Wednesday, November 30, 2011

ዝምታው እስከመቼ ነው?

ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው

"እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፥ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች። "
ትንቢተ ኢሳያስ ፲፫ ፥ ፲፱

"ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም። "
ትንቢተ ኤርሚያስ ፶ ፥ ፵

"ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፦ "
ትንቢተ አሞጽ ፬ ፥ ፲፩

"ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ "
፪ኛ የጴጥሮስ መልዕክት ፪ ፥ ፮

ወገኖቼ እናስተውል ዛሬ እንዲህ ዓይነት በዓይናችን ላይ የሚሰራው ነገር ከምዕራባዊያን የመጣ ባሕል እና ህይወት ነገ የእያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ አይቀሬ ነው፣ ሰዶማውያንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ትቃወማለች፣ ትጸየፈዋለችም እንዲህ ዓይነቱን በሽታም በህዝባችን የእለት ተዕለት ኑሮውን እንዲያበላሸው ወይንም እንዲበርዘው የማናችንም ምኞት አይደለም ስለሆነም፣ ሕፃን፣ ወጣት፣ አዋቂ፣ ሽማግሌ እና አሮጊት እንዲሁም ክርስቲያን፣ እስላም፣ ወይንም ሃይማኖት የለሹም ቢሆን ይሄንን ኢ - ኢትዮጵያዊ የሆነውን ምግባረ ብልሹነት የምዕራባውያን ቅብጠትን ወይም ሰይጣናዊነት አጥብቀን ልንቃወመው የሚገባ ወቅታዊ ጉዳይ ነው ብለን የዚህ ዝግጅት ክፍል ያምናል፡
መልካም ምንባብ 
"የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም" 

  • ‹‹The African Men for Sexual Health and Rights (AMSHeR)›› ብሎ የሚጠራ የዚህ ቡድን/ድርጅት ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ግብረሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወትና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ 
  • የውይይቱ መሪ ቃል ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነት›  (Claim, Scale-Up and Sustain) በሚል መሪ ቃል ኅዳር 23 ቀን 2004 .ከጧቱ 2 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል ድረስ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሔዳል
  • በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል ነው
  • ግብረሰዶማዊው የኬንያው ተቋም ኢሽታር ካነገበው ዓለማዎች መካከል በግብረሰዶም ዙርያ የአቻ ለአቻ ትምህርት የኬንያን አምሳያ በኢትዮጵያ ማዳረስ እንደሆነ አመልክቷል
  • ስብሰባው 15 አገሮች ላይ በጤናና በግብረሰዶማዊያን መብቶች ዙርያ የተዘጋጁ ተሞክሮዎች ይቀርብበታል
መሰይጠን ወይስ መሰልጠን

(አንድ አድርገን ህዳር 20  2004 ዓ.ም ):በመጪው ቅዳሜ እንደሚጀመር የሚጠበቀው እና ከ10ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ICASA (International Conference on AIDS and Sexuallity Transmitted infection) የተለያዩ ሀገራ መሪዎች ቀዳማይ እመቤቶች ፤ ምሁራን ፤ ለጋሾችና ተማሪዎች 5 ቀን የሚቆይ ጉባኤ ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃ፡፡ መንግስትም ለዚህ ጉባኤ መሳካት ያላሰለሰ ጥረት በሆቴሎች ላይ፤ በመሰብሰቢያ አዳራሾች ፤ በፀጥታ እና ጥበቃ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ በመገናኛ ብዙሀን አማካኝነት አሳውቋል፡፡ ይህ እንዲህ እንዳለ ሆኑ ከ15 ሀገራት የተወጣተጡ 200 የሚጠጉ ግብረሰዶማውያን በጉባኤው ላይ እንደሚገኙ እና ከስብሰባው በፊት በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ‹‹ ግብረሰዶምን እንዴት ህጋዊ ማድረግ እደሚቻል እና በየሀገሩ ያሉትን ጥሩ ተመኮሮዎች ላይ ውይይት በማድረግ በተለያዩ አፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ ፤ በህገመንግስታቸው ውስጥ እንዲያስገቡትና የሰዎችን ዲሞክራሲያዊ መብቶች በዚህም አኳያ እንዲያከብሩ›› በሚል መንፈስ እንደሚወያይ ለማወቅ ችለናል››

አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ በተሰበሰቡበት ወቅት

ይህን የሰሙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፤ የእስልምና ፤ የካቶሊክ እና የመካነ ኢየሱስ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮቻቸውን በመላክ ጉባኤውን ለመቃወም ‹‹ይህ አይነቱ ድርጊት በዕምነትም ሆነ በስነምግባር በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ምግባር ነው›› ለማለት ትላንት 19/03/2004 ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን የጠሩ ሲሆን መግለጫው ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ወደ አዳራሹ በመግባት የእምነት አባቶችን ረዘም ላለ ደቂቃ በዝግ ክፍል ያነጋገሯቸው ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ የተቃውሞ መግለጫው አሁን መሰጠት እንደሌለበት ከስምምነት ላይ እንደደረሱ በተወካያቸው አማካኝነት ማሳወቅ ችለዋል፡፡ ለዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ሊሰጡ የነበረው መግለጫ፤ እንዲሁም ለህዝቡ ሊያቀርቡት የነበረው ጥሪ ከጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ጋር ከመከሩ በኋላ፣ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጸዋል። በዚህ ዙሪያ ላይ የመንግስት አቋም ህዝቡንም ሆነ ተሰብሳቢዎችን ላለማስቀየም ስብሰባው በሰላም ያለ ምንም ተቃውሞ ተጀምሮ እዲያልቅ ነው፡፡

አስተያየት ሰጪዎችም በበኩላቸው «ድርጊቱ መታሰቡ፤ በራሱ፤ አስጸያፊ ነው» ማለታቸው ተደምጧል።የሃይማኖት አባቶች፣ ይህንን ጉዳይ፣ ጸያፍ፤ ከሥነ-ምግብር ውጭና ባህላችንን የሚያቆሽሽ አጀንዳ ነው ብለዋለል፡፡


ዝርዝር መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ ላይ 
በኢትዮጵያ የአራቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በአዲስ አበባ በቅርቡ በሚካሄደው 16ኛው የአይካሳ ጉባዔን አስታክኮ በአገሪቱ ጸያፍ፣ ከሥነ ምግባር ውጭና ባህልን የሚያንቋሽሽ አጀንዳ ለማስፈጸም ተነሣሥቷል ያሉትን የአንድ ቡድን እንቅስቃሴን በመቃወም ትናንት ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ፡፡ የሪፖርተር ፎቶግራፍ ጋዜጠኛ መሪዎቹ መግለጫ ለመስጠት እንደተዘጋጁ ያነሳውም ፎቶግራፎች እንዲጠፉ ተደረገ፡፡
መሪዎቹን በመወከል መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ያስታወቁት ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ቄስ ኢተፋ ጎበና ሲሆኑ፣ የጋዜጠኛው ፎቶ ግራፎች እንዲጠፉ ያደረገውም በሥፍራው የነበረ አንድ የደኅንነት አባል ነው፡፡
መግለጫው የሚሰጥበት ትክክለኛው ቀን መቼ ነው ተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ከጉባዔው በፊትም ሆነ በኋላ ሊሆን ይቻላል፡፡ ከዚህ ውጭ ትክክለኛው ቀን ይህ ነው ብዬ ለመናገር ያስቸግረኛል፤›› ሲሉ ቄስ ኢተፋ መልሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መሪዎች በተወካያቸው አማካይነት መግለጫው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ያስታወቁት፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አጽሃኖም በተገኙበት የዝግ ስብሰባ አድርገው በጉዳዩ ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ 
በኢትዮጵያ የአራቱም ሃይማኖቶች መሪዎች ኅዳር 19 ቀን 2004 .. 4 ሰዓት ሊሰጡ ያቀዱትን መግለጫ ለመዘገብ ይጠባበቁ ለነበሩ ጋዜጠኞች ‹‹ብርቱ ማሳሰቢያ›› በሚል ርእስ ከታደለው ጽሑፍ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ራሱን አፍሪካን ሜን ፎር ሴክሿል ሄልዝ ኤንድ ራይትስ (አምሸር) ‹‹The African Men for Sexual Health and Rights (AMSHeR)›› ብሎ የሚጠራ የዚህ ቡድን/ድርጅት ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ግብረሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወትና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ 
ድርጅቱ 13 አፍሪካ አገሮች መቀመጫቸውን ያደረጉ 15 ግብረሰዶማዊነት እንደ በጎ ምግባር የሚያንጸባርቁ ድርጅቶች ያዋቀሩት የጋራ ድርጅት መሆኑን ጽሑፉ አስረድቷል፡፡ 
አምሸር ከአይካስ ጉባዔ ጋር አስታኮ ‹‹ቅድመ ኮንፈረንስ›› በሚል ርእስ ቅዳሜ ኅዳር 23 ቀን 2004 .. በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል 25 አገሮች ለተውጣጡ 200 ታዳሚዎች ኤምኤስኤም ኤንድ ኤችአይቪ (Men who have sex with men and HIV) በሚል  አጀንዳ ላይ ውይይት ለማካሄድ አቅዷል፡፡
የውይይቱ መሪ ቃል ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነትየሚል መሆኑን ጽሑፉ ጠቁሞ፣ አምሸር በዕለቱ አይካስ ከሚያነሳቸው የውይይት ነጥቦች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው፣ ነገር ግን ግብረሰዶማዊነትና ግብረሰዶማዊ የመሆን መብትን በአዎንታዊ መልኩ የሚያንጸባርቁ የውይይትና የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ለማካሔድ ማቀዱን አስረድቷል፡፡
በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል እንደሆነ በግልጽ ተቀምጦ ሳለና 97 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንደ አጸያፊና ኢሞራላዊ አድርገው የሚቆጥሩት መሆኑ እየታወቀ፣ ይህንን ስብሰባ ለማድረግ አምሸር ማቀዱ በኢትዮጵያ ሕግና ለኢትዮጵያውያን ሞራል ቦታ ያልሰጠ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ኢሞራላዊ ስብሰባ በቅድመ ጉባዔ ስም 16ኛው አይካሳ ጉባዔ በፊት መደረግ በጉባዔው ላይ አሉታዊ አንድምታ እንዲያጎለበት ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ 
አምሸር በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል የሚያካሒደው የቅድመ አይካሳ ስብሰባ የማነቃቂያ ጉባዔ ዋና ዓላማዎች፣ በአፍሪካ የወንድ ለወንድ ግብረሰዶማዊ ግንኙነቶችን እውን የማስደረግ ጉዳይ ለኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት አስተዋጽኦ ስለሚያደርግ ትኩረት እንዲገኝ ማስቻል፣ ግብረሰዶማዊነት ሕጋዊ እንዲሆን ከማስቻል አኳያ አፍሪካዊ ምላሽና ነጸብራቅ ማሳየት፣ ኤችአይቪን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ግብረ ሶዶማዊነትን ሕጋዊ ማድረግ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመለየት ለተግባራዊነቱ አቅጣጫን መቀየስ ነው፡፡
ይህንን ስብሰባ የተሳካ ለማድረግ የዕለቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎችም ሚሼል ሲዲቤ የተባበሩት መንግሥታት የኤችአይቪ ዋና ዳይሬክተር፣ ዶክተር ደብረ ወርቅ ዘውዴ የግሎባል ፈንድ ፀረ የኤችአይቪ፣ ቲቢ፣ የአባለዘር በሽታዎችና ወባ ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር፣ አምባሳደር ኤሪክ ጎስቢ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ አስተባባሪ፣ የተከበሩ ሬኔ አላፒኒ ጋንሱ የቀድሞ የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ሊቀመንበርና የወቅቱ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ወገኖችና ይበልጥ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ መብት አስከባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበርና የአይካሳ ተወካይ ናቸው፡፡
ስብሰባው 15 አገሮች ላይ በጤናና በግብረሰዶማዊያን መብቶች ዙርያ የተዘጋጁ ተሞክሮዎች ይቀርብበታል፡፡ በዕለቱ ከተለያዩ 25 አገሮች የተውጣጡ 200 ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የተገመተ ሲሆን፣ ይህ ስብሰባ ለግብረሰዶማውያኑ  አዲስ ትስስር ለመፍጠርና ለመቀናጀት፣ ልምድን ለማዳበር ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋትና ለሚቀጥለው ትውልድ ይህንኑ ዘይቤ ለማስተላለፍ ለየት ያለ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ይታመንበታል፡፡
አቶ ሚኪያስ ሲሳይ የአይካሳ የኮሙዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ ተጠይቀው፣ ጽሑፉ እንዳልደረሳቸውና ምንም እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡ 16ኛው የአይካሳ ጉባዔ ላይም እንዲህ ዓይነት ቡድን ወይም ድርጅት ስለመሳተፉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው የሚካሔድበት ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ሥራ አስኪያጅ / ሮማን ታፈሰወርቅ፣ ‹‹ቅዳሜ የሚካሔድ ስብሰባ የለም፤ ውሸት ነው፤ የወሬው ምንጭ ከየት እንደመጣ አናውቅም፣ በእኛ ስም መጥፎ ወሬ እየተወራብን ነው፤ብለዋል፡፡ 
ሥራ አስኪያጇ ‹‹ዝም ብሎ ወሬ ነው›› ብለው ቢያስተባብሉም፣ አምሸር በድረ ገጹ ‹‹ቅድመ አይካሳ ኮንፈረንስ›› የሚካሔደው ስብሰባ ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነት›› (Claim, Scale-Up and Sustain) በሚል መሪ ቃል ኅዳር 23 ቀን 2004 .. ከጧቱ 2 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል ድረስ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሔዳል ብሏል፡፡ 
በተያያዘ ዜና መንበሩን በኬንያ ያደረገው ግብረሰዶማዊው ተቋም ኢሽታር ኤምኤስ ኤም፣ ለኢንጄንደር ሔልዝ ስታፍ እና ሬንቦ ኢትዮጵያ ከመስከረም 14 ቀን እስከ መስከረም 20 ቀን 2004 .. ድረስ ስለግብረሰዶም የምክክርና ጥናት መድረክ ማከናወኑ፣ በተለይም በመደገፍና በማስተባበር ሚናውን መወጣቱን የአምሸር ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ መሠረቱን በኢትዮጵያ ያደረገው ሬንቦ ኢትዮጵያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የግብረሰዶም አራማጅ ወጣቶች፣ ወንድ አዳሪዎችና ሌሎችም መካከል ኤችአይቪ ኤድስና የአባላዘር በሽታን ለመቀነስ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡
ግብረሰዶማዊው የኬንያው ተቋም ኢሽታር ካነገበው ዓለማዎች መካከል በግብረሰዶም ዙርያ የአቻ ለአቻ ትምህርት የኬንያን አምሳያ በኢትዮጵያ ማዳረስ እንደሆነ ኅዳር 5 ቀን 2004 .. ‹‹Ishtar MSM Hosts Engender health and Rainbow Ethiopia›› በሚል ርእስ የተሰራጨው ዘገባ አመልክቷል፡፡
በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ (1996) ክፍል ሁለት ‹‹ለተፈጥሮ ባሕርይ ተቃራኒ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች›› በሚል ርእስ በአንቀጽ 629 ግብረሰዶም እና ለንጽህና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች በሚል ርእስ፣ ‹‹ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ካለው ከሌላ ሰው ጋር ግብረሰዶም ወይም ለንጽህና ክብር ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነውን ሌላ ድርጊት የፈጸመ ማንኛውም ሰው ከቀላል እስራት እስከ ከባድ ወንጀል ቅጣት እንደሚጠብቀው ይደነግጋል፡፡ 
በአንቀጽ 631 ደግሞ ‹‹ለአካለ መጠን ባልደረሱ ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የግብረሰዶም ጥቃትና ለክብረ ንጽህና ተቃራኒ የሆነ ሌላ ድርጊት›› በሚል ርእስ፣ ንኡስ አንቀጽ 1. ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ባለውና ለአካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመ እንደሆነ፤ የተበዳዩ ዕድሜ አሥራ ሦስት ዓመት ሆኖ አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ሲሆን፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡ የተበዳዩ ዕድሜ ከአሥራ ሦስት ዓመት በታች ሲሆን፣ ከአሥራ አምስት ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ በተጨማሪም አንዲት ሴት ለአካለ መጠን ባልደረሰች ልጅ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመች እንደሆነ፣ ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ትቀጣለች በማለት ደንግጓል፡፡  
ድምፃችን ለምን ፌስ ቡክ ላይ ብቻ ሆነ ? 
ዛሬ አይሆንም ብለን መቃወም ሲያቅተን ነገ ለሚከሰተው ግብረ ሶዶማዊነት ተግባር ተባባሪ መሆናችንን አንዘንጋ ፤ ለምን ? ዛሬ አልተቃወምንምና
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

1 comment:

  1. እባካችሁ፡ይህን፡አጸያፊ፡ፎቶ፡ከተቃውሞ፡ምልክቱ፡በታች፡ያለውን፡አንሱት፡፡

    ReplyDelete