Monday, November 14, 2011

ቀሲስ ኢስሃቅ እና ቀሲስ አቡኑ ብራንች ከፈቱ

". . .እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ። . . ."
ትንቢተ ሕዝቅኤል ፵፬ ፥ ፭

በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ልዩ ስሙ Baily Cross Road በሚባል አካባቢ አዲስ የገለልተኛ ክርስቲያናትን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠን ነው ብለው የሚሉት ሁለት የአሜሪካን ካሕናት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውቅና፣ ያለ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ እንደፈለገን በአሜሪካን ሀገር ነው ያለንው ማንም ሊከለክለን አይችልም በሚል ቤተ ክርስቲያን በዘፈቀደ ከፍተው ኑና አስቀድሱ ብለው ባለፈው ቅዳሜ አገልግሎት አለ በማለት ሕዝቡን ሲያዋክቡ ሰንብተዋል። በልዩ ስሙ "ቤሊ ክሮስ ሮድ" በሚባለው አካባቢ የከፈቱት የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ከወዲሁ ትልቅ የሕብን ቁጣ ሳያስነሳባቸው እንደማይቀር ተገምቷል።

፩ኛ/ ቀሲስ አቡኑ ማሞ
፪ኛ/ ቀሲስ ኢስሃቅ

እንደሚታወቀው ቀሲስ አቡኑ ከዚህ በፊት በአቡነ ፋኑኤል፣ በአባ ሰረቀ፣ እንዲሁም ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን አስተባባሪነት ለተጠራ የገለልተኛ አስተዳደር ስር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት በነበረው ስብሰባ ላይ ቀሲስ አቡኑ ለዚህ ስብስብ "እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን" በማለት የአላማ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በፊት በሊቀ መምዕራን ቀሲስ አማረ ካሳዪ አማካኝነት ለቅዱስ ሲኖዶስ በተላከ ደብዳቤ ላይ በገለልተኛ አስተዳደር ስር ያሉት ካሕናትን አስተባብረው ፊርማ አስፈርመው በብፁዕ አቡነ አብረሃም ላይ ክስ ካቀረቡት ቀንደኛ የገለልተኛ አቀንቃኞች ዋነኞቹ እነዚህ ካህናት እንደሆኑ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እስከ ዛሬ ድረስ ሥርዓቷ፣ ትውፊቷ፣ ቀኖናዋ እና ዶግማዋ ሲጣስ ሲበረዝ እንዲሁም ሲሻር የነበረው በቤተ ክርስቲያኒቷ ሞገስ ባገኙ፣ የክብር ወንበር የተሳበላቸው ለጥቅማቸው እንጂ ለነገው ትውልድ ጨርሶ በማይጨነቁ የጥቅም ሰዎች ካሕናት አገልጋዮቿ ነው ለዚህም የመጀመሪያው ምስክሮች እነዚህ ከላይ የምናያቸው ካሕናት ናቸው፣ ቤተ ክርስቲያን አስተምራ ለወግ ለማዕረግ አብቅታ ድራ ኩላ ለዚህ ሁሉ ክብር ያበቃቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ክደው ሕጓን ወደ ጎን ትተው ከፍቶ ለሌባ እና ለበራዥ መልቀቃቸው እጅግ አሳዛኝ እና ዘግናኝ ድርጊት ነው፣ አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራቸውን እየተከታተልን በቅርብ ባሉ ተወካዮቻቸን ልናቀርብ ቃል እየገባን ለካሕናቱም ልቦና እንዲሰጣቸው እንጸልያለን።

የቤተ ክርስቲያናችንን ትንሣኤ ያሳየን አሜን
ቸር ወሬ ያሰማን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

1 comment:

  1. bertu hulachenm kagonachew nan manem betekerstyanin gabeya ayadergatem

    ReplyDelete