Saturday, December 31, 2011

አባ ፋኑኤል በዋሽንግተን ዲሲ ላይ የተናገሩት ያማፍረስ ሥራ

የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን ባለፈው ስለ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ያቀረብነው ዘገባ መሠረት አቡነ ፋኑኤል በዲሲ ደብረ ምሕረት ተገኝተው ይህ ደክሜ የሰራሁት ቤቴ ነው ከዚህ ማንም ውጣ ሊለኝ አይችልም "ደርግ እንኳን ሁለት ያለውን ነው የሚነጥቀው፣ እኔ ግን ያለኝ አንድ ቤቴን ነጥቃችሁ የት ልሂድ" ብለው አስገርመውናል፣ አሁንም ከፋፋይ ሥራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ በፍትሕ መንፈሣዊ ላይ እንደተገለጸው ቤተክርስቲያንን በደሙ የመሠረታት ክርስቶስ እንጂ አባ ፋኑኤል እንደሚሉት እርሳቸው አልሰሩትም። አሁንም ይህንን ሥርዓት አልበኝነታቸውን በመቀጠል በአካባቢው ከሚገኙት እራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የሚኖሩትን የቦርድ እና የካህናት ስብሰባ ጠርተው በቦታው ግምቱ ከ15 ሰው የማይበልጥ ተገኝቶ በጥያቄ ሲያወዛግባቸው ታይተዋል የውሽታቸው ብዛት ደግሞ ከአንድ የስብሰባው ተከታይ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር ጥያቄውም እንደሚከተለው ነው።
እዚህ አካባቢ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሥም የተቋቋመ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚባል ተቋቋሞ ነበር እና ድጋሚ ለማቋቋም ለምን አስፈለገ? ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልሳቸው: እኔ እስከማውቀው ድረስ ከወሬ ውጪ የሰማሁት ነገር የለም የተሰራም ወይም የታየ  ምንም የማውቀው ነገር የለም ብለው ነበር የሸመጠጡት በጣም የሚያስገርም ነው። ለመቋቋሙም የመጀመሪያው የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው መጥተው ነበር እርሱንም እራሳቸው በዚህ ቪዲዮ ላይ ተናግረውታል።
ሌላው ከስብሰባው ተሳታፊዎች የቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ እንደሚከተለው ነው
በዚህ አካባቢ የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት አለ ሲባል ሰምተናል ግዢውም ከሦስት ዓመት በፊት መገዛቱንም ይታወቃል ስለዚህ ለምን ሌላ ለመግዛት ወይም ለመመስረት አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልስ: ለሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ ጽፈናል ነገር ግን መልስ አላገኘንም  ብለው በሚያሳፍር ሁኔታ "በአንድ ራስ ሁለት ምላስ" እንደሚባለው ሆነው ነበር ነበር ያሳለፉት።
በአጠቃላይ ፍርዱን ለአንባቢያን እንተወዋለን።

Wednesday, December 21, 2011

አስኬማው የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን (የትዝታው ሳሙኤል ግሩፓች)የሥርዓት አልበኞቹ ግሩፕ ቀንደኛ መሪዎች

(አንድ አድርገን ታህሳስ 11 ፤ 2004)፡- በዲላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ህገወጥነት እና ስርዓት አልበኝነት በፊት እነ በጋሻው ደሳለኝ እና ትዝታው ሳሙኤል ባስመረጧቸው የሰበካ ጉባኤ አባላት እየተከናወነ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን በስራ ላይ የሚገኝውን የሰበካ ጉባኤ እንዲበተን እና በምትኩ ህዝቡ ይሆኑኛል ፤ ቤተክርስትያኗን ለማተዳደር እውቀቱም ሆነ ብቃቱ አላቸው ያላቸውን ሰዎች እንዲመርጡ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተፃፈ ደብዳቤ ከሳምንት በፊት በእጃቸው ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፓትርያርኩም ሆነ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አያገባቸውም በሚል እሳቤ ሰውን ለሌላ ብጥብጥ ለማነሳሳት የቤተክርስትያ አስተዳዳሪው የኛ የሚሏቸውን ሰዎች  እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡

ብፁዕ አብነ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

በሕግ አክባሪነታቸው፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በመጠበቅ እና በማስጠበቅ እንዲሁም በብዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ የሚወደዱት እና የሚከበሩት ብፁዕ አብነ አብርሃም የምሥራቅ ሐረርጌ እና የጅጅጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሰየሙበት ካለፈው የጥቅምት ፳፻፬ ዓ.ም. በኃላ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ለመሔድ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገልጿል። ብፁዕ አብነ አብርሃም ከአሜሪካ መዲና ከሆነችው ከዋሽንግተን ዲሲ ሲነሱ በርካታ ካህናትና ምዕመናን በእንባና በልቅሶ ሸኝተዋቸዋል። ብፁዕነታቸው በበርካታ የአካባቢው ምዕመናን እና አድባራት በአይነቱ ልዩ የሆነ የመሸኛ ምሽት አዘጋጅተውላቸው እንደነበር ከቦታው የደረሰን ሪፓርት ይገልጻል። ብፁዓን አባቶች፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ካሕናት፣ ሰባኪያነ ወንጌል፣ ዲያቆናት፣ እንዲሁም በርካታ ከተለያየ ጠቅላይ ግዛት የመጡ ምዕመናን በዚህ የመሸኛ ምሽት ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል። ብፁዕነታቸውም በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ የዋሽንግተን እና አካባቢውን ምዕመናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ምንም አይነት ድርድር ውስጥ ማስገባት እንደሌለባቸው እና ማንኛውንም የቤተክርስቲያን አባት ሊመረመር እና ሊመዘን የሚችለው በሕገ ቤተክርስቲያን እንደሆነ ተናግረዋል።

የአቡነ ገሪማ አምላክ አባ ጳውሎስ ይሆኑ?

በሉልሰገድ እረታ lulsegedrt@gmail.com
          ክርስትና የመከራ ህይወት ነው እንደሚባለው ሆኖ እንደሆነ እንጃ በየትኛውም ዘመን የተፃፈ የትኛውንም የታሪክ መጽሐፍ የተመለከተ ሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፈተና እና ከመከራ የተላቀቀችበት ዘመን እንደሌለ በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ በ10ኛው መቶ ክ/ዘመን የዮዲት ወረራ፣ በ16ተኛው ክ/ዘመን የአህመድ ግራኝ ጭፍጨፋ፣ በ17ተኛው ክ/ዘመን የሱስንዮስ ካቶሊካዊ ወረራ፣ በ18ኛው ክ/ዘመን የዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ክፍፍል፣ በጣም በቅርብ ጊዜ እንኳን የወታደራዊ መንግስት ደርግ ኮሚንስታዊ ተጽእኖ በግምባር ቀደምነት የሚጠቀሱ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች ናቸው፡፡ መሰረታዊው ጥያቄ ግን ቤተ-ክርስቲያን እነዚህን ሁሉ መከራዎች በምን መንገድ እና በማን መስዋዕትነት ተወጣቻቸው የሚለው ሲሆን ለዚህ ጥያቄ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጋራ የሚሰጠው ምላሽ አንድ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም ፡፡
እነዚያ ሁሉ መከራዎች ታሪክ ሆነው የቀሩት ቤተ-ክህነቷ ባፈራቻቸው ልጆቿ በተለይም ደግሞ በአስተዳዳሪዎቿ ብርታት እና መስዋዕትነት መሆኑን ማንም የማይክደው ሐቅ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ምናልባትም ከአንድ ሰው እድሜ ባልዘለለ አመት ውስጥ እንኳን በአንባገነኑ የደርግ መንግስት ስለ እምነታቸው እና ስለሀገራቸው ሰላም መስዋዕት የሆኑትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን፣ ወይም ለፋሽስት ሐገሬን ባርኬ አልሰጥም በማለት ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የሚዘነጋቸው ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡
 ዛሬስ ———

