Thursday, January 31, 2013

የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራውን ጀመረ

His Grace Abune Estifanos
  • ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በኮሚቴው ስብሰባ አልተገኙም
  • ቅ/ሲኖዶሱ የኮሚቴውን ሊቃነ መናብርት ሠይሟል
  • በኮሚቴው እና በቅ/ሲኖዶሱ ሥልጣን መካከል ጥያቄዎች ተነሥተዋል
  • ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ወደ ዋና ጸሐፊነት ሓላፊነታቸው ተመልሰዋል
ቅ/ሲኖዶስ ለ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ የሠየመው አስመራጭ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካሄደ፡፡ የኮሚቴው ቀዳሚ ስብሰባ የተካሄደው ኮሚቴው በአወዛጋቢ ውሳኔ ታኅሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም ከተሠየመ ከአንድ ወር በኋላ በእጅጉ ዘግይቶ ነው፡፡ የመዘግየቱ መንሥኤ ከምርጫው በፊት ለዕርቀ ሰላሙ ፍጻሜ ቅድሚያ ከመስጠት፣ ውጤቱን ከመጠበቅና ለውጤቱ ከመሥራት አኳያ በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ በታየው ከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት ነው፡፡
ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሲጀመር በሚበዙት አባቶች ከፍተኛ ድጋፍ የተሰጠው ይኸው የሰላምና አንድነት አጀንዳ በቀጣዩ የስብሰባው ቀን በውጭ ተጽዕኖ ጭምር ከተቀለበሰ በኋላ የዕርቅና ሰላም ጉባኤው ተስፋ ጨልሞ የምርጫው ሂደት እንዲቀጥል ውሳኔ ተላልፏል፡፡

“መናገር የማልፈልገው ብዙ ነገር አለ” ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል


ከላይፍ መጽሄት የተወሰደ
(ቅጽ 7 ቁጥር 99 … ጥር 2005 እትም)
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የጠቅላይ ቤ/ክህነት ዋና ጸሐፊ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለቀናት ያደረገው ስብሰባ በመጠናቀቅ ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ አሜሪካን ሀገር የሚገኝው ሲኖዶስ ያቀረበውን ጥያቄ ለመቀበል ሕገ ቤተክርስቲያን እንደማይፈቅድለት በመግለጽ  ስድስተኛውን የቤተርክርስቲያን ፓትርያርክ ለመምረጥ መወሰኑን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ የላይፍ መጽሄት አዘጋጆች ከመግለጫው በኋላ ወደ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ አቡነ ሕዝቅኤል ቢሮ በማምራት አቡኑን ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡ አቡነ ሕዝቅኤል የስራ ጫና ውስጥ የነበሩ ቢሆንም  መጠነኛ ጊዜ መስዕዋት በማድረግ ጥያቄዎቻችንን በመቀበል ተገቢ ነው ያሉንን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ነገር ግን አቡኑን በምናነጋግርበተ ሰዓት ማንነቱ ያልለየነው አንድ ሰው ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ ጥያቅና መልሱን ይከታተል ነበር፡፡ ለብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል የምናቀርብላቸው ጥያቄ እኛን እየተመለከቱ ምላሽ መስጠት ይገባቸው የነበረ ቢሆንም በእያንዳንዱ አረፍተ ነገር  ግለሰቡን እየተመለከቱ ማረጋገጫ እንደሚጠይቅ ሰው አይናቸውን ገጽታው ላይ ያንከራትቱ ነበር፡፡ ጥያቄያችን ጨርሰን ከቢሮ ልንወጣ ስንልም“አቡኑን ለማስለፍለፍ ሞክራችሁ ነበር እሳቸው ግን ብልጥ በመሆናቸው አንዳች ነገር አልተናገሩም”ብሎናል፡፡ ለማንኛውን ቃለ ምልልሱን እነሆ፡፡

