ይህንን ጽሁፍ እንድናዘጋጅ ያስገደደን አንድ አንባቢያችን ያደረሱን መልዕክት ነው፣ መልዕክቱም አባ ፋኑኤል እንደተለመደው የመከፋፈል ሥራቸውን በዋሽንግተን ዲሲ እና ካሊፎርኒያ ግዛት ጀምረዋል። በቅርቡ የደረሰን ደብዳቤ እንደሚያመለክተው አባ ፋኑኤል እኔ በሕጋዊ መልኩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወክዬ የመጣሁ ወኪል ነኝ ካሉ በኃላ፣ በመቀጠል በተለያዩ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ለሚገኙ ይልቁንም በገለልተኛ አስተዳደር ስር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ ልከዋል፥ ደብዳቤው እንደሚያብራራው እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን (ደብር) ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንደተከበረ ሆኖ ሃይማኖት እንዳይበረዝና ቀኖና ቤተክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅ እንድንመካከር አብረን ተነጋግረን ልንሰራ የምንችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሚል ይጀምራል። በመቀጠል የደብራችሁ አስተዳዳሪዎች፣ የቦርድ ተወካዮች፣ እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን ይላል። ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ
እረ ለመሆኑ አባ ፋኑኤል ሥርዓት ለማስጠበቅ እና ቀኖና እንዳይፋለስ ብለው የሚሉት የትኛውን ሥርዓት ነው የሚሉት? ቀኖናውንስ ቢሆን ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ አይደለም እንዴ ሥራቸውን እየሠሩ ያሉት እስቲ እነዚህን ነጥቦች እናንሳና እንየው፡
፩/ በመጀመሪያ የየደብራችሁ መተዳደሪያ ደንብ እንደተከበረ ብሎ የማቀራረብ ነገር ካለ ይሄ በርሳቸው መዝገብ ካልሆነ በስተቀር ቤተ ክርስቲያን መመሪያዋም መተዳደሪያዋም ቃለ ዓዋዲዋ ነው ይሄንን ደግሞ ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባቸዋል።
፪/ በደብዳቤያቸው ላይ እንደገለጹት "በመራራቅ ሳይሆን በመቀራረብ፣ በቅያሜ ሳይ በይቅርታ በጋራ እንሠራ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ" እንዳሉት ጥሪውን ለነማን ይሆን ያቀረቡት በዕውነት ጥሪውን ለሁሉም አድባራት እና አጥቢያ አድርሰው ይሆን? እስከ አሁን ባለን መረጃ መሰረት ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት እራሳቸውም በገለልተኛ አስተዳደር ሥር ነን ለሚሉ አጥቢያዎች ብቻ ነው። ነገር ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የተመሠረተው የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ 17 የሚጠጉ አጥቢያዎች ምንም አይነት መጥሪያ እንዳልደረሳቸው ተረድተናል። ታዲያ አባ ፋኑኤል አላማቸው ምን ይሆን ገና በፊት እናት ቤተ ክርስቲያንን ብለው በሀገረ ስብከቱ ስር በቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ ያሉትን አጥቢያዎች ወደ ጎን ትቶ በገለልተኛ አስተዳር ስር ነን ብለው እራሳቸውን በሰየሙ እና ከቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር ውጪ የሆኑትን አድባራት ብቻ ኑና ልባርካችሁ ወይም አባት ልሁናችሁ ማለት ትክክለኛ አካሄድ ነውን? መልሱን ለአንባቢያን እንተወው።
፫/ ከዚህ በፊት ባስነበብነው "አባ ፋኑኤልና ጉዞዋቸው" በሚለው ላይ ለማሳየት እንደሞከርነው ገና ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመግባታቸው እራሴ የሰራሁት ቤቴ ነው ማንም ሊከለክለኝ አይችልም በሚል ፈሊጥ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እንደ ግል ንብረት ማየታቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ መንበረ ጵጵስናዬ በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ነው ማለታቸው ትንሽ ግራ የሚያጋባ ነው። አባ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናቸውን በደብረ ምሕረት ማድረጋቸው ባልከፋ ነበር፣ ችግሩ ግን ደብሩ ከምሥረታው ጀምሮ እራሱን በገለልተኛ አስተዳደር ስር ነኝ ከሚሉት አጥቢያዎች አንደኛውና ግንባር ቀደሙ እንደሆነ ይታወቃል እንደውም የገለልተኛ ዋናው መሥራቹና አቋቋሚው እርሳቸው መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ስለሆነ ወደ እዛኛው ርዕሰ ጉዳይ አንገባም፥ ታዲያ ይህንን አጥቢያ ይልቁንም የግሌ ነው የሚሉትን በገለልተኛ አስተዳደር ውስጥ አስቀምጦ እኔን ግን ቅዱስ ሲኖዶስ የላከኝ ሕጋዊ ወኪል ስለሆንኩ መንበረ ጵጵስናዬ በገለልተኛ አስተዳደር ውስጥ ባለው ደብረ ምሕረት ነው ማለት የት ድረስ ሊያስኬድ እንደሚችል አባ ፋኑኤል የሚያውቁት ጉዳይ ይመስለናል።
፬/ እስከ አሁን ባለን መረጃ መሠረት በቅዱስ ሲኖዶስ ተልከው የመጡት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሥራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ምሥራቅ ሐረርጌ ከሚሄዱት ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አለማድረጋቸውስ? እንደ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑማ መጪው ሊቀ ጳጳስ፣ እንደመጣ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር ተገናኝቶ ጅምር ሥራዎችን፣ እቅዶችን፣ ችግሮችን እና በመሳሰሉት ላይ ንግግር ካደረገ በኃላ ሌላ ሰው እማኝ ተደርጎ የጽ/ቤት እቃዎች እና ንብረቶች ዝውውር ይደረጋል ነገር ግን እንዲህ አይነት ሕጋዊ ሥራዎችን አባ ፋኑኤል የማይገልጉት ወይም ሥርዓትን ከሚያፈርሱ ወገን መሆናቸውን በግልጽ ያሳየ እንደሆነ እንገነዘባለን።
፭/ በጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ያለው "የውጪ ግንኙነት ክፍል" በመባል በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ትዕዛዝ የተከፈተው በአስቸኳይ ሥራውን እንዲያቆም እና ከሕገ ቤተክርስቲያን አንጻር
ኢ-ቀኖናዊ እንደሆነና እንዲዘጋ ቢወስኑም አባ ፋኑኤል ግን በተለመደው ማን አለብኝነታው አሁንም ከጽ/ቤቱ ጋር በቅርብ እየሰሩ እነደሆነ ጠቋሚ መረጃዎች ደርሰውናል።
እንደ እስሳቸው አባባል ሥርዓት ልናስጠብቅ ቢሉም ነገር ግን ሥርዓት እያፈረሱ ያለበትን አካሄድ አጥብቀን እንቃወማለን፣ ቤተ ክርስቲያን መገለጫዋ ሥርዓቷ፣ ቀኖናዋ፣ እና ትውፊቷ ናቸው ነገር ግን እነዚህን የቤተክርስቲያን መገለጫዎች የምንላቸውን ወደጎን እየፉ ሥርዓት ልናስከብር ነው ቢሉን እራስን እንደማታለል ስለሚሆን እንተወዋለን።
ከላይ እንደተመለከትነው አባ ፋኑኤል ጉዞአቸውን በከፋፍለህ ግዛው አካሄድ ጀምረዋል፣ በአዋሳ ሲያደርጉ እንደነበረው አሁንም በካሊፎርኒያ እና በዋሽንግተን ያሉትን ምዕመናን እናንተ ከኛ ወገን አይደላችሁ በማለት ሥራቸውን ጀምረዋል ነገር ግን መጨረሻቸውን ደግሞ የቤተክርስቲያን አንድነት ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደሚሆን ከወዲሁ ለማየት ይቻላል። ምክንያታቸውም አንድ እና አንድ ነው የቤተክርስቲያንን ሥርዓት እና ቀኖና ማፍረስ እና የራሳቸው መጠቀሚያ፣ በክበሪያ እና በመበልጸጊያ ለማድረግ የተነሱ ለመሆናቸው እነዚህ ከላይ የገለጽናቸው ነጥቦች በቂ ማስረጃ ይሆናሉ ብለን እናምናለን።
ቸር ይግጠመን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
aba fanuel is always trying to destroy the way of EOTC. That's why he went to Ethiopia and to become a bishop. Then no one stand infornt of him, specially America not even a church leaders would stop him from what he wants to do. He is one of Ethiopian Orthodox church thorn in our generation. He has been doing all kind of bad things in the past while he was in Hawassa, then he was throuwn out from there and went to the theology school (collage) no one accept him, now he is here after he bribe Aba Paulos to send him here so that he can do what ever out of the ordinary.
ReplyDeletePlease before he does so much damage and bleeding to our church we have to stop him from doing so.
Please help us God
hi, go and get a video please ?
ReplyDeleteit is more powerful than words that you wrote here
ጎበዝ ሰውየው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት እና ትውፊት ሊያስጠብቁ ቀርቶ አሁን አንማ ጭራሽ ቅዱስ ሲኖዶስ በሕግ ከሻረው ጋር "የውጪ ግንኙነት ጽ/ቤት"ጋር ተገናኝተው በቅርብ እየሠሩ ይገኛሉ ምናልባት ካላወቃችሁ ብዬ ነው፣ የውጪ ግንኙነት ተብሎ የነበረው ጎረምሳ አሁን ከሳቸው እግር ሥር አይጠፋም ለምን እንደሆነ አይታወቅም፣ በአለቅነት ተቀብለውት ይሁን ወይም ከበታቻቸው አርገው ባይታወቅም አሁን ግን አብረው እየሰሩ እንደሆነ በደንብ አይተናል እነደውም ማንኛውም ደብዳቤ እንኳን የሚጽፍላቸው እርሱ ነው እሳቸውማ ኮምፒተርም ነክተው የሚያቁ አይመስለኝም ባይሆን ሲንጀር ሊሆን ይችላል እንጂ
ReplyDeleteተመልከቱት ብቻ