Wednesday, August 8, 2012

ውዳሴ ማርያም አንድምታ ዘይትነብብ በዕለተ ስሉስውዳሴሃ ለእግዝትነ ማርያም ድንል ወላዲተ አምላክ ዘይትነብብ በዕለተ ሠሉስ 
ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣች የብርሃ ምንጻፍ ይነጸፋል የብርሃን ድባብ ይዘረጋል ከዚያ ላይ ሁና ሰላም ለከ ፍቁርየ ኤፍሬም ትለዋች እርሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል ወድሰኒ ትለዋች በዕለተ 
ሰኑይ ድርክር አልቋልና ባርክኒ ይላታ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በሳዕሌከ ትለዋች ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡ ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴ በሠሉስ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ ይላል ቃለ ጸሐፊ ነው፡፡ እርሱ ግን አክሊለ ምክሕነ ይጀምራል አክሊለ ምክሕኒ፡፡ አክሊል የወዲህኛው ምክሕ የሰዲያኛው፡፡ ወቀዳሚተ መድኃኒትነ፡፡ ቀዳሚት የወዲህኛው መድኃኒት የወዲያኛው፡፡ መወሠረተ ንጽሕነ፡፡ መሠረት የወዲህኛው ንጽሕ የወዲያኛው፡፡ ኮነ በማርያም፡፡ በማርያም ድንግል ሆነልን አለ በዚህ ቀን ከነገሥታት ዳዊትን ከመሳፍንት ኢያሱን ከደናግል ኤልያስን አስከትላ መጥታለች ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት በህትባ የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለህም፡፡ ኢያሱም መድኃኒት ብትባል የደኅንነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም፡፡ ኤልያስም ንጹሕ ድንግል ብትባል የንጽሕናችን መሠረት ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ምርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም አክሊሎሙ ለሰማዕት እንዲለው አክሊለ ሰማዕት የሚባል ጌታ ጥንተ ሕይወቶሙ እንዲለው ጥንተ ሕይወት የሚባል ጌታ አኃዜ ዓለም በእራኁ ኲሉ ኁዝ ውስተ እዴሁ መሠረተ ዓለም ይጾውር ድደ ወይነብር ጠፈረ እንዲል፡፡ መሠረተ ዓም የሚባል ጌታ በድንግል ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው፤ ለጊዜው መልክ ከደም ግጋት ስተባብራ ተገኝታለች ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና አንድም ጸጋ ወሀብት ማለት ነው፤ ለጊዜው ለናት ላታቷ ጸጋ ሁና ተሰጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁሉ ጸጋ ሁና ተሰጥታለችና አንድም መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማት ነው፡፡ ምዕመናንን መርታ ገነት መንግሥተ ሰማያት አግብታለችና አንድም ልዕልት ማለት ነው ሮም አአርያ ማለት ልዑል ማት እንደሆነ፡፡ እርስዋንም መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ይላታልና፡፡ አንድም ማኅበረ መሃይምናን ወሕዝብ ተለአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ተፈሥሒ ቤተ እስራኤል ወተሐሠዪቤተ ይሁ ማለት ነው፡፡ አንድም ማርያም ማት እግዝእተ ብዙኃን እንዲ አይለውም ብሎ ማርያም ማለት ቅሉ እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ አብሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት እንደሆነ፡፡ እንተ ወለደት ለነ ዘአእግዚአብሔር ቃለ፡፡ መመኪያነቷን በቅጽል አመጣው አካላዊ ቀልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኝልን፡፡ ዘኮነ ሰብአ በእንተ መድኃኒትነ፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ፡፡ እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ፡፡ ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው ፡፡ ሐራ ጥቃ ቃል ሥታ ኮነ ያውን ይዘው ወደታች ተለወጠ ይላሉና፡፡ ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው፡፡ ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡ ስለዚህ ነገር ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡ መንክር ኀይለ ወሊዶታ ዘኢይ ትነገር፡፡ ድንቅ የሚሆን የመውለዷ ሥራ የማይመረመር ነው ፡፡ የማይመረመር የመውለዷ ሥራ ድንቅ ነው፡፡ በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለሚኚልን፡፡ ሐተታ እንደ ሰኞ፡፡ እስመ በፈቃዱ፡፡ በርሱ ፈቃድ፡፡ ወበሥምረተ አቡሁ፡፡ ባበቱ ፈቃድ ወመንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ፡፡ መጽአ ወአድኃነነ፡፡ ሰው ሆኖ አዳን፡፡ አንድም ሰው ሁኖ አድኖናልና፡፡ መንድር ብህ እስር፡፡ መጽአ በኲርሕ፡፡ በግድ ሰው ሆነ የሚሉ መናፍቃን አሉና እሰመ በፈቃዱ አበባቸው፡፡ በዕለተ ፍጥረት አብ መንፈስ ቅዱስ፡፡ አዳም ስሑት ፍጥረት ነው፡፡ አይፈጠር ቢሉ ወልድ እኔ ያዛለሁ ይፈጠር ብሎ ነበርና በግድ ሰው ሆነ የሚሉ መናፍቃን አሉና እስመ በፈቃዱ አለባቸው፡፡ እሊህንም እመቦ ዘይቤ ተሐብዩ ለብእሲ እምቅድመ ይፍጥሮ ውጉዘ ለይኩን ብሎ ሊቁ በዐሥራ አንደኛው ግዝት አንሥቷቸዋል፡፡ ኒህስ ምን ያለውን ይዘው ተነሥተዋል ቢሉ በዕርገተ ኢሳይያስ ሰማዕኩ እዘ ይአኤዝዞ እግዚእ ለእግዚእየ ወይቤሎ ኅልፍ እንተ ሰብዐቱ አናቅጸ ሰማያት ወረደ ላዕሌሁ ለመልአከ ሞት ካው ተሐብዩ የሚል ጥሬ አገኘን ብለው ይኸንን ይዘው ተነሥተዋል፡፡ ዐቢይ ውእቴ ስብሐተ ድንግልናኪ አማርያ ድንግል ፍጽምት፡፡ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትሆኚ እመቤታችን በድንግልና ጸንተሸ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ ርከብኪ ሞገስ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡ እግዚ አብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሸልና፡፡ አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ላንች የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ አንቲ ውእቱ ሰዋሰው ዘርእየ ያዕቆብ እምድር ዘይበጽሕ እስከ ሰማይ ወመላእክተ እግዚአብሔር የዐርጉ ወይወርዱ ወስቴታ፡፡ መጽሐፍ ምሥጢር እንጂ ዘይቤ አይጠነቅቅምና ዘይበጸሕ ብሎ ውሰቴታ አለ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላእክት ስወጡባት ሲወር ዱባት ያዕቆብ በፍኖት ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ ታሪክ ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሲሄድ ሎዛ ሲደርስ ጊዜ መሸበት ከመንገዱ እልፍ ብሎ ድንጊያ ተንተርሶ ተኛ ሌሊት በራእይ የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ዙፋን ባላዋ ላይ ተዘርግቶ ንጉሥ በላዋ ላይ ተቀምጦባት ሲወርዱባት ዙፋን ባላዋ ላይ ተዘርግቶ ንጉሥ በላዋ ላይ ተቀምጦባት ያያል ሲነጋ ተነሥቶ ደንጊያ ተክሎ ዘይት አፍስሶባት ዛቲ ይአቲ ኆኅታ ለሰማይ ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር ብሎ ይሔዳል፡፡ ይኸም ምላሴ ነው የወርቅ መሰላ የመቤታችና ደንጊያው የትንቢተ ነቢያት እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ጸንታ ለመገኘቷ ምሳሌ፡፡ ድንግል አምሳ ወትንቢት ዘነቢያት እንዲል፤ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት አለ ቤታችን ከመቤታችን ሰው ከነሆኑ አስቀድሞ ለተልእኮ አይወጡም አይወርዱም ነበር ጌታችን ከመቤታችን ሰው ከሆነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ሆነዋልና አንድም የዐርጉ ሰው አምላክ ሆነ ይወርዱ አምላክ ሰው ሆነ እያ፤ ዙፋ የማኅፀኑዋ ንጉሥ የጌታ ምሳሌ፡፡ ንድም ደንጊያው የታቦት ዘይት የሜሮን ምሳሌ፡፡ አንድም ያዕቆብ የቀሳውስት ደንጊያው የአሕዛብ ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ፡፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግ፤ማ እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡: ይቆየን...........ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ስሉስ ክፍል 2
በእንቁ ከተመሰለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልናእመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፡፡

ተፈስሂ ወላዲተ እግዚእ ሐሤቶሙ ለመላእክት፡፡

የመላእክት ደስታቸው የሚሆን ጌታን የወለድሽው ተፈስሂ ደስይበልሽ፡፡ ለልሁ ዓለሞሙ ወለሊሁ ተድላሆሙ ወለሊሁ ሀገሮሙ እንዲል፡፡ አንድም ስጋዌውን ተልከው ለነቢያት የሚነግሩ መላእክት ናቸውከዚህ የተነሳ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ኤተውት ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምደር ብለው አመስግነውት በጣእምላይ ጣእም በጸጋ ላይ ጸጋ ጨምራለቸው ደስ ብሎአቸዋልና፡፡ አንዱም የመላእክት ደስታቸው የምትሆኚ ጌታን የወልሽ፡፡ ተፈስሂ ደስይበልሽ፡፡ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን እነያዩ ደስ ይላቸዋልን እና ሐሴቶሙ ለመላእክት አለ፡፡

ተፈስሂ ንጽህት ዜናሆሙ ለነቢያት፡፡

የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽህት ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ኦደንግል አምሳል ወተንቢት ዘንቢያት አንዲል፡፡

ተፈስሂ እስመ ረከብኪ ሞገሰ እነግዚአብሔር ምስሌኪ ፡፡

እግዚአብሔር በነፍስሽ ነግስ ከስጋሽ ስጋ ነስቶ ካንቺ ጋራአንድ ባሕርይ ሆኗልና፡፡ (ተፈስሐ) ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ በለሟልናት 
አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡

ተፈስጆ እስመ ተወከፍኪ ቃሎ ለመልአክ ፍስሐ ኩሉ ዓለም፡፡

የሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን የመለአኩን ቃል እንደ ኒቆዲሞስታትከራከሪ እንደ ዘካርያስ ሳትጠራጠሪ አምነሻልና ተፈስሂ ደስ ይበልሽ ሰብዓ ፊንቆን ተወክፍዎ፡፡ በእለሰ ተወከፎ ወሃቦሙ ስልጣነእንዲል ፍስሐ ኩሉ ዓለም ያለው ለመላክ ሚቀጽሉ ምስጋው ተፈስሂ ተፈስሂ እያለ ነውና ቃል ላለው ቢቀጽሉ ወነዋ ተወልደ ፍስሐ ዘይከውንለክሙ ወለኩ ዓለም ይለዋልና፡፡

ተፈስሂ ወላዲተ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም፡፡

ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታ የወለድሽው ተፈስሂ ደስ ይበልሽ፡፡

ሰዓሊ ለነ ቅድስት፡፡

ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንእት በድንግልና እመቤታችንጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን፡፡

ተፈስሂ እስመ ድልወ ተሰመይኪ ወላዲተ አምላክ፡፡

እሙነ ሲል ነው በውነት ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ተፈስሂደስ ይበልሽ ንስጥሮስ ህስወኬ ተስመይ ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ወአማነ ትሰመይ ወላዲተ ሰብእ ብሏታልና እሙነ አለ፡፡ አንድምበሚገባ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ተፈስሂ ደስ ይበልሽ በስጋ እንጂ በመለኮቱ አትወልደውም እና ማለት ከሷዋ አልተከፈልም እና ሲልነው፡፡ ወአኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ ዘከመ ስርዓተ ትስብእቱ እንዲል፡፡ አንድም ድሎት ሲል ነው በቅተሸ ብትገኚ ወላዲተ አምላክተብለሻልና ወሶብ ረከበ ስጋሃ ቅዱስ ወንፍሳ ቅድስት ፈጠረ ሎቱ በመንፈስ ቅዱስ ሕያው መቅደሰ እንዲል ፡፡

ተፈስሂ መድሃኒታ ለሄዋን፡፡

የሄዋ ድህንነቷ ተፈስሂ ደስ ይበለሽ ዘግይቶ ይከብሩ በልጅ፡፡ወድቆ ይነሱ በእጅ እንዲሉ በሄዋን ሁሉን መናገር ነው ከሁሉ አንዱ ሰለሞን በአለ አእምሮ ንጉስ ነበረ ኋላ መፍቀሬ እንስት ሆነብዙ ሃጢአት ሰራ በፍጻሜ ዘመኑ ንስሐ ቢገባ አይዞህ መርገም የልወደቀባት ንጽሕት ዘር ከአዳም ባህርይ ተከፍላ በሴት አካል ተቀርጻለችከዚያ ሲወርድ ሲዋረድ ከኖህም ወደ ያፌት ወደ ካም አልሄችም በሴም አካል ተቀርጻለች ከዚያም ሲወርድ ሲዋረድ በአብርሃም ከአብርሃምከኬጡራ ወደ ተወለዱ ወደ ስድስቱ ህጻናት ከአጋር ወደ ተወለደ ስምዔል አልሁደችም ቤይሐቅ አካል ተቀርጻለች ከይስሀቅም አንድ ቀንተዘርተው አንድ ቀን የሚታጨዱት ወደ ኤሳው አልሄደችም በያእቆብ አካል ተቀርጻለች፡፡ ከያእቆብ ወደ አስራ አንዱ ወንድሞቹ አልሄችምበይሁዳ አካል ተቀርጻለች፡፡ ከይሁዳ ሲወርድ ሲዋረድ ከእሴይ፡፡ ወሰ ሰብዓቱ እቡዳን ወንድሞቹ አልሄደችም በዳዊት አካል ተቀርጻለች፡፡ከእሷም አምላክ ይወለዳል፡፡ የሮብ ወገኖች ጸልተው ተመቅኝተው ሰቅለው ይገድሉታል እሉያንም የአርዳሜስ ወገኖች አርባ ዘመን ያተፍቸዋልብሎ ከዚያ አያይዞ እስከ ምጽዓተ ድረስ ያለውን ነገር ነግሮታል አይዞህ እርሷን የጸነሰ እርሷን የወለደ ፍዳ የለበትም ብሎ ነግሮታልየእረሷን እማ አባቶች ስንቱና! ብሎ በእርሽ ተስፋ ያመነ በእርሻ ኪዳን የፀ ናፍዳ የለበትም ብሎ ነግሮታል፡፡ አሁን አንዲህ ማለት ደም እንዲህ ሲቀዳ የሆራል ማለት አይደለም ጥንቱን ሰው ሲፈጠር በንጽሐ ጠባይመፈጠሩን በናገር ነው፡፡