እናት ቤተ ክርስቲያናችን አልተከፈለችም


አንድ አንባቢያችን ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የተጻፈውን ይህችን ወቅታዊ የሆነች ጽሁፍ ልከውልናል፣ እኛም እጅግ ጠቃሚ ነችና አንባቢያን ሊጠቀሙባት ይችላሉ ብለን ስላሰብን እንደሚከተለው አቅርበነዋል። አንባቢያችንን ከልብ እናመሰግናለን፥ መልካም ምንባብ ይሁንልዎ።
ሙሉውን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
ጌታቸው ኃይሌ
መግቢያ፤
"ቤተ ክርስቲያናችን ከሁለት ተከፈለች" የሚል ሥጋትና ሐዘን ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል። እውነት ተከፍላ ከሆነ ሥጋቱንና ሐዘኑ የሁላችንም ነው። ግን ለመሥራቿ ክብርና ምስጋና ይግባውና፥ እናት ቤተ ክርስቲያናችን አልተከፈለችም። ከፈሏት የምንላቸው ካህናትም፥ አለመከፈሏን ደጋግመው ተናግረውታል። ሳትከፈል ተከፈለች ማለት ያሳዝናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንኳን ዛሬ፥ መከፋፈልን የሚያመጡ የነገረ መልኮት ብጥብጦች በተነሡባቸው
የተለያዩ ዘመናት እንኳን፥ ጥቂት ተሞክሮ እንደሆነ ነው እንጂ፥ አልተከፈለችም። ስለዚህ ፥ መዓቱ እስኪያልፍ ድረስ፥ ቅዱስ ገብርኤል "ንቁም፡ በበህላዌነ፡" እንዳለው፥ ባለንበት ነቅተን እንጽና፤ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ነፃነት ተባብረን በአንድነት እንሥራ።

Monday, January 28, 2013

ቤተ ክህነት የአዲሱን ፓትርያርክ ምርጫ የሚቃወሙትን እንደምትከስ አስፈራራች

መንበረ ፖትርያሪክ አዲስ አበባ

(ደጀ ሰላም፤ ጥር 20/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 28/2013/ PDF)፦ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ ሰላማዊ የሽግግር ጊዜውን ለማደናቀፍ የሚገኙ ቡድኖችን፣ የመገናኛ ብዙኅንና ግለሰቦችን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል የስድስተኛውን ፓትርያርክ አሿሿም በሚመለከት ሕገ ደንብ ወጥቶ ምርጫውን ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ውስጥ መሆኑን የሚያውቁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙኅን፣ ከውስጥ አፍራሽ ኃይሎች የሚቀበሉትን ፀረ ሰላምና ከእውነት የራቀ አሉባልታ ከድረ ገጽ ያገኙ በማስመሰልና ምንጮቻችን እያሉ በውጭና በአገር ውስጥ ያለውን ምዕመናን እያወናበዱ በሚገኙት ላይ ቤተ ክህነት ክስ መመሥረቷን የዘገበው ጋዜጣው መግለጫውን የሰጡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ መሆናቸውን አብራርቷል።

Thursday, January 24, 2013

ልናስተውል ይገባናል!

ዛሬ ቆም ብለን የምናስብበት ወቅት ነው!
አንድ አንባቢ የላኩልን መልዕክት ደርሶናል መልዕክቱ ጥሩ ስለሆነ እና አንባቢያን ቢያነቡት ይማሩበታል ወይም ይጠቀሙበታል ብለን ስላሰብን አቅርበነዋል።
መልካም ምንባብ . . .

ጽሑን በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


ልናስተውል ይገባናል!

ይሄን ጽሑፍ ልጽፍ የተነሳሁት በደጀሰላም “ሁሉም “የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም!” ቢል” በሚል የተነበውን ጽሁፍ ካነበብሉ በኃላ ነው ጸሓፊው “መልዕክተ ተዋሕዶ-ዘኪሮስ” በመባል ይታወቃሉ መልዕክቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ ትክክለኛ ሆኖ ሳለ ከታች የተሰጡ አስተያየቶችን ሳነብ በጣም አዘንኩ! እንዴት አይነት ዘመን ነው ብዬም አሰብኩ ከዛም እኔስ እስኪ በጎለድፌ ብዕሬ ለምን አልጽፍም ቤዬ ጀመርኩ፣ አንባቢ ያግኝም አያግኝም ሃሳቤን ለመግለጽ ወደድኩ ሚዛን ከደፋች አመልከቷት ካልደፋችም ደግሞ ወደ ሚመለከተው ላኳት።

ሁሉም “የማንም አሿሿሚ አልሆንም! የሥልጣን ጥመኞችንም አላገለግልም!” ቢል



(መልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ ደጀ ሰላማውያን እንደምን ሰነበታችሁ? ብዬ መጠየቅ፥ ዛሬ አልፈለኩም። እንዴት እንደሰነበትን፥ ሁላችንም እናውቀዋለንና። ለመላው የቤተ ክርስቲያን  ልጆች እያሳለፍነው ያለው ሳምንት የሐዘንና፥ ተስፋችንን አጨላሚ፥ ሆኖ ነው የሰነበተው። ይህ ሳምንት፥ ለሃያ አንድ ዓመታት ፥ መከፋፈል በተባለ በሽታ ፥ ታማ የነበረችው እናት ቤተ ክርስቲያን  ፥ ስትሰቃይ ኖራ ፥ ያረፈችበት ሳምንት ነው።  ነገር ግን አጥብቀን ከቀድሞው አብዝተን ከጮህን፥ ልክ በወንጌሉ እንደተጻፈው የሞተውን የሚያስነሳው ትንሣኤና ሕይወት የሆነ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ እስትንፋሷን ሊመልሰው ይቻለዋል። በእምነታችንም ጸንተን እያንዳንዳችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አንበል፤ በማለት ሰሞኑን አእምሮዬን ሲሞግቱኝ ወደ ከረሙት ጉዳዮች ተራ በተራ ልግባ።

ፓርላማው የላከው ቡድን የላሊበላ ቤተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው አለ

ቤተ ጊዮርጊስ ላሊበላ
(Reporter Amharic):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቅርስ፣ የባህልና የመገናኛ ብዙኅን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የአገሪቱ ቅርሶችን እንዲታዘብና ሪፖርት እንደያደርግ የላከው የሕዝብ ተወካዮች ቡድን፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በአሳሳቢ አደጋ ላይ መሆናቸውን ሪፖርት በማድረግ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡

በላሊበላ ተገኝቶ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡትን አብያተ ክርስቲያናት የጎበኘው የፓርላማው ቡድን ከተመለሰ በኋላ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ታደለች ዳለቾና ሌሎች በሚኒስቴሩ ሥር የሚገኙ የሥራ ኃላፊዎችን ባለፈው ሰኞ በመጥራት ምልከታውን በማቅረብ ማሳሰቢያም ሰጥቷል፡፡ 


በንጉሥ ላሊበላ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአለት ተፈልፍለው የተሠሩት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ የመሰንጠቅ አደጋ ላይ መሆናቸውንና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኙም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ቡድኑ ለኃላፊዎቹ ሪፖርት አድርጓል፡፡ 

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ


·       የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል፤
·       ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው” ነው፤
  •       መነኮሳት ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፤
  • ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ የዋልድባ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ። በመነኮሳት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የዘረዘረው ደብዳቤው የክልሉ መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትም ዝርዝር አቅርበዋል። ሙሉ የደብዳቤው ሐሳብ ቀጥሎ ሰፍሯል።
የክልሉ መንግሥት የመናንያኑን አቤቱታ ይቀበል ይሆን? የምናየው ይሆናል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

Tuesday, January 22, 2013

ጉባኤ ኬልቄዶን vs. የጥር 6 የሲኖዶስ ጉባኤ


ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን
ጉባኤ ኬልቄዶን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በመልካም አርአያነት ሊወሰድ ይገባልን?

(አንድ አድርገን ፤ ጥር 10 2005 ዓ.ም)፡- ቤተክርስቲያን እስከ 451 ዓ.ም ማለትም እስከ ጉባኤ ኬልቄዶን ድረስ በመላው ዓለም  ባሉ ክርስቲያኖች ዘንድ አንድ ዶግማና አንድ ቀኖና ነበራት፡፡ ይህ ጉባኤ ግን ቤተክርስቲያንን ከሁለተ ከፈላት፡፡ ነባሩን ሐዋርያዊ አስተምህሮ የያዙት ተዋህዶዎች  የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት(Oriental Churches) በመባል የሚጠሩት  ኢትዮጵያ ፤ ግብጽ ፤ አርመን ፤ ሶርያና ሕንድ  የያዙት መለካውያን በመባል የሚታወቁት ደግሞ የምዕራብ አብያተክርስቲያናቱ (Occidental Churches) ላቲኖችና ግሪኮች ናቸው፡፡ በእነኚህ ሁለት ክፍሎች ጉባኤው ቤተክርስቲያንን ለሁለት ከፈለ፡፡  አስቀድሞ በ325 ዓ.ም በኒቂያ  ፤ በ381 ዓ.ም  በቁስጥንጥኒያ ፤ በ431 ዓ.ም በኤፌሶን የተደረጉት ጉባኤዎች (ሲኖዶስ) ቤተክርስቲያን የገጠማትን ፈተና በመጋፈጥና በአንድ ድምጽ በመወሰን  የተዋጣላቸው ነበሩ፡፡  ጉባኤዎቹ የሚጠሩበት  ምክንያትም ሐዋርያዊ ያልሆነ አዲስ የክህደት ትምህርት ተከሰተ ሲባል ነበር፡፡

