Tuesday, November 15, 2011

በአቡነ ፋኑኤል ሥርዓት አልበኝነት የተቃውሞ ሕዝባዊ ጥሪ ለመላው ዓለም


ለዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ!

አቡነ ፋኑኤል በገጠማቸው ቀውስ እንዳዘኑ!
 ከትላንት በስቲያ ሰኞ ከቀትር በፊት አቡነ ፋኑኤል በድብቅ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ገብተው ማደራቸው ተዘግቧል፥ በእለት በገቡበት ዕለት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ተገምቶ ስለነበር ቀድመው ለሰዎች ሐሙስ ብለው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ አስነግረው ነገር ግን እሳቸው ሰኞ ከእኩለ ቀን በፊት ማንም ሳይሰማ ወደ ከተማው ገብተው አድረዋል። በዚሁ እለት በቨርጂኒያው አየር ማረፊያ እንደደረሱ አጠገባቸው ሆነው እርሳቸውን እና አላማቸውን በመደገፍ የሚታወቁት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካሕናት እንዲሁም ከአካባቢው ካሕናት እነ ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ እና በቀሲስ ኢስሃቅ አማካኝነት ከአየር ማረፊያ ተቀብለዋቸው በቀጥታ በደቡብ ምዕራብ ዋሽንግተን  ወደሚገኘው የደብረ ምሕረት ገንዘብ ያዥ ወደ ሆነው ሰው መኖሪያው ቤት በቀጥታ አምርተው በዛው ቀናትን ለማሳለፍ ተገድደዋል። ባለፈው እንደዘገብነው በዚህ ጉዞዋቸው በጋሻውን ይዘው ለመምጣት ብዙ ጥረቶችን ለማድረግ ቢሞክሩም የተሳካላቸው አይመስልም፣ ነገር ግን እርሱን ለማምጣት የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉም ቅዱስ ፓትሪያሪኩም ቃል እንደገቡላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
አንድ የአካባቢው ክርስቲያን በዛሬው ዕለት በላከልን መልዕክት እንደሚያስረዳን በመጪው እሁድ የሚከበረውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ለማክበር የመጡት አቡነ ፋኑኤል ከባድ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ከወዲሁ በመረዳት የደብሩ የቦርዱ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ አድርገው የሚከተሉትን መመሪያዎች አስተላልፈዋል

፩ኛ/ በክብረ በዓሉ ቀን ማንም ሰው መኪናውን በጊቢው ውስጥ እንዳያቆም (ለጸጥታ ስለማይመች)
፪ኛ/ ከአካባቢው የፓሊስ ቢሮ ከሁለት እስከ አራት የፓሊስ ሰራዊት በቦታው ተገኝቶ ክብረ በዓሉን እንዳይታወክ እንዲቆጣጠሩ
፫ኛ/ አቡኑም ምንም አይነት ንግግር እንዳያደርጉ
፬ኛ/ ቢቻል በዑደቱም ላይ ባይኖሩ የሚሉትን መመሪያዎች አስተላልፏል።

