎልቶ የወጣው ለዓሣው ጥያቄ  ምላሹ እባብ ሆኖ በቀረበው የፓትርያሪክ ምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ በአንደኛ ወገን ያሰቀመጥናቸው ወገኖች እርቀ ሰላሙ እየቀጠለ ነገር ግን ያለምንም መዘግየት የፓትርያሪክ ምርጫ መካሄድ አለበት ሲሉ ሁለተኞቹ ምናልባትም ድምፃቸው ባልፈለጉት መንገድ የታፈነባቸው ደግሞ ያልታረቀች ቤተ ክርስቲያን እንዴት ለሹመት ትጣደፋለች በማለት ልዩነታቸውን ቢያስቀምጡም ለጊዜውም ቢሆን የመጀመሪያዎቹ ያሸነፉ በሚመስል መልኩ የብዙዎቹን ፍላጎት እነደረመጥ በማዳፈን የምርጫ ሽርጉዱ ተጀምሯል፡፡

የአስመራጭ ኮሚቴው መርሐ ግብር የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡን የጣሰ ነው

asmerach com
የአስመራጭ ኮሚቴው መግለጫ ሲነበብ

 • የኮሚቴው መሪ ዕቅድ የጸደቀው በቋሚ ቅ/ሲኖዶስ መመሪያ መሠረት አይደለም
 • በዕጩዎች ላይ የሕዝብ አስተያየትና ጥያቄ የማስተናገጃው ጊዜ 15 ቀን አይሞላም
 • የኮሚቴው ሰብሳቢ ከመግለጫው ቀን በፊት በኮሚቴው ስብሰባዎች አልተገኙም
የስድስተኛውን ፓትርያሪክ ምርጫ እንዲያስፈጽም የተሠየመው ኮሚቴ፣ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው መግለጫ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡንና ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ የሰጠውን መመሪያ የጣሰ መኾኑ ተገለጸ፡፡
‹‹፮ው ፓትርያሪክ የሚሾሙበትን ቀንና የምርጫውን ሂደት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ ለማድረግ›› በሚል ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ÷ ምርጫውን የሚያስፈጽምበትን መሪ ዕቅድ ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ አቅርቦ እንዳጸደቀ ጠቅሶ ነበር፡፡ ይኹንና የመንበረ ፓትርያሪኩ ሐራዊ ምንጮች ዘግይተው እንዳስታወቁት፣ የኮሚቴው መሪ ዕቅድ በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ መሠረት÷ ኮሚቴው በተቋቋመ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማሰናዳት የሚገባውን ዝርዝር የድርጊት መርሐ ግብር ለቅዱስ ሲኖዶሱ አቅርቦ ሊታይና ሊወሰንበት ይገባ ነበር፡፡ በዚህም አገባብ ተፈጻሚ እንዲኾን ኮሚቴው በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ መመሪያ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ነገር ግን ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በኮሚቴው ይፋ የተደረገው መሪ ዕቅድ በሕገ ደንቡ መሠረት ቅ/ሲኖዶሱ ያላየውና ያልወሰነበት እንደኾነ ነው ምንጮቹ የሚያስረዱት፡፡

“በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።” (ኤፌ. ፬፥፫)


/ውሉደ አበው ዘተዋሕዶ/
ቤተ ክርስቲያን ከፓትርያርክ ምርጫና ከአንድነት የትኛውን ልታስቀድም ይገባታል? ስለምን?
ክፍል አንድ
ለሺህ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ የሚለውን የቆየ ብሂል ስንሰማው ወይም ስንናገረው የኖርነው ነውና አዲስ አይሆንብንም። ለፍልጥ ብቻ ሳይሆን ተበታትነው ላሉ የተለያዩ ነገሮች ሁሉ ልጥም ባይሆን በመልክ በመልካቸው አንድነት እንዲቆሙ ለማድረግ የሚያስችል አንድ ማሰሪያ አይጠፋም። የማሰሪያው መኖር አንድነቱን ያጸናዋል። አንድ የሆነ አካል ወርዱም ስፋቱም ርዝመቱም ይታወቃል። ቅርጽና ጠባዩም ይለያል። የአንዱ መኖር የሌላውም የሕልውና መሠረቱ ነውና አንዱ ሌላውን እንደ ዐይኑ ብሌን ይጠብቀዋል። አንዱ ለሌላው ውበቱም ጥንካሬውም ማንነቱም ሥልጣኑም ነው። ከሺሁ መካከል አንድ ስትጎድል የታሰረው ፍልጥ ይላላል። አንዲት ስትጎድል አንድነት አደጋ ላይ ይወድቃል። ስለሆነም አንዲትም ስንኳ እንዳትሾልክ የሁሉም ፍልጦች ሓላፊነት ነው። ካመለጠችና ከሾለከች ግን ሌሎቹም ጠብ ጠብ እያሉ መሹለካቸው አይቀርም። ሰለሆነም አንዷን ማጣት ሁሉንም ከማጣት አይተናነስም። በመሆኑም አንዷ እንዳትነጠል ወይም እንዳትባዝን የሚከፈለው መሥዋዕትነት ሰለሁሉም ተደርጎ ይወሰዳል።

አቶ ስብሓት ነጋ ፍርዳቸውን ሲጨርሱ. . .


