Sunday, September 30, 2012

እንዲህም አለ ለካ?ስሙ ቀሲስ ቸርነት ኅይለሥላሴ ይባላል በፍኖተ ጽድቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቨርጂኒያ በሚገኘው ቤተክርስቲያን አገልጋይ ነኝ ይላል የክህነት ሥነ ምግባር የሌለው፣ የክህነት ለዛ የሌለው፣ ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጋር ሊያገናኝ የሞከረ ተራ አሳሳች ካድሬ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው የአቶ መለሰ ዜናዊ ለቅሶ ላይ ተገኝቶ የበላበትን በደንብ የጮኽ የጌታው አገልጋይ ሰው ነው
አሳፋሪ እና የብዙ ኦርቶዶክሳዊያንን አንገት ያስደፋ ተራ ንግግር ስለሆነ ተናጋሪው ካህን ተብየው በመጪው ዘመኑ ንሰሐ ገብቶ ከዓለም መድኅኒት ስርየት እንዲሰጠው ቢለምን ይሻለዋል
ልቦናውን ይስጠው

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Thursday, September 20, 2012

ቀጣዩን ፓትርያርክ በተመለከተ …ትጉህ እና ቅን ለበጎቹ አሳቢ መሪ ይስጠን
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 9/2004 .ም፤ ሰምቴፕር 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)- ከአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማለፍ በኋላ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቀመጥ የሚገባውን ቀጣይ አባት ከመሾም አስቀድሞ የአራተኛውን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ዕጣ ፈንታ መወሰን፣ ከዚህም ጋራ የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት እንዲሁም የመዋቅር ማሻሻያ የሚመለከቱ ርምጃዎች መውሰድ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ኾኖ ወጥቷል፡፡ በአሜሪካው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ከተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሂደት በተጨማሪ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሥሓቅ የሚመራውና ከዐሥር ያላነሱ ልሂቃንን የያዘው የአገር ሽማግሌዎች ቡድን ሰሞኑን ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ጋራ በመወያየት በቅርቡ ቡድኑ በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ የሚነጋገርበት ኹኔታ እንዲመቻች መደረጉ ተዘግቧል፡፡


በሌላ በኩል የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባናል፤ የቅ/ሲኖዶስን የሰላምና የተቋማዊ ማሻሻያ ርምጃዎች በማገዝ ረገድ የበኩላችንንም ለማበርከት ተዘጋጅተናል የሚሉ የአገልጋዮችና ምእመናን ስብስቦችም ይበጃል በሚሏቸው ሐሳቦች ዙሪያ የሚመለከታቸውን አካላትና ሰፊውን ምእመን በተደራጀ መንገድ እያወያዩ ናቸው፤ ለውይይትና ግንዛቤ የሚረዱ ጽሑፎችም በተለያዩ መድረኮች እየቀረቡና እየተሠራጩ ይገኛሉ፡፡ ከእኒህም መካከል ውሉደ አበው ዘተዋሕዶ የተሰኘውና በዋናነት ለመረጃ፣ ለግንዛቤና ለውይይት የሚረዱ ጽሑፎችን መዘርጋት የጀመረው የአገልጋዮች መድረክ አንዱ ነው፡፡

መድረኩ ባዘጋጀውና ለደጀ ሰላም መድረስ በጀመረው በዛሬው ሁለተኛ ጽሑፉ ከቀጣዩ ፓትርያሪክ ምርጫ አስቀድሞ መከናወን በሚገባቸውና ‹‹መንገድ ጠራጊዎች ናቸው›› በሚላቸው መሠረታዊ ሥራዎች ላይ ሐሳቡን በዝርዝር አቅርቧል፤ እኒህ መሠረታዊ የቅድመ ሢመተ ፓትርያሪክ ተግባራት ለቤተ ክርስቲያናችን፣ ለአገራችንና ለዓለም ሁሉ ያላቸውን በረከት በማመላከትም ተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው ይከራከራል፡፡ ደጀ ሰላማውያን ሁሉ በመድረኩ የጽሑፍ አበርክቶዎች ላይ ሐሳባቸውን በማቅረብ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ በባለቤትነት ለመወያየት እንችል ዘንድ ደጀ ሰላም ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
 +++

Wednesday, September 19, 2012

የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ


የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆነች ትልቋ ተቋም ናት፡፡ በሕዝቡሃይማታኖዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ የማይተካና ወሳኝ የሆነ ሚናም አላት፡፡ ዕድገቷ ለሀገሪቱ ዕድገት፣ ሥልጣኔዋ ለሀገሪቱ ሥልጣኔ፣ አሠራርዋ ለሀገሪቱ አሠራር፣ የችግር አፈታቷም ለሀገሪቱ የችግር አፈታት ወሳኝ ነው::
በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች ለመፍታትና አንዲት፣ ጠንካራ፣ በአሠራርዋ ዘመናዊ፣ በእምነቷ ጥንታዊ፣ በሀገሪቱ ጉዞ ውስጥ ተደማጭና ወሳኝ የሆነ ሚና ያላት፣ ሌሎች ችግሮቻችንን በመፍታት ረገድ ሀገራዊ መንፈሳዊና ተልእኮዋን የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን በማድረጉ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ይመለከተናል፡፡
በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከገጠሟት ፈተናዎች አንዱ የመለያየት ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ ይህ ዕጣ በተለይም በሀገር ቤትና በውጭ በሚባል ሲኖዶስ፣ በማይግባቡና በማይቀራረቡ አባቶች እነርሱም በተከተሉት ሁለት ዓይነት የችግር አፈታት ምክንያት የተከሰተ ነው፡፡

Tuesday, September 18, 2012

‹‹… ሙሴ በድንጋይ ዘመን የገነነ አንድ እረኛ በመሆኑ ቢሳሳት አይገርምም…›› የበዕውቀቱ ስዩም የዕውርነት ፍሬ


                                                                                                                               ቀሲስ  ወንድምስሻ   አየለ
የበእውቀቱ ዘለፋ
በዕውቀቱ ስዩም ደፋርና የራሱን የስነጽሑፍ ዘይቤ ለመፍጠር የሚሞክር ገጣሚና ደራሲ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፤ ብዙ የሚባሉ የወረቀትና የኤሌክትሮኒክስ ኅትመቶችን አዘጋጅቶ ያበረከተ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ የጻፋቸውን ግጥሞች ዋጋ ለክቶ በብልጫው መርጬዋለሁ ያለው ዓለምአቀፍ ድርጅትም በኦሎምፒክ ዋዜማ እንግሊዝ ሀገር ለንደን ወስዶት ግጥሙን አቅርቦና ሌሎችም መርሐግብሮችን አሳትፎ በቴምዝ ወንዝ አካባቢም አዝናንቶትሸኝቶታል፡፡ የሀገራችን የስነጥበብ ባለሙያዎችም ሲሄድ ተሰብስበው ሸኝተውት፣ ሲመጣም ከአቀባበል ጋር ልምዱን ተካፍለውታል፡፡ እንዲህ ነው የሀገር ልጅነት፡፡
የዛሬው መጣጥፌ የወጣቱን ታሪክ ለመተረክ ሳይሆን ከሌሎች በተለየ ደጉን ኢትዮጵያዊነት ደጋግሞ ከመተቸቱ አልፎ በፈጣሪ የተመረጡ በምእመናን የተከበሩ ቅዱሳንን በመዝለፍ እየታወቀ ሲሄድ ዝምታው ተገቢ ስላልሆነ፣ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ላይ የከፈተውን አፍ ያዘጋውን ትችትና ምላሽ አላስተውል ብሎ ዛሬ ደግሞ ሊቀነቢያት ሙሴን መተቸት ውስጥ ስለገባ ለወደፊትም ትምህርት ቢሆነው፣ ሊከተሉት ለሚፈልጉ /እንዳሉ ስለማውቅ/ መንገዳቸውን እንዲያቀኑ ለመጠቆም፣ ምናልባት ከመከራ በፊት ከተመከረ ለራሱና ለሀገር የሚጠቅሙ መጣጥፎችን ያበረክት ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡

Monday, September 17, 2012

ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ንዋያተ ቅድሳት በመዝረፍ ላይ በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር


በቪሲዲ ከተደገፈ መረጃ ጋር
 ፕሮቴስታንት እምነቱ ይህ ነው ሥርዓቱም ይህ ነው ለማለት አይቻለም ይልቁንም በአብዛኛው የራሳቸው የሆነ ወጥ ሥርዓት የሌላቸው በመሆናቸው ማንነታቸውን በትርጉም በትክክል  ለመግለጥ ሁልጊዜ አስቸጋሪ ሆኖ ይኖራል፡፡ በአብዛኛውም ግሎባላይዜሽን ባመጣው አዳዲስ ኩነቶች እራሳቸውን  በማመሳሰልና ጊዜውን በመምሰል የሚያክላቸው እስካሁን አልተገኘም፡፡
ይሁን እንጂመቃወም” “ተቃውሞአዊጠባይ የሚያይልባቸው መሆኑን ከአንዳንድ መረጃዎች መረዳት ይቻላል በየጊዜውም የሚነሡት ሁሉ ከእነርሱ በፊት የነበረውን ትምህርት እየተቃወሙ በየጊዜው አዳዲስ ትምህርት እንዲያመጡና ክፍልፋያቸው (Denomination) እንዲበዛ አድርገዋል፡፡
 በዚህ ጊዜ ውስጥ መሠረታዊና እውነተኛ ትምህርተ ሀይማኖት እንዲኖራቸው ከምክንያቶቻችን ይልቅ በመገለጥ  ሃይማኖት አምነው ትምህረተ ሥላሴን እንዲቀበሉ ያደርጉ ሰዎችም እንደ ተነሱ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ በዓለም ላይ ከደረሱትም ጉዳት አንዱ የሰውን  ምግባር (moral) መለወጥና እንስሳዊና ሰይጣናዊ ማድረግ ነው፡፡

Sunday, September 16, 2012

ገለልተኞች ሆይ የት ናችሁ?


በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ዘመን ታሪክ ከተፈጠሩት ገጽታዎች አንዱ ‹‹የገለልተኛነት›› አቅጣጫ ነው፡፡ ገለልተኛነት በተግባር የታየው 1970ዎቹ አጋማሽ በአሜሪካን ሀገር ከቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው የቀሩትን ሁለት ጳጳሳት ተከትሎ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ጳጳሳት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ራሳቸውን በማግለል በቅዱስ ሲኖዶስ የማይመሩ አብያተ ክርስቲያናትን መመሥረት ጀመሩ፡፡
በወቅቱ ይህንን ተግባር የተቃወሙት በምዕራብ ንፍቀ ክበብ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ይስሐቅ ነበሩ፡፡ አቡነ ይስሐቅ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት አድርሰው እስከ ማስወሰን በመድረሳቸው ሁለቱ ጳጳሳት ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን›› የሚለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም በመተው ‹‹የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን›› በማለት እስከ ማቋቋም ተደርሶ ነበር፡፡ በርግጥ ታሪክ ራሱን ስለ ሚደግም አቡነ ይስሐቅም በተራቸው ሌሎችን ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት አቋቁመው ነበር፡፡