- ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን ያለ መሰብሰቢያ የጊዜ ሠሌዳ ስብሰባ ጠርተዋል
- አቡነ ገብርኤል አቡነ ጋዳፊ ተብለው ተጠርተዋል … በአቡነ ፋኑኤል ላይ ስልታዊ መፈንቅለ መንበረ ጵጵስና ወይም ኩዴታ አደርገዋልም ተብለዋል፣
- ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም የተሳሳተ ሪፖርት አቅርበዋል ተብለዋል፣
- ‹‹የራሳችን አዲስ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ለማሠራት ይፈቀድልን››…. ከላይ የተዘረዘረው ስድብና ጽርፈት በቡድኑ የተሰነዘረ ነው፡፡
ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም ‹‹ትዕይንተ ሕዝብ›› ለማድረግ ያወጣው እቅድ በሰ/ት/ቤቶች ሕብረት የከሸፈበት የተሐድሶ ቡድን ከሀዋሳ ያደራጃቸውን ገንጣዮች በልዩ አገልጋዩ ፓትርያርክ ጳውሎስ አቀናጂነት አቤቱታ አሰምቷል፡፡
ቅዳሜ አመሻሹ ላይ በቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በነበረው ሥነ ሥርዓት የነበጋሻው ቡድን ድምጹ እንዲሰማ ብዙ ቢጥሩም ያልተሳካላቸው አቡነ ጳውሎስ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን ያለ ስብሰባ ጊዜ ሰሌዳ እና ምክንያቱን ሳይገልጹ ትላንት ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ ወደ ስብሰባ አዳራሽ በመጥራት አቤቱታ እንዲሰሙ አድርገዋል፡፡
በማጭበርበር እና እያንዳንዳቸው ደጋግመው በመፈራም ለረጅም ጊዜ የተዘጋጁበትን ሰነድ ‹‹አስር ሺህ ምእመን ወክሎን ነው የመጣነው›› ያሉት ግለሰቦች አባቶችን እና ማኅበረ ቅዱሳንን የሚሳደብ ዶሴ እንብበዋል፡፡
የስድቡ አቅጣጫ በተለየ መልኩ ወደ አቡነ ገብርኤል እና ማኅበረ ቅዱሳን ያዘነበለ ቢሆንም ሌሎች አባቶችም እጣው ደርሷቸዋል፡፡
‹‹ አቡነ ገብርኤል አንባገነን በመሆናቸው የሀዋሳ ሕዝብ አቡነ ጋዳፊ ብሏቸዋል፡፡በአቡነ ፋኑኤል ላይ ስልታዊ መፈንቅለ መንበረ ጵጵስና ወይም ኩዴታ አደርገዋል፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባል በመሆናቸው የእርሱ ጉዳይ አስፈጻሚ ናቸው፣ በየመጽሔቱ ስማችንን አጥፍተዋል›› ወዘተ የሚሉ ስድቦችን ተሳድበዋል፡፡
ተሳዳቢዎቹ በአቡነ ገብርኤል ብቻ ሳይወሰኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ያዘነውን የሀዋሳ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያጽናኑ ግንቦት 19 እና 20 ቀን 2003 ዓ.ም የላካቸውን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስን፣ የሰላሌ እና የአዲስ አበባ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ የሰቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስን እና የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አባ ኃ/ማርያምን ሀሰት እና የተሳሳተ ሪፖርት አቅርበዋል በማለት በቋሚ ሲኖዶስ ፊት ዋሽተዋል፡፡
ከሁሉ በላይ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ የቡድኑ ድምዳሜ ነው፡፡ቡድኑ በማጠቃለያው አቡነ ገብርኤል እና በሀዋሳ የተመደቡ አዳዲስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንዲነሱ እና ‹‹ለእነርሱ የሚመቹ ሰዎች›› እንዲተኩላቸው አሳስበዋል፡፡ይሄ የማይሆን ከሆነ ግን ‹‹በመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ወይም በጠቅላይ ቤተክህነት ሞግዚትነት እያተስተዳደረ የምናመልክበት የራሳችን አዲስ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ለማሠራት እንዲፈቀድልን እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡
ሒደቱን የተከታተሉ ታዛቢዎች ድራማው የተሐድሶ የመጨረሻው ማረፊያ ወደብ ቤተክርስቲያንን መክፈል መሆኑን ከማመልከቱም በላይ አካሄዱ አቡነ ጳውሎስ በውጭ አገር ቤተክርስቲያኒቱ የማታውቀውን መዋቅር ከመዘርጋታቸው ጋር የሚዛመድ ነው ብለዋል፡፡አቡነ ጳውሎስ ሦስት አህጉረ ስብከት ባለበት አሜሪካ ቅዱስ ሲኖዶስ የማያውቀው የውጭ ግንኙነት ጽ/ቤት ከፈቱ፡፡ የሀዋሳዎቹ ደቀመዛሙርቶቻቸው ደግሞ በቃለ ዐዋዲው የሌለ ‹‹በመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ወይም በጠቅላይ ቤተክህነት ሞግዚትነት እየስተስተዳደረ የምናመልክበት የራሳችን አዲስ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ለማሠራት ይፈቀድልን›› ሲሉ ጠየቁ፡፡
የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት በቀረበው መረጃ መሠራት ቅዱስ ሲኖዶስ በተሐድሶ ላይ ተወያይቶ የማያዳግም እርምጃ እንዳይወስድ የተሸረበ አጀንዳ ማስቀየሻ ስልት ነው፡፡ ከትናት ጀምሮ እነበጋሻው እና እጂጋየሁ ተሃድሶ አጀንዳ እንዳይሆን በአንዳንድ ጳጳሳት ቤት ሽማግሌ እየላኩ እንደነበር ላማዎቅ ችለናል
gebrher@gmail.comከተለያዩ ድረ ገጽ የተገኙ መረጃዎች
No comments:
Post a Comment