 • ‹‹ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች መሰቀል አለባቸው፡፡››
  Sebhat's Clock ticking to. . .
  ባለቀ ሰዓት፣ በተቆጠረ ዕድሜ.….
 • ‹‹ታምራት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቅ አይችልም፡፡››
 • ‹‹[ሲኖዶስ ማቋቋም] በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከግራኝ ከጉዲት የባሰ ትልቅ  ወንጀል ነው፡፡››
(አቶ ስብሓት ዛሬ ለንባብ ከበቃው ላይፍ መጽሔት ጋራ ካደረጉት ቃለ ምልልስ)
 • ‹‹ኣቦይ ስብሃት አረጋዊ ናቸው፤ ይሄ የመነጣጠል አባዜ ቢቀርባቸውና ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደው የተጣላ ቢያስታርቁይሻላቸዋል፡፡. . .አርባ ዓመት ሙሉ ቀውስ አታቀጣጥሉ በሉልኝ፡፡›› /አቶ ኣስገደ ገብረ ስላስ ለኢትዮ ምኅዳር ጋዜጣ/

ሩጫው ማንን ለመቅደም ነው?


ከውሉደ አበው ዘተዋሕዶ
Patriarchal competition
የፕትርክናው መንበር
አሁን ፮ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ የሚካሄደው ሩጫ እጅግ አስገራሚ ይመስላል። ምክንያቱም፣
፩. በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመናን እና የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል ብለው ቆርጠው የተነሡ የጡመራ መድረኮች ከምርጫው በፊት እርቀ ሰላም ይቅደም የሚለውን ፍጹም ክርስቲያናዊ አካሄድ በመደገፍ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ባለበት ወቅት
፪. በራሳቸው ተነሳሽነት የማንንም ጉትጎታ ሳይፈልጉ አባቶች እንዲታረቁ እናም አንድ እንዲሆኑ ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ውድ ጊዜያቸውን በማበርከት ቀንና ሌሊት ሲለፉ የቆዩት የአስታራቂ ሽማግሎች “የእባካችሁ ታረቁልን” ልመና ባልቆመበት ወቅት
፫. የተለያዩ የአብያተ ክርስቲያናት እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ጥምረቶች ከፓትርያርክ ምርጫ ይልቅ ታርቃችሁ እንያችሁ እያሉ የተለያየ ተማኅጽኖ እያሰሙ ባሉበት ጊዜ
፬. ከራሳቸው ከአባቶች መካከል የተወሰኑት ሳንታረቅ የምን ፓትርያርክ እያሉ በሚቃወሙበት ሰዓት

Thursday, February 7, 2013

የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ መርሐ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች


የ፮ው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ፣ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ቡራኬ ሥራውን እንደጀመረ ያስታወቀውና በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሰብሳቢነት የሚመራው አስመራጭ ኮሚቴው፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጠው ባለዘጠኝ ነጥብ ጋዜጣዊ መግለጫ ለ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ ሂደት የወጣውን የምርጫ መርሐ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡
በዐቃቤ መንበሩ ጸሎት የተከፈተው የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫው አስፈላጊነት÷ ‹‹የምርጫውን ሂደትና 6ኛው ፓትርያሪክ የሚሾሙበትን ቀን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ ለማድረግ›› እንደኾነም ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአሜሪካ በሚገኙ አባቶች ሲኖዶስ ላይም ሊዘምት ነው


 • አራተኛውን ፓትርያሪክ ጨምሮ ሦስት አባቶች ተተኩሮባቸዋል
 • ጠ/ቤ/ክህነቱ ለዶክመንተሪው ስርጭት ከብር መቶ ሺሕ ብር በላይ መክፈሉ ተነግሯል
የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙ አባቶች ላይ ያነጣጠረ ዶኩመንተሪ etv_liveለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተሰማ፡፡
‹‹የነውጥን ጎዳና የመረጡ የሩቅ አገር ናፋቂዎች›› በሚል ርእስ መቀናበሩ የተነገረለት ይኸው ዶኩመንተሪ÷ በዋናነት፣ በአራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እና አቡነ መቃርዮስ ላይ የሚያተኩር ነው ተብሏል፡፡