Wednesday, November 30, 2011

ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን

ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን


  • በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በአካባቢው ሙስሊሞችና ፖሊሶች የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አፈረሱ
  • ፓትሪያሪኩስ እንዴት ዝም ይላሉ? ለምን ለመንግስት አካላት አያሳውቁም፣
  • ቋሚ ሲኖዶሱስ እንዴት ዝም ይላል፣ ቤተ ክርስቲያን ስትፈርስ ለምን ዝም ይባላል
  • በዓለም ዙሪያ ያለ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጆች ይህንን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ የለብንም
  •   የከተማው ሕግ ቢፈቅድ እንኳ የቤተ ክርስቲያን የበላይ አባቶች እና ተጠሪዎች ይህንን እንዴት ዝም ብለው ይመለከታሉ?



 (አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤2004 ዓ.ም  November 29 2011 ) በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አርብ በ15 /03/04 በሙስሊም ፖሊስ አባላትና እነርሱን ከሚመስሏቸው ማህበረሰብ አካላት ጋር ሆነው ቤተክርስትያኗን ያፈረሷት ሲሆን ፤ በአካባቢው የሚገኝ ታማኝ ምንጭ ለማወቅ እንደቻልነው የቤተክርስትያኒቷ ጉልላት በፖሊስ አዛዡ ግቢ ውስጥ መገኘቱን በዓየይናቸው ተመልክተዋለል ፤ በዞኑ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ አማኞች የሚደርስባቸው ግፍ አስመክቶ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ትናንት በ18/03/2004 ዓ.ም ማለዳ በደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅ/ቤት ክርስቲያኖች ለአቤቱታ በአምስት መኪና የሄዱ ሲሆን :: አቤቱታ አቅራቢዎች የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ቃል አቀባይ የሆኑት እስከ 10 ሠዓት ድረስ ሲሳለቁባቸው ውለው ያለ ምንም መፍትሄ ሸኝተዋችዋል:: አቤቱታ አቅራቢዎቹ ተመልሠው ወደመጡበት አካባቢ ቢመለሱ የመኖር ህልውናቸውናቸው አስጊ በመሆኑ በመጀመሪያ የደቡብ ክልል ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ከዞኑ ፖሊስ ለሚደርስባቸው ጫና ገለልተኛ በሆኑ ፖሊስ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቀጥሎም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ በባዶ ሆዳቸው መሪር እንባ እያነቡ ሲናገሩ ላያቸው ያስለቅሱ ነበር፡፡›› በማለት ዘግቦልናል ፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የሀገረሥብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀሌምጦሰም ለሚመለከታቸው ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ፖሊስ ህገወጦችን በመያዝ ትክክለኛ ምርመራ በማድረግ ለዘር ፤ ለሐይማኖት ፤ ለመንግስት ሳይወግን ፍትህን ፍለጋ  ፍርድ ቤት ማቅረብ ሲገባው በስልጤ ዞን ያሉ ፖሊሶች ግን በእምነት ከሚመስሏቸው ጋር በመሆን ይህን ድርጊት መፈፀማቸው በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ የማህበረሰቡን ፀጥታ ጠባቂ ተብሎ የተቀመጠ አካል ወንጀል የሚፈፅም ከሆነ ማህበረሰቡ ማን ጋር ሄዶ አቤት ይበል? መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሐላፊነት የሚወጡ የፖሊስ አባላት እንዳሉ ሁሉ እንደዚህም አይነት የዘቀጠ ምግባር ያላቸውም አይጠፉም፡፡


ከሁለት ወር በፊት በአዋሽ 7አካባቢ ልዩ ስሙ ቦርደዴ የሚባለው ቦታ ላይ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያንበአካባቢው የሚገኙ ከአክራሪ ወገን የሚመደቡት የእስልምና ተከታዮች በአካባቢው ላይ ለ24 ሰዓት ያህል ከ4 በሚበልጡ መስኪዶቻቸውን ድምፅ ማውጫ Speaker ወደ ቤተክርስትያን አዙረው ‹‹አላህ ዋክበር›› በሚሉበት ሁኔታ ላይ ምንም ጥያቄ ያላቀረቡት በአካባቢው የሚገኙ ክርስትያኖች በዓመት አንድ ጊዜ ለ16 ቀናት ብቻ ያለውን የሱባኤ ጊዜ ለሊት ሰዓታት እና ኪዳኑ ፤ ጠዋት ትርጓሜው እና ስብከቱ ፤ ከሰዓት ቅዳሴው ረበሸን ብለው ቤተክርስትያኒቷ እንድትዘጋላቸው ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡  ይህን ዜና ለማበብ ይህን ይጫኑ ፡፡

እየሆነ ያለውን ነገር ስናየው እና ስንመለከተው ህገመንግስቱ መንግስት ዜጎችን እኩል ማስተዳደር ያስችለው ዘንድ የሀይማኖች እኩልነትን እንደ አንድ አንቀፅ ያሰፈረ ሲሆን ፤ በተግባር እንዳየነው ግን መንግስትም ሆነ ከእሱ በታች የሚገኙት ህጉን የሚያስፈፅሙት አካላት ራሳቸው እየጣሱትና ህዝብን በህዝብ ላይ እነዲነሳሳ መንገድ ጠራጊዎች ሆነው ነው ያገኝናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በጅማ ፤ በስልጤ ዞኖች ፤ በምስራቅ ሐረርጌ እና አንዳንድ አካባቢዎች ብዙ አብያተክርስትያናትን አፍርሰዋል ፤ ንፁሀን ዲያቆናትን ፤ቀሳውስትን ፤ ምዕመናንን በሰይፍ ቀልተዋችዋል ፤ ደማቸውም በቅዳሴ ሰዓት ከመንበሩ ፊት አፍስሰዋል ፤ ለዚህ ሁሉ ህገወጥ አካሄድ መንግስት የወሰደው እርምጃ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ 

‹‹ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።
የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።››
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፤27-28 

በዚህች አገር የሀይማኖት እኩልነት አለ እንዴ? የሀይማኖት መቻቻል እያሉ ጆሯችንን ያደነቁሩናል እነርሱን እኛ ቻልናቸው እንጂ ፤ መቼ እኛን ቻሉን ?

‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ››

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment