Thursday, April 19, 2012

ታሪክን መጠበቅ የማን ሃላፊነት ነው?

ቦታው ቴክሳስ አማሪሎ ይባላል ከዚህች ከተማ ወደ 70 ማይልስ ርቀት ላይ ግሩም የምትባል ከተማ አለች ይህች ከተማ ልዩ የሚያደርጋት ነገር ቢኖር፣ ከተማዋ ሁኔታ ቅድስና ያገኘችበት ነገር የለም፣ በዓመት ውስጥ ቁጥራቸው በሺዎች የሚቆጠሩ 
ወደዚህች ቦታ በመንገድም ተጓዦች፣ ለሽርሽር መጪዎች፣ በሥራ ላይ ያሉ፣ ከባድ እና ቀላል ተሽከርካሪዎች የሚነዱ ሹፌሮች፣ እንዲሁም ሙሽሮች ከዚህች ቦታ ቅድስና ለማግኘት እና በረከት ለመቀበል ወደዚህች ቦታ ይመጣሉ።ይህች ቦታ እንደማንኛውም
የአሜሪካ ግዛት ከተሞች አንዷ ብትሆንም የተለየ ቅድስናዋን (ስያሜውን) ያገኘችው የዓለም መድኅኒት ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህማመ መስቀሉን የሚያሳዩ የጌታን ስቃዩን፣ ግርፋቱን፣ በሰው ፊት ያለሃጢያቱ ለፍርድ መቅረቡን፣ ንጽይተ ንጹሐን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው የሚያሳዩ ቅርጾች የተሰሩበት ቦታ ነው፥በጣም የሚገርመው የዚህ ቦታ አመሰራረት እንደሚከተለው ነው።

ቦታውን ያሰሩት ሰው አቶ ስቲቭ ቶማስ የሚባሉ የፖምፓ ቴክሳስ ነዋሪ የነበሩ ነዋሪ ናቸው፥ በተለያየ ጊዜ በዚያ አካባቢ የሚያያቸው በጣም ትላልቅ አስነዋሪ  (huge billboards advertising XXX pornography) ፎቶግራች በጣም ያሳዝኗቸው ስለነበር ይሄንን ቦታ መቀየር አለብኝ ብለው የጌታን ኅማመ መስቀል የሚያሳየውን ቅርጽ ለማሰራት ጥያቄ ሲያቀርቡ ይህንን የሰሙ የቦታው ባለቤት ለሰውየው በስጦታ ሰጥተውት በዚህ ቦታ ላይ በሰሜን አሜሪካ በጣም ከትልቅነቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለትን
ይህንን ትልቅ መስቀል እና የጌታን ህማማ የሚያሳየውን ቅርጽ በ1995 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሊሰራ ችሏል ቦታውን በአሁን ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ከመላው አሜሪካ እየመጡ ይጎበኙታል፣ ይልቁንም ቅዱስ ቦታ እየተባለም ይጠራል። 
በቅርብ ጊዜ ደግሞ ውርጃን የሚቃወም ሃውልት እንዲሁ በበጎ አድራጊ ተሰርቶ 
ለእይታ በቅቷል።


ታዲያ ይሄ ከኛ ጋር ምን ያገናኘዋል ትሉኝ ይሆናል፣ ልክ ናችሁ ምንም ላያገናኘው 
ይችላል ነገር ግን በቅርቡ በሃገራችን በኢትዮጵያ የምንሰማው የዋልድባ ገዳም አካባቢ የ
ልማት ሥራ እንሰራለን በማለት መንግሥት እያደረሰ ያለውን ጥፋት ትንሽ ለማለት 
ስለፈለኩ ነው፥ ሁላችንም እንደምናውቀው ዋልድባ ገዳም ከተመሠረተ በርካታ 
ዘመናትን ያስቆጠረ ከመሆኑም ባሻገር ቦታው ቅድስናውን ያገኘው የጌታ ምስል
ወይም ቤተክርስቲያን እና ቅዱሳን ስላሉበት ብቻ አይደለም ቅድስናውን ያገኘው 
ከራሱ ሰማይና ምድር ከዘረጋው በቃሉካጸናው መድኅኒዓለም ክርስቶስ ነው 
በድንጋይ ቆብ ደፍቶላቸው ባመነኮሳቸውመነኩሳት የተመሠረተን ገዳም ከ1600 
ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክ ያለውን ገዳም በምን ችሎታና በምን ቅድስና ይሆን 
መንግስት እንዲህ እንግልት እና የማጥፋት ዘመቻውን የቀጠለው ብለን እንድንጠይቅ ነው።


