Tuesday, February 14, 2012

ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን የአገልጋዮች ጉባኤ ተጠሪ ነን አሉ


ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካን መዲና በሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ላይ "የአገልጋዮች ጉባኤ" በሚል ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ጉባኤ ጉባኤውን እንደተለመደው በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ማሪያም ቤተክርስቲያን ማድረጉን ሰምተን ነበር፣ ከተለያየ ቦታ የመጡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካሕናት፣ ዘማሪያን፣ እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገወጥ ሰባኪያን እና ዘማሪያን ብሎ በማንኛውም ዓውደ ምሕረት ላይ ቆመው እንዳይሰብኩ ወይም እንዳይዘምሩ የተለዩትም ዘማሪያን በቦታው በተጋባዥነት ተገኝተው ነበር።


 እንደ ማኅበሩ አወቃቀር ከሆነ አገልጋዮች በአንድነት በመሆን በተለይ በእናት ቤተክርስቲያን እና በገለልተኛ  አስተዳደር ስር ያሉትን አገልጋዮች ለማቀራረብ ብሎም ምዕመናኑን ወደ አንድ መዋቅር ለማምጣት የተጀመረ ጉባኤ እንደነበረ ከመስራቾቹ መካከል ከነበሩት ሰዎች ለመረዳት ችለናል፥ ነገር ግን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እራሱን የቤተክርስቲያን የውጪጉዳይ ተጠሪ ነኝ በማለት ተሰብሳቢውን ሲያደናግር የጥቅም አጋሩም ተስፋዬ መቆያ በመተባበር ተስብሳቢውን በተለያየ መንገድ ሲያደናግሩት ውለዋል፣ ገና ከመጀመሩ የጉባኤውን መርኃግብር ደብቀው አቆይተው ጸሎት ከተደረገ በኃላ ሲያወጡት ከላይ የተጠቀሰው ቅዱስ ሲኖዶስ ያገደው ዘማሪ ነኝ ባዩ ትዝታው ሳሙኤል በተስፋዬ መቆያ ጋባዥነት በጉባኤው እንዲዘምር በመርኃግብሩ መካተቱ ያበሳጫቸው ጥቂት የጉባኤው ታዳሚዎች ከሰውየው ጋር የግል ጥላቻ የለንም ነገር ግን ልዩነታችን የሃይማኖት ስለሆነ እናንተም እርሱን ጋብዙት እኛም ከዚህ በኃላ የጉባኤው ታዳሚ አንሆንም ብለው መውጣት ሲጀምሩ፥ ለስድብ የታደለው ተስፋዬ መቆያ በለመደ አፉ "ተዋቸው ማኅበረ ቅዱሳን ልኳቸው ነው" በማለት ሲያጥላላ በዓውደ ምሕረት ላይ ተሰምቷል። በዚህም ነበር ብዙዎች በማዘናቸው ጉባኤውን እየረገጡ ስለወጡ ዘላለም ወንድሙ "እባካችሁ ጉባኤ ረግጣችሁ አትውጡ" በማለት ሲማጸን የነበረው፤ ይህንኑ ተከትሎ ከሁለት ሰዓት በላይ ውይይት ተደረጎ የጉባኤውን ተሳታፊ ለማሳመን ትዝታውን እናስወጣዋለን እናንተ ብቻ ቁጭ በሉልን በማለት ለማደናገርም ተሞክሮ እንደነበር ከሥፍራው የደረሰን መረጃ አቀባያችን ጨምሮ ገልጸውልናል።

ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን በመጀመሪያ ለቅዱስ ፓትሪያሪኩ ባለው ቅርበት በሕገወጥ መንገድ ተሹሞ ሹመቱን ይመልከቱ ያለቅዱስ ሊኖዶስ እውቅና፣ ሌላው ቢቀር ያለ ቋሚ ሲኖዶሱ እውቅና፣ ያለ ቤተክህነቱ እውቅና በመሾሙ እና በወቅቱ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሦስቱ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት አሠራሩ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ እንደሆነ በመጠቆም ለቅዱስ ፓትሪያሪኩ እንዲሁም ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ አቤቱታቸውን በማሰማታቸው፥ በቅዱስ ሲኖዶስ የጥቅምት ጉባኤ ላይ የወጪ ግንኙነት ተብሎ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ልዩ ፈቃድ ተከፍቶ ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ቢታወቅም በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የቤተክርስቲያኒቱን ቃለዓዋዲ ያልተፈቀደለት፣ ቀኖናን የሚጥስ፣ ከሕገቤተክርስቲያን ጋር የሚጣረዝ በመሆኑ ኦፊሻሊ የተዘጋ ጽ/ቤት ሆኖ ሳለ በብጹዕ አቡነ ፋኑኤል እምቢተኝነት ሥራውን እንደቀጠለ ነው፣ እንደውም ይህ ጽ/ቤት የቤተክርስቲያኒቱን ህግ በተጻረረ መልኩ ሹመት ሁሉ መስጠት እንደጀመረ ቀደም ብለን በዜናችን ላይ ማስነበባችን ይታወሳል። የዲያቆን ዘላለም ወንድሙ ሹመት እና በመቀጠል ደግሞ የአባ ጽጌ ድንግል ሹመት በማድረግ ነው በሕገወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ያለው። ይህ ጽ/ቤት በመጀመሪያ የሚመራው ቤተክርስቲያን በማታውቀው ጥቁር እራስ ድቁናውን ያፈረሰ በሆነ ሰው ቢሆንም እነ ተስፋዬ መቆያ የዓላማ ግንኙነት ስላላቸው አብረው እየሰሩ እና ሥርዓት አልበኞች የሚሰበሰቡበት ጉባኤ መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል።

በተጨማሪ በዚሁ እለት ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ በቀጥታ በተጻፈ ደብዳቤ ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን የውጪ ግንኙነት ተጠሪ በመሆኑ እና የመጀመሪያውም ሰው ለዚህ ጉባኤ እውቅና ሰጪውም እርሱ በመሆኑ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው ጉባኤው ኃይለጊዮርጊስን እንደበላይ ኃላፊ አድርጎ እንዲቀበለው አበክረው መግለጻቸውን ደብዳቤውን ለተሰብሳቢው በሙሉ በንባብ አሰምቷል። ብዙዎችም "ምነው የእስራኤል አምላክ ሆይ ምነው የዚህችን ቤተክርስቲያን ጻሯን አበዛህው" በማለት ምሬታቸውን በግልጽ ተናግረዋል፥ መጀመሪያ ቤተክርስቲያንን እናገልግል ብለን ብንሰባሰብ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው አምጥተው ይምራችሁ ይሉናል "መጀመሪያ እራሱን እና ሕይወቱን መምራት ያቃተው ሰው" እንዴት ሊመራን ይችላል ብለዋል፤ ለዚያውም በቅዱስ ሲኖዶስ ሕገወጥ ሆኖ በተዘጋ ጽ/ቤት እንዴት እንመራለን ባዮች ናቸው፣ በመቀጠልም የተሃድሶ አቀንቃኞቹ በመጀመሪያ በተሰፋዬ መቆያ ሲያዋዙ ቆይተው ጭራሽ ማንም ምንም ሊያደርግ አይችልም በሚል ይመስላል ትዝታውን አምጥተው ለማዘፈን መሞከር እኛን ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱንም ንቀዋት ነው እንዲህ ሕገ ወጥ ሆነው ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩት ብለው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትዝታው ሳሙኤል፣ የዘርፌ ከበደ፣ የምርትነሽ ጥላሁንን ወደ አሜሪካ መግባት ብዙዎችን አነጋግሯል፣ ቀደም ብለን እንደዘገብነው ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል እንዳስመጧቸው ብናውቅም ነገር ለሰው ጆሮ ተብሎ ስደተኛው ሲኖዶስ ነው ያስመጣው በማለት ወሬዎቹን በሰፊው ማስወራት ጀምረዋል፣ ይልቁንም ባለፈው የጥምቀት በዓል ላይ በሎስ አንጀለስ የስደተኛው መቀመጫ እና መናኽሪያ በሆነው ቦታ ተገኝቶ ዝማሬ አይሉት ዘፈን  እንዳቀረበ ከቦታው የዘገቡልን ባልደረቦቻችን ገልጸውልናል። እውነት ተሃድሶያኑ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጀርባ ሆነው ቤተክርስቲያንን እንዴት ሲወጉ ይኖራሉ? ሕዝበ ክርስቲያኑንስ እስከመቼ እያታለሉ ይኖራሉ? ለዚህም ምስክሩ ደግሞ ባለፈው ቅዳሜ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል አዳራሽ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እና አዲስ የሾሙት የቦርድ አባላት ጋር ቅልጥ ያለ ድግስ ደግሰው የተናገሩት ምስክር ነው ብለን እናምናለን፤ እንደደረሰን ለአንባቢ እናደርሳለን።

ለቅድስተ ማሪያም የቦርድ አባላት እንዲሁም ምዕመናን ተስፋዬ መቆያ በአውደ ምሕረት ላይ ቆሞ በተለያየ ጊዜ የሚያስተላልፋቸው የጥላቻ መልዕክቶች፣ ዓውደ ምሕረት ላይ ቆሞ ለምን ተቆጣ በቅርብ ጊዜ በይርጋ ጨፌ ኢትዮጵያ ተገኝቶ የፈጸመው አስነዋሪ ድርጊት፣ እውን ተሃድሶ የለም ?   ማንን ለማሳሳት ተሃድሶ የለም ይባላል አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ በቅድስት ማሪያም አደባባይ ላይ የተሃድሶ አቀንቃኝ የሆነው ትዝታው ሳሙኤልን አምጥቶ አገልግል ማለት ሰዎቹ የዓላም ግንኙነት እንዳላቸው ያሳያል፣ እንዴት እንደዚህ ታደርጋላችሁ ብለው የሚጠይቁትን ደግሞ "እናንተ የማኅበረ ቅዱሳን መልዕክተኞች" በማለት እየዘለፈ የሚገኝ ሰው ነው፤ የተለየ ችግር ካለበት በሌላ ቦታ ሊያደርገው ሲችል በዓውደ ምሕረት ላይ ቆሞ ሰውን መዝለፉን ትቶ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለንሰሐ ቢያበቃ ምልካም ነው ብለን እናምናለን።

በመጨረሻ በዚህ ጉባኤ ተካፋይ ለሆናችሁ አባላት አገልጋዮች፣ ". . .እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።. . ." ትንቢተ ኢዩኤል እንደተጠቀሰው እያንዳንዳችሁ አገልጋዮች ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ዘማሪያን እንዲሙም ምዕመናን ወቅቱ የሱባኤ ወቅት ነው ቤተክርስቲያናችንን ከመናፍቃን፣ ከከሃዲያን፣ ከተሃድሶ እንዲታደግልን አብዝተን ወደ ፈጣሪ ልንጮህ ይገባናል። ልቅሶአችንን ሰምቱ ገጸ ምሕረቱን ወደ እዚች ቤተክርስቲያን እንደሚመልስ ሙሉ እምነታችን ነው፤ ለዚህም ደግሞ እያንዳንዱ ከእናት ከአባቶቻችን እንዲሁም ከአያቶቻችን የወረስነውን (የተረከብነውን) ንጽህይት፣ ርትዕይት፣ ብሔራዊት የሆነችውን ቤተክርስቲያን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ሃላፊነት በሁላችንም ላይ መሆኑን አበክረን ለመግለጽ እንወዳለን።

ቸር ወሬ ያሰማን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

8 comments:

  1. enzhi thadiso khonu mahiber qidusan dagmo khadi new

    ReplyDelete
  2. tahdiso behone erasun goda weym tesaste sahyfywe gyn zefene, akenken malet abro mesasat yemslenjale.
    egyzabher ethiopian yetbyk.

    ReplyDelete
  3. Yihe website lekirestina haymanot endihum leamagnoch tilik fetena neww. Ebakachihu yeseytan sirachihun akkumu.

    ReplyDelete
  4. chere satawea chere were yaseman tilalehe maferiya

    ReplyDelete
  5. abba melakun nefsachewn yemarewna ende ahunu abune fanuel sayhon betam jegana neberu sawkachew.nc

    ReplyDelete
  6. Hey, We know that the source of this site is from Aba Abrham Home in Virginia. The organizers / Adminstrators of this bloog are
    1. Dr. MESFIN TENAGNE mistun fetu America illegally yeminor. Minim ayinet DICUNA and KISINA yelelew...
    2. Efrem Eshete - kezih befit addis ababa KIDIST yemitibal mist yeneberew, ahun degimo Mahlet solomon yemitibal abal yemiamagit.
    3. Dawit, ena Akalu yemibalu yemahiberu buchila kutarawoch
    4. Fantu Wolde yemitibal ye abune abrham wushima yeneberech Zefagne - yezemarian hulu telat nachew

    Hulum Kezih Behuala Bota Yelachewim / Tarikachew tezegitual. Ewunetegna yetewahido wondimoch( Kesis Tesfaye Mekoya, Memher Zelalem, Kesis Sebsebe, Kesis Betire, Memher Mesfen/Kidanhemeret, Melake kidan tadesse, melake meheret Aba Estifanos, Aba Hailegiorgis, Aba Tsege, Kesis Abunu Mamo,Kesis Dereje seyum and others) are closely working with Abd Zekarias, Aba Fanuel and L.S.Hailegiyorgis to clear their mother church from Mahibere Kidusan hidden political agenda.

    Bezih Zemen Le ewunet simachew eyetefa endehawariyat yemiagelegilun ageligayouch yeseten ye dingil Mariam lij eyesus christos yirdachew. Abatoch ena wondimoch Bertulin.ZENDOW TETILUAL / WODIKUAL.

    ReplyDelete
  7. እራስህን "ቀሲስ ታደሰ" ብለህ የጠራህው ሰው በእውነት ትንሽ ለራስህ ልታዝን እና ልትጸጸት የሚገባህ ፍጡር ነህ። በመጀመሪያ አባ አብርሃም እንዳንተ ባለው አቋም የጠፋበት የእስላም ሚዛን እንዳይደሉ ልቦናህ በደንብ ያውቀዋል ትረዳዋለህም። አንተ የጠቀስካቸው ሰዎች ሥራቸውን ስለሚያውቁ እንዳንተ ላለው አግድም አደግ ለከርሱ ያደረ ሰው ጋር መልስ በመስጠት ክቡር ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ አይመስለኝም፣ እንዳንተ አይነቱ ነው ድብቅ አጀንዳ ያላቸው በሄዱበት የተለያየ ካባ እየደረቡ የዕለት ከርሳቸውን የሚሞሉበትን አኩፋዳ ብቻ ለመሙላት እላይ እታች የሚሉ እና ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ወደድንም ጠላንም አምላከ ቅዱሳን ይህቺን ቤተክርስቲያን አይተዋትም ትቷትም አያውቅም እውነተኛ አገልጋዮች ናቸው ያልካቸውን ደግሞ ሥራቸው ነው የሚመሰክረው እንጂ እንዳንተ ያለ ለከርሱ ባደሩ ሰዎች ፊርማ ወይም መግለጫ ሊያስመሰክሩ የሚገባቸው አይመስለኝም፣ ለእናት ቤተክርስቲያኑ ያዘነ ወይም የተቆረቆረ ለትውልድ ያስባል፣ በታሪክ ከመጠየቅ ለመዳን እውነተኛ የሆነውን የተዋሕዶ ሥራ ይሰራል ይህ የዚህ ወገን ስለሆነ አላውቀውም ያ የዚህ ወገን ስለሆነ አይመለከተንም ሊል ባለተገባ ነበር ልብ አድርግ ክርስቶስ ከሰማይ ሰማያት የወረደው ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ለእኔና ላንተ ለተዳደፍነው ነው በመስቀል ላይ ቤዛ የሆነን እና የዘላለም ብርሃን ልናይ የቻልነው እንጂ እንዳንተ ባሉ ፍቃድ ወይም ተስፋ እንዳልሆነ በደንብ ጠንቅቀህ ልትረዳው ይገባህ ነበር።
    ወቅቱ የጾም ነው እስቲ ሰላም ይሁን ልዩነት ይቅር ወንድምነት ይስፈን፣ ክርስቶስ በቃሉ እኔንና አንተን ሊያተነን የሚችል አምላክ እኮ ያንን ሁሉ አጽዋዕተ መከራ የተቀበለው በእርሱ ሞት ብቻ ስለሆነ ነው መዳናችን ያም ደግሞ ለእኛ አርዓያ ተስፋ ሊሆነን ነው እንጂ በቃሉ ዳን ብሎ ምድርን እና ሰማይን እንደፈጠራቸው ይታዘዙለት ነበር እኮ መምጣት ሁሉ አልነበረበትም መንገዱን ሊያሳየን ነው ወንድሜ "ቀሲስ ታደሰ"

