Tuesday, April 3, 2012

ክህነትን በደብዳቤ ማገድ ይቻላል?

ሰሞኑን ከወደ ዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ብዙ ዜናዎችን ሰምተናል አሁንም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ካህንን በደብዳቤ አግጄሃለው በማለት ሥራቸውን እንደቀጠሉ ነው፣ ይሄን ዜና ስናጠናቅር ድረስ ባለን መረጃ መሰረት አንድ ሰው ከሥልጣነ ክህነቱ ሊሻር የሚችለው በምን በምን ምክንያት እንደሆነ ለማየት እንሞክራለን።
ይህንን በተመለከተ ሕገ ቤተክርስቲያን ምን ይላል:

ፍትህ መንፈሳዊ ምን ይላል፣ ሥልጣነ ክህነትን ስለመሻር:
፪፻፳፬ አምስተኛው ክፍል ከሹመቱ የሚሻርበትን ምክንያት የሚናገር ነው። ይህችውም ተጽፋ መኖርዋን ቁጥሯ በአንቀጸ ኤጲስ ቆጶሳት (ፍት. ፭ ፥ ፻፸፪) የተነገረላት ናት። ሁለመናውም ይህ ነው መማለጃ ሰጥቶ ተሾመ ቄስ ሁሉ ይሻር፥ ወይም በማስፈራራት ወይም በማድላት በተንሎል ወይም መማለጃ እሰጣለሁ ብሎ የተሾመ ይሻር ወይም ሁለት ጊዜ የተሾመ ወይም ሁለት ሚስት ያገባ ወይም ወይም ሕዝቡን ከማስተማር ቸል የሚላቸው የማይረዳቸውም ወይም የኃጢአተተኛውን ንስሐ የማይቀበል ወይም በነገር ሠሪነትና ሐሰትን በመመስከር ያታወቀ የሚታበይ፣ ሕግን አውቆ የማይሠራባት ወይም ዘወትር የሚሰክር፣ ክፉ ሥራንም የሚያዘወት፣ በጎ አለመሥራትን የለመደ፣ ከአበደረው ላይ ትርፍን የሚፈልግ ከዘማዊት ሴት ጋር የተኛ፣ ተያዥ የሆናትም ብትሆን እነዚህን የመሳሰሉትን የሠራ ወይም አለቃው ሳይፈቅድለት ወደ ንጉሥ የሚሄድ ወይም ሰዎች ይፈሩት ዘንድ ማንንም የሚማታ፣ ኮከብ በመቁጠር የሚታመን፣ የጠንቋቶችን ነገር ሥር፣ የሚምሱትንም የሚያምን፣ የመናፍቃንን ጥምቀት የተቀበለ፣ ወይም ቁርባናቸውን የተቀበለ ወይም ከእነርሱ ጋር አብሮ የሚጸልይ ቄስ ይሻር።

፪፻፳፭ ከርስዋም በአንቀጸ ካህናት የተነገረ ነው ( ፍ፡ ነ፡ ፫፻፲፮) ከዚህም የተሰበሰበ ይህ ነው፣ ይለይ ወይም ይሻር ዘንድ። ራሱን ጃንደረባ ያደረገ ወይም በዝሙት የተገኘ ወይም ሲሰርቅ የተገኘ ወይም በሐሰት የማለ የጋብቻ ሥራት ሥጋ መብላትና ወይን መጠጣት አይገባም የሚል ወይም በገበያ መካከል የመበላ ከበሸታ ቤት የሚጠጣ፣ ሞቶ የበከተውን ቁርጥራጩን ወይም የአውሬውን ትራፊ የሚበላ ወይም ፈውስ አገኛለሁ ብሎ ወደ መናፍቃን ቤተ ክርስቲያን የሚገባ ወይም የአይሁድን ጾም የሚጾም፣ ከእነርሱም ጋር የሚበላ የበዓላቸውንም እጅ መንሻ የሚቀበል ወይም ወደምኲራባቸው ወይም ወደማያምኑ ሰዎች ቦታ ወይም ሃይማኖትን ወደካዱ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን እጅ መንሻ የሚወስድ ወይም ተወግዞ ከተለየው ጋር የሚናገር፣ ከተለየውም ጋር የሚጸልይ ወይም ያለ ኤጴስቆጶሱ ፈቃድ የሚሄድ ይሻር።
፪፻፳፮ ከእርስዋ በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተነገረው ይህ ነው። ይኽውም ፲ ወገን ነው። ከነርሱ አንዱ ረስጠብ ፫ እግዚአብሔርን  በማገልገል ምክንያት ቄስ ወይም ዲያቆን ከሚስቱ ቢለይ መለየት አይገባውም። በዚህም ምክንያት ሚስቱን ቢፈታት ይሻር ረስጠጅ ፭ እንደዚሁም በምንኲስናና በተባሕትዎ ምክንያት ቢፈታት ይሻር።
፪፻፳፯ ሁለተኛ ረስጠብ ፲፱ ጾክ ፬ በታወቀች ኃጢያቱ በእርግጥ የተሻረ ቄስ ወይም ዲያቆን ቢኖር ከዚህም በኃላ ቀድሞ ሳይሻር በሰሞኑ ወራት ይሠራው የነበረውን የአገልግሎት ሥራ ተደፋፍሮ ቢሠራ ከቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ ይለይ ሥራውንም እያወቀ ከርሱ ጋር አንድ የሆነ ይሻር።
፪፻፳፰ ሦስተኛ ረስጠብ ፳፪ ጾክ ፭ ቄስ ወይም ዲያቆን ኤጴስቆጶሱን ቢንቀው ብቻውንም ቤተ መቅደስ ቢሠራ ኤጴስ ቆጶሱም ሦስት ጊዜ ቢጠራው መልስ ባይሰጠው እርሱ ከማዕርጉ ይሻር ተከታዮቹም ይሻሩ።
፪፻፳፱ አራተኛው ረስጣ ፲፬ ኒቅያ ፲፬ ቄስ ወይም ካህን ወይም መነኲሴ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለው ወደ ቤቱ ይመለስ ዘንድ ይማልዱት እንጂ ሊለመለስም ባይወድ ይለይ። በጉባኤም አይቀላቀል፲
፪፻፴ ፲፫ ቤተ ክርስቲያኑን ትቶ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ሊሄድ ቢወድ በዚያች አገር ውስጥ ያሉትም ሰዎች ቢጠሉት ዳግመኛም ወደ ተወው ቦታ ሊመለስ ቢወድ ከዚህ በኃላ እነዚያ አይቀበሉት በዚህም በዚያም ሹመቱ ይሻር እንጂ፡፡ ለስጠብ ፲፪ ይልቁንም ኤጴስቆጶሱ ወደርሱ መልእክት ቢልክ ወደ ቦታውም ይመለስ ዘንድ ባይሰማ ይሻር።
፪፻፴፩ አምስተኛ ኒቅያ ፳፯ ቀሳውስት ከምእመናን ወገን አምዲምስ እንኳ በቊጣ ወይም ከዚህ ዓለም ሥራ በማናቸውም ሥራ ምክንያት አይከልክሉ። ይህን ያደረገ ከሹመቱ ይሻር፤ ከምእመናንም አምድነት ይለዩት።
፪፻፴፪ ስድስተኛ ኒቅያ ፱ ሥራውን ሳይመረምሩ አንዱ ቅስና ቢሾም ከዚህም በኋላ የሠራት ኃጢያት ብትታወቅ እርሱ ይለይ። በጉባኤውም ቤተ ክርስቲያን አትቀበለው።

፪፻፴፫ ሰባተኛ ቀጠጅ ፱ ኃጢአቱን ባያምን ከዚህም በኃልበሚገባ ገልጠው ከዘለፉት የክህነትን ሥራ ፈጽሞ መሥራት አይገባውም። እርሱ ራሱ ቢያምን ግን ሥጋውንና ደሙን ከመቀበል በቀር በክህነቱ ባገልገል አይገባውም።

፪፻፴፬ ስምንተኛ ኒቅያ ፳፰ ቀሳውስትና ዲያቆናት ወደ ዋስነት አይግቡ። በነገር ሥራ አይመስክሩ ሰውም ለመክሰስ ወደ ንጉሡ አይሂዱ። ሐሜተኞች አይሁኑ ለምእመናንም ክፋትን አይውደዱ። ከእነርሱ ወገን ይህን ያደረገ ከሹመቱ ይሻር በጉባኤም ይለይ።
፪፻፴፭ ዘጠነኛ ኒቅያ ፳፱ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ወገን አንዱስ እንኳ ተደፋፍሮ ከግዳጅዋ (ከደሟ) ያልነጻችን ሴተ ወደ ቤተክርስቲያን ያስገባ፣ በደሟም ወራት ሥጋውንና ደሙን ያቀበላት ቢኖር ከሹመቱ ይሻር። ምንም ከነገሥታት ሴቶች ወገን ብትሆን።

፪፻፴፮ አሥረኛ ኒቅያ ፲፭ ቀሳውስትና ዲያቆናት ከቤተ ክርስቲያናቸው በወጡ ጊዜ ክርስቲያኖች ሊቀበሏቸው አይገባም ወደ ቦታቸው እስኪመለሱ ድረስ የፈቃዳቸውን ምክንያት ሁሉ ይናገሩ ዘንድ ይገባል እንጂ። ባይመለሱ ግን ሊቀበሏቸው አይገባም። ከእነርሱ አንዱ በራሱ ፈቃድ ቤተ ክርስቲያኑን ቢተው ከነርሱ ጋር ባለው ኤጴስቆጶስ ፈቃድ ካልሆነ ስለዚህ ክህነቱ ይሻር።
፪፻፴፯ ክፍል ፮ በማዕረጉ ከአገልግሎት የማይከለከልበትን ይናገራል። በደስ ፰ ቄስ ሚስቱ በወለደች ጊዜ አይከልከል።
፪፻፴፰ ፱ ቦታው ወዳይደለ ቦታ ሄዶ ቢሰነብት የዚያ አገር ካህናትም ቢቀበሉት ኮብሎ የመጣ እንዳይሆን የአገሩን ኤጴስቆጶስ ይጠይቁት። አገሩ ሩቅ ቢሆን ግን አገልጋይ እንደሆነ ይፈተን ከዚህም በኋላ ይቀበሉት። እጥፍ ክብርም ይስጡት።

የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ልብ ያለው ልብ ይበል ብለን እናልፋለን፣

ቸር ወሬ ያሰማን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment