Saturday, October 29, 2011

ለተዋሕዶ ልጆች በሙሉ

         በስመ አብ ወወልድ ወመነፈስ ቅዱስ አሐዱአምላክ አሜን
የተከበራችሁየተዋህዶ ልጆች
በቅድሚያ  እግዚአብሄር አምላክ ቤተክርስቲያናችንንና ይጠብቅልን  የሁላችንም  አንድነት ያጽናልን ስንል የዘወትር ጸሎታችን ነው። መቀጠልም በመቀጠልም በመዝገበ ገጽ(facebook) አጠቃቀም ዙሪያ ጠቃሚ የምንላቸውን አስተያየቶች ልናካፍል እንወዳለን።

፩፡ አንዳንዶቻችን በማህደራችን ላይ (profile) ሃይማኖት (religion) በሚለው ቦታ ላይ  የተለያዮ ገለጻዎችን አስገብተናል።ለምሳሌ  በእግዚዕብሔር አምናለሁ(believe in God) ፥ ፍቅር(love)፥ መልካም ማድረግ(doing God ), ግሪክ ኦርቶዶክስ(greek orthodox) እና ሌሎች። አንዳንዶቻችን ሌሎችን ላለማከፋት ስንል ፥ግማሻችን  ዘመናዊ የሆን እየመሰለን፥  ሌሎቻችን በማፈር ወይንም  በራስ የመተማመን ጉድለት፥ ጥቂቶች ደግሞ ባለማወቅ ሊሆን ይችላል። የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብሎ መፃፍ ይገባል እንላለን። ይህ በማድረግ  ስለሃይማኖታችን  እንመሰክራለን “በሰው ፊት የሚመሰክርልኝን እኔ ደግሞ በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ እንዲል። ማፈርም የለብንም ሌሎች የሚያሳፍር ነገር እንኳን ሲገልፁ  እኛ በሚያኮራ ነገር ለምን እናፍራለን “በወንጌል አላፍርም” ይላል ቅዱስ ጳውሎስ። በተቸማሪም ቤተክርስቲያንም ሆነ ሀገራችንን እናስተዋውቅበታለን።
፪፡ ብዙዋቻችን እምነታችንን ለማስፋፋት ብዙ አስተማሪ የሆኑ ጥቅሶችንና አባባሎችን፥ ታሪካዊቦታዎችንና  እንዲሁም ቅዱሳት ሥዕላትን እናደርጋለን። በበጣም ደስ የሚልና  የሚያበረታታ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ጥንቃቄዎችና  መሻሻሎች ቢደረጉበት መልካም  ነው እንላለን። ለምሳሌ ቅዱሳት ሥዕላትን፣ታሪካዊ ገዳማትን ጥቅሶችን እና የራሳችን የግል ፎቶዎች ለየብቻቸው ማህደር (album or folder) አዘጋጅተን ብናስቀምጣቸው አንደኛ መልእክቱ በቀላሉ ለሚመለከተው ሰው ይደርሳል እንዲሁም በፍለጋም አይደክምም ሚፈልገውን መርጦ ያያል። ሁለተኛ  የግላችን ፎቶን ቅዱሳት ሥዕላት ደበላልቆ ማስቀመጥ አግባብ አደለም ክብርን ይቀንሳል። ስለዚህ ለየብቻ ማድረጉ መለካም ነው እንላለን።\
፫፡ የምናስቀምጣቸው ጥቅሶችና አባባሎች ላይ ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል አንዳንድ መናፍቃን ራሳቸው አድርገው ኦርቶዶክሶች  እንዲህ ይላሉ ብለው ለማወናበድ ይሞክራክራሉና  ። አንድ ወቅት  ወንድሞች “አለም በእመቤታችን በኩል ብቻ  ይድናል” የሚል ጥቅስ አይተው ሲከራከሩ ሰማን።  ይህ አባባል በየዋህነት ተጽፎ ሊሆን ይችላል ;ወይንም ሆን ተብሎ  ይሆናል። በቀጥታ ሲነበብ ግን ከተዋህዶ ትምህርት ትንሽ የሳተ ነው።  ‘ምክንያተ ድኂን’ የሚለውን የአባቶቻን ትምህርት አይወክልም ከክርስቶስ ነገረ ድኅነት ጋር ይጋጫል። እንደ ተዋህዶ የክርስቶስን የማዳን ምሥጢር በጥልቀትና በስፋት የሚያምን ሆነ የሚመሰክር እምነት በአለም አይገኝም። አንዳንዶች ለጥፋታቸው መንገድ ይጠቀማሉና እንጠንቀቅ።
፬፡ ብዙ ወገኖቻችን ለቤተክርስቲያን መልካም ለማድረግ ሲተጉ እናያለን። ከጥቂቶች በስተቀር ብዙዎቻችን ሃሳባችን በመግለጽ አንደግፋቸውም። በመዝገበ ገጽ (facebook) ላይ የሚያወጡትን መልካም ነገር በመደገፍ ልናበረታቸው ይገባል እንላለን። የጓደኛ ፎቶ  እያየን (nice pic, I like ur pic , gorgeous,) ብቻ እያሉ  መወዳደስ ብቻ በቂ አይመስለንም። የድርሻችን በማድረግ ልንደጋገፍና  አንድነታችን ልንገልጽ ይገባል።  በሰለጠነው አለም በዚህ መገናኛ ስንት ታላላቅ ነገሮች እየተሰሩበት ነው ያለው ብዙ ለውጦች አምጥቷል (  የአረብ አብዮትም ትልቅ ምሳሌ ነው) ።  እኛጋ  ግን  ከመወዳደስና ከመሰዳደብ ያለፈ ቁምነገር እስከ አሁን አልታየም። አምላክ የቁም ነገር ልብ ይስጠን።
 እና  ሌሎችም
እናንተስ ምን ትላላችሁ  ??????????????????????????????????
እግዚአብሔር ሁላችንም ይባርክ                                                                                      
    ተዋህዶን ያስፋ                                                                                               
  ሀገራችንን ይጠብቅ                                                                                                    
 የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን    አሜን !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!  


No comments:

Post a Comment