Tuesday, April 24, 2012

አቡነ ፋኑኤል ለምን ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

  • አቡነ ፋኑኤል በአሜሪካ ለ4 ወራት ሲቀመጡ ምን አጋጠማቸው?
  • በመጡ በ4ኛ ወራቸው ተመለሱ?
  • ዓላማቸውን ከሞላ ጎደል ተሳካላቸው ወይስ?
 ዜናውን በPDF ለማንበብ ይጫኑ
አባ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን የገቡ ቀን

አቡነ ፋኑኤል በወረሃ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መጨረሻ አካባቢ ተሳክቶላቸው (በብዞዎች እንደሚባለው ጉቦ ሰጥተው እንደመጡ ይነገራል) ወደ ዋሽንግተን እና ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኃላ፣ በብዙ ቦታዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ማጣት እንደሚፈልጉት በተለምዶ (እንደ አባ ፋኑኤል አባባል) ገለልተኛ በሚባሉት እንኳን ተቀባይነት ማጣቱ ትንሽ ሳያስከፋቸው የቀረ አይመስለንም የተለያዩ የውስጥ ምንጮች እንደገለጹልን እዚህ ከመጣሁ ስኳሬ ሁሉ ጨመረ እንጂ ምንም ያገኘሁት ነገር የለም ሲሉ እንደተሰሙም ተሰምተዋል። ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ፣ በወቅቱ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አባ አብረሃም እስከሄዱ ድረስ እንኳን እንደ ቤተክርስቲያን አባት ተቀራርበው ቤተክርስቲያኒቱን እንዴት እንጥቀማት ለተጠራንበት ዓላም እንዴት እንሥራ ቀርቶ፣ ጅምር ሥራዎች ካሉ እኔ ልረከቦት ከማለት ይልቅ፥ የአብርሃምን ድንኳን አፍርሼ የኔን እተክላለሁ በሚል ፈሊጥ የነበሩትን ጅምር ሥራዎች ሲያፈርሱ አዳዲስ ሥራዎችን ለመሥራት ሲጣጣሩ የተያበት ጊዜ ነበር፣ ባለፉት 4 ወራቶች እንደእውነቱ ከሆነ ከሠሯቸው ብዙ ልማቶች (ካሉ ማለት ነው፣ ምንም እንደሌለ የታወቀ ቢሆንም) ያጠፏቸው በብዞዎች ጎልተው የሚታዩ ሆነው ተገኝተዋል።


ለአብነት ያህል ጥቂቶቹን ለመጠቆም ያህል:-
  • ገለልተኞችን አቀራርባለሁ በሚል፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር ያሉትን ወደ 17 የሚጠጉ አጥቢያዎች ያለ አባት ማስቀረት እና አናውቃችሁም ብሎ ከመዋቅር ለማስወጣት የተደረጉት ትግሎች፥
  • ለቤተክርስቲያኒቱ ብዙ ሥራዎችን ሊሰሩ የሚችሉትን ማኅበራት በቅዱስ ሲኖዶስ የተመዘገቡትን ማኅበራት አቡነ አብርሃም ያቋቋማቸው ማኅበራት ናቸው በማለት ፈርጆ አላውቃችሁም ማለት በራሱ ውድቀት ነው። እውነታውን ግን ለመጠቆም ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመ ወደ ፳ ዓመታትን ያስቆጠረ ነው፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከተመሠረተ ከ፲ ዓመት በላይ ነው፣ ማኅበረ በዓለ ወልድም ከተመሠረተ ከ፰ ዓመት በላይ ነው ነገር ግን አቡነ አብርሃም እዚህ አሜሪካ የተቀመጡት ፬ ዓመት ብቻ ሆኖ ሳለ እርሳቸው ከመምጣታቸው በፊት እነዚህ ማኅበራት ነበሩ ሥራዎችንም በተለያየ ዓለማት፣ በኢትዮጵያ ጨምሮ እየሠሩ ያሉ ማኅበራት ናቸው ወደፊትም ይሠራሉ ብለን እናምናለን።
  • ሕገ ቤተክርስቲያን በማይፈቅደው መልኩ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ባደረጉት የሀገረ ስብከት ሥራ አስፈጻሚ ሲቋቋም የመጀመሪያ ባለ መብቶች በስብሰባው ተገኝተው መምረጥም ማስመረጥም የሚችሉት በቤተክርስቲያኒቱ ቃለዓዋዲ የሚመሩት አጥቢያዎች መሆን ሲገባቸው እርሳቸው ግን በማናለብኝነት ጳጳሱ እኔ ሲኖዶሱም እኔ ስለሆንኩ መቀየር እችላለሁ በማለት ቤተክርስቲያኒቱን ሲከሱ እና ሲዘልፉ፣ ሕዝቧንም ሲያንጓጥጡ፣ ሃብቷን ንብረቷን ሲዘርፉ የበሩትን ቀንደኛ የቤተክርስቲያኒቱን ጠላቶች ጠርቶ ኑ ሥሩ ምን ችግር አለው እኔን ከተቀበላችሁ፣ እኔም እቀበላችኃለው እኔ ከተቀበልኳችሁ ሲኖዶሱ ተቀበላችሁ ማለት ነው በማለት መሄድ፣ የማናችንም ፍላጎን እነዚህን ሰዎች ማውገዝ እና ማሳደድ ሳይሆን ከስህተታቸው ተምረው ቅድስት ቤተክርስቲያናቸውን ሊክሱ ሊሰሩላት ከሆነ እሰየው ቢሆንም ነገር ግን በተቃራኒው ሲሰሩ እየታዩ ይገኛሉ።
  • በአዋሳ ላይ የተበላሸባቸውን የመናፍቃን ማጠናከር ሥራ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ሊሰሩ አልመው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሲመለሱ እንደ ሃሳባቸው የመናፍቃኑን መሚዎች በመሰብሰብ ሥራቸውን መጀመር የመሆኑን እቅድ ገና የዋሽንግተን ዲሲው ሹመት ከመሰጠቱ ማግስት ጀምሮ በስብሰባ የጀመሩትን ውጥን እውን ማድረግ ስለነበር ከነዚህም መካከል ትዝታው ሳሙኤል፣ ዘርፌ ከበደ፣ ምርትነሽ ጥላሁን የሚባሉት ወደ ሰሜን አሜሪካ በማስመጣት የሥራቸው የውጥናቸው ተባባሪዎች ለመሆናቸው በማኅላ የጀመሩትን ሥራቸውን ጀምረውታል ዋናውንም በጋሻው ደሳለኝን ለማምጣት በከፍተኛ ርብርቦሽ ላይ እንደሆኑ የደረሰን ሪፖርት ጨምሮ ያሳያል።
  • እንደ ሃገረ ስብከት አሰራር መዋቅር ዘርግቶ ከመንበረ ፖትሪያሪክ ጀምሮ እስከ እታች እስካለው አጥቢያ ምዕመን ሊያገናኝ የሚችሉትን መዋቅሮች መዘርጋት ሲገባቸው፣ በተቃራኒው ከምዕመናን ጋር ሊገናኙ የሞከሩበት አካሄዶች በሙሉ የተሳሳቱ እና ፈጽሞ ከቤተክርስቲያኒቱ አሠራሮች ጋር የሚጣረዙ ሆነው ተገኝተዋል፣ ለአብነት ያህል የሚጽፏቸውን ደብዳቤውች እንኳን እራሱን "አባ ሰላማ" በሚል የሚጠራው ብሎግ ነበር የሳቸው አንደበት ሆኖ ሲሰራ የነበረው ያ ደግሞ በራሱ እራሱን የቻለ የውድቀት ውድቀት ይመስለናል፣ የቅዱሳንን ግድል እና ቱሩፋት ተረት ነው የሚል፣ የእመቤታችንን ስም በመጥራት በጽርፈት የሚናገር የመላእክትን ክብር እና ገናናነት የማይቀበል እና የሚዘባበት እንዴት ለእርሳቸው አንደበተ ርትዑ እንደሆነ ወደፊትም ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል መሆኑንም እግረመንገዳችንን ለመጠቆም እንወዳለን።
  • በእርሶ አካሄድ፣ በሚያደርጉት ሥራ ተባባሪ አንሆንም፣ አካሄዶትን ያርሙ አብረንዎት እንስራ የሚሉትን የቤተክርስቲያን አገልጋያ አባቶች፣ የተለያየ ማስፈራሪያ ስምህን ነው የማጠፋው፣ ወረቀትህን ነው የማበላሸው፣ ስምህን ለኢሚግሬሽን እሰጠዋለሁ፣ የመሳሰሉትን ማስፈራሪዎች በመላክ እርሳቸውን እንዲቀበሏቸው ሲሞክሩ፥ እውነትም የአባቶችን አምላክ ርቋቸዋል ያሰኛል፤ አባቶቻችን በፍቅር ሲስቡ፣ በማስተማር ሲመልሱ፣ በመምከር ሲማርኩ፣ በጸሎት ሲማልዱ እንጂ እንደዚህ እንደ አሁኑ ማስፈራሪያ እየላኩ አገልጋዮችን ሲያውኩ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም ወደፊትም ይኖራል ብለን አንጠብቅም፣ ይልቁንም ለራስ መጀመሪያ ቢያውቁ ቢመከሩ እንደጎረምሳ ልማታ ማለታቸውን ትተው እንደ አባት የአምላኬን ስም ጠርቼ እማርከዋለሁ ቢሉ ያስኬዳቸዋል እና አጠገባቸው ያላችሁ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስትሉ ምከሯቸው፣ በአካባቢያቸው ያሉት ተሿሚዎች ከሥራ አስኪያጅ ተብየው ጀምሮ በሙሉ ግብረ በላ ስለሆን ዓላማቸውን ለማሳካት እንጂ ለቤተክርስቲያኒቱ አንዳችም ቅንጣት ሃሳብ እና ቅንዓት እንደሌላቸው ሁላችሁ ታውቁታላችሁ፣ ቤተክርስቲያኒቱን ታደጉ. . .
