Tuesday, May 29, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ‹በቦታው› የተገኘበት ስብሰባ እና መግለጫ

ማጠቃለያ ሪፖርታዥ (READ IN PDF)



· የመግለጫው የመጀመሪያ ረቂቅ ምልአተ ጉባኤው ያልመከረባቸውን ዐበይት ጉዳዮች ያካተተ እንደነበር ተጠቁሟል፤ የዋልድባ እና የነ አባ ፋኑኤል የሐሰት ስኬት በሥርዋጽ ገብቶበት ነበር

· አባ ጳውሎስ ምልአተ ጉባኤው ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ውሳኔ ባስተላለፈበት ቃለ ጉባኤ ላይ አልፈርምም ብለዋል፤ ስለማኅበሩ በመግለጫው ላይ የሰፈረውን አንቀጽም አላነብምየሚል አተካራ ውስጥ ገብተው ነበር

· ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስነት አንሥቶ ወደ ጉጂና ቦረና ሊበን ዞኖች ሀ/ስብከት ለማዛወር በፓትርያ የቀረበው ሐሳብ ውድቅ ተደርጎ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ደርበው እንዲመሩ ተወስኗል

· አገር ዓቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መሥራች ጉባኤ ከግንቦት 26 - 27 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ጽጌ ስጦታውና ሰባት ግለሰቦች ማዕርገ ክህነታቸው ተገፎ እንዲወገዙ ተወሰነ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዐሥረኛ ቀን የቀትር በኋላ ውሎ




· ቅዱስ ሲኖዶስ በውሳኔው መግለጫ ዝግጅት ላይ ጥንቃቄ አድርጓል፤ በመላው ዓለምየሚሠራጨውን መግለጫ በጽሑፍ የሚያዘጋጁት ከምልአተ ጉባኤው የተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

· አባ ሰረቀ በተጠየቁበት ጉዳይ እምነታቸውን በጽሑፍ ይገልጣሉ፤ ለ”እውነትና ንጋት” ሌላ ማስተባበያ መጽሐፍ እንዲጽፉ ተወስኗል።

· ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ለፕሮቴስንታንት ቤተ እምነት የጻፉት ደብዳቤ የእርሳቸው ላለመኾኑ በጽሑፍ ያረጋግጣሉ።

· በጋሻው ደሳለኝ ተጨማሪ ስሕተቶቹ ተመርምረውና ራሱም ተጠይቆ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብ ተወስኗል።


· ሊቃውንት ጉባኤው በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚነሡ ማንኛውንም የሃይማኖት፣ የሥርዐትና የታሪክ ጥያቄዎች ለመመለስ በሚያስችል የሰው ኀይልና በልዩ በጀት እንዲጠናከር ተወስኗል።

Wednesday, May 23, 2012

ማ/ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች መምሪያ ሥር እንዲወጣና ራሱን እንዲችል ተወሰነ

የቅዱስ ሲኖዶስ ዐሥርኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎ


· በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ግለሰቦች ላይ የቀረበውን ጥናታዊ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ደግሞ ከሰዓት በኋላ በመነጋገር እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል:: (READ THE DOCUMENT from HERE)

· ማኅበረ ቅዱሳን በአወቃቀሩ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ወጥቶ ለዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ እንዲኾን ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል::

· በእሳታዊው ዘመን ወደ እሳታዊው ቤተ ክህነት - ቀልጦ መቅረት ወይም ነጥሮ በመውጣት የተቋማዊ ለውጥ አብነት መኾን!!

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዘጠነኛ ቀን ውሎ


ቅዱስ ሲኖዶስ የማኅበራት መተዳደርያ ደንብ ጥናት ዳግመኛ ተጠንቶ እንዲቀርብ አዘዘ


አርእስተ ጉዳይ-

  • በማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ ዝግጅት ላይ የቀረበው ጥናት የጽዋ፣ የጉዞና የስብከተ ወንጌል ማኅበራት፤ የጽርሐ ጽዮን አንድነት ማኅበር፣ የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበረና የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና እንዲከስም የሚጠይቅ ነው
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል
  • የሰንበት /ቤቶች / ሊቀ ጳጳስ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተና ጸሐፊውለመሪያው የማይመጥኑበሚል ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ጠይቀዋል
  • ዕንቍ ባሕርይ በማ/ ላይ ተጨማሪ የክስ ደብዳቤ ለምልአተ ጉባኤው አሰራጭቷል፤ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ እና የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ያስረዳሉ
  • ብፁዕ አቡነ አብርሃም አቡነ ፋኑኤልን ቋቋሙ - “እኔ ወጪውን እችላለኹ፤ ከእኔና ከአንተ ማናችን ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ሥራ እንደ ሠራ አጣሪ ተልኮ ይጣራ?”
  • የጨለማው ቡድን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ በኮሚቴው የቀረበውን የጥናት መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ለማስገልበጥ እየተንቀሳቀሰ ነው
  • አባ ጳውሎስ የቀሲስ / መስፍንን አቤቱታመዋቅሩን ጠብቆ አልመጣምበሚል ለማዘግየት እየሞከሩ ነው፤ የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ልኡካንንበነገር አቀጣጣይነትከሰዋል
  • የዕርቀ ሰላም ንግግሩ በሐምሌ ወር ይቀጥላል፤ አባ ጳውሎስና አባ ፋኑኤል አባ መልከ ጼዴቅን በፖሊቲከኛነት ከሰዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በበኩላቸውበውጭ ያሉት አባቶች ዕርቀ ሰላሙን ከልብ የሚፈልጉ ናቸው፤ ችግር ያለው እዚህ ቤት ነውበማለት ለፓትርያርኩ ወቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል

Monday, May 21, 2012

በብዙ ጫና ውስጥ ያለው ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢ ስለሚገነባቸው ፕሮጄክቶች ሪፖርቱን አቀረበ

ሪፖርቱ የጠ/ቤተ ክህነት ሓላፊዎች “አቀረብን” ካሉት በይዘትም በተአማኒነትም የተሻለ ነው።

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 10/2004 ዓ.ም፤ May 18/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢው ሊሠራው ስላቀደው ግዙፍ ሮጄክት “አጠናሁት” ያለውን ሪፖርት አቀረበ፤ ከመንግሥት ጋር መነጋገሩንም ገለጸ። ዛሬ ይፋ የተደገው የማኅበሩ ሪፖርት የቤተ ክህነቱ አዳዲስ ተሿሚዎች ማኅበሩን በዋልድባ ጉዳይ በከሰሱ ማግስት የቀረበ ሲሆን ለእነርሱ ክስ የተሰጠ አፋጣኝ ምላሽ ይሁን አይሁን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

Friday, May 18, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሰባተኛ ቀን ውሎ ሪፖርታዥ


  • አባ ጳውሎስ በእመቤታችን ንጽሕና ላይ እምነታቸውን እንዲገልጡ ቢጠየቁ አንደበታቸው ተሳሰረ፤ ለጥያቄው መነሻ የኾነው ፓትርያርኩ በአባ ሰረቀ ‹መጽሐፍ› ላይ ስለተጠቀሰው የዶክትሬት ጽሑፋቸው ዝምታን በመምረጣቸውና ኮሚቴውም የእርሳቸውን ምላሽ ወይም አቋም አለመመርመሩ ነው - “አባ ሰረቀ ጽሑፍዎን ጠቅሰው መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ ለምን ዝም አሏቸው? ኮሚቴውስ ለምን አልጠየቀም? ይሉኝታ ነው ወይስ ተመሳስሎ ለመኖር ነው?” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም - ነደ ‹ተሐድሶ›/
አባ ጳውሎስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ “አልቀበልም፤ ኮሚቴው በትክክልና በጥራት አልሠራም” በሚል ያመጡትን ተለዋጭ ሐሳብ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውድቅ በማድረግ ሪፖርቱ ተባዝቶ እንዲደርሰው አዝዟል፤ ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል

  • አባ ጳውሎስ የቅዱስ ያሬድን በዓል ለማክበር በሚል ሰበብ የቅዱስ ሲኖዶሱን ስብሰባ አቋርጠው ዛሬ ወደ አኵስም ለማምራት ያሰቡትን ጉዞ ምልአተ ጉባኤው ተቃውሟል - “በሐዋርያት ቃል፣ በሐዋርያት ቃል÷ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው፤ ይህ አጀንዳ ሳምንትም ቢፈጅብን እርስ በርሳችን ሳንፈታተሽ አንድ ሰው እንዳይሄድ!” /ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እንዳስጠነቀቁት/
  • በማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ ዝግጅት ላይ በ”ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች የተጠና ነው” የተባለው ሰነድ በምልአተ ጉባኤው አባላት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፤ ጥናቱ በልዩ ኹኔታ ማኅበረ ቅዱሳንን እንደሚመለከት አባ ጳውሎስ ግልጽ ቢያደርጉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ አርቅቀንና አጽድቀን ሰጥተናል፤ ይህ ጥናት አይመለከተውም፤ ለሌሎቹም ቢኾን ሰነዱን በጥንቃቄ መርምረን ፈትሸን ነው የምንወስነው” በማለት 15 ገጾች ያሉት ጥናት ተባዝቶ እንዲደርሳቸው አዝዘዋል፡፡
  • በመንፈሳውን ማኅበራት ምሥረታ ላይ የተደረገው ጥናት በዋናነት የማኅበራትን አፍራሽ ገጽታ በማጉላት “አሁን ባላቸው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያም ይኹን በጥንታውያን አኀት አብያተ ክርስቲያን ታሪክ ያልተለመደ በመኾኑ ሊስተካከል ይገባዋል፤ ቤተ ክርስቲያን በቃለ ዐዋዲው የተዘረዘሩ መዋቅሮቿን በማጠናከር ምእመናን ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ ይገባል፤” ብሏል፡፡ ማኅበር የሚለው ስያሜ የማይለወጥ የቤተ ክርስቲያን መገለጫ በመኾኑ አሁን በማኅበራት መልክ ለተደራጁትና ለሚደራጁት አካላት “ኮሚቴ፣ ክበብ” የሚል ስያሜ ብቻ እንዲሰጣቸው ሐሳብ ያቀርባል፡፡
  • በሲዳሞ /ሐዋሳ/ ሀገረ ስብከት “ሊቀ ጳጳሱ ሁሉንም አካላት አቅፈው ለመምራት አልቻሉም፤ ለማኅበረ ቅዱሳን ያደላሉ” በሚል ጥቅመኞችና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች “ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የኾነ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዲቋቋምላቸው በአባ ጳውሎስ የቀረበውን ሐሳብ ምልአተ ጉባኤው “የተሐድሶ መንፈስ እንዲህ አድርጎ ቤተ ክርስቲያኒቱን መገነጣጠል ነው፤” በሚል ውድቅ አድርጎታል፡፡ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስነታቸው ለሁሉም ማእከላዊ አባት ኾነው እንዲመሩ፣ ጥያቄ አቅራቢዎቹም ለሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲገዙ እንጂ ለማንም ተብሎ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደማይሻሻል ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል፡፡
  • ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ወጥ መንገድ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ ኾኖ የተሾመው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ “መምሪያውን ለመምራት ብቃት የለውም” በሚል በአስቸኳይ ተነሥቶ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው እንዲመለሱ ትእዛዝ ሰጥቷል፤ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ የተነሡበት መንገድ “ሽፍትነትን በቤቱ ያነገሠ” በማለት ባላመኑበት ደብዳቤ ላይ እንዲፈርሙ መገደዳቸውን አጥብቆ ኮንኗል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ስለተጻፈው ደብዳቤም “ሁልጊዜ ይኼን ማኅበር ምክንያት እየፈለጉ በፖቲካና በአስተዳደር መክሰስ፣ ማሳደድ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? መቼስ ነው የሚቆመው? ማኅበሩን ማዳከም ቤተ ክርስቲያንን በድጅኖ የማፍረስ ያህል ነው፤ የመናፍቃን መቀለጃና መጫወቻ ለማድረግ ነው፤” በሚል ክፉኛ አብጠልጥሎታል፡፡
  • የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ ፊት ቀርበው ከመምሪያው ዋና ሓላፊ በሕገ ወጥ መንገድ መነሣትና በእርሳቸው ምትክ በሽፍትነት ከተሾመው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ ጋራ በተያያዙና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የገጠማቸውን ችግር እንደሚያስረዱ ተነግሯል፡፡ ተወካዮቹ አባ ጳውሎስ ሠርቶ ከማሠራት ይልቅ በአንድ በኩል ማኅበሩን በተለያየ መንገድ እያጠቁና አገልግሎቱ በየምክንያቱ እንዲዳከም በመጣር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መዋቅር በቤተ ክርስቲያኒቱ ጠላቶች እንዲወረር የሚያደርጉበት አካሄድ ከቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ህልውና አኳያ ስለሚያደርሰው ጉዳት አቋማቸውን ገልጠው ይናገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  • አባ ጳውሎስ በሌላቸው ሥልጣን በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ የጣሉት የፊርማ እገዳ ተነሥቶ የኮሚሽኑ የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሒሳቦች በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንደ ቀድሞው እንዲንቀሳቀስ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ አባ ጳውሎስ የኮሚሽኑን ሊቀ ጳጳስ ለምን እንዳገዱ በቤቱ ሲጠየቁ “አልፈርምም፤ አልታዘዝም እያለ፤ በሲኖዶስ እየፈከረ” በሚል ከስሰዋል፡፡ ብፁዕነታቸውም “አዎ! ሕግ ስለተጣሰ፣ ጥያቄው አግባብ ስላልኾነ አልፈርምም ብዬአለኹ፤ በገንዘብ እጦት ከመቶ በላይ ሠራተኞችን በትነናል፤ ኮሚሽኑ የፕሮጀክት ብር ብቻ እንጂ ሌላ ገንዘብ የለውም፤ የፕሮጀክት ብር ደግሞ ለፕሮጀክት ብቻ ነው የሚውለው፤ የፋይናንስ መምሪያ ሓላፊውን ጠይቄ ይህንኑ አረጋግጦልኛል፤ ኮሚሽኑን ከጥፋት ለማዳን ነው ይህን ያደረግኹት፤ ይህ ጉባኤ ገንዘቡ ይውጣ ካለ አይደለም አቶ ወይዘሮም መጥታ ትፈርም! በሕጉ መሠረት ግን ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ ኾነን እኔና የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ነው የምንፈርመው፤” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አባ ጳውሎስ እገዳው ለጊዜው ያስተላለፉት እንደኾነ ቢናገሩም “ለጊዜውም ቢኾን ቅዱስ ሲኖዶስ የሾመውን ሊቀ ጳጳስ እርስዎ ሊያግዱ አይችሉም፤ አሠራሩ ባለበት ይቀጥል” በማለት የፊርማ ስረዛ ጥያቄ ላቀረቡባቸው ባንኮች ሁሉ የጻፉት ደብዳቤ በሌላ ደብዳቤ ተሸሮ አሠራሩ በነበረበት እንዲቀጥል ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
  • አባ ጳውሎስ ግፊት በአኵስም ሀገረ ስብከት ከሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሰላማ ጋራ ስለተፈጠረው ችግር የአኵስም ጽዮን ማርያም ንቡረ እድ በቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ቀርበው ያስረዳሉ፤ አባ ጳውሎስ “በላሊበላ ጉዳይ ላይ የተያዘው አጀንዳ ከማኅበራት ማቋቋሚያ ጥናት ጋራ ተያይዞ ይታይልኝ፤” በሚል “ማኅበረ ቅዱሳን ሕገ ወጥ ጉባኤ አካሂዷል” ብለው ለመክሰስ አሸምቀዋል፡፡ በስደት ላይ የሚገኙት አባቶች ተወካይ በዕርቀ ሰላም ንግግሩ ሂደት ላይ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ሪፖርት አቅርበዋል፤ ንግግሩን በሚያደናቅፉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተዋል፤ በሪፖርቱ ላይ የሚካሄደው ውይይት ዛሬ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 10/2004 ዓ.ም፤ May 18/ 2012)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ዘጠኝ ቀን ሰባተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ስብሰባውን የጀመረው ቀደም ሲል በንባብ ባዳመጠው ባለ60 ገጽ የሃይማኖት ሕጸጽ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበለት ሪፖርት ላይ በመወያየት የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ነበር፡፡