Tuesday, April 3, 2012

ጆሮ አይሰማው ጉድ የለም!

ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ስለ ዋልድባ ገዳማችን ይዞታ እና ከፊታችን የተደቀነውን አደጋ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያን ዜና ጨምሮ ስንሰማው ቆይተናል፥ የሚገርመው ግን የኢትዮጵያ ዜና ዘገባ እና በሌላው ዓለም የሚዘገበው ዘገባ በጣም የተለያየ መሆኑ ብዙዎችን ዜጎች ይልቁንም ኦርቶዶክሳዊያኑን ግራ ሳያጋባ የቀረ አይመስለንም። ለዚህም ነው አንድ የዝግጅታችን የዘወትር ታዳሚ አንድ ዜና ከአሜሪካዋ መዲና ከሆነችው ዋሽንግተን የላኩልን፥

ነገሩ እንዲህ ነው ባለፈው ጥቂት ሳምንት በፊት የቤተክርስቲያኑ ልጆች በአንድነት ተሰባስበው መልስ ቢሰጥም ባይሰጥም ግንዛቤን ለማስጨበጥ ይረዳል ብለው እንደማንኛውም የሀገሪቱ ዜግነታቸው፣ እንደ ሃይማኖተኛነታቸው ድምጻቸውን ለማሰማት ከ1200 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በዚሁ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ታላቅ ትዕይንተ ሕዝብ አድርገው እንደነበረ ለሁላችንም የተሰወረ አይደለም፥ በዚህ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ከመላው ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚከገኙ ቤተክርስቲያናት ወጣቶች፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ አረጋዊያን አባቶች እና እናቶች እንዲሁም ሕጻናት በዚሁ ሕዝባዊ ትዕይንት ላይ ተሳትፎ አድርገው እንደነበረ በተለያዩ የዜና መሰራጫዎች ተገንዝበናል፥ ከዚህ በተጨማሪ በጣም ጥቂት ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ካሕናት ተገኝተው ነበር እና ነገሩን ለማጣራት የዚህ ዝግጅት ክፍል በተለያየ መልኩ ሙከራ ስናደርግ ቆይተናል በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለው ቤተክህነት ምንም ተስፋ የምጣልበት እንዳልሆነ በዘገባቸው ተረድተናል፤ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ካህናት አባቶች በተለይ ህይወታቸውን በምንኵስና የሚኖሩ የዋልድባን ጉዳይ ከማናቸውም የህብረተሰቡ ክፍል በተለየ ይቆረቆሩለታል የሚል በተለያዩ የህብረተቡ ክፍሎች ታስቦ ነበር፥ ነገር ግን ያ ሊሆን ያልቻለበት ምክንያት ለሁላችንም እንቆቅልሽ ሆኖ ሰንብቷል። ለሁሉ በላይ ግን ትልቅ የህዝብ ተቃውሞ ያስነሳል ብለን የገመትነውን ለማጣራት በተለያዩ መንገዶች ሞክረን፣ ሁሉም መንገዶች ተመሳሳይ ናቸው፥ ነገሩ እንዲህ ነው።

አቡነ ፋኑኤል
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው የተመደቡት አቡነ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ ትልቅ ተቃውሞ ሲደርስባቸው ቆይቷል ተቃውሞውም እንደቀጠለ ነው፥ አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ብፁዕነታቸው በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰላማዊ ሰልፍ በተደረገበት ወቅት፣ የብዙዎች ክርስቲያኖች፣ ሀገር ወዳድ ማኅበረሰብ፣ የሀገር ሀብት እና ቅርስ መውደም እና መጥፋት የሚጨንቃቸው በሙሉ የብጹዕነታቸውን መምጣት እና የሰላማዊ ሰልፉ ተካፋይ እንደሚሆኑ ጠብቆ ነበር። ነገር ግን ብጹዕነታቸው ለሃገር፣ ለሃይማኖት፣ ለወገን እና ለቅርሶቻችን መጥፋት ተጨንቀው ድምጻቸውን ሊያሰሙ ከመጡት ኢትዮጵያውያን ጋር መሰለፍ ቀርቶ፣ በዚያው ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ጽፈው "ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተሳተፉት በሙሉ፥ ቤተክርስቲያንን የማይወክሉ ፖለቲከኞች ናቸው" ብለው ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ጽፈው ማስገባታቸውን ስንሰማ "ጆሮ የማይሰማው ጉድ የለም!" ብለን  ብዙ ሙከራዎችን ለማድረግ ችለናል፣ ይልቁንም ደብዳቤውን ለማግኘት የዝግጅት ክፍላችን ሙከራዎችን እያደረገ ይገኛል፤ እንደደረሰን እናቀርበዋለን።


እውን አቡነ ፋኑኤል ሕዝብን ለመንፈሳዊ አባትነት ሊመሩ ነው የመጡት ወይስ የመንግስትን አጀንዳዎች ሊያስፈጽሙ ነው የመጡት? መልሱን እርሳቸው ሊመልሱት ይችላሉ፥ ከዚህ በኃላም ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት እና ጥላቻ በግልጽ አሳይተዋል ለቤተክርስቲያኒቱም መፍረስ እና ታሪክ፣ ሃይማኖት ፣ ትውፊት መጥፋት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠያቂነታቸውን የሚያመለክት ይመስለናል። በዚያ ቀን ዋሽንግተን ዲሲ ላይ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እርግጥ ነው ጥቂት የፖለቲካ ሰዎች ነበሩበት ብንልም፣ ፖለቲከኞችም እኮ ቢሆኑ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም፥ እንደ ሃገር ዜጋ ብሎች እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይነታቸው ተቃውሞዋቸውን ማሰማት ተገቢ ነው ይጠበቅባቸዋልም፣ ነገር ግን እዳር ቁጭ ብሎ የበዪ ተመልካች መሆን እና ወይም አብዛኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝ ይልቁንም ከዚያው ከደብረ ምሕረት ቤተክርስቲያን የመጡትን ካህን እና ምዕመን ልክ እንደ ፖለቲከኛ መፈረጅ በእነቱ የግፍም ግፍ የበደልም በደል ነው፥ እውን አቡነ ፋኑኤል ማንን ለመበደል ብለው ይሆን እንዲህ ያለ ትልቅ ክህደት በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ሊፈጽሙ የበቁት፣ ማንንስ ሊጠቅሙ ነው? እውነቱን ቀስ ብለን እንደርስበታለን ብለን እናምናለን፤ እርግጥ ነው ልሳናቸው በሆነው "አባ ሰላማ" በተሰኘው የጡመራ መድረክ የተናገሩት ነገሩን እውነት ለመሆኑ ግልጽ ማስረጃ ሊሆን ይችላል ስለ ዋልድባ ገዳም የተጻፈው በአባ ሰላማ ብሎግ ይጫኑት እዚህ   ይህ ብሎግ በተለያየ ጊዜ፣ ስለቤተክርስቲያን መጥፋት እና ስርዓት፣ ትውፊት፣ ቀኖና የሚሉትን ነገሮች ግድ እንደሌላቸው በግልጽ ሲናገሩ እና ሲጽፉ የሚታይ ጉዳይ ነው ታዲያ ዛሬ ከአባ ፋኑኤል ጋር ሆነው የዋልድባን አበረንታንት ገዳም መጥፋት እና መፍረስ እያዩ ሲሳለቁ ማየት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንጂ በዓላማም በግብርም አንድ እንደሆኑ በግልጽ ያስቀመጡት ጉዳይ ነው።

እነዚህ በሕዝብ ላይ ቁጭ ብለው የሕዝቡን ሙዳየ ምጽዋት እየበሉ ሕዝቡን ወዳጅ መስለው እና ቀርበው ነገር ግን ልክ ለእርድ የሚቀርብን በግ እራሱን እያሻሹ አይዞህ እንደሚሉት ነው ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮችን ያደረጉት እውን ይሄ ሕዝብ ይሄ ይገባው ነበር? በቤቱ ተቀብሎ አባት ላደረገ ሕዝብ፣ ራባችሁ፣ ጠማችሁ ብሎ ጓዳውን ሳይሞላ ለአባቶቼ መጀመሪያ ላለ ሕዝብ ይሄ ይገባው ነበር? የእውነት አምላክ አምላከ ቅዱሳን እውነቱን ያሳየን። የነዛ የዓለምን ትርኪ ምርኪ ትተው ለክርስቶስ ሕይወታቸውን ሰጥተው ረሃብን ጥሙን ታግሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ታግሰው፣ ጤዛ ልሰው ሌት ተቀን እየጸዩ ሰውንና እግዚአብሔርን የሚያስታርቁ ገዳማውያን ባዕታቸው ተነካ ተደፈረ ብሎ ድምጹን ለማሰማት የወጣን ሕዝብ "ላም ባልዋለችበት፥ ኩበት ለቀማ" እንዲሉ ያለሃጢያቱ እና ያለግብሩ በሰጡት ስም ሳያንስ የሕዝብ ወገንተኝተታቸውን ባለማሳየታቸው ሳያንስ እንዲህ ዓይነት ስም በመስጠታቸው የአባቶቻችን አምላክ ይፋረደን እያልን እንሰናበታለን።
ቸር ወሬ ያሰማን


የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

5 comments:

  1. Egziabeher le ende ABBA FANUEL ayinetu ena meselochachew libonan yisetachew.........!!!

    ReplyDelete
  2. በትክክል ለውንጀላ ትሮጣላችሁ እናንተ እንደሚመቻችሁ ነገሩን ሁሉ ትወስዳላቸሁ እሺ አሳቸው የሀገረስብከቱ ሃላፊ መሆናቸውን፡ከተቀበላችሁ መጀመሪያ እሳቸውን ስለ ገዳሙ ያላቸውን ኢንፎረሜሽን ጠይቃችሓል? ? አማክራችሃል ልጅ፡ያቦካው.....ክረስቲያን የራሱ፡ቦታ፡አለው ወደ፡እግዚአብሄር፡እግዚኦ፡ነው፡ማለት፡የነበረበት፡ግን፡አልሆለንም፡ለራሳችሁ፡ ነበር ግን ....በድጋሚ የ ዲ.ዳንኤል ባለፈው፡ዓመት፡የፃፈውን፡አንቡ፡በድጋሚ፡ከፈለጋችሁ፡ከትንሳኤ፡በሃላ፡አስነብባችሗለው፡ከረሳችሁት፡እናንተ፡ለራሳችሁ፡ማህበር፡ደህንነት፡ከብረ፡እንጂ፡ለተዋህዶ፡ተቆርቁራችሁ፡አይደለም፡በፍፁም..የኛ፡ስርዓት፡እና፡ቀኖና፡አስከባሪ.......እግዚአብሄር፡ልቦና፡ይስጣችሁ፡ነው፡የምለው............

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወንድሜ አባባልህ አልገባኝም ግልጽ ብታደርግልንስ ምን ይመስሀል

      Delete
  3. ሀገር ቤት የሰሩት ተረሳ?

    ReplyDelete
  4. yesu,
    እንደእውነቱ ከሆነ እሳቸው የቤተክርስቲያኗ ችግር የሳቸው ቢሆን ኖሮ፥ ለሆነ ላልሆነው በየሚዲያው ይወጣሉ አይደል ለምን ሕዝበ ክርስቲያኑን ሰብስበው በሉ ጸልዩ ትጉ ቤተክርስቲያን ህልውናዋ ተደፍሯል ሃይማኖታችን ተደፍሯል መቅደሳችን ተደፍሯል ዛሬ የተዋሕዶ አማኞች የትናችሁ ብለው በባትሪ ሊፈልጉ በተገባቸው ነበር። አንተ እንዳልከው ግን እርሳቸው እነዚህ ይህንን ያዘጋጁት ወንድሞች እንዲህ አይነት ቤተክርስቲያንን እንታደግ ብለው አዘጋጅተው እንደገና የሳቸውን ደጅ ይጥኑ ነው የምትለው የሳቸውን አፕሩቫል ለማግኘት? በጣም ነው የሚያሳዝነው እርሳቸው ሕብቡን መክዳታቸው እና ከመንግስት ጋር መወዳጀታቸው ሳያንስ የርሳቸው እንባ ጠባቂ እንዳንተ ያለው ደግሞ እርሳቸውን ደግፎ ሲናገር ማየት ሞት ነው፣ ምናልባት ነገ ያንተ እናት ወይም አባት ይሆናሉ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስለሆኑ ክራችሁን በጥሱ ወይም አንገታችሁ ለካራ የሚባሉት አንተ ደግሞ እዛ እናትና አባትህን እንዲሁም ቤተክርስቲያንህን ከሚያስገድሉት ጋር ተደርበህ እንደ ባንዳ "ልጅ፡ያቦካው....." እያልክ ትመጻደቃለህ እንዴት አይነት ህሊና ያለህ ሰው ነህ ወንድሜ???? በእውነት እራስን ልትጠይቅ እና ከማን ጋር መቆም እንዳለብህ መመዘኛ ጊዜህ ነው፥ አንድም ቤተክርስቲያንን ከሚያፈርሱ ጋር የኛ ናቸው ብለህ አንተም አፍራሽ ትሆናለህ ወይም ደግሞ እውነተኛ ከሆኑት ቅድስት ቤተክርስቲያን ከወለደቻቸው የቁርጥ ቀን ልጆች አባቶች ጋር ሆነን ልንጋፈጠው የሚገባውን እውነታ መጋፈጥ ይገባናል አለበለዚያ እርሳቸው እንደሆኑ ማሊያቸውን ቀይረዋል ከጠላቶቻችን ወገን እንደሆኑ በተለያየ ጊዜ አሳውቀውናል መቼም ዛሬ ያደረጉት ክህደት ከዚህ በላይ መረጃ ሊመጣልህ አይችልም አለበለዚያ ነገም ወዳንተ እንደሚመጡ እንዳትጠራጠር ለማለት ነው
    ልቦና ይስጠን ለማንኛውም
    እራሳችንን የቤተክርስቲያን ልጅ ነን ብለን፣ እርሷን ከሚወጓት ጋር እንዳንወገን ዓይናችንን እርሱ ይክፈትልን

    ReplyDelete