Thursday, July 16, 2015

የስልጤ – ቂልጦ ቅድስት ማርያም አስተዳደር እና ምእመናን: ‹‹የድረሱልን ጥሪ››ው በድረ ገጽ መሰራጨቱ ‹‹ከፍላጎታችን ውጭ ነው፤ አውግዘነዋል›› አሉ


  • የሰበካ ጉባኤው እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው 6 አባላት የሐሰት ወሬ ማሰራጨት በሚል ተከሠዋል
  • ከ11-14 ቀናት እስር በኋላ በዋስ ቢወጡም ሊቀ መንበሩ የማርያም ወርቅ ተሻገር እንደታሰረ ነው
  • ‹‹ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ›› በቤተ ክህነት እና በመንግሥት አካላት ‹‹ጥረት እየተደረገ ነው››
  • የሰላም ጉባኤ በማካሔድ የቤተ ክርስቲያኑን ቅዳሴ ቤት ለማክበር መዘጋጀቱን ሀ/ስብከቱ አስታውቋል
*          *          *Silte01
  • ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ››ው፣ የጥንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል መባሉ ያልተረጋገጠ ነው
  • የስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፤ ዜጎች በመግባባት እና በፍቅር የሚኖሩባት ናት፤ በጽሑፉ ሊቢያን እንደ ንጽጽር መጠቀማችን ተገቢ አልነበረም፤
  • የወረዳ፣ የዞን እና የክልል አመራሮች ከሀገረ ስብከቱ፣ ከወረዳ ቤተ ክህነቱ፣ ከሃይማኖት ፎረም እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው፤
  • ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ›› ከደብሩ ምእመናን፣ ከሰበካ ጉባኤው እና ከሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ዓላማ እና ፍላጎት ውጭ ሐራ ዘተዋሕዶ በተባለው ድረ ገጽ በመለቀቁ ድርጊቱን አውግዘነዋል፡፡