ተፈስሂ እንተ አጥበውሎዮ ሀሊበ ለዘይሰሲዮ ለኩሉ ፍጥረት፡፡

ፍጥረትን ሁሉ በፀሕይ አብስሎ በዝናብም አብቅሎ የሚመግበውን እርሱ ጡትሽን ይዘሽ አጥብተሸዋልናተፈስሂ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ሰው ሁሉ ስጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበውን እረሱን ጡትሽን ይዘሽ አጥብተሸዋልና ተፈስሂ ደስ ይበልሽ፡፡

ተፈስሂ ቅድስት እሞሙ ለኩሉ ህያዋን፡፡

የሕያዋን የጻድቃን እናታቸው ንእድ ክብረት፡፡ ተፈስሂ ደስይበልሽ ተጠብቀው ህያዋን ሁነው የሚኖሩበት ማየ ገቦ ከርሷ የተገኘ ከጌታ የተገኘ ነውና፡፡ እንድም ነዋ ወልድኪ ባለ ጊዜ በዮሐንስእኛን ለእሷ መስጠቱ ነውና እሞሙ ለኩሎመ ሕያዋን አለ፡፡

ናንቃአዱ ኅቤኪ ትስዓሊ በእንቲአነ፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ልምኚልንና ትልምኝልን ዘንድ ዓይነ ህሊናችንን ወደአንቺ እንሰቅላለን፡፡

ሰዓሊለነ ቅድስት የቅዱስ ኤፍሬም አለመሆኑ በዚህ ይታወቃልለምኚልንና ትለምኚልን ዘንድ አይልምና፡፡

ድንግል፡፡ ድንግል፡፡

ቅድስት፡፡ ንዕድ ክብርት፡፡

ወላዲተ እግዚእ ጌታን የወለድሽው፡፡

እስመ ወልዲኪ ለነ ንጉሰ መንክር ምስጢር ሀደረ ላዕልኪ ለመድሃኒትዚዓነ፡፡

ድንቅ የሚያሰኝ ተዋህዶ በአንቺ ቢደረግ ንጉስን የወልድሽልንእና ዓይነ ህሊናችንን ወዳቺ እንሰቅላለን አንድም መንክር በአርያሙ የሚባል ጌታ በማህጸንሽ አደረ፡፡

ናርምም እስመ ኢንክል ፈጸሞ ጥንቁቀ ነጊረ በእንተ እበዩለውእቱ ጌባሬ ሰናያት፡፡

ፈጣቴ ፍትረታት ሲል ነው፡፡ ወር እየ እግዚአብሔር ከመ ሠናይእንዲል ሀያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረት የፈጠረ የርሱን የጌትነቱን ነገር ጠንቅቀን ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ናርምም ዝም እንበል፡፡

በብዙኅ መንክር ራእይ

በብዙ ኅብረ መልክእ በብዙ ፆታ ምልክእ፡፡ ሃያ ሁለቱን ሥነፍጥረት የፈጠረ፡፡ አንድም ሀብትኬ ሠናይ መንፈስ ቅድስ፡፡ እንዲል ሀብተ ምፈስ ቅዱስን በብዙ ፆታ ዕድል ዕድል የሚያድል የችሱንየስጋዌውን ነገር ጠንቅቀን ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ናርምም ዝም እንበል ሀብተ መንፍስ ቅዱስ የሚሰጥ እንደ አእምሮው ስረፋትእንደ ሃይማቱ ጽናት ነውና ወበከመ ይደልዎ ይበቁዖ እንዲል፡፡ ዕበይን ሥጋዌ ሲል ምን አለ ቢሉ ወሰእርገወ ዕበይሃ ለጥበብ እንዲል፡፡አነድም ዕበዩ በብዙኅ መንክ ራእይ በብዙ ወገን የተመሰለ በእሳ በጸሓይ በቀላይ ተመሰለ የርስን ያንድነቱን የሦስትነቱን ነበር ጠንቅቀንፈጽመን መናገር ኤቻለንምና ናርምም ዝም እንበል፡፡ የተነገረ በብዙ ኅብረ እምሳል የተሰመሰለ የርሱን የስጋዌውን ነበረ ጠንቅቀንፈጽመን መናገር አይቻለንመና ናርምም ዝም እንበል፡፡ ኀብረ ትንቢት ወነገር ነኒ ከመ ሕፃን ወከመ ሥራው ኣውስተ ምድረ ጽምዕት፡፡ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ እስመ እምኔኪ የወፅአእ ንጉሥ፡፡ ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ተብሎተነግሯል፡፡ ኅብረ አምሳል በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል በአምሳለ ጠል ወፀምር በአምሳለ ብእሲ መካሕ በአምሳለ አንበሳ በፍርህበአምሳለ እብን ቅውም ተመስሏል፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ሥጋዊው በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል በአምሳለ ጠል ወፀምርከተመሰለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩረን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

ቃለ አብ ሕያው ዘወረደ ውስተ ደብረ ሲና፡፡

ወደ ደብረ ሲና የወረደው የአብ አካላዊ ቃል፡፡

ወወሀበ ሕገ ለሙሴ

ለሙሴ ሕገ ኦሪትን የሠራ፡፡

ወከደነ ርእሰ ደብረ በጊሜ ወጢስ በጽልመት ወነፋስ፡፡

የተራራውን ራስ በጨለማ በእሳት በጽጋግ በነፋስ ሸፈነ አካላዊቃል ወበድምፅ ቃለ አቅርንት ይጌሥፅ ለእለ ይቀውሙ በፍርሃት፡፡

ፈርተው የቆሙትን ፈጥኖ ፈጥሮ በሚሰማ በረቂቅ ነጋሪት ድምጽየሚገስጽ ቃል ወቀርኑ ይበልህ እንዲል፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ለምኝልንና፡፡

ውስቱኬ ዘወረደ ኀቤኪ፡፡

ወዳንቺ የወረደው እርሱ ነዋ ታሪክ እስራኤል ከግብዕ ከመጡበኋላ ሕዝቡን በእግረ ደብር ሌዋው ያኑን በመንፈቀ ደብር፡፡ ሙሴ አሮንን በርእሰ ደብር አድርጎ ሰባት የብርሃን መጋረጃ ጋርዶ የተራራውንእራስ በጨለማ በእሳት በጽጋግ በነፋስ ጋርዶ እንዲህ ባለ ግርማ ታቶላቸዋል፡፡ ለኔ ብትገዙ እንዲህ ባለ ግርማ ጠላታችሁን አጠፋላችኋለሁ፡፡ለኔ ባትገዙ እናንተን አጠፋችኋለሁ ሲል፡፡

ዛሬ ንጉሥ ከዳርቻ ከጋብቻ ለመጣ መከዳ ሰይፉን ተንተርሶጠርሙዝ ቦሎታውን ከራስጌ አስቅሎ ኃያላኑን በገራ በቀን አቁሞ አርዕድ አንቀጥቅጥ የሚላ ገምጃ ልብስ ለብኦ አንዲታይ ለኔ ብትገዛእንደህ ባለ ሥልጣን ጠላትህን አጠፋልሃለሁ ለኔ ግን ባትገዛ አንተን አጠፋሃለሁ ሲል፡፡ ይኽም ምሳሌ ነው፡፡ እሳት የፈታሒነቱ ነፋስየመንቅሒነቱ ጽልመት ርቀቱ ምሳሌ ጽጋግ ዕበየ ልዕላናውን ያጠይቃል፡፡ ዘበእንተ ዕበይከ ትትሜሰል በደመናት አንዲል፡፡ ድምፀ ቃለአቅርንት ምጽአተ ንጉሥን ያጠይቃል፡፡ አንድም ሊቁ እምደገብረ ሲና ወፅአ እሳት ወጽልመት ወእምኔኪ ወፅአ አምላክ ወሰብእ እንዲል፡፡ነፋስ የመንፈስ ቅድሰ ጽጋግ ሰው ሲሆን አለመመ መርመሩ እነዘ አብእ መኑ ይክል ያስእምሮ እንዲል ድምፀ ቃለ አቅርንት ምፅአተ ሰብአሰገልን ያጠይቃል፡፡ እምደብረ ሲነ ኮነ ድንጋጼ ወሀውክ ላዕለ አይሁድ ወእምነኪ ኮነ ድንጋጼ ወሀውክ ላዕለ ሄሮድስ ወሠራዊቱ ላዕለዲብሎስ ወአጋንንቲሁ ርኩሳን እንዲል፡፡

ደብር ነባቢት በትሕትና፡፡ ነባቢት በትሕትና ተሰብአ በትሕትናወረደ በትህትና ብሎ ይገጥሟል፡፡ ደብር አላት በደብረ ዲና ሙሴና ጌተ ተነጋግረውባታል እንጂ አርሷ አልተናገረችም ከዚያ ሲለይ ደብርነባቢት አለ፡፡ አንድም ነባቢት በትሕትና አላት መጽሐፈ ኢሳይያስ ስትመለከት ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ከሚል አንቀጽብትደርስ ከዘመንዋ ደርሼ ወትቼ ወርጄ አገልግያት አለች እንጂ ሁኜ አለለችምና፡፡

መፍቀሬ ሰብእ ተሰብእ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ፡፡

ሰውን የሚወድ ሰው የሚወደው ጌታ ሳለወጥ ካንቺ ከሥጋሸ ሥጋከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆነ፡፡

ፍጹመ ሥጋ ነባቤ ዘከማነ፡፡

እንደና የሚናገር ሥጋን ነስቶ ሰው ሆነ አንድም ነባቢ ይላልእንደኛ በሚናገር ሥጋ የተፈጸመ ሆኖ፡፡ በመንፈስ ጥበብ አማላክ ኅደረ ላዕሌሃ፡፡

ጥበብን በሚገልጽ ሥጋዌን በሚያስፈጽም በመንፈስ ቅዱስ አምላክበማኅፀንዋ ቢያደር፡፡

ኮነ ፍጹመ ሰብአ፡፡

ፍጹም ሰው ሆነ፡፡

ከመ ያድኅነ ወይስረይ ኃጢአቶ ለአዳም፡፡

አዳምን ድነው ዘንድ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘንድ፡፡

ወያንብሮ ውስተ ሰማያት፡፡

በሰማያዊ ቦታ በሰማያዊ መዓርግ ያኖረው ዘንድ

ወያግብኦ ኅበ ዘትካት መንበሩ፡፡

ወደ ቀደመው ቦታው ወደ ቀደመው ክብሩ ይመልሰው ዘንድ፡፡

በዐዕበየ ሣህሉ ወምሕረቱ፡፡

በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት አዳምን ወደ ቀደመው ቦታ ከመለሰውልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፡፡ እመቤታችን ጸጋውን ክበሩን እንዳይነሳን ለምኚልን፡፡

ዕበያ ለድንግል ኢይትከሃል ለተነግሮ፡፡

የድንግል ክበሯ ሊናገሩት አይቻልም መናገርማ ምነዋ! ለርሷእንደሚገባ አድርጎ መናገር የሚቻለው የለም ሲል ነው፡፡

እስመ እግዚእ ጎረያ፡፡

ጌታ መርጧታልና ቢመርጣትማ ምን ድንቅ ነዋ እንድትመረጥ ሁናተገኝታለችና፡፡

መጽአ ወኀደረ ላዕሌሃ ዘየኃድር ውስተ ብርሃን ኀበ አልቦዘይቀርቦ፡፡

በመመርመር ገንዘብ በማድረግ የሚቀርበው በሌለው ብርሃን ባሕርዩአድሮ የሚኖረ እርሱ ሰው ሆኖ በማኅፀንዋ አደረ፡ ለሊከ ኪያከ አንጦላዕከ ሰውር ብከ ዕበይከ ወለሊከ ተከደንከ እንዲል፡፡

ተጸውረ በከርሣ 9 አውራኃ፡፡

ዘጠኝ ወር ከአምስተ ቀን በማኅጸንዋ ኖረ አምስት ቀን ወዴትአለ ቢሉ መጽሐፍ ቢረተረፍ ትቶ ቢጎድል መልቶ መቁጠር ልማዱ ነውና፡፡

ከዚያ ሰሎሞን ወነበርኩ ውስተ ከርሠ እምየ ዐሰረተ አውራኃርጉዐ በደም ወተገለፍኩ ሥጋ ከመ ኩሉ ሰብእ እንዲል አምስት ቀን ከተረፈ ብሎ አሁንም ቀን ከጎደለ ብሎ 9 አውራኃ አለ፡፡

ዘኢይትረአይ ወዘኢይትዐወቅ ወለደቶ ማርያም እንዘ ድንግልይእቲ፡፡

ሰውም ከሞሆኑ አስቀድሞ ሰውም ከሆነ በኋላ የማመረመር እርሱንማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ሰውም ከመሆኑ አስቀድሞ ሰውም ከሆነ በኋላ የማይመረመረውልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

አወእቱ እብን ዘርእየ ደናኤል ነቢይ

ዳንኤል ያየው ደንጊያ፡፡

አተበተከ እምደብር ነዋህ ዘእንበለ እድ

እጅ ሳይፈነቅለው ከረጅም ተራራ የወረደ ዳንኤል ያየው ደንጊያ፡፡

ዘውእቱ ዋል ዘመፅአ እምኃበ አብ፡፡

በውእቱ እብን ያውን፡፡ ዘውእቱ ቃል ዘተበትከ እምደብ ነዋህለው ዘወፅአ እምኀበ አብ አለ ዘእንበለ እድ ያለውን ዘእንበለ ዘርዕ ብሎ አመታው፡፡

መጽአ ወተሰብኦ እመድንግል ዘእንበለ ዘርዓ ብእሲ ወአድኃነነ፡፡፡

ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ ተወልዶም አዳነን፡፡

ታሪክ ናሁከደነጾር የሚባል ገናና ንጉሥ ነበር ከገናንነቱየተነሣ ይኽን ዓለም እንደገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ ገዝቶት ነበር አንድ ቀን በልቶ ጠጥቶ ተኝቶ ተነሥቶ በሰገነት ሲመላለስእኔ ይኽን ዓለም እነደ ሰም አቅልጬ እንደ ገል ቀጥቅጬ ገዛሁት ከእኔ ቀጥሎ የሚነግሠውን ደካማን ይሆን ኃይለኛን ይህን ባውቀውበወደድሁ አለ፡፡ ሌሊት በራእይ ራሱ የወርቅ አንገቱ ደረቱ የብር ወገቡ የብረት ጭንና ጭኑ የብረት እግርና እግሩ የብረትና የሽክላቅልቅል ምስል ቁሞ እሱን እርሱን ሲያይ እጅ ሳይፈነቅለው ከረጀም ተራራ ደንጊያ ወርዶ አድቆት ተመልሶ ተራራ ሲያኽል ነፋስ መጥቶሲበትነወ ያያል ቢደነግጥ ሕልሙም ትርጓሜውም ጠፋው በድርጎ የሚያኖራቸው ጠቢባን መፈክራነ ሕልም ነበሩት ሕልም አይቼ ንባቡም ትርጓሜውምጠፍቶብኝ ንገሩኝ አላቸው ንጉሥ አንተ ከፍዖን አታንሥ እኛ ከዮሴፍ አንበልጥ ለዮሴፍ ነገረው ተረጎመለት እኛም ንገረንና እንትርጉምልህአሉት ለኔማ ጠፋኝ ይለቁን ጊዜው ሳያልፍ ንገሩኝ ፈጠራ ፈጥራች ብትነግሩኝ ነገሩ ከልቤ ይወጣል የወርደል ዐውቀዋለሁ አላቸው ይህንጉሥ የሚናገረው ነገር ከሰው ለተለዩ ቢቻል እንጂ ለኛ አይቻለንም አሉ መንፈስ ቅዱስ አፋቸውን ከፍቶ ፊታቸውን ጸፍቶ እንዲህ እንዲሉአደረጋቸው፡፡ ከሰው ለተለዩ ለመላእክት ለሥላሴ ለነዳንኤል ቢቻል እንጂ ለኛ አይቻለነም ሲያሰኛቸው ነው፡፡ የሊያስ ይሁን የእነዳንኤልከሰው መለየታቸው እንደምን ነው፡፡ ቢሉ በትኅርምት ነዋሪዎች ናቸውና፡፡ እንኪያስ በቅሎን ናችሁ አሰግራችሁ ፈረስ ናችሁ እጋልባችሁብሎ ወወፅአ ያሮክ ሰያፊ ይላል ያሮክ የሚባል ሰይፍ ጃግሬ አለው ወስደህ ፍጃቸው አለው፡፡ ስሱም መካነ ምቅታል ኣላቸው ወዲያ ዟቸውሲሄድ ዳንኤል ቁጥሩ ከተበብተ ባቢሎን ነው ሲሄድ አገኘው ወዴት ትወስዳቸዋለህ አለው፡፡ ንጉሥ ሕልም አይቶ ንባቡም ትርጓሜውም ጠፍቶትንገሩኝ ቢላቸው ጠፍቷቸው ፍጃቸው ብሎኝ እወስዳቸዋለሁ አለው ደግ ሰውን ከመንገድ አቁሞ መነጋገር አይገባምና ተከትሎ ሂዶ፡፡ ከዚያዲደርስ ተዋቸው እኔ እነግረዋለሁ ቀን ስጠኝ አለው፡፡ ሦስት ቀን ሰጠው፡፡ ለሠለስቱ ደቂቅም እንዲህ ያለ ነገር ተገኝቷልና እዘኑብሎ ይልክባቸዋል ለነዚ በሦስተኛው ቀን ተገልጦላቸዋል ለእርሱ ግን ዕለቱን ተገልጦለታል፡፡ ሰለ ትህትና ይሰነብታል፡፡ በሦስተኛውቀን ሔዶ ንገሩልኝ አለ ከደቀቀ ጼዋ ወገን የንጉሥን ሕልሙን እንረወለሁ የሚል አለ አሉት፡፡ ግባ በሉት አለ፡፡ ትክልኑ ብልጣሶርአይ ድዖጸ ሕልም ወፍካሬሁ አለው እግአብሔር እንጂ የገለጸለት ይተረጉማል ብሎ በነገሩ ወደ ሃይማኖቱ ይስበዋል ብልጣሶር ማለት አምኃቤል ማለት ነው ስማቸውን ለውጦ አውጦቶላቸዋ፡፡ አንድ ቀን በልተህ ጠጥተህ ተኝተህ ተነሥተህ በሰገነት ስተመላለስ እኔ ይኅን ዓለምእንደሰም አቅልጬ እንደ ገል ቀጥቅጬ ገዛሁት ከኔ ቀጥሎ የሚነግሠው ኃያል ይሆን ወይስ ደካምና ይሀን ባውቀው በወደድሁ አልህ ከዚህበኅላ ሌሊት በራእይ ራሱ የወርቅ አንገቱ ደረቱ የብር ወገቡ የበርት ጭንና ጭኑ የብረት እግርና እግሩ የብረትና የሸክላ ቅልቅልምስል ቁሞ አንተ አንተን ሲያይ እጅ ሳይፈነቅለወ ከረጅም ተራታ ደንጊያ ወርዶ አድቆት ተመልሶ ተራታ ሲያህል ነፋስ መትቶ ሲበትነውአላየህም አለው አዎን አለው ርስቱ ዘወርቀወ የተባለህ እንተ ነህ ወርቅ ከሁሉ በላይ ነው አንተም ንጉሠ ንገሥት ነህና አንተን አንተንቅሉ ሲያይ ማየትህ አንተን ነኝ ሲል ነው፡፡ አንገቱ ደረቱ የብር ረተባለ ዳርዮስ መንግስተ ሜዶን ነው፡፡ የብር መዓርጉ ከወርቅበታች ነው ካንተ ቀጥሎ ንጉሠ ነገሥት የሚሆን እሱ ነው፡፡ ወገቡ የብርት የተባለ ቂሮስ መንግሥተ ፋረስ ነው የብርት መዓርጉ ከብርበታች ነው ከዳርዮስ ቀጥሎ ንጉሠ ነገሥት የሚሆን እርሱ ነውና ጭንና ጭኑ የብረት የተባለ እስክንድር ንጉሠ ፅርዕ ነው፡፡ ብረትሰብዓቱን መዓድናት አንድ ያደርጋል እሱም ሠራቱን ማዕዘን እግሩ የብረትና ሸክላ ቅልቅል የተባለ ዐራቱ ልጆቹ ናቸው ልጅስ የለወምፈላስፋ ነው ብሎ ሠራቱ ባሮች ሁቱ ደካሞች ሁለቱ ኃያላን ዳካሞቹ ሰልደስ ድማጥርያኖስ ኃያላኑ በጥሊሞስ አንጥያኮስ ናቸው፡፡ እጅሳይፈነቀለው ከረጅም ተራራ ደንጊያ ወርዶ አድቆት ተመልሶ ታታ ሲያህል ማየትህ ልዑል እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በኋላ ዘምን የሚሠራወንሥራ ገልፆልሃል ነፋስ የሥላጣን እግዚአብሔር ምሳ ነው፡፡

