Monday, November 21, 2011

እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው አቡነ ፋኑኤል

  • "እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው"
  • "14 ዓመት ደክሜ ከሰራሁት ቤቴ የትም አልወጣም"
  • "ወደዳችሁም ጠላችሁም ከዚህ የትም አልሄድም"
  • "አዎ አዲስ አበባ ላይ ቪላዎች ቤቶች አሉኝ፣ ያንን ትቼ ይህንን ህዝብ ላገለግል መጣሁ"
  • "ከዋሺንግተን ዲሲ እስከ ካሊፎርኒያ የኔ ግዛት ነው"
  • "ከዚህ በኃላ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ መፃተኛ የሚባል ቤተ ክርስቲያን የለም"

የደብረ ምሕረት የትላንትናው ትዕይንት ይሄን ይመስል ነበር

በትላንትናው እለት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ላይ የተገኙት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ላይ ልክ እንዳደረጉት ምንም የምታመጣው ነገር የለም የኔን የላከኝ ቀበሌ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስ ነው በማለት ለበዓል የታደመውን ምዕመን አስገርመውት ውለዋል። ትላንት በጠዋት የተጀመረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በፓሊስ ውጪው በተቃዋሚ ታውኮ ውሏል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኃላ በመምህር ዘላለም ወንድሙ አማካኝነት የማስፈራሪያ መልዕክት እንዲያስተላልፍ በተሰጠቅ ጥብቅ መመሪያ መሰረት መጥቶ በማያውቅበት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ቆሞ ባለሙዋልነቱን


 በሚገባ አረጋግጧል፣ እንደሚታወሰው መምህር ዘላለም ወንድሙ ከዚህ በፊት በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ፈቃድ በአቡነ ፋኑኤል አደራጅነት እና አዋቃሪነት በተከፈተው  "የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት ጽ/ቤት" በሚባለው የሰሜን አሜሪካ የሰባኪያን እና ዘማሪያን ባለሙሉ ሥልጣን የበላይ ኃላፊ በሚል እንደተሾመ ይታወሳል። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ በትላንትናው ድራማ ላይ አቡነ ፋኑኤል ለእኔ የሚናገርልኝ ሰው ከሌለ እኔው እራሴ ስለ እራሴ ማንነት እነግራችኃለው ብለው ህዝቡን ስለራሳቸው ግድል እና ድርሳን ሲናገሩ ከግማሽ ሰዓት በላይ አሳልፈዋል መዚህም መሠረት እኔ ልሰራ እንጂ ልከፋፍል አልመጣሁም ስለዚህ ከዚህ በኃላ ስደተኛ ወይም ገለልተኛ ሳንል በተጠራንበት በመሄድ እናገለግላለን በማለት አስጨብጭበዋል፣ እንደእውነቱ ከሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ከለየው ጋር ሄዶ መባረክም ሆነ እናቀራርባለን ብሎ ማለት ሥርዓት አልበኝነታቸውን የበለጠ ያጎላዋል እንጂ የሥራ ሰው መሆናቸውን አያስመሰክርም፡ ከዚህ በተጨማሪ "እኔ የሁሉም አባት ነኝ ማለታቸውም" ነገ የአባ ሰላማ ብሎግ ባለቤቶች (ፕሮቴስታንቶቹም) ቢጠሯቸው የሁሉም አባት ስለሆኑ ሄደው ሊባርኩ ነው ማለት ነው አንባቢ ያስተውል።


አቡነ ፋኑኤልና ካሕን መስሎ የቆመው body gourd
 የዛሬ 5 ዓመት ቅዱስ ሲኖዶስ መድቦኝ እዚህ መጥቼ ነበር፣ ነገር ግን  ሕዝቤብ በሀገሩ ማገልገል አለብኝ ከሚለው ጽኑ ፍላጎቴ የተነሳ ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ጽፌ አዛውሩኝ በማለት ተዛውሬያለሁ ያሉት አቡነ ፋኑኤል አሁን ደግሞ ለ17 ዓመት ደግሜ በገዛ ገንዘቤ ያቋቋምኩትን ቤቴን እና  ሕዝብ ለገልግል ብዬ አዲስ አበባ ላይ ካሉት ቪላዎቼ እናንተን መርጬ ላገለግላችሁ መጥቻለው ብለዋል። ትላንት ከታዩት አስገራሚው ትዕይንት የህዝቡን ቀልብ የሳበው አባ ፋኑኤል ልክ እንደ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ የግል ጠባቂ (body gourd) የካህን ልብስ አልብሰው ጥቁር መነጽሩን ደንቅሮ በተጠንቀቅ ሲጠብቅ እና የሙያውን ሥራ በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፣ የፓሊሱ ግርግር፣ ያቦዲ ጋርዱ ጥበቃ፣ የተቃዋሚዎች ስድብ በቤተ ክርስቲያናችን እስከ መቼ እንደሚቀጥል እና ታቦታችን ፊት እንዲህ አይነት ስድብ እና ውርደት መቀጠል እንደሌለበት የሁላችንም እመነት ቢሆንም አቡኑ ግን ወደዳችሁም ጠላችሁም ከሰራሁት ቤቴ ማንም አያስወጣኝም በማለት "ደርግ እንኳን ሁለት ያለውን አንዱን ነው የነጠቀው፣ እኔ ግን አንድ ስለሆነ ያለኝ እሱንም ስጥ የሚል ህግ የለም" ነበር ያሉት።


በእለቱ ከታዩት በርካታ ካሜራዎች እና ተቃዋሚዎች ጥቂቱ
 ሌላው አስገራሚው ትዕይንት ደግሞ አቡነ ፋኑኤል እስከ ዛሬ ድረስ እርሳቸውንም ጨምሮ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ተቀማጭ ሆነው ብዙ ሥራዎችንም የሰሩም ነበሩ የሞከሩም ደግሞ ነበሩ ነገር ግን አቡነ ፋኑኤል እርሳቸው የመጀመሪያው ለሥራ የመጡ የቅዱስ ሲኖዶስ ተወካይ እንደሆነ ሲናገሩ ምዕመናኑን ሁሉ አስገርመዋል፣ በተለያየ ጊዜ እየመጡ ያደራጇቸው የገለልተኛ አስተዳደር በሙሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ነበር የተናገሩት በመቀጠልም ሁሉንም ይዘው ሥራ ለመስራት እንደተዘጋጁ እና ምዕመናኑንም ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ ሙያ ያለህ በሙያህ ተባበረኝ ብለው ነበር የተናገሩት። እንደሚታወቀው የራሳቸውን ዝናና ክብር ሲወራ የሚወዱት አቡነ ፋኑኤል ትላንት የርሳቸውን ገድለ ፋኑኤል የሚያወራ ስለጠፋ "ስለ እኔ የሚናገር ከሌለ እኔው ስለራሴ ልናገር" ብለው ነበር እስቲ ስለ እኔ ገድል ተናገሩ ያሏቸው በሙሉ ለመናገር ባይደፍሩም ሕዝበ ክርስቲያኑን ከንቀታቸው የተነሳ ይሄንን ቤተ ክርስቲያን "ተቃዋሚዎች ጥይት ግዛ ብለው ሲሰጡኝ፣ እኔ ቤተ ክርስቲያን ገዛሁበት" "በመሆኑም አሁንም የእኔ ነው ወደፊትም የራሴው ነው" ነበር ያሉት ታዲያ እንዲህ አይነት "እኔነት" የተጠናወታቸው አባት እንዴት ነው ይህንን የተለያየ አላማ እና አካሄድ ያለውን ሕብረተሰብ እመራለሁ ብለው የተነሱት፣ ሲሆን እንደ ጥንት አባቶቻችን በትህትና እና በፍቅር መጀመር ሲገባቸው ገና ሲጀምሩ በትዕቢት እና በማናለብኝነት የጀመሩት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ሕዝብ ላይ ያደረሱትን በደል በዋሽንግተን ሕዝብ ላይ እንደሚያደርጉት ይጠበቃል።

በዋሽንግተን አካባቢ በተለያዩ አስተዳደር ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አሉ ከነዚህም ጥቂቶቹ
፩/ በእናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር
፪/ በስተደኛው ሲኖዶስ አስተዳደር ያሉ
፫/ ያሉበገለልተኛ አስተዳደር ያሉ
፬/ ስደተኛውም ሲኖዶስ ወይም የሀገር ውስጥ ሲኖዶስ የማይመሩ ነገር ግን በራሳቸው የቦርድ አስተዳደር ያሉ
፭/ በእናት ቤተ ክርስቲያን ያሉ ነገር ግን ያፓትሪያሪኩን ስም በጸሎት የማይጠሩ
፮/ በገለልተኛ አስተዳደር ያሉ ነገር ግን የባለቤቶቻቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጥቂት አባላት ስር የሚተዳደሩ

እውነት ታዲያ አቡነ ፋኑኤልን መሪ አድርጎ ተቀብሎ የሚሰራ የትኛው ክፍል ነው እንደእርሳቸው አባባል የመጡት ለሁሉም ነው ብለዋል ታዲያ ይሳካላቸው ይሆን? ለጊዜው አሸንፈው የገቡት የራሴ ነው የግል ንብረቴ ነው ታክስ እከፍልበታለሁ ወይም መጦሪያ ቤቴ ነው በሚሉት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፣ ቀጥሎስ የትኛውን አሸንፈው ወይም ብልጣ ብልጥ አባባላቸውን ተጠቅመው ማስተዳደር ይችሉ ይሆን? ጥያቄውን ለአናባቢ በመተው የደፊቱን አብረን ለመመልከት የዛሬውን በዚህ እያጠቃለልን በመቀጠል የአቡነ ፋኑኤልን አካሄድ ለአንባቢ እየተከታተልን ለማቅረብ ቃል እንገባለን።

ኢትዮጵያ ሀገራችንን፣ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን አሜን


የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

7 comments:

  1. zendro yemansemaw gude yelem gobze, belew belew demo tebaki yezewben metu. ቀጥሎ ታጣቂ ይዘውብን እንዳይመጡ እኚህ ሰውዬ ለዝርፊያ እንዲመቻቸው ነው መሰለኝ ጠባቂ ይዘው የመጡት፣
    ተዋሕዶዎች ያልጠቀሳችሁትን ነገር ልንገራችሁ፡
    አቡነ ፋኑኤል ትላንት ያሉት ነገር ቢኖር እኔ ኢንተርኔት የለኝም፣ ሬዲዮን የለኝም፣ ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያም የለኝም ስለዚህ ያለኝ መድረክ ይሄ አውደ ምሕረቱ ብቻ ስለሆነ በእዚሁ ላይ የምፈልገውን በሙሉ አስተላልፋለሁ ብለው ሰዎችንም አመጣለሁ ብለዋል እነማን እንደሆኑ ባይጠቅሱም ማንን እንደሚያመጡ በብዙ መገናኛዎች የተገለጸ ነው (በጋሻውን) እንደሚያመጡ የተረጋገጠ ነው ያኔ ግን ከአሁኑ በበለጠ የእግዚአብሔርን ቤት ሊያፈርሱ እንደሆነ ይታወቃል፡

    ReplyDelete
  2. ok what si gone hapen is st george churc can u guies please say something about st george church

