Monday, February 6, 2012

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


·         በስብሰባው ያልተገኙት አቡነ ፋኑኤል ከአካባቢው ለሰበሰቧቸው ካህናት አዲስ ሹመት ሰጥተዋል፤
(ደጀ ሰላ ጥር 28/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 6/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ አጠቃላይ ጉባዔውን በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት በማካሄድ እና መሠረታዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ እንደተጠናቀቀ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል። ጥር 25 እና 26/ 2004 ዓ.ም በሀ/ስብከቱ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተገኙበት በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ “የሀ/ስብከቱን መኖር አላውቅም” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አለመገኘታቸው ታውቋል።



የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የምእመናን ተወካዮች እና የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎች በተሰበሰቡበት በዚህ ጉባኤ ላይ ሀ/ስበከቱ አሁን ስላለበት ሁኔታ በሰፊው እንደተመከረበት የተገለፀ ሲሆን የሀ/ስብከቱን አገልግሎት የበለጠ አጠንክሮ ለመቀጠልም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሀ/ስብከቱን አላውቀውም በሚል ዕውቅና ነፍገው የራሳቸውን አዲስ መስመር የጀመሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው፣ በሀ/ስብከቱ ውስጥ የሌሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናትን በመያዝ የጀመሩትን የራሳቸውን እንቅስቃሴ በመግፋት ሹመት መስጠታቸውን ከዚያው አካባቢ የተላከልን ደብዳቤ ያመለክታል።
በቀጥታ ለቅዱስ ፓትርያርኩ አድራሻ በተደረገው እና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ግን በግልባጭ በተጠቀሰው ደብዳቤ ላይ “በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት” ሊቃነ ካህናት፣ ፀሐፊዎች እና ሒሳብ ሹሞች እንዲሁም የሰንበት ት/ቤት ኃላፊዎች መሾማቸውን አሳውቀዋል።
ሊቀ ካህናት ተደርገው የተሾሙት ካህናት የመጡባቸው አብያተ ክርስቲያናት ገሚሶቹ የቅዱስ ፓትርያርኩን ስም የሚጠሩ ገሚሶቹ ደግሞ ራሳቸውን ገለልተኛ ብለው ያሉ እና ከሀ/ስብከቱ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የሚታወቁ ሲሆኑ የተቀሩት ካህናት ደግሞ ምንም አጥቢያ የሌላቸው፣ አቋቁመውት የነበረውም የፈረሰባቸው፣ አንዳንዶቹም አዲስ ለማቋቋም ደጅ በመጥናት ላይ የሚገኙ ናቸው።
እስካሁን ባለን መረጃ የእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት “ቦርዶች” የተስማሙበት ይሁን ወይም አይሁን የታወቀ ነገር የለም። የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ
በቅርቡ በሹመቱ ላይ ስለተጠቀሱት ተሿሚዎችን የሚያገለግሉበትን አጥቢያዎች፣ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ፣ ምን እያደረጉ እንደሆነ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸውን አቋም ጨምሮ ከነ መረጃው ወደ አንባብያን ለማድረስ ቃል እየገባን ለአሁን ያሉበትን ወይም አቋማቸውን ለማሳወቅ ያህል እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል ።
* አባ ኃይለ ጊዮርጊስ መረሳ?
* አባ ጽጌ ድንግል ? (ገለልተኛ) ይመልከቱት
* ቀሲስ መንግስቱ?
* ንቡረ ዕድ አባ ዘካሪያስ?
* አባ ተስፋ ማርያም? (ገለልተኛ)
* አባ ተስፋ ሚካኤል? (ገለልተኛ)
* አባ ወልደ ጻዲቅ
* ቀሲስ ኤፍሬም? (ገለልተኛ)
* ቀሲስ ታደሰ?? (ገለልተኛ)
* ቀሲስ ብሩክ? (ደጅ ጠኚ)
* ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ (የበጋሻው ደሳለኝ እንደራሴ) ይመልከቱት 
* ቀሲስ ደረጀ ስዩም (ደጅ ጠኚ)
* ቀሲስ ሰብስቤ (ደጅ ጠኚ)
* ቀሲስ ይስሐቅ (ገለልተኛ) ይመልከቱት
* ቀሲስ መስፍን
በቅርቡ ሙሉውን ሪፓርት እናቀርባለን

ቸር ወሬ ያሰማን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

1 comment:

  1. እግዚአብሄር ምህረት ያድርግልን ምን ይባላል

    ReplyDelete