    የሆነ ሆኖ እውነት የእውነት ሰው ከሆንክ እስቲ ሁሉንም መርምር ከጽንፈኝነት እራስህ አውጥተህ መርምረው ሁሉንም እውነተኛ ናቸው የምትላቸውን በሙሉ ከሃሰተኞቹ መርምራቸው አንድን ሰው ወይም አገልጋይ እውነተኛ ነው የሚያስብለው ምኑነው? ምን አይነት ጠባያት አሉት? አገልግሎቱስ ምን ዓይነት መምሰል አለበት? ከነማን ጋር ይተባበራል? አካሄዱ ምን ይመስላል? የሚሉትን ጥያቄዎች እስቲ መዝናቸው ዝም ብሎ የሆነ ያልሆነ ነገር ከመቀባጠር።
    ምናልባት የልጆች አባት ከሆንክ ልጆችህን ምን ብለህ ነው ስለ ቤተክርስቲያን የምትነግራቸው የየትኛውስ ሃይማኖት ተከታይ ነን ብለህ ትነግራቸዋለህ? ስለምን እንዲቆሙ ትነግራቸዋለህ? ወይስ እንደኛ የሰው ቲፎዞ ብቻ ሆነው እንዲኖሩ? መልሱን ለራስህ እተውልሃለው፣ ለነገሩ በዚህ በእኛ ዘመን "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል" አይደለ የሚባለው ምናልባት እራሳችን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እየካድነው እና ሰዎች ድስ እንዲላቸው ብቻ እየሄድን ግን እራሳችን ሥርዓት ፈረሰ የአባቶቻችንን ርስት ተጣሰ የምንል ስንቶቻችን እንደሆን በርግጥ አላውቅም ነገር ግን እዚህ እኛ ባለንበት ሃገር ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው ለየትኛው ይሆን የቆምነው "ለሥርዓት ወይስ ለገንዘብ" እራሳችን እንመልሰው እግዚአብሔር ቤቴ በቅን የሚያገለግሉኝ ናት ነው እንጂ ያለው በፍቅረ ንዋይ በሰከቱ ትመራ ያለ አልመሰለኝም፣ ስንቶቻችን ነን ለእራሳችን ሥርዓት ሳንጨነቅ ቀርተን የሰውን የምናደንቅ ሥርዓት፣ ትውፊት፣ ቀኖና ቤተክርስቲያን ለማስጠበቅ እና ለመጠበቅ የማንም ማኅበር አባል መሆን እኮ አይጠበቅብንም ለሥርዓቱ፣ ለቀኖናው እና ለትውፊቱ ቀናይ መሆን ብቻ ሊጠበቅብን ይችላል ለሁሉም መዝን ዝም ብለህ ሰው ስም አትጥራ፣ ከመሰለህም ቀጥልበል በርታ እላለሁ
    ጾሙን የረደኤት፣ የስርየት ይሁንልን አሜን

    ReplyDelete