    ReplyDelete
  3. waeye america, ye-egziyabeher hager....ye-dengele-maryam.. hager..yekedusan-melaket..hager..ye-tsadekan,ye-kedusan,ye-semaetat...hager... wenetem kedeset hager america....des yebelesh america...DC ke-awasa gar yasebachuhut neger hulu yetekedes ena egziyabeherem asekedemo
    besenefeteret lay endebarekachu tsga new...ahunem egziyabeheren yemetaqelegelut yemigeremew yatachuhut awasa ena DC sew
    new....ayegeremem america egziyabeherem eko hule gize felego yemiyatawe sew new...! DC-YE ena awasaye enen gen asebugne sew hogne enkuwan belegegne betsegachu geta becherenetu endiyasebegne betselotachu hateyaten shefenugne.....yemigerem new telanetena america bemetsehaf kedus lay aletetsafechem eyaleku erasen leyu kedus aderege ke-metsehaf kedus lay lefekesh setagel lekas enen balemaweke betselotesh tasebegne neber zare tarikeshen setenegerigne ewenetaw sigeletelegne ewenetawe lekas kedeset hager mehoneshen teredahu ahunem yedengel maryam lej tsegashen yabezaw.....eneho metemeku kedus yohanesen teketa bemedere beda ye-metechohe hager kedeset america ....mekerashen geta yasebelesh betselotesh ena bemegebaresh asebigne.....awasa dehenetowa betelehem siyasegegnat anchi amereciye bewebetesh eyerusalemen mehonesh new gelilanem temesiyalesh....ye-hagere eyerusalem hawariyat hager Dc ena awasa ...tamagne hawareyatoch hager dc ena awasa des yebelachu... behuletachuhem weset ahunem bihon yedenegel maryam lej egziyabeher ena enatu dengel maryam bewesetachu alu des yebelachu... kedusan melaketem yetayalu bewesetachu yelele yelem hayaratu ke-hanate semay ena tsadekan kedusan semaetatem alu ....enanetem awasana DC kenesu yetemarachuheten new lene temeheret yasetemarachuhegne.......kale heyeweten lenanetem lelelochem hager yasemalegne fetariyachu yedengel maryam lej egziyabeher....be-selamawi selefachu asebugne awasana DC...dengel hoy lemegnilegne.....cher yegetemen

    ReplyDelete
  4. selam lezi bet yehun

    ReplyDelete
  5. ጥቁር መነጽሩን ገርግዶ እንደ አባ ፋኑኤል የግል ጠባቂ አክት የሚያደርገው መነኩሴ እኮ ዲሲ አካባቢ አባ ሠረቀ የተሃድሶን ስራ እንድያቀላጥፍላቸው ያስመጡት ሰው ነው::

    ReplyDelete
  6. አቤቱ መንጋዎችህን አስብ ቤተክርስቲያንን ጠብቅ! ተዋህዶ ሃይማኖቴ ምነው ፈታኞችሽ እንደዚህ በዙ መቼ ይሆን ኡፈይ የምትይው... ታሪክሽ በፈተና የታጠረ ነው የቀደሙት አባቶችስ ፈተናውን በተጋድሎ በትሩፋት አለፉት እኛስ...?? ታሪክሽን ትውፊትሽን ዶግማሽን ቀኖናሽን ስርዓትሽን ጠብቀን ለልጆቻችን እናስተላልፍ ይሆን.... በዚህ ዘመን እየተፈጸመ ያለው ግፍ ያልፍ ይሆን........ ድንግል ሆይ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ጠብቂልን ጻድቃን ሰማዕታት ቅዱሳን በሙሉ እኛ አቅም የለንምና እረዳትነታችሁ አይለየን። አቤቱ በደላችንን አታስብ ምህረትህና ቸርነትህን ላክልን አሜን።

    ReplyDelete
  7. አባ መላኩ አላማዎት ከማን ጋር ይመሳሰላል እንደ ህገ ቤተክርስቲያ ቤጓዙ የሰው ልብ ይማርኩ ነበር 1ኛ እኔን ቀበሌ አልላከኝም ላሉት አዎን ሊመስል ይችላል ግን 2ኛ ሁለት ቤት አለኝ ላሉት ለቤተክርስቲያን ምኗም እንዳልሆነ መረዳት አለብዎት በጣም ማስተዋል ይጎድሎል እባክዎትን እባክዎትን የቀደሙትን ሐዋርያታዊ ንጽህይት ቅድስት አገልግሎት ይመለሱ አደራ አደራ አደራ

    ReplyDelete