Monday, January 21, 2013

የብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ መልዕክት

በብፁዕ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው በውጪ የሚገኙት አባቶች በኢትዮጵያ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን መግለጫን ተከትሎ በውጪ የሚገኙት አባቶች መግለጫ አውጥተዋል። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን እና ምዕመናን ግራ የተጋቡበት ዘመን እንደመሆኑ መጠን ምዕመናን የሚቻላቻችውን የቀደመችውን ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችንን ይዘን ይሄ የአድርባዮች ጊዜ እስከሚያልፍ እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያንን ወደ ቀደመ ክብሯ እስኪመልስ እና ጥቅመኞች፣ እከብር ባዮች፣ ግብረ በላዎችን ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ከቤቱ ጠራርጎ በማስወጣት ቤተክርስቲያንን ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኙበት ቦታ እስኪያደርጋት ድረስ እንድንጸና መልካሙን እንዲያመጣልን በያለንበት እየጸለይን ፈጣሪያችንን ፊቱን ወደ እዚህች ቤተክርስቲያን እና ምዕመኗ እስኪመልስ ድረስ እንድንጸና አደራ እንላለን።
በውጪ የሚገኙት አባቶች ያወጡትን ሙሉውን ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Thursday, January 17, 2013

የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የተቃወሙት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ


  • ‹‹ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም››Ab Hizkiel
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለዐቃቤ መንበሩ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑትና ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያቀረቡት ከጥር 6 – 8 ቀን የቆየው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንደተጠናቀቀ መኾኑ ተገልጧል፡፡
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከሐላፊነታቸው እንዲለቁ ለውሳኔ ያበቋቸው ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች እንዳሉ የዜናው ምንጮች አስረድተዋል፡፡ የመጀመሪያው÷ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዐራተኛው ፓትርያሪክ ላይ ስላለው አቋም፣ ዕርቀ ሰላሙንና የፓትርያሪክ ምርጫውን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት ያሳለፈው ባለሦሰት ነጥብ ውሳኔና ውሳኔውን ተከትሎ ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠበት መንገድ ነው፡፡

Wednesday, January 16, 2013

ከዕርቀ ሰላም ይልቅ ለ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ቅድሚያ የሰጠው የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ተስፋዎችን አጨላሚ ሆነ


(ደጀ ሰላም፤ ጥር 8/2005፤ ጃኑዋሪ 16/2013/ PDF) በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና ከመነሻውም በውጪ ተጽዕኖ ሥር የወደቀው የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተፈራውም ዕርቀ ሰላሙን አሽቀንጥሮ ወርውሮ 6ኛ ፓትርያርክ በመፈረሙ ላይ ጸንቷል። በብፁዕ አቡነ አብርሃም በተነበበው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው ቅ/ሲኖዶሱ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካው በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ባቀረቧቸውና ከዕርቁ ጋር በማይገናኙ ሌሎች ምክንያቶች የተነሣ ነው። ይህ “ከእርቁ ጋር የማይገናኝ” የተባለው ምክንያት አሜሪካ ያሉ አባቶች የሚያነሧቸው “ፖለቲካዊ ጥያቄዎች” መሆናቸውን ደጀ ሰላም ትረዳለች። በተለይም ለብዙዎቹ የቅ/ሲኖዶስ አባላት የተነገራቸው ምክንያት “አገር አቀፍ ዕርቅ” ይውረድ ይላሉ፤ ውጪ አገር አሉት ፖለቲከኞችም አብረውን ካልገቡ ይላሉ የሚለው መልዕክት ነው።

ቅ/ሲኖዶስ ስለ ዐራተኛው ፓትርያሪክ፣ ዕርቀ ሰላምና ስለ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች


1.  ሥልጣነ ፕትርክና ሲፈልጉ ተረከቡኝ፣ ሲፈልጉ መልሱኝ እየተባለ የሚከራከሩበት ሥልጣን ባለመኾኑ ዐራተኛውን ፓትርያሪክ ወደ መንበረ መመለስ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውስጥ ሥርዐተ አልበኝነት እንዲሰፍን መፍቀድ ነው፡፡ ከዚህም ጋራ አምስተኛው ፓትርያሪክ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው የተሠራው የኻያ ዓመታት ሥራ ደምስሶና ሠርዞ ወደኋላ በመመለስ ዐራተኛው ፓትርያሪክ ብሎ መቀበል ፍጹም የማይቻል በመኾኑ፣ የቀድሞው ዐራተኛ ፓትርያሪክ በፓትርያሪክነት የሥልጣን ደረጃ እንደማይቀበል ቅዱስ ሲኖዶስ በማያሻማ ኹኔታ በድጋሚ ወስኖአል፡፡