Wednesday, December 14, 2011

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪ ትዘረጋለች

በዚህ እኛ በተፈጠርንበት ዘመን በጣም ለጆሮ የሚቀፉ፣ ለማየት የሚያስደነግጡ፣ የሰሚን ጆሮ ጭው የሚያደርጉ ብዙ ክስተቶች ተከስተዋል እየተከሰቱም ነው። በተለይ በእኛ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ይልቁንም ባለፉት ፳ ዓመታት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የተለያዩ አስደንጋጭ ክስተቶች ተከስተዋል፣ የብዙ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት አስደፍቷል፣ ለብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን መሰደደ እና ሕልፈት እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው ብለን እናምናለን። ለምን በዘመነ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን በቤተክርስቲያን ላይ ይህ ሁሉ ፈተና በዛባት? ፈተነውስ ከየት የመጣ ፈተና ነው? እንደሚታወቀው በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን ብዙ ክፍተቶች፣ ግድፈቶች፣ ቀኖና ጥሰቶች፣ ግድያዎች፣ አፈናዎች፣ ስም ማጥፋቶች፣ እንዲሁም ብዙ መጠነ ሰፊ ዘረፋዎች እና ሙስናዎች ተፈጽመዋል እነዚህ ሁሉ ግፎች እና በደሎች ሲፈጽሙ ማንም የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ወይም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጭምር "ይደልዎ" ከማለት በስተቀር ምንም ዓይነት ተቃውሞ ያቀረቡም ሆነ የተለያዩ አቤቱታዎችን ለሚመለከተው የቤተክርስቲያን አካል ከዚያም ባሻገረ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ ያቀረቡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሉ ብሎ ለመናገር አያስደፍርም።

Monday, December 12, 2011

አባ ፋኑኤል እስከ መቼ ቤተክርስቲያንን እያመሱ ይኖራሉ?

ይህንን ጽሁፍ እንድናዘጋጅ ያስገደደን አንድ አንባቢያችን ያደረሱን መልዕክት ነው፣ መልዕክቱም አባ ፋኑኤል እንደተለመደው የመከፋፈል ሥራቸውን በዋሽንግተን ዲሲ እና ካሊፎርኒያ ግዛት ጀምረዋል። በቅርቡ የደረሰን ደብዳቤ እንደሚያመለክተው አባ ፋኑኤል እኔ በሕጋዊ መልኩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወክዬ የመጣሁ ወኪል ነኝ ካሉ በኃላ፣ በመቀጠል በተለያዩ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ለሚገኙ ይልቁንም በገለልተኛ አስተዳደር ስር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ ልከዋል፥ ደብዳቤው እንደሚያብራራው እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን (ደብር) ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንደተከበረ ሆኖ ሃይማኖት እንዳይበረዝና ቀኖና ቤተክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅ እንድንመካከር አብረን ተነጋግረን ልንሰራ የምንችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሚል ይጀምራል። በመቀጠል የደብራችሁ አስተዳዳሪዎች፣ የቦርድ ተወካዮች፣ እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን ይላል። ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ

Thursday, December 1, 2011

እንኳን ለጽዮን ማርያም በዓል አደረሳችሁ

"ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።" መዝ ፻፴፮ ፥ ፩ "የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሯት፤ ስለበደል መባእ ካሳ አድርጋችሁ ያቀረባችሁትን የወርቁንም ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቷ አጠገብ አኑሯት፤ ትሄድም ዘንድ ስደዱአት።"
፩ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፩ 
የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ጣዒሟንና ፍቅሯን በልባችን ጽላት ያሳድርብን ከበዓሉ ረድሄት በረከት ያካፍለን። አሜን!!!

፩፦ «ሰው እናታችን ጽዮን ይላል»
«
እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፥ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ ወውእቱ ልዑል ሣረራ። ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጧም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።» ይላል። መዝ ፹፮፥፭። ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን እናት ብሏታል። እናት፦ ወላጅ፥ መገኛ፥የአባት ሁለተኛ ናት። እግዚአብሔር በአሠርቱ ትእዛዛት፦ «አክብር አባከ ወእመከ፤ ከመ ይኩንከ ጽድቀ፥ ወይኑኅ መዋዕሊከ በውስተ ምድር ዘይሁበከ እግዚአብሔር አምላክከ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ (ቸርነቱ ረድኤቱ ይደረግልህ ዘንድ) እግዚአብሔር አምላክህ በሚስጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም፤ » እንዳለ፦ እናት ከአባት እኲል ክብር ይገባታል። ዘጸ ፥፲፪። ጽዮን ማለት ደግሞ አምባ መጠጊያ ማለት ነው።