ከዚህ የቦርዱ መመሪያ እንደምንረዳው በደብረ ምሕረት አካባቢ አቡኑ ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ አለመረጋጋት እና መሸበር እንዳለ ከአካባቢው መረጃውን ያደረሱን ክፍሎች ያስረዳሉ። በተያያዘ ዜና በዚሁ እሑድ በሚደረገው የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል ላይ ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ተቃውሞ እንደሚደረግ ከዚህ ጋር አያይዘው ገልጸውልናል፣ በመጪው እሑድ ከፍተኛ ትዕይንቱን በማዘጋጀት ላይ ያሉት ወገኖቻችን እንዳስረዱን ከሆነ አላማቸውን በግልጽ አስቀምጠው የአቡነ ፋኑኤልን አስተዳደርም ሆነ ውክልና አንቀበልም። ልክ እንደ ከዚህ በፊቱ በተለያዩ የሀገራችን የኢትዮጵያ ክፍሎች ተመድበው ሥራ ከመስራት ይልቅ መከፋፈልንን እና ሕዝብን በሕዝብ ላይ በማነሳሳት ሥራ ላይ ተሰማርተው አብሮ ለብዙ ዘመን የኖረውን ሕብረተሰብ ለያይተው ሲያበቁ እርሳቸውም ከሀገረ ስብከታቸው በሕዝቡ ብሶት እና በቅዱስ ገብረኤል ረዳትነት ከቦታቸው ተነስተዋል። እዛ በነበሩባቸው ጊዚያት አቡነ ፋኑኤል "እኔ አሜሪካው ነኝ ምንም ልታደርጉኝ አትችሉም" እያሉ በደሃው ሕዝብ ላይ ሲንቀባረሩ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፣ ሆኖም በአሁን ሰዓት ቤተ ክርስቲያንንም ወክለው ይሁን በገንዘብ ገዝተውት ወደ ዋሺንግተን አመጣታቸውንም ሆነ ውክልናቸውን እንደማይቀሉ አስታውቀው፣ ጥያቄያቸውንም በአቸኳይ የማይመልሱ ከሆነ ማንኛውንም እርምጃ ለማድረስ ማንኛውንም ዝግጅት አድርገው ለዚህም ደግሞ በማንኛውም መልኩ የገንዘብም ሆነ የሰው ሃይል በሚገባ ስላላቸው በሕግም ይሁን ከሕግ ውጪ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጅታቸውን እና ቁርጠኝነታቸውን አሳውቀውናል።

በቤተ ክርስቲያኑ አካባቢም ምዕመናኑ፣ አገልጋዮች ካሕናት እንዲሁም ዲያቆናት ለሁለት እነደተከፈሉ ይነገራል። በአገልጋይ ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በኩል ባለፈው እሑድ ተሰባስበው ግማሹ የሰንበት ት/ቤት ከአየር ማረፊያ ሄደን መቀበል እና ማጀብ ይኖርብናል ሲሉ እንዲሁ ግማሹ ደግሞ አይደለም አየር ማረፊያ ሄደን ልንቀበላቸው እዚህ መቀመጥ የለባቸውም፣ እስከ ዛሬ ድረስ በእንግድነት ነው ተቀብለናቸው ያስተናገድናቸው ከዚህ በኃላ ግን ሥልጣኑን በምንም መንገድ ያግኙት እኛ ከዚህ በኃላ ሊወክሉንም እንደ አባት ልንቀበላቸውም አንችልም በማለት አማረው ተናግረዋል። በአገልካይ ካሕናትም በኩል ገሚሶቹ ምን ችግር አለው ተቀብለን ማገልገል ነው እንደውም እስከ ዛሬ ድረስም የሳቸውን ሥም ነው ጠርተን ሥርዓተ ቅዳሴውንም የምንፈጽመው አሁን ደግሞ ሕጋዊ ወኪል ስለሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ስለላካቸው መቀበል የግዴታችን ነው በማለት በብልጥነት ለማስቀመጥ ይሞክራሉ። ከፊሎቹ ደግሞ የሰንበት ት/ቤቱ ዓይነት ተመሳሳይ አቋም ይዘው እስካሁን ስማቸውን የምንጠራው ከሰሩት ሥራ አንፃር ነው እንዲሁም ባለቤትነቱ የርሳቸው ስለሆነ ነው ይሁንና ከዚህ በኃላ እርሳቸውን እንደ ዋሽንግተን ዲሲ እና የምዕራብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብንቀበል ፓትሪያሪኩን የመቀበል እና በሥርዓተ ጸሎቱ ላይ የመጥራት ግዴታ ሊመጣብን ይችላል፥ ያማለት ደግሞ ሕዝባችንን በጣም ስለሚያስቆጣው ይሄኛው አካሄድ ሊያዋጣን አይችልም በሚል ከፍተኛ ተቋውሟቸውን ግልጸዋል። እንደ መረጃ አቀባያችን አገላለጽ ከሆነ በማንኛውም መልኩ የደብረ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በኃላ ለሁለት ወይም ለሦስት ቦታ የሚከፋፍለው መንገድ እንዳለ በግልጽ አሳይቷል በመሆኑም የአቡነ ፋኑኤል አመጣጣ በማንኛውም መመዘኛ የአካባቢውን ሕዝብ ቀርቶ የደብረ ምሕረትን ሕዝበ ክርስቲያን እንኳ ሊወክሉ እንደማይችሉ ከወዲሁ ተፈርቷል፣ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያኗ ሕልውና ያሰጋቸው ምዕመናንም የፊርማ ማሰባሰቢያ እና ደብዳቤ አዘጋጅተው ለወከላቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲነሱልን ሲሉ ደብዳቤዎችን እና የፊርማ ማሰባሰቡን ሥራ ከወዲሁ እንደጀመሩት ከወዲሁ ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በዚሁ በመጨው እሑድ ህዳር ፲ ቀን (Nov. 20, 2011) ማለትም የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግስ እለት ታላቅ የሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደሚያደርጉ እና አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት አድርገው እንደጨረሱ እና የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ እርዳታ እና ትብብር በመጠየቅ አስፈላጊውን ትብብር እንዲደረግላቸው ከወዲሁ ጥሪ እንድናደርግላቸው ከመልዕክቱ ጋር ተያይዞ ደርሶናል። በዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ ላይ እያንዳንዱ ሀገር ወዳድ እና የኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያኑ ሥርዓት ግድ የሚለው ሁሉ የዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተካፋይ እንዲሆን ከወደሁ አዘጋጆቹ አስቀድመው ጥሪያቸውን አድርሰውልናል። የዚህ ዝግጅት አስተባባሪዎች እንደገለጹልን ከሆነ አቡነ ፋኑኤል እና ተባባሪዎቻቸው ይሄንን ክብረ በዓል ተጠቅመው የቪዲዮ ቀራጭ ባለሙያ ግምቱ $2000.00 ብር ከፍለው በቪዲዮ አስቀርጸው እና አቀናብረው ልክ ሕዝቡ እንደተቀበላቸው አስመስለው "ሕዝቡ ተቀብሎናል ሃሳብ አይግባችሁ" ብለው ፕሮፓጋንዳቸውን ለመሥራት እና ወደ ኢትዮጵያም ለመላክ ቅድመ ዝግጅትም እያደረጉ እንደሆነ ከወዲሁ ለመረዳት ተችሏል። አባ ፋኑኤል እና ግብረ አበሮቻቸው እንዲህ ዓይነት ትውልድን የማያንጽ ሥራ እየሰሩ፣ ጽድቅ ያይደለ ተንኮል፣ እውነት ያይደለ ሐሰት የተሞላበት እየሰሩ እንደገና ልክ በጣም ትጉህ የሆኑ ዓይነት መለስ ቀለስ በማለት ሰውን ለማወዳበድ የሚያደርጉትን ሤራ እና ተንኮል ከወዲሁ ልንገነዘብ ያስፈልጋል እንላለን። አሁንም ሥራ ሰርተናል ብለው ለማለት እንዲህ አይነት ድራማ በማን ላይ የሠሩ እንደሆነ ያልተገነዘቡት እነዚህ ክፍሎች ከተንኮል ይልቅ፣ ትህትና፣ ከበደል ይልቅ ፍቅርን ቢማሩ እና ቢያስተምሩ ይሻላል እንላለን። እነዚህን ሁሉ የተንኮል እና የድራማ ዝግጅቶችን ለመሥራት መዘጋጀታቸው በራሱ እራሳቸውን እና ሕሊናቸውን እያታለሉ ጊዜያቸውን ለመፍጀት ያሰቡ አባት እንጂ ለሥራ የመጡ አባት እንዳልሆኑ ይሄ ሥራቸው እራሱ ትልቅ ምስክር ነው በማለት አዘጋጆቹ በምሬት ገልጸውልናል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን አሜን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

17 comments:

  1. Jib yemayawkut hager hedo kurbet antifulign ale yibalal. "Abune" Fanuel edndelemedut ezihm libetebitu newna bemetubet menged endimelesu hulum betselot fetarin meteyek yinoribetal. Amlak yirdan.
    Mengedun zegtobin komoal mekinaw
    wey addis algezan beshita yelelew
    gifu meche yihon megelageyaw.
    Ene negn

    ReplyDelete
  2. Jib yemayawkut hager hedo kurbet antifulign ale yibalal. "Abune" Fanuel edndelemedut ezihm libetebitu newna bemetubet menged endimelesu hulum betselot fetarin meteyek yinoribetal. Amlak yirdan.
    Mengedun zegtobin komoal mekinaw
    wey addis algezan beshita yelelew
    gifu meche yihon megelageyaw.
    Ene negn

    ReplyDelete
  3. tint abatoch sele betekrstian demachewen afesesu atentachewen kesekesu yezarewochu ye Business abatoch sele betekrstian litselyu,lisewu sayhon yetewahido betesebun kefaflew dem liafasesu kemechewem gize belay kortew tenestewal.yehen sel wesen abatawi sine migbar yalachew abatoch endeminoru amnalehu.ERE BESENTU ENEKATEL,bekachehu yebelen.

    ReplyDelete
  4. ersewen atakefaflut gobez egha yande agere hezebe nene meleyayet kseytan new krestose yene alastemarem egezeabhere ethiopian yebark

    ReplyDelete
  5. please break the silence. ere eskemeche new zimita? beka linilachew yigebal. lelijochachin min enitewulachew? min aynet betekristian? mechiw tiwlid yiwoksenal.
    Egziabher beka yibelen.

    ReplyDelete
  6. Amlake kidusan yebetekrestianehen neger Adera zim endatel.

    ReplyDelete
  7. ስልጣን ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ነው በሐጢያተኛ ሕዝብ ላይ ክፋ ባለስልጣን ይሾምበታል በፃድቅ ሕዝብ ላይ ደግሞ መልካሙን ባለስልጣን ይሾማል ስለዚህ ሁልጊዜ ባለስልጣኖች የሕዝብ ውጤት ናቹው፡፡

    ReplyDelete
  8. bertu tanekeru engame ka gonachew alen!!!!

    ReplyDelete
  9. አባ ፋኑዔልንና ተከታዮቻቸውን መደኃኒዓለም ይቅር ይበላችው ! ! ! ምን ነው ግን? ሠይጣን እንዲህ የሚጋልባቸው መሞት ከሆነ ምርጫችው በጀመሩት መንግድ ይሂዱ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለምን ያሣዝናሉ? ተዋህዶ እና እመቤታችን አይለያዩም ለዘላለም በዓለም ላይ ብርሃናቸው ጎልተው ፀንተው ይኖራሉ እንጂ! በአዋሣ የሠሩት ሣጥናዔልዊ ሥራ ሣያንሣቸው ወገኖቻችን በስደት ሃገር ያለሐዘን በተስፋ የሚኖሩትን ለምን ያበሳጫሉ!; ለነገሩ አባ ፋኑዔል የተዋህዶ አባት ይቀርና ተራ ራፐር ዓይነት መናኛ ወሬ ነው የሚያወራው ስለዚህ ከሱ መልካም ነገር መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደሚጠቅ ጅላጅል መሆን ነው፡፡ ተከታዮቹም እውነን ሕይዎትን ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይደረሰውና ጌታችን መድኃኒታችን መድኃኒዓለም ክርስቶስ ኢየሱስና የሕይዎት እናቱን እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን የሚያስተምሩ የሚያከብሩ መስሎኝ የከበረውን መድኃኒታችንን ስሙን ለገንዘብ መሰብሰቢያነት ለመሸቀጥ መንገብገባቸውን ሣልረዳ ሸቀጣቸውን እየገዛሁ ስጠቀም ነበር ፡፡ አሁን ግን ነቅቻለሁ ነቅተናል ከዚህ በኋላ አንታለልም እምቢ ካሉ ለራሳቸው መሄድ ይችላሉ ሌላ ሠው ለማጥፋት ግን ስዓቱ አልፏል እኛ ዝም ብንል እንኳን እግዚአብሄር ዝም እንደማይል መረዳት መቻል አለባችው ለነገሩ ሕሊና የላቸውም ዓይናቸው ገንዘብና ገንዘብ ብቻ ነው የሚያይ ፡፡
    እግዚአብሔር ሃገራችንን ፤ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን አሜን!!!
    በስላሴ ስም ተሐድሶን እናወግዛልን!!!!
    እመቤታችን አደራ

    ReplyDelete
  10. እረ እንዴት አይነት ዘመን ላይ ደረስን ወገኖቼ? እንዲህ አይነት ሥራ ለምን ይሰራል በእውነት አባ መላኩ እንዲህ አይነት ሰው ነበሩ ማለት ነው? በጣም ጎበዝ አባት ናቸው ብዪ ከምላቸው አባቶች አንዱ ይመስሉኝ ነበር ነገር ግን እንዲህ አይነት አባቶች ደግሞ ያሳፍራሉ እንኳን ህዝብን ሊመሩ እራሳቸውን መምራት አቅቷቸዋል ስለዚህ ልንተዋቸው ይገባል ማለት ነው። ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን እንዲህ አይነት በደል በሕዝብ ላይ እየፈጸሙ አሁንም አባት ብሎ እንዲቀበላቸው የሚፈልጉ ምን ሆነው ነው ባለፈው ስስማ አንጎላቸው ላይ ውሃ ተፈጠረ ለምርመራ መጡ ሲባል እውነትም አንጎላቸው ከውሃ ስለተቀላቀለ መሆን አለበት እንዲህ አይነት በደል የሚሰሩት ማለት ነው ብዬ አሰብኩ በትክክል አዕምሮ ያለው አባት ለዚያውም ጳጳስ እንዲህ አይኑን አውጥቶ ከመናፍቃን ጋር የሚተባበር የሚረዳ የአዋሳን ሕዝብ ክርስቲያኖች እንደዚያ ያስለቀሰ ለምን ሲባል ነው እንደገና እዚህ እኛን ሊያሳዝኑን የመጡት እሳቸው ቢያስቡበት ኖሮ እንዲህ ሰው ካልወደደኝ ምናለ እዚያው ብቀመጥ አይሉም ነበር? ነገር ግን እውነትም አላማ አላቸው ማለት ነው ቤተ ክርስቲያንን ሊያበጣብዙ ነገር ግን እኛም ዝም አንልም እንደ ሃዋሳ ህዝብ ዝም ብለን አንገፋላቸውም ድሮ ያሞኙን ይበቃናል ለመሆኑ ቦርዱ ምን ይላል ለነገሩ ሁሉም በጥቅም የተሳሰሩ ስለሆኑ ምን ይላሉ በሙሉ ሙዳየ መጽዋት ገልባጮች ናቸው ስለዚህ ምንም ሊሉ አይችሉም ጥቅማቸውን እስካገኙ ድረስ ለምን ብለው ይቃወሙአቸዋል?

    እንደ እኔ እንደ እኔ ከሆነ ግን ቦርዱ እራሱ አባ መላኩን መቃወም አለበት ካልሆነ ግን በጥቅም ይዘውታል ማለት ነው ለውነተኛ ነገር መቆም አለባቸው እንጂ ለጥቅም መቆም የለባቸውም ለነገሩ ከሥልጣን አንወርድም የሚሉት የሆነ ጥቅም ስላለ ነው እንጂ ለምን ብለው የዚህን ሁሉ ሰው አፍ ለምን ብለው ይችሉታል... ጥቅም ገንዘብ በደንብ አለ እኛ የዋሃኖች ቤተ ክርስቲያን ሄደን ሙዳየ ምፅዋት እንሰጣለን ለቤቱ ብለን ነገር ግን እነዚህን ቦርዶችን ነው ያወፈርነው ስለዚህ ለሚካኤል ግን አገሬ በሶስ አመት ስሄድ እዛው ብሰጥ ይሻለኛል እላለሁ እዚህ ግን ቦርዱ ለእኛ መስራት ሲገባው ቤተ ክርስቲያንን ለሚያፈርስ ለመናፍቃን ለመስጠት ደፋ ቀና ለሚል ይደግፋሉ ስለዚህ ለራሳችሁ እወቁበት ብየ ምክሬን በዚህ አጋጣሚ እሰጣለሁ

    ReplyDelete
  11. What is going on in our church it is very sad, that we can not get along!!Aba Fanuel is one person. Instead of criticizing, attacking add judging him ,why we do not focus on the church comming ceremony of St.Micheal.The day should be a calm and peaceful day for not distructing the parishioner.We can not restore or save the church if the people are not happy.For once let's leave the judment of the service people of the church to the Almighty God. I am not living in D.C or its vecinity. I live in somewhere where we dont have Ethiopian church to gather us.We attend Greece orthodox church wishing we have one.I hope God will bless us with peace.

    ReplyDelete
  12. aba fanueal ezaw bihonu yishalot neber

    ReplyDelete
  13. እንዴት ነዉ ነገሩ ጎብዝ? እኚህ አባት በሐዋሳ ምህመን ላይ ያደረጉትን ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰጥተን ዕድሜ ለንስሀ እንዲሰጣቸዉ ለመንን እግዚአብሔርም ቸር አይደል? ዕድሜ ለንስሀ ሰጣቸዉ እሳቸዉ ግን ቸርነቱን ንቀዉ ትላንት በዐይናችን ፊት ያለ ሀገረ ስብከታቸዉ ክህነት ሲሰጡ ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ሲባርኩ ከረሙ ታዲያ ትላንት ያላከበሩትን ሀገረ ስብከት ዛሬ እንዴት ሊያስተዳድሩተ ይችላሉ? በቃን በቃን ማልት ይገባናል። ይህን ሁሉ ነገር የሚያደርጉት አቡነ ጳዉሎስ ናቸዉ። ምህመናን ሆይ መታገል ያልብን አቡነ ጳዉሎስን በቃዎት ለመናፍቃን የጀርባ አጥንት መሆንን ያቁሙ።

    ReplyDelete
  14. Yeweset dekemezamurt nachu. wesetamoche

    ReplyDelete
  15. Yehe ye Orthodox sera befutsum lihon aychlem. Haymanotuan mekefafel new enji minem aynet yematnker huneta ayasayem. Yemetserut sera ye menafek sera andehon endetredu eflegalhu. Erasachihun bicha sayhon sewunem megbat wedmayfelegbet hatiatust ayasgebachehu new! Honem Kere ewnetun yemiyawkew esu becha selhone, esu yeserachenen yesten!

    ReplyDelete
  16. Ebakachu wede egziabeher uu belu neger kemarageb wengel sebeku. tera were yaklesheleshal.Yetenaw wengel newe neger yemiyawera. Ebakachu, endayeferedbachu atbedelu

    ReplyDelete
  17. እግዚአበሄር ሆይ እብዶችን ፈውሳቸው!እንደዚህ ዓይነት የእበደት ዘመን ይምጣ?አንድ ቤተ ክርሲቲያን ለስንት ቦጫጭቃችሁ ልትበሏት ታስባላችሁ?

    ReplyDelete