"ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።" መዝ ፻፴፮ ፥ ፩ "የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሯት፤ ስለበደል መባእ ካሳ አድርጋችሁ ያቀረባችሁትን የወርቁንም ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቷ አጠገብ አኑሯት፤ ትሄድም ዘንድ ስደዱአት።"
፩ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፩
የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ጣዒሟንና ፍቅሯን በልባችን ጽላት ያሳድርብን ከበዓሉ ረድሄት በረከት ያካፍለን። አሜን!!!
፩፦ «ሰው እናታችን ጽዮን ይላል»
«እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፥ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ ወውእቱ ልዑል ሣረራ። ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጧም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።» ይላል። መዝ ፹፮፥፭። ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን እናት ብሏታል። እናት፦ ወላጅ፥ መገኛ፥የአባት ሁለተኛ ናት። እግዚአብሔር በአሠርቱ ትእዛዛት፦ «አክብር አባከ ወእመከ፤ ከመ ይኩንከ ጽድቀ፥ ወይኑኅ መዋዕሊከ በውስተ ምድር ዘይሁበከ እግዚአብሔር አምላክከ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ (ቸርነቱ ረድኤቱ ይደረግልህ ዘንድ) ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚስጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም፤ » እንዳለ፦ እናት ከአባት እኲል ክብር ይገባታል። ዘጸ ፳ ፥፲፪። ጽዮን ማለት ደግሞ አምባ መጠጊያ ማለት ነው።

፩፥፩፦ የጽዮን ተራራ፤
ጽዮን ኢየሩሳሌም ከተሠራችባቸው ተራራዎች አንዷ ናት። በመጀመሪያ ኢያቡሳውያን መሸገውባት ይኖሩ ነበር። እነዚህም ከከነዓን የተገኙ ወገኖች ናቸው። ከነዓን የካም ልጅ ፥የኖኅ የልጅ ልጅ ነው። ዘፍ ፲፥፮ ንጉሣቸውን የገደለው ኢያሱ ወልደ ነዌ ነበር። ኢያ ፲፥፳፫። ነገር ግን፥ ንጉሥ ዳዊት፦ እስኪያስለቅቃቸው ድረስ ጽዮን የተባለች አምባቸው በእጃቸው ነበረች። ኢያ ፲፭፥፷፫። በጽዮን ላይ ኢያቡስ የሚባል አምባም ነበራቸው። መሳ ፲፱፥፲።
ንጉሥ ዳዊት በኬብሮን ለሰባት ዓመታት ከነገሠ በኋላ ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። እነርሱም ዳዊት ወደዚህ ሊገባ አይችልም ብለው አስበው ነበር። ነገር ግን፥ ዳዊት፦ አምባይቱን ጽዮንን ይዞ በዚያ ተቀመጠ። የዳዊት ከተማ ብሎ የሰየማትን ይህቺን አምባም ዙሪያዋን፦ ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ በግንብ አጠራት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለነበረ እየበረታ ሄደ። ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገ አወቀ። ፪ኛ ሳሙ ፭፥፩-፲፪።
ጽዮን የሚለው ስም በኋላ ላይ ለሞሪያ ተራራ ተሰጥቷል። ይኸውም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በዚያ ስለተሠራ ነው። ሞሪያ፦ አብርሃም ይስሐቅን ለመሠዋት የሄደበት ተራራ ነው። በዚያ መሠዊያ ሠርቶ ልጁን ለእግዚአብሔር አቅርቧል። እግዚአብሔር ከላይ ከሰማይ ጠርቶ፦ «እምነትህ ታይቷልና፥ በብላቴናው ላይ እጅህን አንዳትዘረጋ፤» ባይለው ኖሮ፥ ስለቱን በአንገቱ ላይ አሳርፎ ነበር። ሊቃውንቱ በኅሊናው ሠውቶታል፦ ይላሉ። በመጨረሻም እግዚአብሔር ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ የተያዘ ነጭ በግ አሳይቶት ስለ ይስሐቅ ፈንታ ሰውቶታል። ዘፍ ፳፪፥፩። ይህም...

፩፡፪፦ ታቦተ ጽዮን፤
የነቢያት አለቃ ሙሴ፦ እግዚአብሔር፦ «አስቀድመህ እንዳየሃቸው ዓይነት አድርገህ ጽላት አዘጋጅ፥ ቃሎቹን እኔ እቀርጽባቸዋለሁ።» ባለው መሠረት ሁለት ጽላት አዘጋጅቷል። ያንንም ይዞ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ጾሟል። እንጀራ አልበላም ውኃም አልጠጣም። በጽላቱም ላይ አሥሩን የኪዳን ቃሎች እግዚአብሔር ፈቅዶለት ቀረጸ። ጽላቱንም ይዞ ከደብረ ሲና በወረደ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ጋር ተናጋግሮ ነበርና ፊቱ አንጸባረቀ። ዘጸ ፴፬፥፩፥፳፱። ከዚያ በፊት ለጽላቱ ማኖሪያ ታቦት እንዲያዘጋጅ እግዚአብሔር ነግሮት ነበር። ታቦቱም በውስጥም በአፍአም በወርቅ ተለብጦ ነበር። መክደኛውም በወርቅ የተሠራ ነበር። በላዩም ሁለት የኪሩቤል ሥዕል ተቀርጾ በወርቅ ተለብጦ ነበር። እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት ስለ ታቦቱ ክብር በታቦቱ ዙሪያ የወርቅ አክሊል አድርጐለት ነበር። በመጨረሻም፦ «በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እናገርሃለሁ። » ሲል እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሰጥቶታል። ዘጸ ፳፭፥፩-፳፪
የነቢያት አለቃ ሙሴ ታቦቱን ወደ ማደሪያው ካስገባ በኋላ በመጋረጃ ሸፍኖታል። በእግዚአብሔር ማደሪያ፥ በመገናኛው ድንኳን ሊሠራው የሚገባውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ደመናው የመገናኛውን ድንኳን ከደነው። የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ሞላው። ደመናው በላዩ ስለነበረ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ስለሞላው ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም ነበር። ዘጸ ፵፥፳-፴፰

፩፥፫ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን፤
ቤተ ክርስቲያንም ጽዮን ትባላለች። ደብረ ጽዮን የሚሠዋበት መሥዋዕተ ኦሪት ነበር። በደብረ ጽዮን ዘሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ግን የሚሠዋው መሥዋዕተ ሐዲስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። « በጽዮን መለከት ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራ ላይ ዓዋጅ ንገሩ፤» እንደተባለ፦ ሐዲስ ሕግ ወንጌል ይታወጅባታል። ኢዩ ፪፥፩። በተጨማሪም፦ «በጽዮን መለከትን ንፉ፤ ጾምንም ቀድሱ፤ ምሕላንም ዓውጁ፤» የሚል አለ። ኢዩ ፪ ፥፲፭። በመሆኑም ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት ይታወጅባታል። ጸሎተ ምሕላ ይያዝባታል። ጡት ከሚጠ ቡት ሕፃናት ጀምሮ እስከ ሽማግሌዎቹ ድረስ ሕዝቡን ሰብስቡ፤ እንደተባለ፦ ሁሉም ለቅዳሴ፥ለማኅሌት፥ ለሰዓታት ፥ ለመዝሙር ይሰ በሰቡባታል። ሕፃናት በአርባ በሰማኒያ ቀን እየተጠመቁ አባል ይሆኑባታል። ጌታችን በወንጌል፦ «ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤» ያለው ለዚህ ነው። ማቴ ፲፱ ፥፲፬። ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስም፦ ሕፃናቱን ፥ ወጣቶቹን እና አ ረጋውያኑን፦ በግልገሎች ፥ በጠቦቶችና በበጎች መስሎ ጠብቃቸው ብሎታል። ዮሐ ፳፩፥፲፭።

፩፥፬፦ ጽዮን ማርያም ፤
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ጽዮን» ተብላ ትጠራለች። ምክንያቱም ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ እመቤታችንም፦ ለነፍስና ለሥጋ ፥ለኃጥአንና ለጻድቃን፥ አምባ መጠጊያ ናትና። ቅዱስ ዳዊት፦ «እስመ ኀረያ እግዚ አብሔር ለጽዮን ፥ ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ ፥ ዛቲ ይእቲ ምእራፍየ ለዓለም፤ ዝየ አኅደር እስመ ኅረይክዋ። እግዚአብሔር ጽዮን መርጧታልና ፥ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና ፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።» ያለው እመቤታችንን ነው። መዝ ፩፻፴፮ ፥ ፲፫። ምክንያቱም ፦ ለእናትነት መርጦ ያደረው በእርሷ ማኅፀን ነውና። «ለ ዘላለም መረፊያዬ ናት፤» ማለቱም፦ እርሱ የዘለዓለም አምላክ እንደሆነ ፥ እርሷም ለዘለዓለም ወላዲተ አምላክ ተብላ እንደምትኖር የሚያመለክት ነው። በሌላ ምዕራፍም፦ « ደብረ ጽዮን ዘአፍቀረ ፥ ሐነፀ መቅደሶ በአርያም ፥ወሳረረ ውስተ ምድር ዘለዓለም። የወደ ደውን የጽዮንን ተራራ ፥ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ። ለዘለዓለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።» ብሏል። መዝ ፸፯፥፷፰።
ጽርሐ አርያም ከሰባቱ ሰማያት አንዱ ነው። በዚያ፦ ኪሩቤል የሚሸክሙት ፥ ሱራፌል የሚያጥኑት የእግዚአብሔር የእሳት ዙፋን አለ። ዙፋኑም በሰባት የእሳት መጋረጃዎች የተጋረደ ነው። ኢሳ ፮፥፩ ፣፪ኛ ሳሙ ፬፥፬ ፣ ሕዝ ፩፥፭-፲፰ ፣ ራእ ፬፥፮-፱። ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ፦ እመቤታችንን፦ «በሰማይ ባለ ጽርሐ አርያም ፈንታ በምድር ላይ አርያምን ሆንሽ፤» ብሏታል። ከ ዚህም፦ ቅዱስ ዳዊት «የወደደውን የጽዮንን ተራራ፥ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፤» ያለው ለእመቤታችን እንደሆነ እንረዳለን።
ድንግልናዋን በተመለከተም፦ «ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፥ ወሰብሒዮ ለአምላ...

፩፥፭፦ ጽዮን መንግሥተ ሰማያት፤
የምእመናን ሁሉ ተስፋ መንግሥተ ሰማያትም ጽዮን ተብላለች። ይኽንን በተመለከተ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «እናንተ ግን የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰማያት ወዳለችው ኢየሩሳሌም ፥ ደስ ብሏቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክት ደርሳችኋል። ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኲርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር ፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃን ነፍሳት ፥ የአዲስ ኪዳንም መካከለኛ ወደ ሚሆን ኢየሱስ ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋል። » ብሏል። ዕብ ፲፪፥፳፪-፳፬። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደግሞ፦ በራእይ መጽሐፉ ላይ ፦«እነሆ ፥ በጉን (ኢየሱስ ክርስቶስን) በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ አየሁ፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም የመንፈስ ቅዱስም ስም በግንባራቸው የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ። እንደ ብዙ ውኃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ ፥ ደርዳሪዎችም እንደሚደረድሩት በገና ድምፅ ያለውን ሰማሁ። በዙፋኑም ፊት በአራቱ እንስሶችና (በኪሩቤልና) በአለቆቹ ፊት (በሱራፌል ፊት) አዲስ ምስጋናን አመሰገኑ። ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ በቀር ፦ (ሄሮድስ ካስፈጃቸው ሰማዕታተ ሕፃ ናት በቀር) ያን ምስጋና ሊያውቅ ለማንም አልተቻለውም። ከሴቶችም ያልረከሱ እነዚህ ናቸው ፤ ደናግል ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበ ት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው፤ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኲራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው። በአንደበታቸውም ሐሰት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውምና፤ » ብሏል። ራእ ፲፬፥፩-፭። እግዚአብሔር በቅዱስ ዳዊት አንደበት፦ «እኔ ግን በእነርሱ ላይ ንጉሥ ሆኜ ተሾምሁ ፥ በተቀደሰ ተራራው በጽ...

by: Tsegazeab Syoume
ከጸጋዬ ስዩም የፌስ ቡክ የተገኘ፡
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
ትክክለኛ ምንጩ ቤተ ደጀኔ ነው።
ReplyDelete