የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን ባለፈው ስለ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ያቀረብነው ዘገባ መሠረት አቡነ ፋኑኤል በዲሲ ደብረ ምሕረት ተገኝተው ይህ ደክሜ የሰራሁት ቤቴ ነው ከዚህ ማንም ውጣ ሊለኝ አይችልም "ደርግ እንኳን ሁለት ያለውን ነው የሚነጥቀው፣ እኔ ግን ያለኝ አንድ ቤቴን ነጥቃችሁ የት ልሂድ" ብለው አስገርመውናል፣ አሁንም ከፋፋይ ሥራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ በፍትሕ መንፈሣዊ ላይ እንደተገለጸው ቤተክርስቲያንን በደሙ የመሠረታት ክርስቶስ እንጂ አባ ፋኑኤል እንደሚሉት እርሳቸው አልሰሩትም። አሁንም ይህንን ሥርዓት አልበኝነታቸውን በመቀጠል በአካባቢው ከሚገኙት እራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የሚኖሩትን የቦርድ እና የካህናት ስብሰባ ጠርተው በቦታው ግምቱ ከ15 ሰው የማይበልጥ ተገኝቶ በጥያቄ ሲያወዛግባቸው ታይተዋል የውሽታቸው ብዛት ደግሞ ከአንድ የስብሰባው ተከታይ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር ጥያቄውም እንደሚከተለው ነው።
እዚህ አካባቢ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሥም የተቋቋመ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚባል ተቋቋሞ ነበር እና ድጋሚ ለማቋቋም ለምን አስፈለገ? ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልሳቸው: እኔ እስከማውቀው ድረስ ከወሬ ውጪ የሰማሁት ነገር የለም የተሰራም ወይም የታየ ምንም የማውቀው ነገር የለም ብለው ነበር የሸመጠጡት በጣም የሚያስገርም ነው። ለመቋቋሙም የመጀመሪያው የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው መጥተው ነበር እርሱንም እራሳቸው በዚህ ቪዲዮ ላይ ተናግረውታል።
ሌላው ከስብሰባው ተሳታፊዎች የቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ እንደሚከተለው ነው
በዚህ አካባቢ የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት አለ ሲባል ሰምተናል ግዢውም ከሦስት ዓመት በፊት መገዛቱንም ይታወቃል ስለዚህ ለምን ሌላ ለመግዛት ወይም ለመመስረት አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልስ: ለሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ ጽፈናል ነገር ግን መልስ አላገኘንም ብለው በሚያሳፍር ሁኔታ "በአንድ ራስ ሁለት ምላስ" እንደሚባለው ሆነው ነበር ነበር ያሳለፉት።
በአጠቃላይ ፍርዱን ለአንባቢያን እንተወዋለን።
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

ቸር ይግጠመን
ከሁሉ በፊት ይህን አስተያየት ስሰጥ ከድፍረት እንዳይቆጠርብኝ እጠይቃለሁ:: እንደማንኛውም በአሜሪካ እንደሚኖር የኢ/ኦ/ተ/ቤ ምዕመን የአቅሜን ያህል አስተዋጽዖ ለማድረግ ብዙ ሙከራ አድርጌአለሁ:: ከአስራ አምስት አመታት በኋላ የደረስኩበት ውሳኔ ግን ይህ ተቋም አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደኋላ የሚጓዝ እንደ ካሮት ወደታች እንጂ ወደላይ ለማደግ የማይችል የራሱን ማለትም የሲኖዶሱን ውሳኔ እንኳ ተግባራዊ ማድረግ ያልቻለ ድርጅት ስለሆነ ወርቃማ ጊዜያችንን ልናጠፋበት የማይገባ መሆኑንን ነው:: ከላይ ፓትርያርክ ከተባሉት ጀምሮ ዘወትር ሸፍጥና ሐሰት የተሞላበት ተግባር ከመፈጸም የማይመለሱ ስለሆነ የአባ ፋኑኤል ተግባር ሊያስደንቀን አይገባም:: ክርስትናው ውስጣቸው የሌለውን ከየት ያምጡት ብለን እንጠይቃቸዋልን:: ያገራችን ሰው እኮ ሲተርት ያልዘሩት አይበቅልም ይላል::
ReplyDeleteበኢትይጵያ ኦርቶዶክስ ስም የሚጠራ ሁሉ ቤቴ ነው ካሉ እኚህ ሰው ነገ በኢትዮጵያ ስም ወደሚጠራው የአሜሪካኑ ሲኖዶስ የማይሄዱበት ምክንያት የለም ብለው ያሰባሉ?
ReplyDeleteከሁሉ በፊት ይህን አስተያየት ስሰጥ ከድፍረት እንዳይቆጠርብኝ እጠይቃለሁ:: እንደማንኛውም በአሜሪካ እንደሚኖር የኢ/ኦ/ተ/ቤ ምዕመን የአቅሜን ያህል አስተዋጽዖ ለማድረግ ብዙ ሙከራ አድርጌአለሁ:: ከአስራ አምስት አመታት በኋላ የደረስኩበት ውሳኔ ግን ይህ ተቋም አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደኋላ የሚጓዝ እንደ ካሮት ወደታች እንጂ ወደላይ ለማደግ የማይችል የራሱን ማለትም የሲኖዶሱን ውሳኔ እንኳ ተግባራዊ ማድረግ ያልቻለ ድርጅት ስለሆነ ወርቃማ ጊዜያችንን ልናጠፋበት የማይገባ መሆኑንን ነው:: ከላይ ፓትርያርክ ከተባሉት ጀምሮ ዘወትር ሸፍጥና ሐሰት የተሞላበት ተግባር ከመፈጸም የማይመለሱ ስለሆነ የአባ ፋኑኤል ተግባር ሊያስደንቀን አይገባም:: ክርስትናው ውስጣቸው የሌለውን ከየት ያምጡት ብለን እንጠይቃቸዋልን:: ያገራችን ሰው እኮ ሲተርት ያልዘሩት አይበቅልም ይላል::
ReplyDeletemefethew menden newe?
ReplyDelete