አባ ፋኑኤል እና የአባ ሰላማ ግንኙነት
በወርሃ ጥቅምት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በስተ መጨረሻ ሹመታቸውን አረጋግጠው ወደዋሽንግተን ዲሲ በድብቅ የገቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የእስከ አሁኑ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ አካሄዳቸው ብዙዎችን አስደምሟል፣ እንደ አንድ መንፈሳዊ መሪ በተቻለ መጠን ልዩነትን ወደ ጎን ትቶ ለመሥራት እንደ መሞከር ይባስ ብለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያዎችን የአባ ፋኑኤል አፈ ቀላጤ በሆነው አባ ሰላማ በተሰኘው የመናፍቃኑ አንደበት በሆነው የብሎግ መድረክ ማስፈራሪያዎችን ጨምሮ ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስፈፃሚ ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት ለቀሲስ ዶ/ር መስፍን ልከውላቸዋል።
በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው አቡነ ፋኑኤል ቀሲስ ዶ/ር መስፍን የጀመሩትን ሥራ ካላቆሙ እርምጃ እወስዳለው በማለት ማስፈራሪያን ጨምረው በደብዳቤው ገልጸዋል የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ያገኙታል እንደ አቡነ ፋኑኤል ከሆነ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ቤተክርስቲያን ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉት አጥቢያዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ እንዲሁም ሕዝበ ክርስቲያኑ የጣለችባቸውን ሃላፊነት ባስቸኳይ ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። እረ ለመሆኑ የሚሰሩት መንፈሳዊ ሥራ ነው ወይስ ሌላ የፓለቲካ ሥራ ነው? አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በሀገረ ስብከቱ ታቅፈው ከነበሩት አጥቢያዎች ወደ አንደኛው እንኳን በመሄድ ለማግባባት አለመሞከራቸው፣ የነበረውንም ሥራ አስፈጻሚ እንደ ቤተክርስቲን መዋቅር እኔ አላውቅህም ከማለት የፍትህ መንፈሳዊ በሚያዘው መሠረት ሰብስቦ ሥርዓት ባለው መንገድ መሥራት አለበለዚያም በሌላ መተካት ሲቻል፥ ጭራሽ መኖሩንም አላውቅም ሲሉት የነበሩትን ሥራ አስፈጻሚ ማስፈራራት ምን የሚሉት አካሄድ ነው።
አባ ሰላማ የሚባለው ብሎግ በመሠረቱ የቅዱሳን፣ የሰማዕታት፣ የመላዕክት፣ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ጠላት ሆኖ ሳለ በምን መመዘኛ ነው ከአቡነ ፋኑኤል ጋር በመተባበር መስራት የጀመረው? እንደ አባ ሰላማ ብሎግ ከሆነ አንደበታቸው ለቅዱሳኑ ያልተመለሰ ለእመቤታችን ያልተመለሰ አንደበት ዛሬ በምን መመዘኛ እንደሆነ ባናውቀውም ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እጅና ጓንት መሆናቸው በጣም የሚያስገርም ክስተት ነው እንደምሳሌ በዚህ ብሎግ ከሚቀርቡ ጽሁፎች በቅርቡ በአንድ አድርገን ብሎግ የተነበበውን የታቦተ ህጉ ከቦታው አልንቀሳቀስም ማለት እንዴ ብለው ሲዘባበቱ መስማት ለኦርቶዶክሳዊያን ከዚህም በላይ ስንት ተዓምራት ሲደርግ ያየን
ይህን ማየት ምንም አያስደንቅም ነገር ግን ለአባ ሰላማዎች መሳለቂያ መሆኑ አያስገርምም በብሎጉ ላይ የወጣው ጽሁፍ አላማቸውም ሆነ ህልማቸው ግልጽ የሆነ የፕሮቴስታንት ተሀድሶ አቀንቃኞች ስለሆኑ ይህ ምንም ሊያስገርም እንደማይችል ለሁላችንም ግልጽ ነው፥ በሌላው ጽሁፍ በዚህ ብሎግ ላይ ከሚወጡት አስነዋሪ እና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ጽሁፎች መካከል ስለ ድርሳነ ሚካኤል የጻፉት ኢ-ሞራላዊ የሆነ ጽሁፋቸው ስለ ድርሳነ ሚካኤል የተጻፈው በእውነት ለማንም ኦርቶዶክሳዊ የሚያስደነግጥ እና የሚያስፈራ ነው። ታዲያ እነዚህ የዘመኑ ቢጻሳዊያን እና አቡነ ፋኑኤልን ምን አንድ አደረጋቸው? የአላማ ወይስ የጥቅም ግንኙነት እስቲ በተለያየ መንገድ እንመልከተው።
አብነ ፋኑኤል በአዋሳ በነበሩበት ጊዜ በብዙ ምዕመናን ሲመከሩ ሌላው ቀርቶ እርሳቸውን በሚቀርቡ አባቶች ተመክረው አሻፈረኝ ብለው የገቡበት መንገድ ከነ በጋሻው ጋር ቅዱስ ሲኖዶስ እግድ ከጣለባቸው በኃላ "ኑ በኔ ሀገረ ስብከት ማንም ሊከለክላችሁ አይችልም" በማለት ነበር ሥራቸውን የጀመሩት በጥቅም ታስረው ፍቅረ ንዋይ ይዟቸው የጀመሩት የመናፍቃኑ አካሄድ በዚያ ጊዜ ነበር በጥልቀት የገቡበት፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተለያየ የሀገረ ስብከቱ አጥቢያዎች በመዘዋወር ብዙ አፍራሽ የሆኑ ስራዎችን ሲሰሩ፣ እንዲሁም ልክ አሁን በቅዱስ ሚካኤል አውደ ምሕረት ላይ ቆመው እንደሚያደርጉት ምዕመናንን መዝለፍ፣ ማንቋሸሽ፣ እሳቸው የቤተክርስቲያኑ የመጨረሻ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉ በመሆናቸው ማንም ምንም ሊያደርጋቸው እንደማይችል ሲዘባበቱ ቆይተዋል። ይልቁንም በቅዱስ ሲኖዶስ የታገዱትን ሰባኪያን እና ዘማሪያን በመያዝ በየ አዳራሹ እና በየአደባባዩ ባራኪ እና የጉባኤ ከፋች በመሆን አጋርነታቸውን አሳይተዋል፣ በመቀጠልም በቆራጥ የአዋሳ ምዕመናን ብርታት እና የአባቶች ጸሎት ከቦታቸው የተነሱት አቡነ ፋኑኤል በመጀመሪያ በመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመድበው ቦታ ባለማግኘታቸው፣ ከጥሎም በድሬደዋ ሀገረ ስብከት ተመድበው ማንም ሊቀበላቸው እንደማይችል ሲረዱት ያኔ ነበር ወደ አሜሪካ በማምራት በወቅቱ አቡነ አብርሃም በሚያስተዳርሩት ሀገረ ስብከት በመምጣት ያለእርሳቸው እውቅና በሕገ ወጥ መንገድ የገለልተኛ ቡድኖችን በመባረክ እና በማጠናከር የረሳቸውን ደጀን ማጠናከር የጀመሩት፣ በእቅዳቸውም መሰረት ከህገ ወጦቹ ዘማሪያን እና ሰባኪያን ወደ አሜሪካ በመውሰድ ይህንኑ የገለልተኛ ለቤተክርስቲያን የማይስማማትን አካሄድ በሰፊው ጀምረው ለጥቅምቱ ጉባኤ ልክ በጎ እንደሰራ አባት በምልዓተ ጉባኤው ለመገኘት ከአሜሪካ ተመለሱ።
አስቀድመው መክረውበት ስለነበር እነ ሊቀ መምዕራን ቀሲስ አማረ ካሳዬን እነ እነ ሊቀ ካህናት ኃይለስላሴን በማነሳሳት አቤቱታ እንዲያቀርቡ ቀደም ተብሎ የቤት ሥራ ተሰጥቷቸው ስለነበር በሚቻላቸው መጠን ተቃዋሚዎችን በፊርማ በመያዝ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሳት የነበሩትን ክስ አቅርበው ካስነሱ በኃላ ሀገሩን አውቀዋለው፣ ሕዝቡንም ባህሉንም በደንብ ጠንቅቄ አውቃለው በማለት እንዲሁም እንደ እውነቱ ከሆነ በወቅቱ ፈቃደኛ የሆነ አባት ባለመኖሩ እነዚህ ሀገረ ስብከቶች በጋራ እንዲያስተዳድሩ እና ሕዝበ ክርስቲያኑን እንዲያጽናኑ በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ተመድበው ነበር የመጡት፣ ያንን የመጡበትን ኃላፊነት እና ውክልና ትተው ነው ዛሬ "እኔ የራሴ የሆነ አካሄድ አለኝ" በማለት መልክአ ቦርድ በሚያዘው አካሄድ እየሄዱ ያሉት ታዲያ መጨረሻቸው የት ይሆን? ራዕያቸው ምን ይሆን? እውነት ለቅድስት ቤተክርስቲያን አስበው ነው ወይስ ለግል ጥቅማቸው እና ክብራቸው አስበው ነው እንዲህ አይነት እስከ አሁን በቤተክርስቲያን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ ሥራ እየሰሩ ያሉት መልሱን ሁላችንም በቅርቡ አላማቸውን በተግባር ሲያሳዩን የምናየው ነው።
በሌላ ዜና የፕሮቴስታንታዊያን ተሃድሶ አቀንቃኞች ትዝታው ሳሙኤል፣ ምርትነሽ ጥላሁን በቅርቡ ወደ አሜሪካ መግባታቸው ይታወሳል ዘርፌ ከበደም ቀደም ብላ ገብታለች እንደእውነቱ ከሆነ ያስመጧቸውም የስደተኛው ሲኖዶስ እንደሆነ በሰፊው ይነገራል፣ ነገር ግን እኛ በደረሰን መረጃ መሰረት በተለይ ለትዝታው ሳሙኤል እና ምርትነሽ ጥላሁን ወደ አሜሪካን መግባት አይነተኛው ምክንያት አቡነ ፋኑኤል እንደሆኑ ይነገራል። ባለፈው የአቡነ ፋኑኤል ሹመት እንደተረጋገጠ በቃሊቲ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ በአይነቱ ትልቅ የሆነ ስብሰባ ማድረጋቸው ይታወሳል፣ በወቅቱ የስብሰባው ተሳታሪዎችም ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ በጋሻው ደሳለኝ፣ ትዝታው ሳሙኤል፣ አባ ሰረቀ፣ ያሬድ አደመ፣ እንዲሁም ሌሎች ቁጥራቸው ከስድት የማይበልጡ ሰዎች ከአባ ፋኑኤል ጋር ተገናኝተው ስለ ቀጣዩ ስራቸው ተወያይተው እቅዶችን ነድፈው እና መንገዱንም ቀይሰው ነበር የተለያዩት፣ በስተ መጨረሻ ላይም አሜሪካ ላይ ታሪክ እንሰራለን ተባብለው ነበር የተለያዩት ታዲያ ያ ታሪክ እየመጣ ይሆን? የበጋሻው ደሳለኝ በተከታታይ ለመምጣት በአሜሪካን ኤምባሲ ቪዛ ክፍል መከልከል እና እና እነ ትዝታው፣ ዘርፌ፣ እና ምርትነሽ ቀደም ብለው መምጣት ገጠመኝ ይሆን ወይስ የእቅዱ ክፍል ይሆን? አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ከተመደቡ በኃላ እነዚህን ህገወጥ ዘማሪያን እና ሰባኪያን ለምን ማሰባሰብ ፈለጉ? ለምንስ አብረዋቸው ወደ አሜሪካ እንዲዘልቁ አጥብቀው ፈለጉ? ስለምን ሲባል በጣም ብዙ ሰባኪያን ባሉበት ኢትዮጵያ ለምን ህገወጦቹን ፈለጉ? ዘማሪያኑም እንዲሁ በጣም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ቢኖሩም በቅርቡ መልሶችን እናገኛለን ብለን እናምናለን።
ይቆየን
ቸር ወሬ ያሰማን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
አቡነ ፋኑኤልን እና "አባ ሰላማን" ምን አገናኛቸው??? |

No comments:
Post a Comment