Tuesday, April 3, 2012

እናመሰግናለን! ለምታደርጉት ሁሉ

እናመሰግናለን!

(አንድ አድርገን መጋቢት 25 ፤ 2004 ዓ.ም)፤- ከቀናት በፊት በሰላ ድንጋይ አካባቢ የሚገኙ ስድስት አብያተክርስትያናትን የመዘጋት ድባብ እንዳጋጠማቸው መልእክት ቢጤ ትንሽ ጹሁፍ መፃፋችን ይታወቃል ፤ ለእነዚህ አብያተክርስትያናትን ለመርዳት የሚፈልጉ ሰዎች ፤ ከአደጋው ሊታደጓቸውና የጎደላቸውን ንዋየ ቅዱሳትን ለማሟላት ፍቃደኛ ለሆኑ ሰዎች የአስተባባሪዎችን ስልክ ቁጥር ማቀመጣችን ይታወቃል ፤ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ይህ ፅሁፍ ብሎጋችን ላይ ወጥቶ መረጃ የደረሳቸው ምዕመናን ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ጧፍ ፤ እጣን ዘቢብ የረዱ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፡፡ ከሀገረ ጀርመን አንድ ወንድማችን 304 ትልልቁን ጧፍ ፤ 19 ኪሎ አንደኛ ደረጃ እጣን እና 5 ኪሎ ዘቢብ ከቦታው በመደወል በሰዎች አማካኝነት ለአስተባባሪዎቹ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ሲስተር እታገኝሁ 100 ጧፍ 5 ኪሎ አንደኛ ደረጃ እጣን እና 5 ኪሎ ዘቢብ ሰጥታለች ፤ በደብረብርሀን አካባቢ የሚገኙ ምዕመናንም የቻለትን ያህል በመርዳት ለአብያተክርስትያናቱ የሚሆን ንዋየ ቅዱሳትን በማሟላት ለተቸገሩት አብያተ ክርስትያናት በጊዜው በመድረስ ክርስትያናዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል ፤ ከተለያየ ቦታም እርዳታ ተደርጓል ፤


እነዚህን የቤተክርስትያን ለመርዳት የተቋቋመው ኮሚቴ (ከ8 ያላነሱ የወጣቶች ስብስብ) መገልገያዎችን በአግባበቡ በመቀበል ቤተክርስትያናቱን ከሰላ ድንጋይ(ጻድቃኔ ማርያም) ከአራት ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት የእግር መንገድ በመሄድ ይህን የጾም ወቅት ካለችግር እንዲሻገሩት ሀላፊነታቸውን በመወጣት የተጋረጠባቸውን አደጋ በትንሹም ቢሆን መቅረፍ ችለዋል፡፡ ይህ ማለት የተገኝው ነገር በቂ ነው ለማለት ፈልገን ሳይሆን የተገኝውን እና የተሰራውን ስራ ሰዎች እንዲውቁት ለማድረግ ያህል ነው ፤ በተጨማሪም አመስግኑልን ስላሉ ለማመስገንም ጭምር ፤ እነዚህ አብያተ ቤተክርስትያናት ወደፊት የቻልነውን መርዳት እንፈልጋለን ለምትሉ ሰዎች ደብረብርሀን አካባቢ የሚገኙ አስተባባሪዎችን ስልክ ስላስቀመጥን ደውለው ማግኝት ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የተቸገሩት እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም ፤ ቦታው ላይ ያሉ ምዕመናን እንድንተባበራቸውና መረጃውን ሰዎች ዘንድ እንድናደርስላቸው ቋሚ ሳይሆን ጊዜያዊ መፍትሄ ከመሻት አኳያ ይህን ስራ ለመስራት ችለናል ፤ የተቸገሩ መረዳት እየቻሉ ፤ ምዕመኑም መርዳት እያለበት ከመረጃ እጦት አኳያ ጧፍ እና እጣን የሚቸገሩ ቤተክርስትያኖች በርካታ ናቸው ፡፡

የተረዱ ቤተክርስትያናት
1. ጅማይ ቆላ ሚካኤል ፤
2. ጋንቆላ ካህናተ ሰማይ
3. ጋንቆላ ጊዮርጊስ
4. ዛሮ ኪዳነ ምህረት5. አዘዥ አንባ ሚካኤል
6.
ጉይ መድሀኒአለም
እነዚህን የጠቀስናቸውን ቤተክርስትያናት ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብ ፤ የተቸገሩ ቤተክርስትያናት ናቸው ፡፡ አንዳንዶቹ ችግራቸው ጠለቅ የሚሉት ቤተክርስትያኖች መጽሀፍት መቋሚያ ..ወንጌል መጎናጸፊያ መንበር እና ሌሎቹንም መሰረታዊ ነገሮች ማግኝት ከባድ ሆኖባቸዋል እኛ ከአዲስ አበባ በጥቂት ኪሎ ሜትር ተጉዘን ይህን ችግር ለማየትና በቃን እንጂ በየበርሀው ፤ በየገጠሩ የሚገኙትን አብያተክርስትያናት ከዚህም የዘለለ ችግር ይኖርባቸዋል ብለን እናስባለን፡

በሌላ በኩል ከአረብ አገር ከሁለት እህቶች ባገኝነው 2000 ብር የ930 ብር ጧፍና በተቀረው እጣን በመግዛት ቦርደዴ አካባቢ ለሚገኙ ለ4 አብያተክርስትያናት በጧፍ እና በእጣን መልኩ መላክ ችለናል፤ ጧፍ የገዛንበትን ደረሰኝም ለመረጃ ያህል እዚህ ላይ አታች አድርገናል ፡፡

To read the previous post click her ስድስት አብያተክርስትያናት በጧፍና እጣን እጦት የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸዋል

ሰላ ድንጋይ አካባቢ ያሉትን ቤተክርስትያናት ለመርዳ ይህን ስልክ ይጠቀሙ ፤ ( አቶ ጥበበ 0913-164550)

እግዚሐብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን

እናመሰግናለን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment