Saturday, February 18, 2012

የአብነ ፋኑኤል ስብሰባ ለምን ይሆን?


የስብሰባው ቦታ

በዚህ በጨረስነው ሳምንት ውስጥ በአሪዞና የተጀመረው ጥቂት እንደሄደ ያለምንም ስኬት ተጠናቋል፣ በብዙ ተንታኞች ከበፊተኛው በበለጠ መቀራረብ ቢኖርም እስከ አሁን ብዙ መፈታት ያለባቸው ችግሮች ግን ሊፈቱ እንዳልቻሉ ይነገራል። እንደ ተንታኞቹ በተለይ ከአስታሪቂዎቹ ውስጥ ሌላ ስውር የሆነ መንገድ ይዘው እሚንቀሳቀሱ ሰዎች እንዳሉ ታውቋል፥ እውነታው ግን ጊዜው ሲደረስ ይታወቃል ብለን እናምናለን፥ ለሁሉም የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ጸሎት እንደሚሆን እናምናለን፣ ሰላሙ ወርዶ ቤተክርስቲያን ወደ አንድ ሥርዓት የምትመጣበት ጊዜ እሩቅ የሚሆን አይመስለንም፣ ለዛ እንዲያበቃን እንመኛለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ፋኑኤል ለእርቅ የመጡትን አባቶች ይዘው በዋሽንግተን አካባቢ ተከታይ አለኝ፣ ሥራ እየሰራሁ ነው ለማለት ይመስላል ከእላይ ታች እየተባለ ነው። ከአካባቢው ምንጮች እንደተረዳነው በመጪው እሁድ የካቲት ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. (Feb. 19, 2012) በፎልስ ቸርች አካባቢ በሚገኘው የሜቶዲስት ቸርች ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ እየተጣደፉ እንደሆነ ከአምንጮቻችን ተገልጾልናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ያላደረጉት ለምንድነው ብለው ሲጠየቁ፣ የተለያዩ ምክንያቶች እንዳላቸው ይነገራል ከነዚህም ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ነው፡

  • የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በገለልተኛ አስተዳደር ስር ስላለ በእንግዶቹ ጥያቄ ሊቀርብላቸው ስለሚችል (ምናልባትም እዚህ አንገባም ይሏቸዋል በሚል ፍራቻ)
  • በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ብዙ ተቃዋሚ ስላላቸው በጸጥታ መልክ እንግዶቹን ማነጋገር ስለማይቻል፣ በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የምዕመናን ተቆርቋሪ ክፍል መውጫ መግቢያ ያሳጣኛል ብለው ስለሰጉ፣
  • ቨርጂኒያ በብዛት የጸጥታ ቦታ መሆኑ ስለታመነ እና ተቃዋሚዎቻቸው ቨርጂኒያ ድረስ ይመጣሉ ብለው በማሰባቸው፣
  • ስለስብሰባው በድብቅ ተነግሮ ጥቂት ሰዎችን ከእንግዶች ጋር አገናኝቶ ይህው ስራ እየሰራን ነው ለማሰኘት የተሸረበ ሴራ እንደሆነ ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸውልናል።
በተጠቀሰው ቦታ ላይ ሌላው ይከሰት ይችላል ተብሎ የሚጠበቀው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የታገደው ትዝታው ሳሙኤል ይዘምራል ተብሎ ስለሚጠበቅ ቤተክርስቲያን ያገደችውን ህገወጥ ዘማሪ በመድረክ መቆም የለበትም በሚል ብዙ የቤተክርስቲያን ልጆች በቁጭት መሆን የለበትም በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል፤ ይህው ሕገወጥ ዘማሪ ባለፈው እሁድ በማኅደረ ስብሃት ልደታ ማርያም በመገኘት ቀድሶ አቁርቦ እንዲሁም ዘምሮ እንደነበር ከስፍራው የደረሰን ሪፓርት ይገልጻል፤ እንደሚታወቀው ይሕ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ገብርኤል የተመሰረተ እና እስከ አሁን ተጠሪነቱ ለብፁዕነታቸው እንደሆነና በገለልተኛ አስተዳደር ቦርድ እንደሚመራ እና የቅዱስ ፓትሪያሪኩም ስም እንደማይጠራበት እና የብጹእነታቸው ስም ብቻ በሥርዓተ ቅዳሴው እንደሚነሳ ከሪፓርቱ ጋር ተያይዞ ደርሶናል።