  • በየጊዜው እየተነሱ ስልጣንህን ይዣለሁ ወስጃለሁ የሚሉት አካሄድ ፈጽሞ የቤተክርስቲያን ያልሆነ እንደሆነ ማናቸውም ይቅር ካህናት ምዕመናን የሚያውቁት ብዙዎች ናቸው፣ ይልቁንም እርሳቸው በኃይለጊዮርጊስ ተጽፎ የተሰጣቸውን ዝም ብሎ ከመፈረም እና ማኅተም ከመምታት ሌላው ቢቀር እንኳን እንደው ቃላቱን እንኳን አስተካክለህ አምጣ የማለት ሥልጣን የላቸውም እንዴ፣ የሚጻፍበት አማርኛ እንኳን የሦስተኛ ተማሪ ከሚጽፈው አማርኛ ያነሰ ነው እና እርሱ ጽፎ ሲሰጣቸው አንብበው ይስተካከል ማለት ቢችሉ የርሳቸውንም አዋቂነት ስለሚያሳይ በዚህ ላይ ቢሰሩ ጥሩ ነው እንላለን ከዚህ በተረፈ እያንዳንዱ ደብዳቤዎችዎን ቢያነቧቸው ያፍራሉ፣ ለዛ የለውም፣ ቅንነት የለበትም፣ የአባት ርህራሄ የለበትም ስለዚህ ጎረምሳ የጻፈውን ተቀብለው ሳያነቡ ሲፈርሙ ወደፊትም ድረስ ይተቻሉ ስለዚህ በዚህ ዙሪያ ወይ ጸሐፊዎን ያሰናብቱት ወይም እርሶ proof read ማድረጎን አይርሱ ለአብነት ያህል ጥቂቶቹን ደብዳቤዎች ለማንበብ እዚህ ይጫኑ 
ከላይ ለመግለጽ የሞከርናቸው አቡነ ፋኑኤል በአራት ወራት ውስጥ የሠሩት ገድሎች ናቸው የልማት አባትነታቸውን ደግሞ እነ "አባ ሰላማ" ስለሚመሰክሩ እኛ ወደዚህ ውስጥ አንገባም፣ ነገር ግን በተቀመጡባቸው 4 ወራት ውስጥ የተሰሩትን ግድፈቶች አንኳር አንኳሩን ለመግለጽ እንወዳለን ለወደፊት ሥራቸው ሊረዳቸው ስለሚችል አልያም ግማሽ ገደል ደርሻለው፣ ጨርሶ ይውሰደኝ ካሉም ምርጫው የርሳቸው ስለሆነ እንደሚከተለው ይቀርባል።

  • የነበረን አላውቅም ብሎው የክህደት ቃላቸውን የሰጡበት የቪኦኤ ቃለ መጠይቅ ላይ ሀገረ ስብከት የለም፣ በአሜሪካ በቃለዓዋዲ የሚመራ ቤተክርስቲያን የለም ብሎ መዋሸት ያስገምታል፤
  • በዳላስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት አለማየሁ በጠሩት ስብሰባ ላይ ሲናገሩ ምዕመን በጥያቄ "እንዴት በቤተክርስቲያኒቱ ሥር የተሰባሰቡትን አጥቢያዎች እያሉ፣ ለምን ወደ ገለልተኛ መሄድ አስፈለገ?" ተብለው ሲጠየቁ "እናንተ የራሳችሁ አካሄድ አላችሁ፣ እኔ የራሴ አካሄድ አለኝ፥ እኔን ሊጠይቅ የሚችለው አካል እናንተ ሳትሆኑ ሲኖዶሱ ነው፣ ከሲኖዶሱ ደግሞ እኔ ስለሆነንኩ ትክክል ነኝ" በማለት የመለሱት የትእቢት ንግግር
  • በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ስር የተገዛውን የሀገረ ስብከቱን ጽሕፈት ቤት እወስዳለሁ ብለው ለሕግ ባለሙያዎች ገንዘብ መክፈላቸው እና ማነጋገራቸው በሰው ሁሉ ዘንድ "እንዴት ፌዘኛ ናቸው" ነው ያስባላቸው እንደእውነቱ ከሆነ ወደ መንበርዎ ተመለሱ ቤቱ የቤተክርስቲያኒቱ ነው ተብለው ነገር ግን ከነጓዜ ካልሆነ ስላሉ ነው መምጣትም ያልደፈሩት። አሁንም በፌዛቸው ቀጥለዋል ለዚህም ሙግት ነው ወደ ኢትዮጵያ የሄዱት የሚል ጭምጭምታ ይሰማል እንደደረሰን እንዘግባለን፣
እውነተኛ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንዑዳን፣ ቅዱሳን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መድኀኒዓለም ክርስቶስ በደሙ ቤተክርስቲያኒቱን ከመሠረተባት ከዛሬ ፳፻፬ ዓመታት ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም ተገምቶም ወይም ሊገመት የማይቻሉትን ታሪካዊ ስህተቶችን እየሰሩ እንዲሁም እያስተባበሩ የሚገኙ በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ያሉ ብቸኛው አባት እንደሆኑ እራሳቸውም ሳይውቁት የሚቀሩ አይመስለንም፣ ምናልባት አሁን እየሩጡበት ያሉበት ሩጫ የት ይወስዳቸው እንደሆን ሁላችንም ዓይናችን እንደፈጠጠ የምናየው ጉዳይ ስለሆነ በጊዜው ልንተራረም እንችላለን፣ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት አቡነ ፋኑኤል በግልጽ በሥራቸው እንደምንገነዘበው ልክ የደብረ ዘይትን የጋሪ ፈረስ ይመስል በዓይናቸው ግራና ቀኝ ግርዶሽ ተጋርዶባቸው ወደፊት ብቻ ለማየት እና ከፊት፣ ከኃላ፣ ከግራ፣ እና ከቀኝ ያለውን ውድመት እና ጥሰት ላለማየት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብዙ ጉዳት እያደረሱ፣ ብዙ ፍላጻ እየፈጠሩ፣ ስብራቶችን እያሰፉ፣ መለያየቱን ይበልጥ እያሰፉት፣ (ጭራሽ መልሰን እንዳንገናኝ) ለማድረግ በመሥራት ላይ እንደሆኑ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተረዳው ይመስለናል ለዚህም ደግሞ ጥሩ ምስክሩ አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ተሹመው ከመጡ ጊዜ ጀምሮ የተነሳባቸው የተለያዩ አመጾች ምስክሮች ናቸው፣ ከነዚህም በጥቂቶቹ የደረሰባቸውን ለማየት እንሞክራለን
  • በአንድ ወቅት ገለልተኛን አቀራርባለው በማለት ወደ ደብረ ገነት መድኀኒዓለም ሜሪላንድ (ቀሲስ መምህር ዘበነ የሚያስተዳድረው ቤተክርስቲያን) በጠዋት ተገኝተው ነበር፣ ነገር ግን ሳይጋበዙ ወይም ሳይፈቀድሎት መጥተዋል በመባላቸው በጓሮ በር በቤተክርስቲያኑ ዲያቆን እንዲሸኙ ተደርገው ተመልሰዋል፥ ውድቀት አንድ ጳጳስን የሚያህል አባት እንዴት ቡራኬዎትን አያሰኘንም መባላቸው፣ እርገጠኞች ነን ቅን፣ ታማኝ፣ ለሀገር ለወገን አሳቢ፣ የጸሎት እና የልመና አባት ቢሆኑ ኖሮ እንኳን እመቅደሳቸው ተገኝተው ቀርቶ ተጠርተው ባርኩን ይባሉ ነበር። አለመታደል ሆነ ያ ሊሆን አልቻለም ለምን ይሆን መልሱን ለርሳቸው
  • በየእሁዱ አቡነ ፋኑኤል በሄዱበት በደረሱበት እየተከታተሉ ይበልጡኑ ደግሞ ለህሊና የሚከብድ ስድብ የሚሰድቧቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ምን ሆነው ነው? እርግጥ ነው የተለያየ የፖለቲካ ዓላማ እና መንገድ ያላቸው ወገኖቻችን ቢሆኑም ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ጥርጥር የለንም ነገር ግን ማወቅ ያለብን አቡነ ፋኑኤልን ለምን ተቃወሟቸው ከዚህ በፊት እርሳቸው ባሉበት በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀወስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል ከማናቸውም የኅበረተሰባችን ክፍሎች ተቃውሞ እና ጸያፍ ስድብ ሲደርስባቸው ተሰምቶ አያውቅም እስከ አሁን ድረስ፤ እውነት ታዲያ ችግር ያለው ከኅብረሰባችን ክፍል ካልሆነ ከአባቶቻችን ካልሆነ ስህተቱ ጎልቶ የሚታየው አባ ፋኑኤል ጋር ብቻ መሆኑን መመልከት ይቻላል። በአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ስለ አባ ፋኑኤል በድጋሚ አባ ፋኑኤል በVOA ቃለ ምልልስ  ሌላው ተቃውሞ በአባ ፋኑኤል ላይ በተለያዩ ሃይሎች የዛሬ 9 ዓመት ገደማ ወደ ኢትዮጵይ  ሲገቡ የዋሹት ወሸት ደግሞ ያድምጡት ከዚህ በፊት ሀገረ ስብከት የለም ብለው የዋሹበት ሲጋለጥ ለማየት ይጫኑ በሚገርም ሁኔታ እንዲህ ሲሉ የነበሩት አባ ፋኑኤል ወደ ኢትዮጵያ ሳይመለሱ እዚህ እያሉ በነፃነት ለኢትዮጵያ ቀርበው የተናገሩትን ለማዳማመጥ እዚህ ይጫኑ እዚህ ጋር ደግሞ ብታዳምጡት ወደ አሜሪካ ተመድበው እንደመጡ ደብረ ምሕረትን በግላቸው እንደሰሩ ያለእርሳቸው ማንም እንዳልደከመበት እና የግል ቤታቸው መሆኑን በአንደበታቸው የመሰከሩበት ነው ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ ሁለተኛውን ለማዳመጥ ይህንን ያድምጡ ይጫኑ ።
  • በዚህ ዓመት የጌታችን የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንዳለ የደብረ ምህረት ቤተክርስቲን ዲሲ (የወቅቱ የአባ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስና)፣ የዲሲ ርዕሰ አድባራት ቤተክርስቲያን፣ የሜሪላንድ ደብረ ገነት ቤተክርስቲያን በተለምዶ የገለልተኞች ሕብረት በማለት ጥምቀትን እና መስቀልን በጋራ ሲያከብሩ ዓመታት አስቆጥረው ነበር፣ በዚህ ዓመት ደብረ ምሕረት ዘንድሮ ጳጳሱ እኛ ጋር ናቸው የኢትዮጵያ ሲኖዶስ ተወካይ ናቸው፣ መንበረ ጵጵስና ነን እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ያለ ተራችን በዓሉን በእኛ ደብር መደረግ አለበት የሚል አቋም ይዞ ተነሳ በዚህም ምክንያት ተሰብሳቢዎቹ ይልቁንም ቀሲስ መምህር ዘበነ በቀደምትነት እኛ ብንቀበል ከዚህ በፊት የነበሩ ሊቃነ ጳጳሳት ነበሩ ሳንቀበላቸው ኖረናል ገለልተኞች ስለሆንን፣ እኔ በበኩሌ የደብረ ገነትን ጽላት ወደዚህ ይዘን አንመጣም ብለው ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፣ አሁን አቡነ ፋኑኤልን በምን መስፈርት ነው የምንቀበላቸው በሚል  እርሳቸውንም ተከትሎ የሁሉም ተወካዮች እና አስተዳዳሪዎች ትተው ወጥተው በዓሉን ለየብቻ ሊከበር ችሏል፣ በዚህም ሰበብ በተነሳው በርዕሰ አድባራት ጸብ የሦስት ካህናት እና አገልጋዮችን የሥራ መፈናቀል እና ወደ ቤተመቅደሱ እንዳይደርሱ መባልን ያመጣው መዘዝ የአቡነ ፋኑኤል ከህግ የወጣ አካሄድ እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው። 
  • በቅርቡ ወደ ዴንቨር መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በሊቀ ካህናት አለማየሁ ተጋባዥነት ወደ ዴንቨር ያመሩት አባ ፋኑኤል እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው በዴንቨር መድኃኒዓለም ተገኝተው ለመባረክ እድሉ ሳይገኝ ስለቀረ ወዳልታሰበበት በዴንቨር ኪዳነምሕረት ተገኝተው ተመልሰዋል። ነገሩ እንዲህ ነው በዓሉ በዓብይ ጾም ውስጥ ስለነበር የበገና ምሽት በሚል የዴንቨር መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ዝግጅት ይጀምራል፣ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ከአባ ፋኑኤል ጋር ባላቸው ቅርርብ የተነሳ ለሰበካ ጉባኤው ሳያሳውቁ፣ ለሰንበት ት/ቤቱ ሳያሳውቁ፣ እንዲሁም አብረዋቸው በቤተመቅደስ ለሚያገለግሉት ካህናት ሳያሳውቁ አባ ፋኑኤልን ይጋብዛሉ፣ ቀኑ ሲደርስ በአጋጣሚ እንደመጡ አስመስሎ እዚህ ከተገኙ ደግሞ እንጋብዛቸው እና ይገኙልን የሚል ብልጣብልጥ አካሄድ ይመስላል ሊቀ ካህናት በእለቱ ተጋባዥ ዘማሪያን ከተለያዩ ስቴቶች መጥተው ስለነበር ሰንበት ት/ቤቱ፣ ሰበካ ጉባኤው፣ ተጋባዥ ዘመሪያኑ እና እንግዶች አቡነ ፋኑኤል ከመጡ እኛ እንወጣለን ብለው ለሊቀ ካህናት ስለነገሯቸው፣ እርሳቸውም ሳይወዱ በግድ ተቀብለው አባ ፋኑኤልም የመጡለት ጉባኤ ሳይሳካላቸው ቀርቶ ወደ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ሊሄዱ ችለዋል ይህ የሚያሳየው በየትኛውም ክፍል ውስጥ ተቀባይነትን፣ ድጋፍን፣ አብሮ ለመሥራት አለመፈለግን፣ ዓላማቸው የተሳሳተ እንደሆነ መገንዘብን ያሳያል ብለን እናምናለን።
ከላይ እንደገለጽነው በየትኛውም የኅብረተሰብ ወይም የቤተክርስቲያኒቱ ክፍሎች ወይም ቀና ወገኖች ተቀባይነታቸው በጣም በመጥፋቱ፣ ይልቁንም እላይ እንደገለጽነው ልዩነቶቹ በጣም በመጨመራቸው ልክ እንደ መካሪያቸው ኃይለጊዮርጊስ በጊዜ ኢትዮጵያ ገብተን ማመን የሚችውን እናሳምን ያልቻለውን እንደለመድነው የማስፈራሪያ ጽሁፎችን እየጻፍን በየሀገረ ስብከታቸው እናድርስ በሚል ይመስላል ለግንቦት ጉባኤ ባለፈው አርብ ከዋሽንግተን ዲሲ የተነሱት አቡነ ፋኑኤል ቅዳሜ እለት ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን በዜና ደጀ ሰላም መዘገቡን ሰምተናል፤ ቀደም ብሎ መሄዳቸውም በጉዳዪ ላይ መሥራት ያሰቡት የተለመደው የውሸት መንገዳቸውን ማጠናከሪያቸውን ለመሥራት እንደሆነ ከወዲሁ ተገምቷል፣ በተያየዘ ዜናም የማስፈራራቱን ሥራ መጀመራቸውን ከወዲሁ ደርሶናል በትላንትናው እለት ለሁለት የቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች የማሳመኛ ወይም ማስፈራሪያ ያልለየለት የስልክ ጥሪዎች እንደደረሳቸው ሰምተናል፣ የነዚህ ሁሉ ሥራዎችም አቀነባባሪ እና የአባ ፋኑኤል አለቃ ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን የሚባል ጎረምሳ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል።

የአቡነ ፋኑኤልም በቅዱስ ፖትሪያሪኩም ወይም በመንግስት ተወዳጅነትን ለማትረፍ ይሁን ወይም የቆየ የቤተክርስቲያን ማፍረስ ዓላማ ባልታወቀ መልኩ በሰሜን አሜሪካ በቆዩባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ በደረሱበት ቦታ ሁሉ፣ በተለያየ ጊዜ ቪዲዮግራፈሮችን በመግጠር የሚናገሯቸው ነገሮች እነዚህን አባባሎች የሚያጠናቅሩ እንደሆኑ ይገመታል፥ እውነታውን ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ማወቅ ስላለባቸው እስቲ እንመልከተው

፩/ ቅዱስ ፖትሪያሪኩ የጀመሩት በትግራይ ክልል አክሱም ላይ ሊሰራ የታሰበው የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ግንባታ ገንዘባችሁን አውጡ፣ በሙያ እርዱ፣ የሃይማኖታችን አሻራ መገኛ የሆነችውን ታቦተ ጽዮንን በሙዚየም እናስቀምጥ እና እናስጎብኝ በሚል ቂላቂል ጥበብ ገንዘብ ገንዘብ ገንዘብ አውጡ በማለት ሲለመን፣ ሲወሰድ፣ ይታያል የዋሁ የተዋሕዶ ምዕመን ታሪክ ብቻ ስለተባለ ወዴት እንኳን ለማያውቀው ገንዘቡን 16 ሰዓት ሰርቶ ያጠራቀመውን ጥሪቱን ይሰጣል፣ መስጠት መልካም ሆኖ ሳለ ዓላማውን በግልጽ ላልታወቀ፣ ግባቸው ምን እንደሆነ ያልተነገረ ቅዱስ ፖትሪያሪኩ እና የትግራይ ክልል መስተዳደር ቢሮ ብቻ የሚያውቁትን ዓላማ በመደገፍ ሲሰሩ አንድም የፖትሪያሪኩን cheep popoularity ፈልፈው ነው፤ ሁለተኛው ቤተክርስቲያንን ከማፍረስ ጋር አብሮ ስለሚሄድ ነው፣ እርግጠኞች ነን መልሱን እርሳቸውም የሚያውቁት አይመስለንም፥ ለመሆኑ የቤተመዘክር ዓላማው ምንድነው?
  • ታሪክ ጸሐፊዎችን፣ ጎብኚዎችን፣ ተመራማሪዎችን፣ ቅርስን በተለያየ ቦታ አስቀምጦ ለነዚህ ታሪክ ጸሐፊዎች ችግር ከመፍጠር ሁሉንም በአንድ ቦታ ማስቀመጥ ሁሉንም በፈለጉበት ጊዜና ቦታ እንዲያገኛቸው ስለሚጠቅም፤
  • የቤተክርሲያኗ ብቸኛ፣ ልዩ እና ርዕሰ አድባራት አክሱም መገኛ ስለሆነች ከታሪክም አንጻር ብቸኛ ቦታው ስለሆነ፤
    • እውነታው ግን ከግሸን ደብረ ከርቤ የጌታ ግማደ መስቀል ተነስቶ አክሱም በምን መልኩ ይሂድ አባቶቻችን ከጌታ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ያረፈውን ግማደ መስቀል በምን መልኩ፣ ጎብኚዎችም እኮ ቢሆኑ ቅርሱን ሲያዩ ከቦታው ታሪክ ጋር ነው ሊጽፉ፣ ሊረዱ የሚችሉት እንጂ እንደተባለው ወደ አንድ ቦታ መውሰዱ፣ ዓላማው ሌላ እንደሆነ ይነገራል እርሱም፣ The great empire of Tigray ምስረታ ላይ ኢትዮጵያ ካሏት ቅርሶች አንዱም ሳይቀር ወደ ትግራይ መሻገሩን ዓላማው ምን እንደሆነ መገመቱ የሚያዳግት አይመስለንም፣ ኢትዮጵያን፣ ታሪኳን፣ ባሕሏን፣ ትውፊቷን፣ ማንነቷን ከታሪክ እና ከትውልድ አሳብ ውስጥ ማውጣት ዓላማቸው የሆኑ ጥቂት elite እንዳሉ እናውቃለን ጊዜ እና ሃይል እግዚአብሔር በሰጠን ሰዓት እንፋረዳቸዋለን፤
    • በጎንደር የተለያዩ ገዳማት የሚገኙት የተለያዩ ነገሥታት ገጸ በረከት ለነዚያ ገዳማት ወይም አብያተ ክርስቲያናት እንጂ ለአክሱም ጽዮን አልተሰጠም፣ በነዚያ ገጸበረከቶችም አክሱም ጽዮንም አትታይበትም ታዲያ ለምን ተጠነሰሰ??
    • በጣና ደሴቶች የሚገኙት የቃልኪዳኑ ታቦት በቦው ለመድረሳቸው መስዋዕት ይሰዋባቸው የነበሩት ንዋየ ቅድሳት በሙሉ የሚታወቁት በጣና ደሴቶች ላይ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት እንጂ ርዕሰ አድባር አክሱም ጺዮን እኮ አትታይበትም፤
    • በደብረ ሊባኖስ፣ በደብረ ወጋግ፣ በዝቋላ አቦ፣ በዋልድባ፣ በደብረ ዳሞ፣ እንዲሁም በተለያዩ ገዳማት የሚገኙት ቅርሶች ለርዕሰ አድባራት አክሱም ጺዮን በምን መልኩ ነው መገለጫ የሚሆኑት? ይህንን መቼም ማንም ሊያውቀው የሚችለው እውነታ ሆኖ ሳለ፣ ጸረ ሰላም፣ ጸረ ልማት ሃይሎች ናቸው የሚያስወሩት በሚል መልኩ መሸፋፈት ከታሪክ ተጠያቂነት ልናመልጥ ስለማንችል ከወዲሁ ገልጸን እና አሳውቀን ከዛ በተረፈ ታሪክ እና የቤተክርስቲያን አምላክ ይፍረድ ብለን እንድናልፍ ግድ ይለናል፣ "የሌባ ዓይነ ደረቅ፣ መልሶ ልብ አድርቅ" እንዲሉ ትላትን እኮ ጽላተ ሙሴን ለዓለም ማሳየት አለብን ብለው ሲሞግቱ የነበሩ፣ በድብቅ ለተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶች ሊሸጡት ሲያስማሙ የነበሩት፣ የጽላቱ መቀመጫ ቤተመቅደስ ጣሪያ አፈሰሰ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ ለዓለም እናሳየው ታሪካችንን፣ ቅርሳችንን በማለት ሲሞግቱን የነበሩት እኖ ናቸው ዛሬ ደግሞ ቤተመዘግር ወቤተመትሐፍት ብለው display እናድርጋቸው በአደባባይ እያሉን ያሉት፣ አባቶቻችን እኮ እነዚህን ታሪኮች እና ቅርሶች ያቆዩልን ምስጢርነታቸውን አክብረው በደማቸው ፍሳሽ እና በአጥንታቸው አጥረው ነው እዚህ ያደረሱልን ከ3000 ዓመታት በላይ ተጠብቆ እኛ ጋር የደረሰው፤ ዛሬ ዛሬ ያን ሁሉ መስዋዕት የተከፈለበትን አውጥተን ካልሸጥን፣ አሳልፈን ለጠላት ካልሰጠን ያም ካልሆነ ደግሞ ለመንታፊዎች እና ሰራቂዎች ያለበትን አውጥተን በግልጽ እናስቀምጥላቸው እና ይውሰዱት ብለው እየቀለዱብን ነው ያሉት፣ እነ አባ ፋኑኤል ትብብራቸው ወደ ምን ለመውሰድ እንደሆነ መገመት አያዳግተንም፤ ወዲሁም ለፖትሪያሪኩ ያላቸውን ታማኝነት እያስመሰከሩም ስለሆነ
