Monday, September 17, 2012

ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት በመዝረፍ ላይ በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር


በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር
 ፕሮቴስታንት እምነቱ ይህ ነው ሥርዓቱም ይህ ነው ለማለት አይቻለም ይልቁንም በአብዛኛው የራሳቸው የሆነ ወጥ ሥርዓት የሌላቸው በመሆናቸው ማንነታቸውን በትርጉም በትክክል  ለመግለጥ ሁልጊዜ አስቸጋሪ ሆኖ ይኖራል፡፡ በአብዛኛውም ግሎባላይዜሽን ባመጣው አዳዲስ ኩነቶች እራሳቸውን  በማመሳሰልና ጊዜውን በመምሰል የሚያክላቸው እስካሁን አልተገኘም፡፡
ይሁን እንጂመቃወም” “ተቃውሞአዊጠባይ የሚያይልባቸው መሆኑን ከአንዳንድ መረጃዎች መረዳት ይቻላል በየጊዜውም የሚነሡት ሁሉ ከእነርሱ በፊት የነበረውን ትምህርት እየተቃወሙ በየጊዜው አዳዲስ ትምህርት እንዲያመጡና ክፍልፋያቸው (Denomination) እንዲበዛ አድርገዋል፡፡
 በዚህ ጊዜ ውስጥ መሠረታዊና እውነተኛ ትምህርተ ሀይማኖት እንዲኖራቸው ከምክንያቶቻችን ይልቅ በመገለጥ  ሃይማኖት አምነው ትምህረተ ሥላሴን እንዲቀበሉ ያደርጉ ሰዎችም እንደ ተነሱ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በዓለም ላይ ከደረሱትም ጉዳት አንዱ የሰውን  ምግባር (moral) መለወጥና እንስሳዊና ሰይጣናዊ ማድረግ ነው፡፡


 እስካሁንም በነበራቸው አካሄድእግዚአብሔርን እናመሰግንበታለንየሚሉትመዝሙራቸውዘመናዊ ዘፈን እንደሆነ የራሳቸው ሰው የተናገረውን እናነሳለንለእኛ እንደ ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የሚያስፈልገን ሽብሸባ  እንጂ ዳንስ ሊሆን አይገባም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዓለም ከታወቀችበት ትውፊቶች የራሷ የሆነ አገራዊ ዝማሬ ያላት መሆኑ ነው፡፡ ይህም ብዙዎቻችን የምንወደው ያሬዳዊ ዝማሬ ነው ያሬዳዊ ዝማሬ ለብዙዎቻችን የምንወደው ያሬዳዊ ዝማሬ ለብዙ የኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ የሚሰጠው ምልክት ቀውስ ዳንስ ወይም ጭፈራ ሳይሆን አምልኮ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የበገናን ስንትርትር ዜማ ስንሰማ ልባችን ይቀልጣል እንግዲያው እግዚአብሔር በባህላችን ውስጥ ባስቀመጠው በዚህ መልካም ነገር ተጠቅመን ለማገልግልና ለማነጽ  ብንሞክር መልካም ይመስለኛል፡፡ ቀናነት ካለን!”  በማለት ብሶቱን አሰምቷል ዳንሳቸው እያደረሰ ያለውን ጉዳት ቀውስ ብሎ በመጥራት ገልጦታል፡፡  ይህ ግርማዊ የተባለ ፀሐፊ የብልፅግና ወንጌል ብሎ 1992 ባሳተመው መጸሐፍ ላይ የተገለጸ ሲሆን ዛሬ ላይ ደግሞ ሰሞኑን ባሳተሙት የመዝሙር ካሴቶች ቅዱስ ያሬድን ሊያስተዋውቁን እንዲህ ዳዳቸው፡፡     “ለቀባሪው አረዱትእንዲሉ:: ይህን ቪሲዲ ይመልከቱ




ቤተክርቲያናችን ለዘመናት የሃይማኖትና የሥርዓት ብቻ ሳይሆን ታሪክና ቅርስ ጠባቂ ሆና የቆየች ናት 

ቤተክርቲያናችን ለዘመናት የሃይማኖትና የሥርዓት ብቻ ሳይሆን ታሪክና ቅርስ ጠባቂ ሆና የቆየች ናት አብዛኞቹ ታሪኮቻችንም የተመዘገቡት በብራና መጽሀፍት ላይ ሲሆን በቃል የሚነገሩትም ብዙዎች ናቸው፡፡  እነዚህም ለፕሮቴስታንት ስብከት የማይመቹ በመሆናቸው በሚገባውም በማይገባውም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እየጠቀሱ እንደ ፈለጉትም እያጣመሙ በመተርጎም በቤተክርሲቲያናችን ተጠብቀው ለሀገር የቆዩትን የቤተክርሲቲያን ሀብት የሀገር ቅርስ የሕዝቡንም ባሕል በእጅጉ ለማጥፋት ሲጥሩ እና ሲያጠፋ እንዳልነበር ዛሬ የእነሱም ሀብት እንደሆኑ ሊነግሩን ሊያስረዱን ደከሙ ዛሬ ስለ ቅዱስ ያሬድ የነገሩን ከየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አገኘነው ይሉ ይሆን? አዋልድ መጻኅፍትን አይቀበሉ እንደሆንምንስ ምክነያት ያቀርቡ ይሆን? የሆነው ሆኖ  ስርዓቱን ሳያጓድሉ ቢይዙት መልካም በሆነ ነበር ከውስጣቸው ሲዋሀድ ወደ ማንነታቸው በተመለሱ ነበር ነገር ግን ያሬዳዊ ብለው ጀምረው ካልበረዙ ካልቀላቀሉ ዓላማቸው እውን ሰለማይሆን ትክክለኛ ስርዓቱን ለማስቀመጥ አዳጋች ይሆንባቸዋል ፡፡
ይህን የቤተክርስቲያን ስርዓት የመበረዝ ተግባር የውስጥ ጠላቶቻችን ተሐድሶዎችም እየተጠቀሙበት ኖረዋል፡፡  ዛሬ ጋብ ያሉ ሲመስሉ ደግሞ ዋናዎቹ ፕሮቴስታንት ምን እንስራ ብለው ብቅ ማለታቸው በጣሙን ያስገርማል፡፡
 ያስገርማል፡፡
በቅርብ ጊዜም ከበሮውና ፅናፅል መቋሚያ በመያዝ እና አባ ናትናኤል ተብየው  ከላይ በቪዲዮ 


በቅርብ ጊዜም ከበሮውና ፅናፅል መቋሚያ በመያዝ እናአባናትናኤል ተብየው  ከላይ በቪዲዮ እንደምትመለከቱት ስርዓታችንን ሲበረዝ አና ንዋያቶቻችን ሲያራክስ ተመለከትን ፡፡ ሰሞኑን በወጣ አንደ ካሴታችውም ላይ ደግሞ ከዚህ በባሰ መልኩ የቤተክርስቲያናችንን የመዝሙር ዜማዎች፣ መሳሪያዎች በገናን ጨምሮ ቅጥ ላጣ ሙዚቃቸው ሲገለገሉበት እንመለከታለን፡፡
  
 እስካሁንም በነበራቸው አካሄድ ከዚህም ይባስ ብሎ በያሬዳዊ ዜማችን ከቅዳሴያችን ላይ ካወጡት 
 እስካሁንም በነበራቸው አካሄድ ከዚህም ይባስ ብሎ በያሬዳዊ ዜማችን ከቅዳሴያችን ላይ ካወጡት ሀረግ ለካሴታቸው ማሻሻጪያ በያሬዳዊ ዜማችን ላይ ሲዘባበቱ ይታያል፡፡ ይህን ቪሲዲ ይመልከቱ፡፡

  ይህን ቪሲዲ ይመልከቱ፡፡

ሌላው ይቅርና የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ዛሬ ላይ እነሱ እንደሆኑ ለመግለጽም ለኢትዮጵያ የፅድቅ ፀሐይ ወጣ እያሉ ገና ለገና ፕሮቴስታንታዊ መሪ ሀገሪቱ እንደሚቀጥል ባልታወቀበት በዚህ አጭር ጊዜእሰይ እስይ ዘመን መጣ ለኢትዮጵያ ፀሐይ ወጣ እንባዋ ታበሰ፡ ኢትዮጵያ ትነሳለች እግዚአብሄርን ታመልካለችፀኻይ አሁን እንደውጣላት በዚሁ ቪሲዲ ላይ የተካተተ ነው እኛ ባናቀርበውም ፡፡ እዚህ ጋር ባለፈውኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮቴስታንታዊ መሪ አስተናገደችበሚል  ባስነበበናችሁ ርዕስ ላይ ከተሰጠን አንደ የፕሮቴስታንት የውስጥ መልእክት ውስጥ አንዱን ለማንሳት እንወዳለን  “you are surprised because our current prime minster is protestant? Just wait and see we will capture all the land of Ethiopia...I'm sure God will like that” ተመልከቱ ከአሁን በኋላ ጊዜው የእነሱ እንደሆነ እና ማንም ሊቀናቀናቸው እንደማይችልየኢትዮጵያ ምድርን እንቆጣጠራለንሲሉ ፕሮፓጋንዳቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚያስችላቸው በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡
እየሆነብን ያለው ቤተሰባዊ ማህበረሰባዊ ሀገራዊ የሆኑ እሴቶቻችንም ጥላሸት መቀባት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ስርዓቶችን ማጥፋት በዚህም አዲሱ ትውልድ  የነገው ዜጋ በማንነቱ እንዳይኮራ የራሴ በሚላቸው ንዋያተ ቅድሳት  እንዲያፍር የእኔ አይደለም እንዲል በአጠቃላይ ፀረ ዜግነት ጦርነት ተከፈቶበታል፡፡
ጎበዝ ምንድነው እየሆነ ያለው  ቤተክርስቲያንን አምላክ መቼም እንደማይተዋት ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ግልፅ ነው ግን  ቤተ ክርስቲያናችን በፕሮቴስታንት በግልጽ የቅርስና የንዋያተ ቅድሳት ዘርፍ እየተደረገባትም እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡  ፕሮቴስታንት በዚሁ አሁን ባወጡት ሲዲ ላይ ቁልጭ ብሎ እንመለከታለን ከበሮ፣ ጸናጽል፣ መቋሚያ፣ በገና፣ ጽንሐ፣ መረዋ፣ መለከት፣ መስንቆ፣ ዋሽንት ሁሉንም የመዝሙር ንዋያትን ያለምንም ከልካይ የራሳቸው እንደሆነ አድርገው በንዋየተ ቅድሳታችን ላይ ሲዘባበቱ  ይታያል ድሮ የመስቀሉ ጠላቶች እንዳልነበሩ መስቀሉን ይዘው እነሱም መስቀልኛ ነጠላ አጣፍተው እውነተኞች ለመምሰል ሲሯሯጡ ይሰተዋላሉ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የእኛው በሆኑ መዝሙር የመዝሙር ስንኞችን በመውሰድ ለመዝሙራቸው ተጠቅመዉበታል ለሁሉም ቀጥሎ ያለውን ቪሲዲ ይመልከቱ፡፡

 ቀጥሎ ያለውን ቪሲዲ ይመልከቱ፡፡

  •  ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ስርአት መከበር እና ማስከበር ከላይ እታች የሚል 

 ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ስርአት መከበር እና ማስከበር ከላይ እታች የሚል ትውልድ የጠፋው ለምን ይሆን?
 በቅርሶቻችን በመዝሙር መሳሪያዎቻችን በራሷበሆኑ ንዋያተ ቅድሳት የባለቤትነት መብትስ የማታስከብርበት እስከመቼ ነው? መናፍቃኑ ቀድመው የእኛ ነው እስኪሉ ይሆን?
ተሐድሶው ተነስቶ የፈለገውን ሃሳብ ሲያንፀባርቅ ብሎም ፕሮቴስታንቶች ከላይ እንዳየነው ለኢትዮጵያ ፀሀይ ወጣላት ሲሉ በእኛው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ዘማሪ ተብዬ ደግሞ ኢትዮጵያ ቀኑ ጨለመባት ይላል፡፡ ቤተክርስቲያናችንን በአንድም በሌላም መልኩ የማፍረስ እስትራቴጄ በውስጥም በውጪም እንቅልፍ አጥተው ሲሯሯጡ ይታያሉ፡፡ በተሐድሶዉም ይሁን በፕሮቴስታንቱ ስርአትን የመበረዝ እንቅስቃሴዎች ቤተ ክርስቲያን የማታወግዘው እስከ መች ነው?
ስርአት በተጣሰ ቁጥር ምእመናን እስከመቼ ዝም ብሎ ይመለከታል?
ዛሬም በያሬዳዊ ዜማችን ሲቀለድ እንደለመድንው አሁንም ይህን አይተን  ዝም ብለን እንመለከት ይሆን?
ሁሉም ጥያቄዎች የእያንዳንዳችን ጥያቄ ሊሆን እንደሚችል በጣም እናምናለን፡፡ መፍትሄውም የእያንዳንዳችን መሆን እንዳለበት ከማንም የተደበቀ አይደለምም የተደበቀም ሊሆን አይችልምም፡፡ እስኪ ምዕመናን እናስተውል ኢትዮጵያ በቤተ ክርስቲያናችን አጋዥነት መቼም ለጠላት  ተንበርክካ አታውቅምመቼም ተሸንፈን አናውቅም ከእኛ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣልና ታዲያ በነዚህ ሚሲዮናውያን እየደረሰብን ያለውን ታላቅ የማንነት ወረራ የማንዋጋው እስከመቼ ነው እስኪ መፍትሄ እንፈልግ እንወያይበት ፡፡
በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።ማቴ.16:18
ይቆየን
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ይሁን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከላይ በትንሹ ያሳየናችሁን ቪሲዲ ለማየት ብላችሁ ለመግዛት እንዳትሞክሩ ምክነያቱም አላማው ገቢው የእኛኑ ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት የሚውል ነው ከፈለጋችሁ በኢሜላችሁ እየሰሩብንን ያለውን ሌላውን እናስተምርበታለን  ብላችሁ ለምትፋልጉት ብቻ ሌሎቹንም መዝሙራት እንልክላችኋለን በኢሜላችን ፃፉልን፡:

ከደቂቀ ናቦቴ የተወሰደ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

5 comments:

  1. send me your email information jackkoprisky@yahoo.com about protestants please

    ReplyDelete
  2. betam asazagn werara new sinodos mawgezin enadalachihut yebetekristianen niwaye kidusat be balebetenet masmezgeb alebeleziya nega zerfe bizu chigroch likesetu yichilalu lemisale teraneger yizewu tabot bilunaa sewungirabiyagabut tifat bekelalu aymelesim. egzer yerdan, amen!!!

    solomemekonn@gmail.com

    ReplyDelete
  3. pls bahun sehat bezihe zuriya sera eyeseran selehon ebake yetekmachuale yemeteluten tsafulegn aglegelote besenbt tmehert bet nw yene2121@gmail.com

    ReplyDelete
  4. የገረመኝ ነገር፡- ያሬዳዊ ዜማንና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ቅርሶችን ከቻልን ለመላው ዓለም እናስተዋውቃለን፣ እናስለምዳለን እየተባለ ጥረት በሚደረግበት በዚህ ዘመን ኢትዮጵያውያን እራሳቸው ያሬዳዊ ዜማን ተገለገሉበት ብሎ በክስ መልክ ማቅረብ እጅግ ግራ አጋቢ ነው፡፡ የድረ-ገጹ ዓላማ እውነትም ስለ ቅርስና ባህል እንክብካቤ መቆርቆር ሳይሆን ለኢትዮጵያውያን ከቶ ፋይዳ የሌለው፣ በሕዝቦች መካከል ጥላቻን የመጫር ጥረት ነው፡፡ መኮነን ካልቀረ ደግሞ ያሬዳዊ ዜማን ለዓለማዊ ዘፈን የሚጠቀሙትን ሰዎች ጭራሽ ዝም ብሎ በማለፍ በአንጻሩ ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር በዶክትሪን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለየት በሚል ቤተክርስቲያን ጥቅም ላይ ስለዋለ ብቻ ስድብና ዘለፋ ለዓለም ማሠራጨት አደገኛ ሥራ-ፈትነት ይመስለኛል፡፡ እነ ክራር፣ ከበሮ፣ መሰንቆና ሌሎች ለመንፈሳዊ መዝሙር የምንጠቀማቸው የዜማ መሣሪያዎች በየመሸታ ቤቱና ለጾታዊ ፍቅር መግለጫ ለዘመናት አገልግሎት ላይ ሲውሉ እንደነውር ሳይቆጠር በ“ፕሮቴስታንት” አብያተክርስቲያናት ስለታዩ ብቻ “ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት በመዝረፍ ላይ በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር” የሚል ከንቱ ወሬ ማስተላለፍ ባዶነት ብቻ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ግለሰቦችንና የሌሎችን ኃይማኖት በመሳደብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ተግባር መሆኑን ነው እኔ የምረዳው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን መከባበርንና መቻቻልን ይስጠን!

    ReplyDelete