በዚህ ስብሰባ አቡነ ፋኑኤል ሊያሳዩ የሚፈልጉት:-
  • ለሰላሙ ድርድር የመጡት አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና የቅዱስ ፓትሪያሪኩ የቅርብ ረዳቶች በመሆናቸው፣ ምንም ስህተት ሊፈጠርና ሊታይባቸው ስለማይፈልጉ
  • የተላኩበትን ሀገረ ስብከት ትተው ሌላ መዋቅር ዘርግተው እንደሚንቀሳቀሱ ላለማሳየት በተቻለ መጠን (Low profile) በሆነ መልኩ ስብሰባው ተደርጎ በፎቶና በቪዲዮ አስደግፈው ተቃዋሚ እንደሌላቸው ለማሳየት፣
  • ይበልጡኑ ደግሞ ከተሃድሶ አራማጆቹ ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት በተለይ በቅዱስ ሚካኤል አካባቢ እንዲታወቅ ስለማይፈልጉ (የቤት ባለንብረትነታቸውን ጥያቄ ውስጥ እንዳይገባ) ስለሚፈልጉ በተቻለ መጠን እራቅ ባለ ቦታ ማድረጉን መርጠዋል፣
  • በመጨረሻ ይህ አሁን ስብሰባ ሊደረግበት የታሰበው ቦታ ቀሲስ ኢስሐቅ እና ቀሲስ አቡኑ ሳይባረክ የከፈቱት ቤተክርስቲያን ስለሆነ እግረመንገዳቸውንም ለማስባረክ እና ትክክለኛነቱን በቃላቸው እና በአካል በመገኘታቸው ሊያጸድቁላቸው ታስቦ የተደረገ ነው።
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተመደቡ ጀምሮ እየሰሯቸው ያሉትን ሥራዎች እና በቅዱስ ሲኖዶስ የተመሰረተውን መዋቅር አላውቅም ብለው በራሳቸው መንገድ ሌላ አዲስ መዋቅር መመስረታቸውን ብዙዎችን ያሳዘነ እና ሕገወጥ መሆኑን ቢያምኑም አቡነ ፋኑኤል ግን ከመጪው ግንቦት ወር ርክበ ካሕናት እንደማያልፉ በሰፊው ይነገራል እርሳቸውም በተለያየ ምክንያት ለወዳጆቻቸው እንደሚሉት በዚህ ግንቦት ወር ርክበ ካሕናት ላይ እንደማይገኙ ይነገራል ከዚህም በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት እና ለመሥራት ፈቃደኛ እንደማይሆኑም ተሰምቷል፥ እንደርሳቸው አባባል "የገለልተኛው ጳጳስ" ተብለው እዚሁ መኖርን እንደሚመርጡ ይነገራል፣ ለሁሉም ጊዜው ሲደርስ እንደሚታይ ይጠበቃል።
የስብሰባውን ቦታ ድጋሚ ለመጠቆም
5901 Leesbug pike
Falls Church, VA 22041
5:00 - 8:00 pm.
እስከዛው ቸር ይግጠመን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

3 comments:

  1. ያሰፈራቸሁት በሬ ወለደ የውሸት መዓት አንዱም ትክክል አይደለም ምንድን ነው የሚቀጥለው ውሸት? ? ? ? ? ? ? በሰላም ተጠናቀቀ::
    - እግዚአብሔር ይመስገን
    በዚህ ስብሰባ አቡነ ፋኑኤል ሊያሳዩ የሚፈልጉት:

    ለሰላሙ ድርድር የመጡት አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና የቅዱስ ፓትሪያሪኩ የቅርብ ረዳቶች በመሆናቸው፣ ምንም ስህተት ሊፈጠርና ሊታይባቸው ስለማይፈልጉ
    የተላኩበትን ሀገረ ስብከት ትተው ሌላ መዋቅር ዘርግተው እንደሚንቀሳቀሱ ላለማሳየት በተቻለ መጠን (Low profile) በሆነ መልኩ ስብሰባው ተደርጎ በፎቶና በቪዲዮ አስደግፈው ተቃዋሚ እንደሌላቸው ለማሳየት፣
    ይበልጡኑ ደግሞ ከተሃድሶ አራማጆቹ ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት በተለይ በቅዱስ ሚካኤል አካባቢ እንዲታወቅ ስለማይፈልጉ (የቤት ባለንብረትነታቸውን ጥያቄ ውስጥ እንዳይገባ) ስለሚፈልጉ በተቻለ መጠን እራቅ ባለ ቦታ ማድረጉን መርጠዋል፣
    በመጨረሻ ይህ አሁን ስብሰባ ሊደረግበት የታሰበው ቦታ ቀሲስ ኢስሐቅ እና ቀሲስ አቡኑ ሳይባረክ የከፈቱት ቤተክርስቲያን ስለሆነ እግረመንገዳቸውንም ለማስባረክ እና ትክክለኛነቱን በቃላቸው እና በአካል በመገኘታቸው ሊያጸድቁላቸው ታስቦ የተደረገ ነው።

    ReplyDelete
  2. You guys are full of hate, you are not kristiyan
    Abune Fanueal is wonderful Abat. A lot of yetewahedo people enwodachewaln. We know you
    very well yesytan mahiber. yilek saymeshibachehu heseha gibu. Lehulet geta megezat aychalim. Leboch, balegewoch hulu.

    ReplyDelete