2.  ቤተ ክርስቲያን በአሁን ጊዜ ከዚህ በላይ ያለመሪ ለብዙ ጊዜ እንድትቆይ ማድረግ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥራዋ እንዲስተጓጎል፣ መልካም አስተዳደሯም እንዲዳከም የሚያደርግ ስለኾነ ቀደም ሲል በተወሰነው መሠረት የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ቤተ ክርስቲያንነና ቀኖናው ተጠብቆ የምርጫው ሂደት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡ 

3. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም የሰላምና የአንድነት መሪ እንደመኾኗ    መጠን የተጠቀሱት አባቶች የተሰጠውን የሰላም ዕድል ተጠቅመው ወደ ሰላሙና አንድነቱ ለመምጣት ፈቃደኞች ኾነው እስከተገኙ ድረስ ኹኔታዎች ሲመቻቹ ቀደም ሲል የተጀመረውን የሰላምና ዕርቅ ሂደት እስከመጨረሻው ድረስ ለማስቀጠል አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁ መኾኗን ቅዱስ ሲኖዶስ በማረጋገጥ ጉባኤውን አጠናቋል፡፡

    የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ እዚህ ይመልከቱ

    የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

    Tuesday, January 15, 2013

    ሰበር ዜና – በውጭ ለሚገኙት ብፁዓን አባቶች ጥሪ ተደርጎ ምርጫው እንዲካሄድ ተወሰነ

    አርእስተ ጉዳይ፡-
    His Grace Abune Natnael
    ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
    • የዕርቀ ሰላሙ ሂደት ከፓትርያሪክ ምርጫው ጎን ለጎን ይቀጥል ተብሏል
    • በውሳኔው ያልተስማሙት የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ስብሰባውን ጥለው ወጡ!
    • የዐቃቤ መንበሩ አቋም በዕርቀ ሰላም እና ምርጫ መካከል ሲዋዥቅ ውሏል
    • ዐቃቤ መንበሩ ለምርጫው በቶሎ መፈጸም የፌዴራል ጉዳዮች ሚ/ርን እገዛ ጠይቀዋል
    • መንግሥት አስቸኳይ ስብሰባው በቶሎ እንዲፈጸም ይሻል
    • የምልአተ ጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ ነገ ያበቃል፤ ጋዜጣዊ መግለጫም ይሰጣል
    በከፍተኛ ጥበቃ ሥር የተከናወነው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ በውጥረት ተጀምሮ በውጥረት ለመጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ በስብሰባው ዋዜማ ባስነበብነው ዘገባ እንደተመለከተው÷ የፓትርያሪክ ምርጫው እና ዕርቀ ሰላሙ በተጓዳኝ እንዲካሄድ፣ ለምርጫው በሚደረግ ዝግጅትም በውጭ ለሚገኙት ብፁዓን አባቶች በሙሉ ጥሪ እንዲደረግላቸው ከፍተኛ ውዝግብ ከታየበት የምልአተ ጉባኤው ውሎ በኋላ ውሳኔ ላይ የተደረሰ መስሏል፡፡

    የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ በከፍተኛ ጥበቃ ውስጥ ተጀምሯል

  1. ‹‹ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ›› የሚሉ አባቶች በአቋም ተጠናክረዋል፤ በቁጥር ጨምረዋል
  2. የዕርቀ ሰላም ንግግሩ ፍጻሜ ሳይታወቅ አንዳችም ተግባር መከናወን እንደማይገባው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ተሳታፊዎች አሳሰቡ፡፡ ከቀን ወደ ቀን በአቋም እየተጠናከሩና በቁጥርም እየጨመሩ የመጡት እሊህ ብፁዓን አባቶች፣ የዕርቀ ሰላሙ ፍጻሜ ምንም ይኹን ምን ለሰላም ጉባኤው ቅድሚያ ሰጥቶ ውጤቱን መጠበቅ እንደሚገባና ለውጤቱም መሥራት እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተው መናገራቸው ታውቋል፡፡
    የምርጫ አጀንዳውን በተመለከተ÷ ቤተ ክርስቲያናችን ባለፉት ፓትርያሪክ ዘመን ለኻያ ዓመታት ተቸግራ መኖሯን ያስታወሱት የምልአተ ጉባኤው አባላት÷ ‹‹ሌላ ኻያ ዓመት መቍሰል አይገባንም፤ ወደ ምርጫው የምንገባው በአንድነትና በተረጋጋ መንፈስ ለቤተ ክርስቲያን እረኛ የሚኾነውን አባት ለመምረጥ መኾን ይገባዋል›› ማለታቸውን ከዕለቱ የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ውሎ ለመረዳት ተችሏል፡፡

