Friday, June 29, 2012

በባቦጋያ መድሃኒአለም የቦታ ጉዳይ 13 ሰዎች ላይ እያንዳንዳቸው ሰባት ወር ተፈረደባቸው

  • ከ400 በላይ ምዕመናን በእንባ ወደ እስር ቤት ሸኝተዋቸዋል፡፡
  • የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የበላይ አካል ተጽህኖ አለበት ፤

(አንድ አድርገን ሰኔ 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በፍርድ ቤቱ ውሳኔ በጣም አዝነናል ፤ ሲጀመር አንስቶ በባቦጋያ መድሃኒዓለም ቦታ እና በኩሪፍቱ ሪዞርት መካከል ያለው የቦታ ውዝግብ በየጊዜው ማቅረባችን ይታወቃል፤ አቅማችን በፈቀደው መጠን ጉዳዩን ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ የመፍትሄ አካላት እንዲሆኑ ያላሰለሰ ጥረት አድርገናል ፤ ከወራት በፊት የቤተክርስትያኑን ቦታ በአካባቢው ምዕመናን ጉዳዩን ዳር እዲያደርሱ የተወከሉ ሰዎች በፍርድ ቤት “እናንተ መጠየቅ አትችሉም ቤተክርስትያኒቱ የወከለቻችሁ አካላት አይደላችሁም” በማለት ለኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት እንደተወሰነለት ገልጸን ፅፈን ነበር ፤ 

ከዚህ በኋላ ምዕመኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተስፋ ለማስቆረጥ ወደፊት ምንም ጥያቄ እንዳይጠይቁ ለማሸማቀቅ አቶ ጌታቸው ዶኒ ፤ የሪዞርቱ ባለቤትና የፍርድ ቤት ጠበቃቸው ከባቦጋያ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን የሀሰት ክስ ማቅረባቸውን ይታወሳል ፤ ይህ በእንዲህ እያለ አቶ ጌታቸው ዶኒ የሀሰት ምስክሮችን አስመጥቶ ፍርድ ቤት በማቆም ማስመስከሩ ይታወቃል ፤ በዚህ የፍርድ ቤት የምስክር ሂደት የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ፍርድ ቤት ውስጥ የሚሰሙትን ምስክርነት ለሶስተኛው ምስክር አሳልፈው ሲናገሩ በመያዛቸው ለ24 ሰዓት ታስረው በ2000 ብር ዋስ መፈታታቸው ይታወቃል ፤ ፍርድ ቤቱ እኝህን አስተዳዳሪ  አቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርት ቢያዝም አቃቢ ህግ ልብ አግኝቶ ይህን ሲያደርግ መመልት አልተቻለም ፤ ፍርድ ቤቱ የተቀመጠው ህግ ከባለስልጣናት ትዕዛዝ ሲበልጥበት መመልከት አልቻልንም ፤ አስተዳዳሪው ምስክሮቹ ቃላቸው አንድ አንዲሆን በማሰብ የውስጡን ለውጩ ምስክር አሳልፈው ምስክርነቱን ሲናገሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በዝምታ መታለፋቸው ሁሉን አስደምሟል ፤ በመሰረቱ ምስክርነት እየተሰማ ሳለ አይደለም መስካሪ የችት ታዳሚው ችሎቱን አቋርጦ መውጣት እንደሌለበት ያስቀምጣል ፤ ዳኛው  “ችሎትን በማወክ” በሚል አንቀጽ እዚያው ሌላ ፋይል ሳይከፍት የቅጣተኝነት ፍርድ ማስተላለፍ ይችል ነበር ፤

Saturday, June 23, 2012

በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ



·         የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በአስተዳዳሪው ላይ ያቀረበው የሙስናክስ በመጣራት ላይ ነበር::
·         ወርቅ፣ የውጭ ምንዛሬና የሌሎች ነዋያት ግምት ሳይጨምር በጥሬ ብር ከ200,000 በላይ መዝብረዋል::
·         የአስተዳዳሪውን ሹመት በማስፈጸም የእጅጋየሁ በየነ ሚናአለበት::
·         የሀ/ስብከቱን ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች ለዐመፅ ለማዘጋጀት አባ ጳውሎስ ያሰቡት ዕቅድ አካል ይኾን?
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- ሰባኬ ወንጌል ከነበሩበት የመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን  ብቻ ነው ያስቆጠሩት - አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ፡፡በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትንጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢየመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነትአስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይአደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።

Friday, June 22, 2012

በጀርመን የቅ/ሚካኤል በዓለ ንግሥ በመናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ



(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ የነበረው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ሆን ብለው ከረፈደ በቦታው በተገኙት መናፍቁ «ቄስ» ገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ። በሀገረ ጀርመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኑፋቄያቸው ምክንያት በምእመናን ዘንድ ትልቅ ቁጣን እያስነሱ ያሉት መናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ “ከልካይ የለኝም” በሚል መንፈስ በአካባቢያቸው የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን በአውቶብስ ጭነው ከአካባቢያቸው ወጥተው በአገልግሎት እንዳይስተፉ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የጣሉባቸውን እግድ በመተላለፍ እሑድ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘት ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።


ገዳሙ ከግብር አበሮቻቸው ጋር
በጀርመን በአራቱም አቅጣጫ ካሉት የኢ/ኦ/ተ አብያተ ክርስቲያናት በኮሎኝ ከተማ የሚከበረውን ዓመታዊውን የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን የንግሥ በዓል ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ በታላቅ ቁጥር ተገኝተው የነበሩት ምእመናን በዓሉን በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ሳሉ ግለሰቡ እሑድ ጠዋት ግብር አበሮቻቸውን ይዘው በአገልግሎት ላይ ያሉ በሚመስል መልኩ ፈረጅያቸውን ለብሰው፤ ቆባቸውን አጥልቀው በቤተ ክርስቲያኑቱ የተገኙ ሲሆን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ፤ ዑደቱ አብቅቶ፤ ምእመናኑ ቃለ ምእዳን የሚሰጥበት ቦታ በመሰባሰብ ላይ ሳሉ እኚሁ ግለሰብ ከካህናቱ ጋር ለመቆም ወደፊት ለመቅረብ በሚሞክሩበት ጊዜ በግለሰቡ በቦታው መገኘት በተለይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በግለሰቡ ላይ የጣሉት የእንቅስቃሴ እግድ አለመከበሩ ያቃጠላቸው ምእመናን በንዴት “፤ወደ ታቦተ ሕጉ አይቀርቡም አልተፈቀዶለትም” ብለው መንገድ ዘግተውባቸዋል። በዚህ ጊዜ በዋነኝነት መንገዱን ዘግተው ወደፊት አይሄዱም ብለው ከፊታቸው የከለከልዋቸውን ጎበዝ ምእመን ገፍትረው ለመሄድ በመሞከራቸው ረብሻ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር አልሠራም አለ

ከላስ ቤጋስ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተጻፈው ደብዳቤ
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸሙትንም ሹመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ ምልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

Monday, June 18, 2012

አቡነ ጳውሎስ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘ ቡድን እያደራጁ ነው


አርእስተ ጉዳዮች፡- (READ THIS ARTICLE IN PDF)
  • ·    አቡነ ጳውሎስ በግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መናጋቱ የተረጋገጠውን የዐምባገነንት ሥልጣናቸውን ያድሱልኛል ያሏቸውን ሦስት ቡድኖችን አቋቁመዋል፤ “ጉባኤ አርድእት” አንዱ ነው።
  • ·         የ”ጉባኤ አርድእት” መተዳደርያ ደንብ ከሰሞኑበአቡነ ጳውሎስ ፊርማ እንደሚጸድቅ እየተነገረ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ቢሮ ተሰጥቶታል፤ ምንጩ ያልታወቀ በጀትም ተመድቦለታል፤ 25 መሥራች አባላት እና 180 ተባባሪ አባላት እንዳሉት ተገልጧል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሂደቱን በትኩረት እየተከታተሉት ነው።
  • ·       ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንን ጨምሮ በአእመረ አሸብር፣ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ እና ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የሚመራ ነው የተባለው “ጉባኤ አርድእት” የአቡነ ጳውሎስን የጠቅላይነት ሥልጣን የሚያጠናክር የሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹ማሻሻያ› ረቂቅ አዘጋጅቷል፤
  • ·      ቤተ ክርስቲያን ራሷ ማኅበር ስለሆነች በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም በሚል እንደ ማኅበረ ቅዱሳን እና የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበርያሉትን ማኅበራት ለማዳከምና ለማፍረስ ይሠራል፤ ይህም ካልተሳካ ራሱን ወደ “ማኅበረ አርድእት” ለውጦ በማኅበራቱ ላይ የማያባራ ቀውስ ለመፍጠር ይንቀሳቀሳል፤ “ከማኅበረ ቅዱሳን ያኮረፉ” የሚባሉ ሰዎችን ሰብስቦ ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥቃት አንዱ ስልቱ ነው፤
  • ·   በሰላም፣ ልማትና ሰብአዊ ተራድኦ ዙሪያ ከተደራጁ የወጣት ማኅበራት ጋራ እሠራለኹ በሚል አባላትን በአፈሳ ለመመልመልና መንግሥትን በማወናበድ የፖለቲካ ድጋፍ ለመሸመት ይጠቀምበታል፤
  • · በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠንካራ አቋም የያዙ ብፁዓን አባቶችን በፖለቲከኛነት በመወንጀል፣ በአሉባልታዎች ስማቸውን በማጥፋት፣ በየአህጉረ ስብከታቸው ሁከት በመፍጠር የተቀናጀ የማሸማቀቅ ዘመቻ ይከፍታል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ ሕዝቅኤል፣ አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ቀውስጦስ፣ አቡነ አብርሃም፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና አቡነ ገብርኤል የወቅቱ ዒላማዎች ናቸው፤
  • ·   አቡነ ጳውሎስ የግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች በአራቱ ቃለ ጉባኤአልፈረሙም፤ ቋሚ ሲኖዶስ ፓትርያርኩ አራቱንም ቃለ ጉባኤ ካልፈረሙ በእርሳቸው ርእሰ መንበርነት እንደማይሰበሰብ በመግለጽ አቡነ ጳውሎስን አስጠንቅቋል፤
  • ·    በአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ “በጄነራል ዳይሬክተር ማዕርግ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት” እንደተሰጠው የሚነገርለት የ”ጉባኤ አርድእት” ቀንደኛ አስተባባሪ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን “ጉባኤ እግዚአብሔር” (Ethiopia Assemblies of Godየተሰኘ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት እንደሚያዘወትር፤ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነቱ ተወግ የተባረረውን የሃይማኖተ አበው አባላት በጎጠኝነት ስሜት እያነሣሣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ እየዶለተ መኾኑ ተገልጧል፣

Saturday, June 16, 2012

ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ

·         መናፍቃ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም አይጠሩም
·         የቤተ ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ
·         መናፍቃ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ
·         ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት ይጠናከራል
·         ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያኩ መልእክቶች ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር ይመልከቱ)
·         “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤ ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡

Friday, June 15, 2012

የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት፣ ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ት/ቤት በ”ችግር ፈጣሪው” አስተዳዳሪ አባ ሚካኤል ታደሰ ታውከዋል


 READ THIS ARTICLE INPDF.
·        በአስተዳዳሪነት የተሾሙት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ቃለ ዐዋዲውን በመጣስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመኾናቸው ማዕርገ ክህነታቸው ተሽሮ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ከተወገዙ በኋላ ነው።
·         ሀ/ስብከቱ የሀብት ቁጥጥርን ለማጠናከር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ ዘረፋን ያበረታታሉ።
·        ሰንበት ት/ቤቱን ‹ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው› በሚል አገልግሎቱን የሚያደናቅፉ ርምጃዎች ወስደዋል።
·        አስተዳዳሪው ከአባ ጳውሎስ የኤጲስ ቆጶስ ሢመት ተስፈኞች አንዱ ናቸው።

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 8/2004 ዓ.ም፤ ጁን 15/ 2012/በማዕርገ ዲቁናቸው በእቲሳ ደብረ ጽላልሽ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በዐቃቢነት አገልግለዋል፡፡ ያን ጊዜ ስማቸው ዲያቆን ሙሉነህ ታደሰ ይባል ነበር፡፡ በገዳሙ ማዕርገ ምንኵስና ሲቀበሉ ስማቸው አባ ኀይለ ኢየሱስ ታደሰ መባሉን የገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 79/05/98 በቀን 16/05/1998 ዓ.ም የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የግለሰቡን ማንነት አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡

Monday, June 11, 2012

ዝቋላን መልሰን እናልማ


“ይህን ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
(አንድ አድርገን ሰኔ 4  2004 . )- የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መጋቢት 9 2004 . ለቀናት በዘለቀው እና ለማጥፋት አዳጋች የሆነው እሳት ደኑ ላይ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ ይታወቃል በጊዜው እሳቱን ለማጥፋት በርካታ ምዕመናኖች ከአዲስ አበባ  ከአዳማ እና ከደብረዘይት ወደ ቦታ አምርተውየተቻላቸውን ሁሉ አድርገው እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል ይህን በእሳት ምክንያት ገዳሙ ያጣውን ደን መልሶ ለማልት ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር የመጀመሪያዙር የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ሰኔ 24 እና ሰኔ 25 ቦታው ድረስ በመሄድ በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናና የሚሳተፉበትየጉድጓድ ቁፋሮ እና ዛፎችን የመትከል መርሀ ግብር አውጥቷል በዚህ የተቀደሰ መንፈሳዊ አገልግሎት ገንዘብያላችሁ በገንዘባችሁ ጉልበት ያላችሁ በጉልበታችሁ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ  ይህን የዛፍ ተከላፕሮግራም ለመርዳት የምትፈልጉ ሰዎች ችግኞችን በመግዛት  ብር በማዋጣት እና ቦታው ድረስ በመሄድ የጉልበትአገልግሎት መስጠት ይምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አለን? ዓላማውና ስልቱስ ምንድን ነው?


ሰኔ 11 ቀን 2003 ዓ.ም
/ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ግንቦት 2003 ዓ.ም/ አትምኢሜይል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “መታደስ አለባት” የሚሉ ድምፆችን     የሚያሰሙ አካላት አሳባቸውን በተለያዩ መንገዶች ማሰማት ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ እነዚህ አካላት በመጽሔቶች፣ በጋዜጦች፣ በመጻሕፍት፣ በበራሪ ወረቀቶች፣ በዓውደ ምሕረት ስብከቶችና በሚያገኟቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ይኸን ጩኸታቸውን ማስተጋባቱን       ተያይዘውታል፡፡ እንዲህ እያሉ ያሉትም “ኦርቶዶክሳውያን ነን” እያሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በተለያየ ቦታና ሓላፊነት ላይ ካሉና እንጀራዋን ከሚበሉ፣ ጥቂቶች እንዲሁም ደግሞ በኅቡእና በግልጽ በተለያየ መልክና ቅርጽ ራሳቸውን አደራጅተው ቤተ ክርስቲያኗ ሳትወክላቸው እርሷን ወክለው፣ “እኛም ኦርቶዶክስ ነን” በሚል ካባ ራሳቸውን ደብቀው እምነቷንና ሥርዓቷን “ይህ ሳይሆን ሌላ ነበር” እያሉ ፕሮቴስታንታዊ ትምህርትና መንፈስ የተዋረሳቸው ሰዎች ናቸው፡፡
 
ተሐድሶ የሚባል ነገር አለን? እነዚህ አካላት በአንድ በኩል ተሐድሶ የሚባል ነገር እንደሌለና ተሐድሶ የሚባለው ጉዳይ የሆነ አካል (እነርሱ እንደሚሉት ማኅበረ ቅዱሳን) ስም ለማጥፋት ሲል የፈጠረው የፈጠራ ወሬ እንጂ በሕይወት የሌለ ምናባዊ ነገር እንደሆነ ያስወራሉ፣ ይናገራሉ፡፡ ግን በእውነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማዋ፣ ቀኖናዋና ትውፊቷ መታደስ አለበት በማለት የሚሠራ የተሐድሶ እቅስቃሴ የለምን?

ይህን ጉዳይ እነርሱው በይፋ ካወጧቸው የኅትመት ውጤቶቻቸው ለመመልከትና ለመታዘብ ይረዳ ዘንድ ራሳቸው በተለያዩ መጻሕፍቶቻቸው፣ መጽሔቶቻቸውና ጋዜጦቻቸው ካወጧቸው መካከል የተወሰኑትን ብቻ እንመልከት፡-
hohitebirhan.jpg
“እንደ እውነቱ ከሆነ በወንጌል እውነት ከታደሱ በኋላ በየጊዜው እየተመዘዙ የወጡት ምእመናኖቿና አገልጋዮቿ በውስጧ ቆይተው የተሐድሶን ሥራ እንዲሠሩ ቢደረግ ኖሮ፣ በወንጌል ተሐድሶ ያገኙ ክርስቲያኖች ለዓመታት የጸለዩበትንና የጓጉለትን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ በቅርብ ጊዜ ሊያዩ ይችሉ እንደ ነበር የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም፡፡” (ኆኅተ ብርሃን፣ መጋቢት 2002፣ ገጽ 15)

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች!

ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በ‹‹ግብረሰዶምና ተያያዥ ማኅበራዊ ቀውሶች›› ላይ ለመነጋገር በተጠራው አገራዊ ኮንፈረንስ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፓርላማ አባላት፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ‹‹ግብረሰዶምንና ግብረሰዶም የሚያስፋፉ ምዕራባዊያንን›› አወገዙ፡፡ በዚሁ ታሪካዊና አንገብጋቢ በተሰኘው አገራዊ ኮንፈረንስ ላይ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስቱ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት የኦርቶዶክት ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ያወጡትን የግብረሰዶማዊነት የተቃውሞ መግለጫ በአንድ ድምፅ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ የሚያነሱና ዕርዳታ እንከለክላለን ለሚሉ የምዕራብ አገሮችም ‹‹ዕርዳታቸው በአፍንጫችን ይውጣ›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

በስብሰባው ላይ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማትን በሙሉ ወክለው ጉባዔውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ሕግ ሳይጻፍ ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ ነበራቸው፤ የዛሬ ሳይንቲስቶችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆንዋን ይናገራሉ፤›› በማለት በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እርስ በርስ ተረጋግጠዋል፤ ብቸኛ ነፃ አገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል፡፡ ‹‹አሁንም የተረገጡትና የማንነት ቀውስ ያለባቸው ወገኖች ተናገሩ ብላ የምትሰማ አይደለችም፡፡ ባህላችን አልተለወጠም፣ ታሪካችን አልተቀነሰም፣ ማንነታችን አልተበረዘም፤ እንዲሁ ዝም ብለን የምንለወጥ አይደለንም፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ 

Sunday, June 10, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ከ20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል

(አንድ አድርገን ግንቦት 2 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ፤ የመወያያ መድረኮች ውጤት እያመጡ አይደሉም ፤ መንግስት ዘነዘና የዋጠ ይመስል የአቋም ለውጥ ማድረግ ተስኖታል ፤ የሚሰራውን ስራ አሁንም ገዳሙ ላይ ተጽህኖ የለውም ብሎ አምኗል ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ከ3ሺህ የሚበልጥ የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በቦታው ላይ መግለጹን ገልጸን ነበር ፤ ከዚህ ተቃውሞ በኋላ 10 የሚሆኑ የገዳሙ አባቶችን የአካባቢው ባለስልጣናት ሰብስበው አነጋረዋቸው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል ፤ በቀጣይ ሰኔ 7 ፤ 2004 ዓ.ም ተጨማሪ የስብሰባ ፕሮግራም መያዛቸውን ጭምር ፤ ከዚህ በፊት የተደረጉት የስብሰባ ውጤቶች መስማት ባንችልም አሁንም ስብሰባዎች እየተደረጉ ናቸው ፤ ከእነዚህ ስብሰባዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ረቡዕ የአካባቢውን ወጣቶች በመሰብሰብ ስለ ግድቡ ለማወያየትም ባለስጣናቱ ሞክረው ነበር ፤ በስብሰባው ላይ የተገኙት በርካታ ወጣቶች ስብሰባውን አድርገው ከጨረሱ በኋላ በያዙት አቋምና ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ከየቤታቸው እና በተገኙበት እየተለቀሙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው  ወደ እስር ቤት ገብተዋል  ፤ ለእስር የሚፈለጉ ሰዎች ወሬው እንደደረሳቸው ግማሾቹ ጎንደርና ሌሎች ቦታዎች ሲሸሹ ብዙዎች ደግሞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?” ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፤ 35 በማለት መታሰርን መርጠው እዚያው አሳሪዎቻቸው ይጠባበቃሉ ፡፡ ጉዳዩ የእምነትና በእምነት ስለሆነ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ፤  ወንጌሉ እንዲህ ይላል “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” ማቴዎስ ወንጌል 10፤28

Friday, June 8, 2012

እውን የማኅበረ ቅዱሳንና የኦርቶዶክስ "ተሐድሶ" ፍልሚያ ወይስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ?


(አዲሱ ተስፋዬREAD IN PDF):- ከትላልቆቹ ያገራችን ባለስልጣናት ጀምሮ ታች እስካለው ሕዝብ ድረስ  ማኅበረቅዱሳን  የበርካቶች መነጋገርያ ከሆነ ከራርሟል:: የሰሞኑን ግን ለየት የሚያደርገው ራሱን " ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” "በማለት የሚጠራው ድርጅት በማኅበሩና በተዋሕዶ እምነታቸው ላይ ጽኑ አቋም ባላቸው  ኦርቶዶክስ ሃይማኖትአባቶች ላይ ለማንበብ የሚዘገንኑ (character assassinating) ጽሑፎችን እያስነበበ ነው  ከዚህም አልፎ የ”ተሐድሶ”  ቡድኖች አቡነ ጳውሎስን የተቃወሙ አባቶች ላይ ስማቸውን የሚያጠፋ በርካታ መጽሀፍትእስከመታተም ተደርሷል (አቡነ ሳሙአልን አቡነ አብርሃምን አቡነ ሚካኤል እና ሌሎች ጳጳሳትን ስም እያጠፉ የወጡትመጻህፍትን ያስታወሷልአንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸውና የድረገጻቸውን traffic rank ከመጨመር የዘለለ አርቀውማሰብ የተሳናቸው የፖለቲካ ዌብሳይቶችም እነዚህኑ ጽሑፎች በየድረ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ ለብዙዎች አስነብበዋል
ጽሑፎቹን ያነበቡ በርካቶች የዋሀንም የችግሩን መሰረታዊ ምክንያት ባለመረዳት "የ”ተሐድሶ” ና የማኅበረ ቅዱሳንጦርነት"በማለት እንደዘበት ሲመለከቱትና ሲገረሙበት ይስተዋላል ውስጠ ሚስጥሩን ያወቁና ውዝግቡ "የውክልናጦርነት " መሆኑን የተገነዘቡ ጥቂቶችም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ”  ችግርውስጥ መግባቷን ይተነትናሉ ለመሆኑ ግን የማኅበረ ቅዱሳንና የ”ተሐድሶ”  ገመና ምን ይመስላል። ከሁለቱምበስተጀርባ ያለው አካል ማነውየሁለቱ አካላት መሰረታዊ አለመግባባትስ ምክንያቱ  ምንድነው?