ትርኅሜውስ መልካም ነበረ ነገር ግን ጌታ ሰው መሆኑ በመንግሥተሮም ነው እንጂ መች በንግስተ ጽርዕ ነዋ፡፡ ወበመዋዕሊሆሙ ለእሱ ይመጽእ አምላከ ሰማይ ወምድር ይላልና ብሎ፡፡ ራሱ የወርቅ የተባልህአንተ ነህ አይለወትም፡፡ አንገቱ ደረቱ የብር ዳርዮስ ምነግሥተ ማዶን፡፡ ቂሮስ ምንግስተ ፋርስ ነው፡፡ ወገበ የብርት የተባለ እስክድርንጉሠ ጸርዕ ነው፡፡ ጭንና ጭኑ የብረት የተባለ መንግሥተ ሮም ነው፡፡ እግርና እግሩ የብረትና የሸክላ ቅልቅል ምስል የተባለ በመንግሥተሮም ውስጥ የነገሡ እኩሉ ደካሞች እኩሉ ኃያላን ናቸው፡፡ እጅ ሳይፈነቅለው ከረጅም ተራታ ደንጊያ ወርዶ አድቆት ተመልሶ ተራራ ሲያህልማየትህ ልዑል እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በኋላ ዘመን የሚሠራወን ስራ ገልጦልሃል፡፡ ነፋስ የሥልጣነ እግዚአብሔር ምሳሌ፡፡ መምህር ኤስድሮስግን ወርቅ ብር ብርት በሦስቱ ሰማያት ያሉ መላእክት ጭንና ጭኑ የብርት በአየር ያሉ አጋንንት እግረና እግሩ የብረትና የሸክላ ቅልቅልምስል ደቂቀ አዳምና ልቡሳ ሥጋ አጋንንተ፡፡ እጅ ሳይፈነቅለው ከረጅም ተራራ ደንጊያ ወርዶ አድቆት ተመልሶ ተራራ ሲያህል ማየቱሥጋ አምላክ ሆኖ እንዚህን ሁሉ መለግዛቱ ምሳሌ፡፡

ነፋስ የስላጣነ እግዚአብሔር ምሳሌ ነው ብለው ተርጉመዋል፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ደንኤል በአምሳ እብን ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችንጻጋውን ክብሩን እንዳይናን ለምኚልን፡፡

ኮነኪ ዐፅቀ ንጹሐ፡፡

ሐሩረ ፀሓ ያወደቀባት፡፡ ነፋስ ያልወዘወዛት፡፡ ለታብቁልባለው ቃል ከልምላሜ ከጽጌ ከፍሬ የተገኘች ተፅቀ ሠሉስ አንች ነሸ፡፡ አንድም ዐፅቀ አቤሜሌክ አንች ነሽ፡፡ ታሪክ ለኤርሚያስ አቤሜሌክባሮክ የሚሉ ደቀ መዛሙርት ነበሩት፡፡ የምድያም ሰዎች ናቸው፡፡ የፄዋዌን ነገር ሲነገር እሰሙ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለኢሩሳሌም እያሉይጸልዩ ነበር፡፡ ጼዋዌ ቢደርሰ እቤሜሌክን ለድውያን የምንቀባው ዐፅቀ በለስ አምጣ ብለህ ላከው፡፡ ባክንም መቃብረ ነገሥት አስጠብቀውአለው፡፡ እንዳው አደረገ በዚያ ሌሊት እስራኤል ተማርከው ወረዱ አቤሜሌክ ዐጽቀበለስን ቆርጦ በመሶበ ወርቅ አድርጎ ይዞ ሲሄድ ከጥላ ዐረፈ፡፤ ወዲያው እንቀልፍ አንቅልፍ አለው ተኛ፡፡ 6 ዘመን ተኝቶ ቢነቃ ጊዜ ገጥሞት ከተናበት ሰዓት እልፍ ብሎ አገኘው ዘግይቻለሁ መምሬ ይቆጣናልብሎ መንገድ ጀመረ፡፡ አገሩ ተፈቶ መንገዱ ጠፍቶ ለመሄድ ቸገረው፡፡ እንቅልፉ ባይለቀን ነውን ወይስ አእምሮዬን ተለይቶኛል ብሎቁሞ ሲመለከት አንድ ሰው ከተራራ ላይ አየ፡፡ ሰውስ በ፷6ዘመን አይገኝም መልአክ በአምሳአረጋዊ ታየው፡፡ ከዚያ ሄዶ አይቴ ሀለወ ኤርምያስ ወአኃውየ አለው፡፡ አንተኑ ነግድ ለኢየሩሳሌም ለኢየሩሳም አንተ እንግዳ ሰውነህ አለ ኤርምያስ ያሉ ባቢሎን በስደት ኢየሩሳሌም ከጠፋች 6ዓመት አለው፡፡ ኦሪት አክብርገጸ አረጋዊ ብላኛለች እንጂ ይህ ጅጂ ባልሁህ ነበር፡፡ ለድውያን የምቀባው ዐፅቀበለስ ቆርጠህ አምጣ ብሎ መምሬ ልኮኝ ደሟ ይንጠፈጠፋልቅጠሏ አልጠወለገም እነሆ አለው፡፡ እስኪ ክፈታት አለው ቢከፍታት ደሟ ሲነጠፋጠፍ ቅጠሏ ሳይጠወልግ ተገኝታለች፡፡ አንተን ከመከራወሰውሮህ ነው እንጂ፡፡ ሲልክህ ወራቱ ምን ነበረ አለው፡፡ በርኀ ጽጌ ቢለው ወርኀ ዘርዕ ሁኖብሃል ይለዋል፡፡ ወርኀ ዘር ነው ቢለው፡፡ ወርኀ ጽጌ ሆኖብሃል ይዋል፡፡ ከዚህ በኋላና ከወንድምህ ላገናኝህ ብሎ ወስዶ አገናኛው፡፡ ሁለቱ ተያይዘው ቀኖና ቢገቡ ለሚጠት ዐራት ዓመት እንደ ቀረው ተገልጾላቸው ያንበወረቀት ጽፈው የሚወስድላቸው አጥተው ሲጨነቁ የታዘዘ ንሥር መጣ፡፡ ወረቀቱንና ዐፅቀ በለሱን አርገው ካንገቱ አስረወ ሰደዱለት፡፡ኤርምያስ ሰው ሙቶበት ከንጉሥ ተሰናብቶ መቃብር ሊያሰቀብር ሲሄድ ከፈረስ ገንብ አጠገብ አስከሬኑን አሳርፎ ሳለ ኤርምያሰ ኤርማያስብሎ በቃል ሰብአዊ ጠርቶ ጣለለት ወዲያው ነገሩን እንዲረዳለት ወኬዶ በእግሩ ለምውት ይላል፡፡ በእግሩ ተረግጦ ምውቱን አስነሥቶታል፡፡ያም ተነሥቶ በወረቀቱ ያውን መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡ ያች ስሳ ስድስት ዘመን ቅጠሏን ሳይጠወልግ ደሟ ሲንጠፈጠፍ እንደ ተገኘችእመቤታችንም በስድሳ ስድተኛው ትውልድ ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባት ተገኝታለችና፡፡ ወበከመ ነፋሕኩ ወስተ ገጹ ለአዳም ከማሁ አንቲኒሀሎኪ ወኢረሳሕኪ እንዲል አንድም ወለተ ንጽሕተ ሲል ነው የልደታ ትረጓሜ፡፡

ወሙዳየ አሚን፡፡

ሙዳይ እርሷ አሚን ልጅዋ፡፡ ዘውእቱ አሚን እንዲለው፡፡

ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ፡፡

ያባቶቻችን የቀናች ሃይማኖታቸወ፡፡

ንጽሕት ወላዲተ አምላክ፡፡

አምላክን የወለድሽ ንጽሕት፡፡

ደንግል ኅትምት፡፡

በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ኅትምት የምትሆኝ፡፡

ወለድኪ ለነ ቃለ አብ፡፡

አካላዊ ቃን ወለድሽልን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በጽአ ለመድኃኒትነ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ሰለ ማዳን ሰው ሁኗልና፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

እናን ስለማዳን ሰው ከሆነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችንጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

አንቲ እሙ ለብርሃን ክብርት ወላዲተ እግዚእ፡፡

የከበርሽ አምላክን የወለድሽ የብርሃን እናቱ አንች ነሽ፡፡

እነተ ፆርኪዮ ለቃል ዘኢይትረአይ የማይመረመር ቃልን የወሰንሺው፡፡እምድኅረ ወለድኪ ኪያሁ ነበርኪ በድንግልና፡፡

እሱንም ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኖረሻልና፡፡

በስብሐት ወበባርኮት ያዐብዮኪ፡፡ በአፍኣ በውስጥ በሥጋ በነፍስያከብሩሻል ያገኑሻል፡፡

እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንእት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውንክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

አይ ልሳን ዜክል ነቢብ ዘይትነገር በእንቲኣኪ፡፡ (ብኪ)

ስለአንቺ ደንቅ ሆኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለወምን አንደበት ነው፡፡ ብኪ ባለው ይተርካል ሐዋርያት እመቤታችንን እንደምን ፀነሺው እነደ ምን ወለድሽው ንገሪን አሏት አንግዲያስሳስበው ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል እጄን እግሬን ያዙኝ አለቻቸው ወትሮ የማውቀው መልአክ ቀርቶ ወትሮ የመላውቀው መልአክ መጣ ጊዜው ካፊያነበረ ቀኝ ዐፅፋን ቢባርከው ኃብስተ ሕይወት ሆኖ በልቶ አበላኝ ግራ ዐፅፉን ቢባርከው ጽዋዐ ሕይወት ሆኖ ጠጥቶ አጠጣኝ ብላ ነገርጀምራላቸው ሳለች ግሩም መለአክ ከሰማ ወርዶ ድምጽ አሰማቸው እንደቅጠል ረገፉ እርሷ ለበቃችው ምሥጢር አልበቃችሁም ሲል ነው፡፡መምህር ኤስድስ ግን ብቻ መውለድን ቀምሶ አቀመሰኝ፡፡ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ተወልዶ ድኅረ ዓም አባት እንድወልደወ አደረገኝሰትል ነው ብለዋል፡፡ ድንግል ንጽሕት እሙ ለቃለ አብ፡፡

የአካላዊ ቃል እናቱ ንጽሕት ደንግል፡፡

ኮንኪ መንበሩ ለንጉሥ ለዘይጸውርዎ ኩሩቤል፡፡

ኪሩቤል ሊሚሸከሙት ለንጉሥ ማደሪያ ሆንሽ እሱ ይሸከማቸዋልእንጂ ይሸከሙታልን አኃዜ ዓለም በእራኁ ኩሉ እኁዝ ውስተ እዴሁ፡፡ መሰረተ ዓለም ይተውር ድደ ወይነብር ጠፈረ እንዲለው፡፡ በዘፈቀደየሚታይባቸው በንበሩን ተሸክመው የሚዩ ሚቀድሱት በጸጋ የሚያድርጋቸው ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ መሸከምስ እሱ ነው የሚሸከማቸው፡፡

ናስተበፅዐኪ ቡርክት፡፡

ንዕድ ክብርጽ ከብርስን ገናንነትሽን ዕፀብ ዕፁብ እያልንአንመሰግንሻለን፡፡

ወንዘክር ስመኪ በኩሉ ትውልደ ተውልደ፡፡

ስምሽንም በትውልደ ሴም በትውልደ ካም ያፌት እንጸራለን ኩሉአለ ከዚህ የወጣ ትውልድ የለምና፡፡

ርግብ ሠናይት እሙ ለእግዚእኒ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡

የአካላዊ ቃል እናቱ መልካሟ ርግብ አንድም ርግብ ኖኅ፡፡ያች ነትገ ኤኅ ሐፀ ማየ አይኅ ስትል ቄጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች፡፡ እመቤታችንም ነትገ ማየ ኃጢአት ሐፀ መርገም ስትልጌታን ፀንሳ ተገኝታለችና፡፡ አንድም ርግበ ዳዊት ርግበ ሰሎሞን አላት፡፡ ሰሎሞን ርግብየ ርግብየ ይላታልና፡፡ አንድም በርሷ ርግብነትየልጅዋን ርግብነተት ተናገረ፡፡ በደብተራ ኦሪት ቀይሓን ጸሊማን ኪሳኪሳን አርጋብ ይኖራሉ በነዚ መካከል ፀዓዳ ርግብ ኖራል ሌዋዊአውታረ ደብተራ ይቆርጥብኛ ብሎ መትቶ ገድሎታል፡፡ ቀይሓን ጸሊማን ኪሳኪላን የነቢያት የካህናት ምሳሌ፡፡ ቀይሓን አላቸው ደማቸወንያፈሳሉና ጸሊማን አላቸው፡፡ መከራቸው ጽኑ ነውና ኮሳኩሳን አላቸው ባለተስፋ ናቸውና ፀዓዳ ርግብ የተባለ ጌታ ነው፡፡ ፀዓዳ በመለኮቱእንዲለው፡፡ ሌዋዊ አውታረ ደብተራ ይቆርጥብኛል ብሎ መትቶ እንደ ገደለው አሌ ለክሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን መደልዋን እያለ በግራቸወቢዘልፋቸው ጠልተወ ተመቅኝተው ሰቅለው ገድለውታልና፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