    Monday, January 14, 2013

    ሰበር ዜና – ዐቃቤ መንበሩ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸው ተሰማ

    • ዕርቀ ሰላሙንና የፓትርያሪክ ምርጫውን በተጓዳኝ እንዲካሄድ ለማስወሰን ታስቧል
    • ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉት አባቶች አቋምና ብዛት እየተጠናከረና እየጨመረ ነው
    • የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶሱ ደብዳቤ ጽፏል
    • ከ4ው ፓትርያሪክ ጋራ ፊት ለፊት መወያየት ቀጣይ የመነጋገሪያ ነጥብ ነው ተብሏል
    ቅ/ሲኖዶስ በነገው ዕለት አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ለመቀመጥ በሚዘጋጅበት ዋዜማ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ መጠየቃቸው ተሰማ፡፡ ዐቃቤ መንበሩ ጥያቄውን ያቀረቡት ለመንግሥት አካል በጻፉት ደብዳቤ ነው ተብሏል፡፡ ደብዳቤው የተጻፈው ሁለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት (አቶ ኣባይ ፀሃዬ እና ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም) በሳምንቱ መጨረሻ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ቢሮ ተገኝተው ከተወያዩ በኋላ መኾኑ ተገልጧል፡፡

    Saturday, January 12, 2013

    የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራ እንዲጀምር የታዘዘበትን ደብዳቤ ሊሽረው ይችላል


    • ከውጭ አህጉረ ስብከት ብፁዓን አባቶች ከግማሽ ያላነሱ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል
    • የሰላምና አንድነት ጉባኤውን በተጨማሪ ሽማግሌዎች የማጠናከር አማራጭ ተይዟል
    በመጪው ሳምንት ሰኞ፣ ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም፣ ለዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ሪፖርትና ተጓዳኝ ሐሳቦች ቅድሚያ በመስጠት የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብስባ÷ በአወዛጋቢ ውሳኔ የተቋቋመው የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ሥራውን እንዲጀምር የታዘዘበትን የማሳሰቢያ ደብዳቤ ሊሽረው እንደሚችል ተጠቆመ፡፡
    የማሳሰቢያ ደብዳቤው የተጻፈው በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊልጶስ ነው፤ በይዘቱም እስከ ጥር 30 ቀን ድረስ ከአምስት ያላነሱ ከሦስት ያልበለጡ የፓትርያሪክ ዕጩዎችን እንዲያቀርቡ የተሠየሙት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተገኝተው ሥራ እንዲጀምሩ የሚያሳስብ ነው፡፡
    የመንበረ ፓትርያሪኩን አስፈጻሚ አካል ብቻ የመምራት ሓላፊነት ያለባቸው የጠ/ቤ/ክህነቱ ዋ/ሥ/አስኪያጅ÷ ይህን ዐይነቱን ማሳሰቢያ መስጠት ‹‹የማይመለከታቸውና ያለሥልጣናቸው የገቡበት ነው›› ብለዋል ኮሚቴው በቅ/ሲኖዶሱ የተሠየመበት የቀደመው ደብዳቤ ተፈርሞ የወጣው በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ፊርማ እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች፡፡Abune Filpos
                                                                       አቡነ ፊልጶስ

    Friday, January 4, 2013

    ‘ እዚህ የተገኘነው ላንተ ክብር ነው!’ እነ ‘ ሊቀ ትጉሃን’ መኩሪያ ጉግሳ



    ዳንኪራው በከበሮ ሲቀልጥ እንዴት ያሳዝናል
    ይህ አነጋገር ሲሰማ በአንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነኝ በሚል ሰው የተነገረ በመሆኑ ክብር ለሚገባው ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ አልያም ቅዱስ ጳውሎስ “ክብር ለሚገባቸው ክብርን ስጡ” ብሎ ለመሰከረላቸው ለቅዱሳን የተነገረ እንዳይመስለን። ይልቁንም በአንድ አሜሪካን ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ በመገኘት የጫጉላ ሽርሽር በማድረግ ላይ ለሚገኘው ለድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ለተሰኘው ዘፋኝ የተነገረ ነው።

    በእርግጥ በዘመናችን ላሉ አገልጋይ ነን ባዮች ብዙ ነገር ግራ የገባቸው ይመስለናል። ዓለማዊው ከመንፈሳዊው፣ ምድራዊው ከሰማያዊው፣ ሥጋዊው ከነፍሳዊው፣ ጊዜያዊው ከዘላለማዊው ነገር ጋር የተምታታባቸው ይመስለናል። ይህ ባይሆን ኖሮማ ‘ቴዲ ላንተ ክብር ነው እዚህ የተገኘነው’ በማለት በ’ሊቀ ትጉሃን’ መኩሪያ ጉግሳ ፕሮግራም መሪነት፣ በ’ቀሲስ’ ተስፋዬ መቆያ ባራኪነት፣ ‘በዘማሪ’ ቸርነት ሰናይ ዘማሪነት ለአንድ ዓለማዊ ዘፋኝ ያውም የዓለም ዳንኪራ ሲደለቅ በሚያመሽበት ሬስቶራንት ውስጥ በመገኘት እንዲህ አይነት ዝላይ እና ድሪያ ባልተደረገ ነበር።
    ለነገሩ ያልተማሩትን ያልዋሉበትን ወንጌል እናስተምራለን በማለት ከመናፍቃኑ ስብከት እየለቃቀሙና እየቃረሙ በሚያመጡት ‘ስብከት’ ፤ ‘ወንጌል ምዕመኑ አልገባውም’ በሚል ያልበሰለ ንግግር ታጅበው በመድረክ ላይ ከወጡ መምህራን እና ዘማሪያን ነን ባዮች ከዚህ ሌላ ምን ሊጠበቅ ኖሯል። ወንጌል የሚለው ትርጉም ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ እንኳን መልስ የሌላቸው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ልብ አማርኛ በማራባት እና በእንቶ ፈንቶ ልቡን ይዘው የተናገሯትን እንዱን እንኳን በተግባር ከማያውሉ ‘ወንበዴዎች’ ከዚህ ሌላ ምን ይጠበቃል።

    Thursday, January 3, 2013

    የሰላም ልኡኩ መ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ በቅ/ሲኖዶሱ ደብዳቤ ተሸኙ

    መ/ር ዓንዱአለም ዳግማዊ

    • ልኡኩ ዛሬ ምሽት ወደ አሜሪካ ያመራሉ
    • በዐቃቤ መንበሩ ተጠርተው ከገቡም በኋላ የጥበቃ ሓላፊው ለማስወጣት ሞክረዋል
    • በቅ/ሲኖዶሱ ፊት የተጠየቁት የጥበቃ ሓላፊ የእገዳው ምንጭ ማስረዳት አልቻሉም
    • የሰላም ልኡካኑ ለአዲሱ አደራዳሪ አካል ረዳት (facilitators) ኾነው ይሠራሉ ተብሏል
    • ‹‹ሰው በማያስፈራ ነገር ሲፈራ፣ በማያሰጋ ነገር ሲሰጋ በተለይ ከሃይማኖት አባቶች አልጠብቅም፡፡›› /የቪ.ኦ.ኤው ጋዜጠኛ የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ እንደታዘባቸው/
    በዳላስ ቴክሳስ የተካሄደው ሦስተኛ ዙር ጉባኤ አበው÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባላት ወደ ሁለቱም አካላት ምልአተ ጉባኤ ተልከው ለቀጣዩ የዕርቀ ሰላም ጉባኤ የማግባባት ሥራ እንዲሠሩ በደረሰበት ስምምነት መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ሁለት ልኡካን አንዱ መ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ÷ በዛሬው ዕለት ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ጋራ ከተወያዩ በኋላ ከጽ/ቤታቸው በወጣ ደብዳቤ ወደመጡበት ተሸኝተዋል፡፡

    አባቶች ሆይ አብነታችሁን አሳዩን



    መ/ር ጳውሎስ መልአከ ሥላሴ
    (/ ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ/ PDF):- በቀድሞ ዘመን ማዶ ለማዶ በመንደር ተለያይተው በቅርብ ርቀት ላይ  የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ እነዚህ ህዝቦች ታዲያ ባልታወቀ ምክንያት ቅሬታ ፈጥረው በሆነው ባልሆነው ምክንያት እስከ መካሰስ ደርሰው ነበር፡፡ ልዩነታቸውም እየሰፋ ሲመጣ አንዱ ለሌላው መጥፎ ስም መስጠት ጀመረ፡፡ ከአሉባልታዎቹም መካከል፡- የታችኛው መንደር የላይኛዎቹን፤እዚያ ማዶ ያሉት ቡዳ ናቸውሲሉ፡- በላይኛው መንደር ያሉትም በተራቸው፤ታች መንደር ያሉት ቡዳ ናቸው”  እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ይተማሙ ነበር፡፡ በሌላ መንደር የሚኖረው ሕዝብም ሁለቱን በቡዳነት ፈርጆ የሚቀርባቸው እስኪያጡ ድረስ ራሳቸው ባመጡት ጣጣ ገለልተኞች ሆነው ብዙ ዘመን ኖሩ፡፡


    ከቀኖች በአንደኛው ቀን ከታችኛው መንደር አንድ የመሸበት መንገደኛ ወላጆቹቡዳእንደሆኑ ከነገሩበት ላይኛው መንደር ደረሰ፤ እንዳይገባ ፈራ፤ አልፎ ከሄደ ደግሞ መሽቷልና የጅብ እራት ሊሆን ነው፡፡ ስለዚህም ጥቂት ካመነታ በኋላ፣ጅብ ከሚበላኝ ቡዳ ቢበላኝ አይሻልምን? ቡዳውንስ በጸበል እድናለሁ፤ ጅብ ከበላኝ መሞቴም አይደል? ደግሞስ ቡዳ ይሁኑ፣ አይሁኑ፣ ሰማሁ እንጂ የበሉት የለ? እንዲያውም በዚሁ አጋጣሚ ጉዱን ልወቅበማለት አማራጭ ያጣለትን ማደር እውነቱን ማረጋገጫ አድርጎ ሊጠቀምበት በማሰብ ፍርሃቱን አስወግዶ ወደ መንደሩ ገባ ይልና፤የእግዚአብሔር እንግዳ፣ የመሸበት መንገደኛ ነኝ፤ አሳድሩኝይላል፡፡ በተሰጣቸው መጥፎ ስም ምክንያት እንግዳ የናፈቁት የመንደሩ ሰዎች እጅግ ደስ ብሏቸው ልብን በሚነካ ሁኔታ ተቀብለው፣ እግሩን አጥበው፣ ጥሩ እራት አዘጋጅተው በክብር አስተናገዱት፡፡ በመስተንግዷቸው ውስጡ በጣም የተነካው እንግዳም ለጊዜውም ቢሆንቡዳ ናቸውየሚለውን ነገር ዘንግቶ ነበር፡፡

    Wednesday, January 2, 2013

    “ቤተ ክርስቲያንን ለፈተና አጋልጠን ወደ ገዳም አንገባም” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)

    • ከሰሜን አሜሪካ የተመለሱ የሰላም ልዑካን የጉዞ ሪፖርታቸውን ለሚ ሲኖዶስ ቅርበዋል።
    • የሰላም ልዑካኑ  ዕርቀ ሰላሙ መቀጠል እንዳለበት በአት አሳስበዋል፡፡
    (ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 24/2005 ዓ.ም፤ January 2/2013/ PDF)፦ ላለፉት ሦስት ዓመታት  ሁለቱን ሲኖዶስ ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል የነበረ አስታራቂ ጉባኤ ባወጣው መግለጫ መግለጫው ለሽምግልና ከተቋቋአካል አይጠበቅም በሚል  ተቃውቸውን የገለጡት ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጉባኤው ይቅርታ ካልጠቀ አብረውት ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
    ይህንንም አአስቀድመው ይፋ ያደረጉት ወደ ሰሜን አሜሪካ ተላኩት ልዑካን  ሲሆኑ በመግለጫቸው አስታራቂ ስሕተት ፈጽሟል፣ ይቅርታ ካልጠየ አብረነው አንሠራም ማለታቸው የዕርቁ ተስፋ ላይ ጥላ አጥልቶበት ሰንብቷል፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳቱ  መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አዲስ አበባ  ከገባን  በላ መግለጫ  እናወጣለን  አሁን ምን ያስቸኩለናል ማለታቸውም ተጠቁሟል፡፡