፪ኛ/ የዋልድባ ጉዳይ ዛሬ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እያሳሰበ ባለበት ጊዜ፣ ይህ የሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ገዳማችን በመንግሥት በግፍ በጸሎተኛ አባቶቻችን ላይ እጆቻቸውን አንስተው ሲያንገላቷቸው፣ ባእታቸውን ሲወስዱባቸው፣ የቅድስናው ሥፍራ ቤተመቅደሱ በአረማውያን ከነእግራቸው እና ሃጢያታቸው ሲገቡ እና ሲወጡ ማየቱን ተሰቀው፣ የአበው ቅዱሳን ተረፈ አጽማቸው በዶዘር ሲፈልስ ማየት ያላስቻላቸው፣ ታሪክንም ቤተክርስቲያንንም ማጥፋት ነው ብለው ባሉ፣ ዋልድባ የጸሎት እንጂ የፖርክ ይዞታ የላትም ብለው በመላው ዓለም የተነሱ ክርስቲያኖችን የኢትዮጵያ መንግሥት ጸረ ሰላም፣ ጸረ ልማት፣ ፖለቲከኞች እያለ ሕዝቡን እንደሚያደናግረው ሁሉ አባ ፋኑኤልም በዋሽንግተን ዲሲ ይህንን በደል በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሱትን ግፎች ተመልክቶ ልክ አይደለም የገዳማውያኑ ሕልውናቸው ይከበር! ዋልዳብ የጸሎት ቦታ እንጂ የኢንቬስተር አትሆንም! ብለው የነተሱትን ኢትዮጵያውያን ልክ የኢትዮጵያው መንግሥት እናዳለው እና እንዳሳየው አባ ፋኑኤልም ጸረ ሰላም፣ ጸረ ልማት የሆኑ ፖለቲከኞች ናቸው እንጂ ቤተክርስቲያንን አይወክሉብ ብለው በዋሽንግተን ዲሲ ላለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደብዳቤ ማስገባታቸው አጋጣሚ ወይስ ታስቦበት የተደረገ ቤተክርስቲያንን ከማፍረስ እና ሕጓን  እና ሕልውናዋን ለማሳጣት ከሚያደርጉት ሥራዎች ጋር ስለገጠመላቸው ይሆን? እውነታው ግን እንመልከት፡-

  • ዋልድባ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዋልድባ ነች፣ ለእስላሙ፣ ለክርስቲያኑ፣ ሃይማኖት ለሌለው በሙሉ ላለፉት 1600 ዓመታት ታሪክን፣ ቅርስን፣ ሃይማኖት፣ ጠብቃ እና አስጠብቃ የኖረች ገዳም እንደመሆኗ መጠን በምንም መመዘኛ የገዳሙን መደፈር፣ መፍረስ እና የጸሎት አባቶችን መሰደድ ማንም የማየት ፍላጎት ያለው ኢትዮጵያዊ አለ ብለን አናምንም፣ ነገር ግን በዘመኑ የተነሱ ታሪክን፣ ሕዝብን፣ ሃይማኖትን ለያይተው፣ ከፋፍለው ለማጥፋት የሚሞክሩ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ መሪዎች፣ የሃይማኖትም የመንግሥትም መሪዎች መኖራቸው ግልጽ ነው። ነገር ግን ካድሬዎች እንደሚያወሩት ማንም የተለየ interest በዋልድባ ላይ የለውም እንደሚሉት ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማትም አይደለም፣ ልማት እኮ ቢያስፈልግ ያልተነካ ብዙ ድንግል መሬቶች ያሉባት ኢትዮጵያ እኮ የመሬት ችግር የለባትም የወንዝም ችግር የለባትም፣ የሰው ሃይልም ችግር የለባትም፣ ታዲያ ችግሩ ምንድነው ዋልድባ ገዳም ድረስ ምን ወሰዳችሁ ነው ጥያቄው

    • ልዩነቱ የመንግስት ካድሬዎች ወይም እነ አባ ፋኑኤል ለመንግሥት ያላቸውን ታማኝነት ለመግለጽ፣ ወይም የሰሯቸውን ሦስት ትልልቅ ቪላ ቤቶች እንዳይወረስባቸው እንደ ማግባቢያ እንደሆኑ ግልጽ ነው። እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል እንደሚባለው እውነተኛ ያልሆኑትም ለጥቅም፣ ለዝና፣ ለፍቅረ ንዋይ፣ ለመታወቅ፣ ለማፍረስ የተሰለፉትንም ወገኖች በመጨረሻው ቀን የቤተክርስቲያኗ አምላክ እንደዳጎን ድራሻቸውን ከመቅደሱ እንደሚያጠፋቸው ጥርጥር የለንም፥ አለዚያም ደግሞ ይህንን የበደሉትን ሕዝብ እና ቤተክርስቲያን ክሰው ወደ ንሰሐ መመለስ ለራስ ነው፤
    • በዋልድባ በተለይ በቤተ ሚናስ መናኒያን እና በቤተ ጣማ መናኒያን ለምን ልዩነት ተፈጠረ? ሁለቱም የገዳሙ ክልሎች ሲሆኑ እንደ ቤተክርስቲያኗ አስተዳደር እና ሥርዓት በኅብረት በመኖር ኅልወተ እግዚአብሔርን አክብረው እና አስከብረው ኖረው ነበር ነገር ግን የዛሬ 20 ዓመታት ገደማ ሕዋሃት በጫካ በነበረት ጊዜ የደርግ መንግስት የደፈጣ ውጊያ በሚያደርግበት ጊዜ የቤተ ጣማ ማናኒያን አብላጫው የትግራይ ተወላጆች በመሆናቸው የሕዋሃትን ሰራዊት በገዳማቸው መሽገው ደብቀው ከመከራ ሞት አትርፈዋቸዋል፣ ቀጥሎም በገዳሙ ክልል ገብተው ለረጅም ጊዜ ተጠናክረው እና አገግመው ወጥተዋል፣ በዚህ የተነሳ የገዳሙ አቤሜኔት ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል የቤተ ሚናስ፣ የአባ ነፃ፣ የሰቋር፣ የአበረንታት በአጠቃላይ ከቤተ ጣማ በስተቀር አሁንም የገዳሙን ክልል አልፎ ገብቶ መንግስት ማረስ ሲጀምር ቤተ ሚናሶች ተቃውሞአቸውን አቀረቡ ለመንግሥት አካላት ከማይ ፀብሪ አውራጃ አስተዳደር ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ድረስ፣ እንዲሁም ለመንበረ ፖትሪያሪክ ጽ/ቤት ጨምሮ ነገር ግን በተቃራኒው የቤተ ጣማ መናኒያን በተለያየ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በመቅረብ ይልቁንም በትግርኛው ፕሮግራም ላይ በመቅረብ እኛ ፈቅደናል ገዳማችንን አይነካም በማለት እንደ ትግራይ ልጅነታቸው የወገንተኝነታቸውን አስተዋጽዖ ለማድረግ ሞክረዋል፣ እውነታው ግን በተለያየ ሚዲያዎች እንደተገለጸው ቁጥራቸው 4 የሚሆኑ በገዳሙ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት፣ ከገዳሙ ውጢ ደግሞ 14 የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ሕልውና ይጋፋል እንዲሁም መፍረስ እንዳለባቸውም የመንግስት ተወካዮች ተናግረዋል፣ አሁንም በዚህ ሰዓት ከ4 በላይ ቤተክርስቲያናት ፈርሰዋል በመንግሥት ትዕዛዝ ታዲያ ልማት በሚል ሰበብ ቤተክርሲያንን ሲፈስ ዝም ብሎ የሚያይ ኦርቶዶክሳዊ እንዴት ነው ይልቁንም ጳጳሳት፣ ያለእነዚህ ቤተክርስቲያናት እኮ ማንም እንደሆኑ ሳያውቁ የሚቀሩ አይመስለንም፣ የነ አባ ፋኑኤል የተነሱበት ዓላማ ስለሆነ ቤተክርስቲያናችን ፈራርሳ እስከሚያዩ ድረስ እረፍት አይኖራቸውም ሌሎቻችንስ?
በመጨረሻ ልንጠቁም እምንወደው እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ በሙሉ እንደነዚህ ዓይነቶች በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ተሰግስገው የሚያደሟትን እግዚአብሔር አምላክ ነቅዶ እንዲጥልላት የእያንዳንዳችን ጸሎት እና ልመና ስግደት ከልብ ያሻል ስለዚህ በዚህ ዘመን እያንዳችን በሰርክ ጸሎታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን እያሰብን፣ ገዳማቱን እያሰብን፣ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተጋረጠውን ፈተና በቸርነቱ እንደነነዌ ከተማ እንደነ ነብዮ ዮናስ ያሉትን ቅዱሳን ልኮልን አልቅሰን እና ጾመን እና ጸልየን ፈተናዋን እንደ ጉም ብን አድርጎ እንዲያስወግድልን የሁላችንም ጸሎት እንዲሆን እንለምናለን፣ መጪውንም የግንቦት ርክበ ካህናት እግዚአብሔር አምላክ ለአባቶቻችን ወኔውን ሰጥቷቸው ለማፍረስ የተነሱትን ሃይሎች በአምድነት እንዲያሳፍርልን የርሱ ቅዱስ ፈቃድ ይሁን  እንላለን እስከዚያው . . .
ቸር ያሰማን አሜን

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment