Monday, October 31, 2011

አባ ሰረቀ ተሰናበቱ፣ የሀይማኖታቸውም ጉዳይ እንዲመረመር ተወሰነ

(ሰበር ዜና) ቅ/ሲኖዶስ አባ ሰረቀን ከሥልጣናቸው አወረደ


Adios Abba Sereke!!!!!!!!!!!!!!
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 18/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 29/2011, እዚህ ይጫኑ)፦ አወዛጋቢው የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣
ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው።

አባ ሰረቀ ከሓላፊነታቸው እንዳይነሡ በጥብዓት ሲከራከሩላቸው የቆዩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይዘውት የነበረውን አቋም እንዲቀይሩ ወጣቱ በቅርቡ ያሳየውን ተቃውሞ የተረዳው መንግሥት ተጽዕኖ ሳያደርግ አልቀረም ተብሏል። መላው ኦርቶዶክሳዊ እና የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶው ቤተሰብ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እና ለቅ/ሲኖዶስ ያለውን አክብሮት በመግለጽ ላይ ይገኛል።

ሰበር ዜና

  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን በሰሜን አሜሪካ ያሏትን ሦስት አህጉረ ስብከት “ከመንበረ ፓትርያኩ ጋራ ለማገናኘት” በሚል ተጠሪነቱ ለመንበረ ፓትርያኩ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሆኖ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና የተቋቋመው “የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት” አገልግሎቱና ጥቅሙ በሚገባ ተመርምሮ በሦስቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሥር እንደ አንድ የመረጃ ክፍል ሆኖ እንዲዋቀር፣ ይህ ካልሆነ ግን እንዲዘጋ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡
  • በአጀንዳ ተ.ቁ ስምንት እንደተመለከተው ምልአተ ጉባኤው “ዝውውር የጠየቁ ሊቃነ ጳጳሳት” በሚል አጀንዳ ሥር በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የካሊፎርኒያ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አዎስጣቴዎስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያኩ የላኳቸውን የቅሬታ ማመልከቻዎች በንባብ ካዳመጠ በኋላ ተወያይቶበታል፤ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያኩ ሁለቱም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከቦታቸው እንዲነሡ ምልአተ ጉባኤውን ጠይቀው ነበር፤ ምልአተ ጉባኤውም፣ “ሁለቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና በሚመሰክር መልኩ ጉዳያቸውን በአካል መጥተው ማስረዳት ሲገባቸው አለመምጣቸው ተገቢ አይደለም፤ በመሆኑም በቀጣይ በአካል ቀርበው ጉዳያቸውን እንዲያስረዱ” ሲል ትእዛዝ መስጠቱ ተዘግቧል፡፡
  • ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስ “የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት” በሚል በራሳቸው ትእዛዝ እንዲዘጋጅ ያደረጉት ሪፖርት ዛሬ ከቀትር በፊት በተካሄደው የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ መደናገርን ፈጥሯል፤ አጀንዳው በስብሰባው የተባበረ ድምፅ በደረሰበት ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አጀንዳው በራሱ ውድቅ ተደርጓል - “ይህ የሁላችሁ ሐሳብ ከሆነ ከእናንተ ቃል ውጭ አልሆንም፤ እንለፈው፤” (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ)

Saturday, October 29, 2011

ለተዋሕዶ ልጆች በሙሉ

         በስመ አብ ወወልድ ወመነፈስ ቅዱስ አሐዱአምላክ አሜን
የተከበራችሁየተዋህዶ ልጆች
በቅድሚያ  እግዚአብሄር አምላክ ቤተክርስቲያናችንንና ይጠብቅልን  የሁላችንም  አንድነት ያጽናልን ስንል የዘወትር ጸሎታችን ነው። መቀጠልም በመቀጠልም በመዝገበ ገጽ(facebook) አጠቃቀም ዙሪያ ጠቃሚ የምንላቸውን አስተያየቶች ልናካፍል እንወዳለን።

Friday, October 28, 2011

  • ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን ያለ መሰብሰቢያ የጊዜ ሠሌዳ ስብሰባ ጠርተዋል
  • አቡነ ገብርኤል አቡነ ጋዳፊ ተብለው ተጠርተዋል … በአቡነ ፋኑኤል ላይ ስልታዊ መፈንቅለ መንበረ  ጵጵስና ወይም ኩዴታ አደርገዋልም ተብለዋል፣
  • ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም የተሳሳተ ሪፖርት አቅርበዋል ተብለዋል፣
  • ‹‹የራሳችን አዲስ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ለማሠራት ይፈቀድልን››…. ከላይ የተዘረዘረው ስድብና ጽርፈት በቡድኑ የተሰነዘረ ነው፡፡

አጥብቀን ልንታገለው የሚገባን እውነታ!

  • ስደተኛው ሲኖዶስ ብለው ሲነሱ፣ ተው አይሆንም ሲኖዶስ አይሰደድም ስንል፥ ዛሬ ደግሞ በአንድ መንበር ሥር በሚያገለግሉ ነገር ግን ግብራቸውን የለዩ ለከርሳቸው ያደሩ ከሃዲያን ተነስተውብናል

“በቀልን ለተጠማ አባት ራሴን አሳልፌ አልሰጥም” - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

  • ሊቃነ ጳጳሳቱ ፓትርያሪኩን በጣልቃ ገብነት ወቀሱ
  • ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት በፓስፖርት እና በመኖሪያ ፈቃድ እድሳት እጦት እየተንገላቱ ነው
  • በ’ተሐድሶ’ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ ተባብሶ ቀጥሏል
  • የማያቋርጥ አቤቱታ መብዛት ጠቅላይ ቤተ ክህነታችን የመዋቅርና የሥራ ሂደት መሻሻል እንደሚያስፈልገው አመላካች ነው” - የጠ/ቤ/ክ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥናት

መልዕክት

በመላው ዓለም ለምትገኙ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ብሎግ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳስተማረችን የአበው ድምጾች ይስተናገዱበታል፣ በወቅቱ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች መጣጥፎች ከተለያይ አንባቢያን እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይቀርብበታል፡፡ አስተያተት ቢኖራችሁ ወይም ጥያቄዎች ቢኖራችሁ አሳውቁን እንስተናግደዋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ለበጎቹ መልካም እረኛን ያምጣልን
ቤተ ክርስቲያንንም ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅልን።

kurtegnalejoch@gmail.com ላሉልን ይደርሰናል

የበግ ለምድ ለብሰው ከምመጡብን እንጠንቀቅ

" የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።" ማቴ. ፯ ፥ ፲፭

"ድሮ ድሮ ነጣቂ አውሬ ሲመጣ ሳር ቅጠሉ ሁሉ ይናገር ነበር"  ይላሉ አንድ አረጋዊ አባት በሀዘኔታ በዚህ በእኛ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ፣ በደል፣ እንዲሁም ስደት እያሰቡት። አዎ ዛሬ ትላንት አይደለም፣ ትላንትም ለዛሬ ሰጥቶ ለተረኛው ሄዷል የተራውን ማስተናገድ ያለበት ተረኛው ዛሬ ነው ነገር ግን ዛሬ ዛሬነቱን ሊለውጥ ሊክደው አይችልም የመጣውን ጽዋ በትዕግስት መጎንጨት ወይም ደግሞ ጥንት የነበሩ አበው "የአንገቴን መሀተብማ አትበጥስም፣ ከነ አንገቴ ትወስዳታለህ እንጂ" ብለው ሰማዕትነትን እንደተቀበሉት።