በርግብ ከተመሰለወ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውንክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን፡፡

ተፈሥሒ ማርም እም ወእመት አናትነት ከገረድነት ያለሽእመቤታችን ተፈስሒ ደስ ይበልሽ አንድም አዕመተ ዲብሎስ በተባሉበት ወራት አመተ እግዚአብሔር መባል ደስ ያሰኛልና፡፡

እስመ ለዘውስተ ሕፅንኪ ይሴብህዎ መላእክት፡፡

በክንድሽ የያዝሺውን መላእክት የመሰግኑታልና፡፡

ወኪሩቤል ይሰግዱ ሎቱ መፍርሃት ኪሩቤልም እየፈሩ የሰግዱለታልና፡፡ወሱራፌል ዘእንበለ ጽርዓት፡፡

ሱፌልም ሳያቋርጡ፡፡

ይሰፍሑ ክነፊሆሙ፡፡

ክንፋቸወን ዘርግተው፡፡

ወይብሉ ዝንቱ ውእቱ ንጉሠ ስብሐት፡፡

የክብር ባለቤት ይህን ነው ይላሉ መጽአ ይዕረይ ኃቲአተ ዓለም

በዕበየ ሣህሉ፡፡

በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት የሰውን ሁሉ ኃጢአት ለማስተሥረይሰው የሆነ የክብር ባለቤት ይህ ነወ እያሉ ያመሰግናሉ ታሪክ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉሥ ረኢክዎ ለእግዚአብሔር ጸባዖት እንዘ ይነብርዲበ መንበሩ ነዋኅ ወብሩህ ወምሉዕ ቤተ ስብሓቲሁ ወሱራፌል ይቀውሙ ዐወዶ ወለለ አሐዱ በበስድስቱ ክነፋሆሙ በክለኤ ክነፊሆሙ ይከድኑገጾሙ ወበክልኤ ክነፊሆሙ የክድኑ እግሮሙ ወበክልኤ ክነፊሆው ይሠሩ አንፃረ ኅቡረ ወይብሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖትፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ሰብሓቲከ፡፡

በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውንይሸፍናሉ ሁለቱን ክንፋቸውን ወዲያና ወዲህ ደርጋሊ አለ፡፡ ይኽንንም ሊቁ ከመ ኢያውዕዮሙ እሳት በላዒ ብሎ ወስዶል፡፡ ሐተታ፡-፡፡ ይህ ያድናቸዋል ቢሉ ትእምረተ ፍርሃት ነው፡፡ አንድም በሁለቱ ክንፋቸው ፊቸውን ይሸፍናሉ አለ፡፡ ፊትህን ማየት ኤቻለንም ሲሉ፡፡በሁለቱ ክንፋቸው እግራውን ይሸፍናሉ አለ፡፡ ከፊትህ መቆም አይቻለንም ሲሉ፡፡ ሁለቱን ክንፋቸውን ወዲያና ወዲህ ያደርጋሉ አለ፡፡ትእምርተ ተልእኮ፡፡ አንድም በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ አለ፡፡ ባሕርይህን መመርመር አይቻለንም ሲሉ፡፡ በሁለቱ ክንፋቸውእግራቸውን ይሸፍናሉ አለ፡፡ ባሕርይህን መረማመድ መተላለፍ አይቻለንም ሲሉ፡፡ ሁለቱን ክንፋቸውን ወዲያና ወዲህ ያደርጋሉ አለ፡፡ከአእምሮ ወደ አእምሮ ለመፋለሳቸው፡፡ አንድም ሁለት ክንፋቸወን ወደ ላይ አድርገው ይታያሉ አለ፡፡ ወደላይ ቢወጡ ቢወጡ አትገኝምሲለ፡፡ ሁለት ክንፋቸውን ወደ ታች አድርገው ይታያሉ አለ፡፡ ወደ ታች ቢወርዱ ቢወርዱ አትገኝም ሲሉ፡፡ ሁለት ክንፋቸውን ወዲያናወዲህ ደርጋሉ አለ፡፡ ወዲያና ወዲህ ቢሉ አትገኝም ሲሉ፡፡ ይህንም በአርአያ ትእምረተ መስቀል ብሎ ሊቁ ወስዶታል፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

የሰውን ኃጢአት በቸርነቱ ብዛት ከሚያሰተሠርይ ልጅሽ ጽንዕትበድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ቅድስት አለ፡፡ ንጽኽጽ ክብረጽ ልዩ ሲል ነው፡፡ ንጽሕትም አለ፡፡ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን ከነቢብ ከገቢር ከሐልዮ ንጽሕት ናትና ወኢረኩሰት በምንተኒ አምዘፈጠራድንግል በሥጋሃ ወድንግል በኃሊናሃ እንዲል፡፡ ጽንዕትም አለ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ እስከ ጊዜው ነው፡፡ ኋላ ግን ተፈተሖ አለባቸው፡፡እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ ድኅረ ፀኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት ናትና፡፡ ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶችብናከብራቸው ጻድቃንን ሰማዕታትን ወልደዋል ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ብለን ነወና፡፡ ልዩም አለ አናትናተ ከድንግልናአስተባብራ የምትገኝ ሌላ ሴት የለችምና፡፡ ዐይኑ ቢሆን አእምሮውን ለብዎውን ሳይብን ማለት ነው አልፋው ቢሆን ለምኚልን ማለትነው፡፡ ልመናስ ከዚ በኋላ ስንኳንስ በሷ በሌሎችም የለባቸው፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ሆነ አንዲህ አለ አንጂ፡፡ ይህንሲጨር በያዘችው መስቀል ብርሃን ባርካወ ታርጋለች፡ እሱም ተባርኮ እጅ ነሥቶ ይቀራል፡፡

አነሣሥቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለእግአብሔር ክብርምስጋና ይግባው አሜን፡፡
ይቆየን.........
ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና እመቤታችን ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን!
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

1 comment:

  1. Ye Enatalem Emebetachin miljana bereket zewotir ayleyen. Bertu.

    ReplyDelete