አሜሪካዊው አቶ ስቲቨን ቶማስ ቅድስና የሌለውን ቦታ ቅዱስ ሲያሰኙ፥ የእኛ መንግስት ግን ቅድስናውን ከክርስቶስ ያገኘውን ቦታ ወደ መረንነት ለመለወጥ እላይ ታች እያሉ እንደሆን ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግልጽ እየሆነ የመጣበት ጊዜ ይመስለናል። በንግሥት ሲባል የዜጎችን መብት፣ እያንዳንዱ የእምነት ተቋማት የእኩልነት መብቶች፣ በቀደሙ ነገሥታት እና መሳፍንት ተከብረው የኖሩትን የመሬት ሥሪቶች የማክበር ሃላፊነቱን ዘንግቶ ዛሬ በተለያየ ሀገራችን ክፍሎች ውስጥ በርካታ ኦርቶዶክሳዊያን ታርደዋል፣ ተገለዋል፣ ተሰደዋል፣ የእምነት ቦታቸው በግፍ ተወስዶ ለባለሃብት፣ ለተለያየ የእምነት ድርጅቶች ተሰጥቷል። እነዚህን ቤዚክ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ማስጠበቅ ያልቻለ መንግሥት ደግሞ አወዳደቁ እንደማያምር ታሪክን መመርመር ይገባል እንላለን።


ጌታ ባርኮ ሐዋርያቱን ሲመግብ
የጌታ ስቅለት በሁለቱ ወንበዴዎች መካል እንደተሰቀለ

በኬሚስትሪ: ውሃውን ወደ ወይን ለወጠ መባሉ ያስደንቃል

በኖርዝ አሜሪካ ከሚገኙት በትልቅነቱ የመጀመሪያው የሆነው መስቀል

በባዮሎጂ: ያለ ወንድ ዘር ተጸንሶ ከእናታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ተወለደ መባሉ ያስደምማል


በፊዚክስ: በውሃ ላይ ተራመደ መባሉ፣ የዓለምን ግራቪቲ ቴዎሪ ውድቅ ያደርጋል፣ በመጨረሻም በእርገቱ ቀስ በቀስ ከዓይናቸው ተሰወረ በማሉ ድንቅ ያሰኛል።

እንዴት ያለ ፍቅር ነው እስከ ሞት ድረስ ያደረ?

በኢኮኖሚክስ: ቁጠባን ምንም ያደርገዋል እነዚያን ያንድ ገበያ ሰዎች ወደ 5000 የሚጠጉትን በ2 ዓሳና 5 ቁርጥ ዳቦዎችን አብዝቶ መመገቡ የድንቅ ድንቅ ያሰኛል

በሜዲስን: በሽተኞችን መፈወሱ፣ እውራንን ማብራቱ ያለምንም ጠብታ መድኃኒት መፈወሳቸውን ለሰማው ለተመለከተው አቤቱ ሥራህ ድንቅ ነው ያሰኛል።



በታሪክስ: መጀመሪያ እና መጨረሻ የሌለው ድንቅ መካር አምላክ በማሉስ? 


በአገዛዙ: መልካም፣ ድንቅ፣ የሰላም መሪ የተባለለት አምላክ መሆኑስ


በእምነት: ከእኔ በቀር ወደ አባቴ የሚሄድ ማንም የለም፤ እኔ እውነትም፣ መብራትም፣ እኔ ብቻነኝ ብሏል።



ይሄ የኛ አምላክ ማነው ቢሉ?


ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው



ስለእኛ ተሰቃየ፣ መከራን ተቀበለ፣ ተተፋበት፣ ተገረፈ፣ ተሰቀለ በሞቱ ለእኛ ህይወት ሰጠን።


ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤ ዕውሮች ያያሉ፥ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ፥ ደንቆሮዎችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ፥ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ ሉቃስ ፯ ፥ ፳፪



"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።
፩ኛ ቆሮንጦስ ፲፭ ፥ ፳ - ፳፪







እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። . ሉቃስ ፳፬ ፥ ፳


ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካርኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
ኢሳያስ ፱ ፥ ፮


ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል። ሉቃስ ፲፰ ፥ ፴፫


አንድ ጻፊም ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው።
ማቴ. ፰ ፥ ፲፱



ማዳኑን ያያችኊ፣ ለምናችሁ ያገኛችሁ፣ ጠይቃችሁ መልስ ያገኛችሁ፥ እርሱ ድንቅ መካር ጌታ እግዚአብሔር ነው።


ጦር ወታደር የለውም፣ ነገሥታት ሲፈሩት እና ሲያከብሩት ኖረዋል እያከበሩትም ነው


ዓለምን በፍቅሩ ገዛ፣ በመዳፉ ውስጥ ነችና
ያለምንም ጥፋቱ፣ በመስቀል ሰቀሉት
በመቃብርም ቀበሩት፣ እስከዛሬ ሕያው ነው
ስለስሙ ምስጋና በሰማይ በምድር ይሁን አሜን

 የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment