Wednesday, December 14, 2011

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪ ትዘረጋለች

በዚህ እኛ በተፈጠርንበት ዘመን በጣም ለጆሮ የሚቀፉ፣ ለማየት የሚያስደነግጡ፣ የሰሚን ጆሮ ጭው የሚያደርጉ ብዙ ክስተቶች ተከስተዋል እየተከሰቱም ነው። በተለይ በእኛ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ይልቁንም ባለፉት ፳ ዓመታት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የተለያዩ አስደንጋጭ ክስተቶች ተከስተዋል፣ የብዙ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት አስደፍቷል፣ ለብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን መሰደደ እና ሕልፈት እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው ብለን እናምናለን። ለምን በዘመነ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን በቤተክርስቲያን ላይ ይህ ሁሉ ፈተና በዛባት? ፈተነውስ ከየት የመጣ ፈተና ነው? እንደሚታወቀው በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን ብዙ ክፍተቶች፣ ግድፈቶች፣ ቀኖና ጥሰቶች፣ ግድያዎች፣ አፈናዎች፣ ስም ማጥፋቶች፣ እንዲሁም ብዙ መጠነ ሰፊ ዘረፋዎች እና ሙስናዎች ተፈጽመዋል እነዚህ ሁሉ ግፎች እና በደሎች ሲፈጽሙ ማንም የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ወይም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጭምር "ይደልዎ" ከማለት በስተቀር ምንም ዓይነት ተቃውሞ ያቀረቡም ሆነ የተለያዩ አቤቱታዎችን ለሚመለከተው የቤተክርስቲያን አካል ከዚያም ባሻገረ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ ያቀረቡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሉ ብሎ ለመናገር አያስደፍርም።


በዚህ ዓመት የተለያዩ የፓብሊክ ሚዲያዎችን ስንከታተል የተለያዩ ዜናዎችን ተመልክተን ብዙ ግር የሚያሰኙ ነገሮችን ተመልክተን እንዴት ሊሆን ይችላል በማለት ብዙ ጥያቄዎችን ፈጥሮብናል ከነዚህም መካከል የአክሱም ጺዮን ማርያም ጽላት፣ ዓለም ካሏት ዕፁብ ድንቅ ከሚባሉት የሃይማኖት ምስክሮች እና ጥንታዊ ከሚባሉት የተቀደሱ (artifect) የመጀመሪያው ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም። የአክሱም ጺዮን ጽላታን የኢትዮጵያውያን ብቸኛ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ቃል ኪዳን እንደሆነ ዓለም እራሱ ምስክር ነው፥ ለዚህም ነው የተለያዩ አሳሾች እና ተመራመሪ ነን በማለት በተለያየ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ወረራዎችን፣ ዝርፊያዎችን፣ እንዲሁም የታሪክ የመበዝ ሥራዎችን ሲሰሩ መኖራቸው ለማንም ግልጽ ነው። በአሁኑ ጊዜ የተነሱት የውስጥ ጠላቶች ደግሞ ታሪካችንን ለሰው ሀገር ለማፍያ በመሸጥ እና የግል ሀብታቸውን በማደረጀት ላይ የተሰለፉ ናቸው፤ እነዚህ ግለሰቦች ለቤተክርስቲያን ባላቸው ቀረቤታ እና በሀገሪቱ የከፍተኛ ሥልጣን ስለተቀመጡ ሥልጣናቸውን እና ሹመታቸውን በመጠቀም ታሪክን እያዛቡ እንዲሁም ከጥንት ጠላቶቻችን ጋር በመተባበር ሀገራችንን በመመዝበር እና በመዝረፍ ሙያ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ለዚህም ደግሞ ሰሞኑ የወጡ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ምስክሮች ናቸው እስቲ አንዱን እንመልከት

እንግዲህ ወገኔ ንቃ ሀብት ንብረትህን ጠብቅ እንዲሁም ቤተክርስቲያንን ጠብቅ ብለን ለእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ልብ ልንለው የሚገባ ነብ ውለን እናምናለን።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ በቅርብ የወጣ ዜናም ስላለ ከዚህ ጋር አንባቢያን ይመልከቱን ብለን አቅርበነዋል ልብ ያለው ልብ ይበል እንላለን።
መልካም እይታ እንመኛለን
ቸር ይግጠመን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment