Wednesday, November 30, 2011

ዝምታው እስከመቼ ነው?

ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው

"እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፥ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች። "
ትንቢተ ኢሳያስ ፲፫ ፥ ፲፱

"ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም። "
ትንቢተ ኤርሚያስ ፶ ፥ ፵

"ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፦ "
ትንቢተ አሞጽ ፬ ፥ ፲፩

"ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ "
፪ኛ የጴጥሮስ መልዕክት ፪ ፥ ፮

ወገኖቼ እናስተውል ዛሬ እንዲህ ዓይነት በዓይናችን ላይ የሚሰራው ነገር ከምዕራባዊያን የመጣ ባሕል እና ህይወት ነገ የእያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ አይቀሬ ነው፣ ሰዶማውያንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ትቃወማለች፣ ትጸየፈዋለችም እንዲህ ዓይነቱን በሽታም በህዝባችን የእለት ተዕለት ኑሮውን እንዲያበላሸው ወይንም እንዲበርዘው የማናችንም ምኞት አይደለም ስለሆነም፣ ሕፃን፣ ወጣት፣ አዋቂ፣ ሽማግሌ እና አሮጊት እንዲሁም ክርስቲያን፣ እስላም፣ ወይንም ሃይማኖት የለሹም ቢሆን ይሄንን ኢ - ኢትዮጵያዊ የሆነውን ምግባረ ብልሹነት የምዕራባውያን ቅብጠትን ወይም ሰይጣናዊነት አጥብቀን ልንቃወመው የሚገባ ወቅታዊ ጉዳይ ነው ብለን የዚህ ዝግጅት ክፍል ያምናል፡
መልካም ምንባብ 
"የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም" 

ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን

ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን


 • በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በአካባቢው ሙስሊሞችና ፖሊሶች የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አፈረሱ
 • ፓትሪያሪኩስ እንዴት ዝም ይላሉ? ለምን ለመንግስት አካላት አያሳውቁም፣
 • ቋሚ ሲኖዶሱስ እንዴት ዝም ይላል፣ ቤተ ክርስቲያን ስትፈርስ ለምን ዝም ይባላል
 • በዓለም ዙሪያ ያለ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጆች ይህንን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ የለብንም
 •   የከተማው ሕግ ቢፈቅድ እንኳ የቤተ ክርስቲያን የበላይ አባቶች እና ተጠሪዎች ይህንን እንዴት ዝም ብለው ይመለከታሉ? (አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤2004 ዓ.ም  November 29 2011 ) በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አርብ በ15 /03/04 በሙስሊም ፖሊስ አባላትና እነርሱን ከሚመስሏቸው ማህበረሰብ አካላት ጋር ሆነው ቤተክርስትያኗን ያፈረሷት ሲሆን ፤ በአካባቢው የሚገኝ ታማኝ ምንጭ ለማወቅ እንደቻልነው የቤተክርስትያኒቷ ጉልላት በፖሊስ አዛዡ ግቢ ውስጥ መገኘቱን በዓየይናቸው ተመልክተዋለል ፤ በዞኑ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ አማኞች የሚደርስባቸው ግፍ አስመክቶ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ትናንት በ18/03/2004 ዓ.ም ማለዳ በደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅ/ቤት ክርስቲያኖች ለአቤቱታ በአምስት መኪና የሄዱ ሲሆን :: አቤቱታ አቅራቢዎች የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ቃል አቀባይ የሆኑት እስከ 10 ሠዓት ድረስ ሲሳለቁባቸው ውለው ያለ ምንም መፍትሄ ሸኝተዋችዋል:: አቤቱታ አቅራቢዎቹ ተመልሠው ወደመጡበት አካባቢ ቢመለሱ የመኖር ህልውናቸውናቸው አስጊ በመሆኑ በመጀመሪያ የደቡብ ክልል ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ከዞኑ ፖሊስ ለሚደርስባቸው ጫና ገለልተኛ በሆኑ ፖሊስ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቀጥሎም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ በባዶ ሆዳቸው መሪር እንባ እያነቡ ሲናገሩ ላያቸው ያስለቅሱ ነበር፡፡›› በማለት ዘግቦልናል ፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የሀገረሥብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀሌምጦሰም ለሚመለከታቸው ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tuesday, November 29, 2011

ከደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ምዕመን ምልከታ


አባ ፋኑኤል እና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

አንድ የዝግጅታችን ተከታታይ የደብረ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኑን አጠቃላይ ምልከታ እና የአቡነ ፋኑኤልን የባለቤትነት ጥያቄ አስመልክቶ ሰፊ ሀተታ ልከውልናል እኛም ለአንባቢያን እንደሚከተለው አቅርበንዋል፡ መልካም ንባብ


የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ


Monday, November 28, 2011

አስደንጋጩ የክርስቶስ ፊልም


አስደንጋጩ የክርስቶስ ፊልም

 • THE ABODE OF GOD በኢትዮጵያ የሚል ስያሜ አለው
 • ክርስቶስ እና ይሁዳ ከንፈር ለከንፈር ይሳሳሙበታል
 • የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ተዋናዮች ፔቲሽን ተፈራርመው አሳግደውታል
 • የሀገራችንን ገፅታ የሚያጠፋ ነው መሰራት የለበትም :: ነብዩ ባዩ(የአ.አ.የ. ቲያትር ዲፓርትመንት ዳይሬክተር)
 • ፊልሙ በኢትዮጵያ ካተቀረፀ በሌላ ሀገር ይሰራል::  ጫንያለው ወ/ጊዮርጊስ
 • ፊልሙ እንዲሰራ ቤተክህነት ፍቃድ ሰጥቶታል
 • ሀዋርያው ቶማስም በተባበሩት መንግስታት በሚደረግ ስብሰባ ላይ በድንገት በመግባት ስለመልካም አስተዳደር ንግግር ሲያደርግ ፍትህ እና ርትእ ለማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር መብት እንደሆነ ሲያውጅ እንድርያስ ደግሞ በጀርመን አገር ቤት ንብረት የሌላቸው ሰዎች በሚመገቡት ምግብ ቤት ውስጥ ምግብ እየበላ እና ‹‹ ጎረቤትህን እንደራህ ውደድ›› የሚለውን ወርቃማ ህግ እንዲሁም ‹‹ ሁሉም በእግዚያብሄር ፊት እኩል ነው›› የሚለውን መልዕክት ፊልሙ ላይ ያስተላልፋል
 • አስተባበርኩ እንጂ ስለ ፊልሙ ብዙም አላውቅም ዳይሬክተር ሚካኤል ታምሩ
 • ይህ ፊልም እየሱስ ክርስቶስን ‹‹ ድንቆችን እና ተአምራትን አድርጓል ነገር ግን እርሱ ወደፊት የሚመጣውን ትክክለኛውን አፅናኝ የእግዚአብሔር ነብይ መምጣት ሲያበስር ከፈጣሪ ተልኮ የመጣ ነው፡፡ በእርግጥም ኢየሱስ ለሚመጣው ቅዱስ ነብይ ክብር ምስክር እና መንገድ ነው ይለዋል
 • አቡነ ፊሊጶስ ጉዳዩ በጣም አስደንግጧቸው በአስቸኳይ ስክሪፕቱ እንዲገመገም የሚል ደብዳቤ ፅፈዋል
 • ጌታ እዚህ ፊልም ላይ አፉን በአላዛር አፍ ላይ ገጥሞ ያስነሳዋል ይላል
 • እየሱስ ክርስቶስ አልተሰቀለም በእሱ ፋንታ ሌላ መልአክ ነው የተሰቀለው ይላል
 • መቅደላዊት ማርያም ሐዋርያትን የማቁረብ ስልጣን አላት ይላል
 • ኢየሱስ ከመቅደላዊት ማርያም ጋር የተለየ ግንኙነት ነበረው ይላል
 • የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ፒቲሽን ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስገብተዋል
 • የቀረፃ ቦታዎች የኦርቶዶክስ ገዳማት ናቸው ፤ ላሊበላ ፤ አሽተን ማርያም ፤ ይምርሀነ ክርስቶስ ..ሌሎችም
 • ክርስትያን ያልሆኑ ተዋናዮች መኖራቸው ታውቋል
 • የፊልሙ ፀኀፊ ጀርመናዊት ሀገር ለቃ ሄዳለች እና ሌሎችም

Saturday, November 26, 2011

ፓትሪያሪክ ጳውሎስ የጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መረቁከደሴ ደብረ ቤቴል ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምረቃ የቀሩት አቡነ ጳውሎስ የጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መረቁ


 •  መኖሪያ ቤቱ ብር 1.5 ሚልዮን ያህል እንደወጣበት ተነግሯል 
 •  አቡነ ጳውሎስ ያለጥንቃቄ ባደረጉት ጉዞ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል
 •  “አይ ቅዱስነትዎ፣ ተዋረዱ!! አሁን ይህ ለእርስዎ ክብር ነውን? የመቂ ሕዝብ እርሱን [ጌታቸው ዶኒን] ከእኛ የተሻለ ጠንቅቆ ነው የሚያውቀው፤ እንግዲህ የጌታቸው ዶኒ ጓደኛ ነው የሚልዎ!” /አቡነ ጎርጎርዮስ በድርጊቱ ማዘናቸውን ለአቡነ ጳውሎስ የገለጹበት መንገድ/
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 15/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 25/2011/ PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ኅዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት መቂ ከተማ ተገኝተው የሊቀ ካህናትጌታቸው ዶኒን መኖሪያ ቤት መርቀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ 98 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው መቂ ከተማ ከድልድይ በላይ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በ400 ሜትር ካሬ ስፋት ያረፈውና በ‹ሀ› ቅርጽ የተገነባው የሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቪላ 1.5 ሚዮን ብር ማውጣቱን ግለሰቡ በምረቃው ዕለት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ባቀረበው አጭር ሪፖርት ገልጧል፡፡ በምረቃው ላይ በግለሰቡ ጥሪ የተደረገላቸው 200 ያህል እንግዶች የታደሙ ሲሆን ድግሱም ሞቅ ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

Wednesday, November 23, 2011

አባ ሰረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል በሎስ አንጀለስ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

አባ ሰረቀ ማን  ናቸው?
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ ለማለት ቢያስቸግርም የቤተክርስቲያናችን ሥርዓት፣ የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ አንቱ በማለቱ እቀጥላላልሁ ።
አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበት ሎሳንጀለስ ከተማ) ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈዋቸው ስለሄዱ አባ ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል ። አንዲ የቤተክርስቲያናችን አዛውንትማ ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው ነው የሚያንገሸግሻቸው።
ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ በሎሳንጀለስ እንደት ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦
አባ ሰረቀ ብርሃን በ1993 መስከረም ላይ ከኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ይህንን መረጃ የሰጡን አባት እንዲህ ያጫውቱናል።
አባ ሰረቅ ብርሃንን ለማስመጣት ሂደቱን የጀመእኩት እኔ ነኝ። በ1993 እ.ኤ.አ. የእህቴን  ባል እባክህ ጥሩ ካህን የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ሰው ፈልግልን ብየ ነገርኩት።
እርሱም ወዲያው አንድ በጣም የተማሩ ሰው አግኝቸልሃልሁ ብሎ አጫወተኝና (በኢትዮጵያብክረምት አካባቢነው)ደስ አለኝ። ደውየም እንዳነጋግራቸው አመቻቸልኝና  አባ ሰረቀን ድውየ አግኘኋቸው።  እርሳቸውም ለመምጣት እፈልጋለሁ ግን ለመጉዋጓዣ 2000 ዶላር ያስፈልገኛል ብለው ነገሩኝ። እኔም ቦርዱን አስፈቅጀ የመምጫቸውን ሁኔታ ጀመርን።2000 ዶላርም ተላክላቸው።

ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የተቃውሞ

ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ እይታዎች ሙሉዉን ቪሲዲ አቅርበንላችኃል

video


ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተሐድሶ መናፍቃን ላይ ያደረጉትን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያሳይ የ 20 ደቂቃ ቪሲዲ ለዛሬ አቅርበንላችኋል ሙሉውን ታሪክ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Monday, November 21, 2011

አቡነ ፋኑኤልን ለምን ለመቃወም አስፈለገ (በደብረ ምሕረት ምእመናን)

አንድ እራሳቸውን የደብረ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ምዕመን ነኝ ያሉ ሰው ይህንን አቤቱታ በጡመራችን እንድናስተናግድላቸው ልከውልናል እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ጋር ይጫኑ

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው አቡነ ፋኑኤል

 • "እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው"
 • "14 ዓመት ደክሜ ከሰራሁት ቤቴ የትም አልወጣም"
 • "ወደዳችሁም ጠላችሁም ከዚህ የትም አልሄድም"
 • "አዎ አዲስ አበባ ላይ ቪላዎች ቤቶች አሉኝ፣ ያንን ትቼ ይህንን ህዝብ ላገለግል መጣሁ"
 • "ከዋሺንግተን ዲሲ እስከ ካሊፎርኒያ የኔ ግዛት ነው"
 • "ከዚህ በኃላ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ መፃተኛ የሚባል ቤተ ክርስቲያን የለም"

የደብረ ምሕረት የትላንትናው ትዕይንት ይሄን ይመስል ነበር

በትላንትናው እለት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ላይ የተገኙት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ላይ ልክ እንዳደረጉት ምንም የምታመጣው ነገር የለም የኔን የላከኝ ቀበሌ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስ ነው በማለት ለበዓል የታደመውን ምዕመን አስገርመውት ውለዋል። ትላንት በጠዋት የተጀመረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በፓሊስ ውጪው በተቃዋሚ ታውኮ ውሏል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኃላ በመምህር ዘላለም ወንድሙ አማካኝነት የማስፈራሪያ መልዕክት እንዲያስተላልፍ በተሰጠቅ ጥብቅ መመሪያ መሰረት መጥቶ በማያውቅበት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ቆሞ ባለሙዋልነቱን

Tuesday, November 15, 2011

በአቡነ ፋኑኤል ሥርዓት አልበኝነት የተቃውሞ ሕዝባዊ ጥሪ ለመላው ዓለም


ለዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ!

አቡነ ፋኑኤል በገጠማቸው ቀውስ እንዳዘኑ!
 ከትላንት በስቲያ ሰኞ ከቀትር በፊት አቡነ ፋኑኤል በድብቅ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ገብተው ማደራቸው ተዘግቧል፥ በእለት በገቡበት ዕለት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ተገምቶ ስለነበር ቀድመው ለሰዎች ሐሙስ ብለው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ አስነግረው ነገር ግን እሳቸው ሰኞ ከእኩለ ቀን በፊት ማንም ሳይሰማ ወደ ከተማው ገብተው አድረዋል። በዚሁ እለት በቨርጂኒያው አየር ማረፊያ እንደደረሱ አጠገባቸው ሆነው እርሳቸውን እና አላማቸውን በመደገፍ የሚታወቁት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካሕናት እንዲሁም ከአካባቢው ካሕናት እነ ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ እና በቀሲስ ኢስሃቅ አማካኝነት ከአየር ማረፊያ ተቀብለዋቸው በቀጥታ በደቡብ ምዕራብ ዋሽንግተን  ወደሚገኘው የደብረ ምሕረት ገንዘብ ያዥ ወደ ሆነው ሰው መኖሪያው ቤት በቀጥታ አምርተው በዛው ቀናትን ለማሳለፍ ተገድደዋል። ባለፈው እንደዘገብነው በዚህ ጉዞዋቸው በጋሻውን ይዘው ለመምጣት ብዙ ጥረቶችን ለማድረግ ቢሞክሩም የተሳካላቸው አይመስልም፣ ነገር ግን እርሱን ለማምጣት የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉም ቅዱስ ፓትሪያሪኩም ቃል እንደገቡላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Monday, November 14, 2011

ቀሲስ ኢስሃቅ እና ቀሲስ አቡኑ ብራንች ከፈቱ

". . .እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ። . . ."
ትንቢተ ሕዝቅኤል ፵፬ ፥ ፭

በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ልዩ ስሙ Baily Cross Road በሚባል አካባቢ አዲስ የገለልተኛ ክርስቲያናትን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠን ነው ብለው የሚሉት ሁለት የአሜሪካን ካሕናት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውቅና፣ ያለ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ እንደፈለገን በአሜሪካን ሀገር ነው ያለንው ማንም ሊከለክለን አይችልም በሚል ቤተ ክርስቲያን በዘፈቀደ ከፍተው ኑና አስቀድሱ ብለው ባለፈው ቅዳሜ አገልግሎት አለ በማለት ሕዝቡን ሲያዋክቡ ሰንብተዋል። በልዩ ስሙ "ቤሊ ክሮስ ሮድ" በሚባለው አካባቢ የከፈቱት የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ከወዲሁ ትልቅ የሕብን ቁጣ ሳያስነሳባቸው እንደማይቀር ተገምቷል።

እኔ እና አቡነ አብረሃም

እኔ እና አቡነ አብርሃም የምንተዋወቀው ገና ወደዚህ መዓርግ ሳይመጡ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሳይሆኑ፣ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ሲማሩ ነው፡፡ ይበልጥ ያወቅ ኳቸው ግን ብዙ በሠሩበት እና ማንነታቸውንም ባስመሰከሩበት በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አለቃነ ታቸው ነበር፡፡

የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ትምህርት ቤት ሲከፈት ከመድኃኒት ዘዋለ እና ከዳግማዊት ግርማይ ጋር የት/ቤቱ ቦርድ ሆኜ ሠርቼ ነበር፡፡ አቡነ አብርሃምን በሚገባ ያወቅኳቸው ያኔ ነው፡፡ እንደ አለቃ ይመራሉ፣ እንደ ባለሞያ ይሞግታሉ፣ እንደ አባት ይጋብዛሉ፣ እንደ ወንድም ስንጠፋ ይፈልጋሉ፣ እንደ ኃላፊ ይከታተላሉ፡፡

ትምህርት ቤቱን ለመስከረም ለማድረስ የነበረን ጊዜ ከሦስት ወር የማይበልጥ ነበር፡፡ ተማሪ መዝግበን፣ መምህር ቀጥረን፣ መዋቅር ዘርግተን፣ ቁሳቁስ አሟልተን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ፈቃድ አግኝተን ለማጠ ናቀቅ ሦስት ወር፡፡ መቼም በቦታው እርሳቸው ባይኖሩ ኖሮ ይሳካ ነበር ብዬ ለመገመት ይቸግረኛል፡፡

Sunday, November 13, 2011

አባ ፋኑኤል እና ጉዞዋቸው!

 • አቡነ ፋኑኤልን ለምን የአሜሪካን ክርስቲያኖች አይቀበሏቸውም?
 • አቡነ ፋኑኤል የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዴት ተሾሙ?
 • አቡነ ፋኑኤል ከዚህ በፊት ምን አይነት አቋም ነበራቸው? አሁንስ?
 • የአቡነ ፋኑኤል ከነ ወ/ሮ እጅጋየሁ እና በጋሻው ጋር ያላችው ግንኝነት ምንድነው?
 • አቡነ ፋኑኤልን እና የመናፍቃኑ ድምጽ የሆነው "አባ ሰላማን" ምን አገናኛቸው?
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከተመሰረተች ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ቢሆናትም እንደ አሁኑ ያለ ከፍተኛ ፈተና የገጠማት ለመጀመሪያ በታሪኳ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጉዞዋ ያሁኑ በጣም አስቸጋሪ እና ከፈተናዎች ሁሉ የከፋ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያኗ ጥላ ስር ያሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መዕመናን እና ምዕመናት በምሬት ይናገራሉ። ከዛሬ ሃምሳ አመት በፊት በቅዱስ ፓትሪያሪክ ሊቀጳጳስ ዘኢትዮጵያ በሆኑት ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሊዎስ ተባርካ በብሩክላን ኒው ዮርክ ከተማ ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ልካ ሐዋሪያዊት አገልግሎቷን ስትፈጽም ቆይታለች፥ በዚህ በነበራት ጉዞዋ ብዙ ውጣ ውረዶች በተለያየ ጊዜ የገጠማት ቢሆንም ካለፈው አምስት ዓመት በኃላ በሰሜን አሜሪካ ሦስት ሀገረ ስብከቶች ሆነው እንዲሰሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ባዘዘው መሠረት ከተመሠረተ ጀምሮ ግን አመርቂ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይዞታዋን ከማስመለሱም በላይ ታላላቅ ገዳማትን እና አድባራትን መሥርታ በላከቻቸው ብፁዓን አባቶች አማካኝነት ታላላቅ የሆኑ ይዞታዎችን ቤተ ክርቲያኗ እንድትይዝ እና ሐዋሪያዊት ተልዕኮዋን ስትፈጽም ስታስፈጽም ቆይታለች።

Saturday, November 12, 2011

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል


ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል


ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል፣ቅዱስ ሲኖዶስ በሰሜን አሜሪካን የቤተ ክርስቲያን ችግር ንክኪ የሌለባቸው አባቶች እንዲመድብ ፊርማ እየተሰባሰበ ነው

 READ IN PDF
የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 02/2004 ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገቡነት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸ እየተነገረ ነው:: ብፁዕነታቸው ከዚህ በፊት የሰሩዋቸው ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባራት በዚህ አካባቢ በሰፊው የሚታወቅ ስለሆነ ተቃውሞው የከፋ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል:: በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ማኅበር፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት፣ በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና በሰሜን አሜሪካ የማኅበረ በዓለ ወልድ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል ተብሎዋል:: “የግል ቤተ ክርስቲያን ያለው አባት እንዴት ቤተ ክርስቲያን አንድ ሊያደርግ ይችላል”? የሚል ጥያቄ እየተነሳ መሆኑም እየተነገረ ነው::

"የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አከብራለሁ፣ የተመደብኩበት ቦታ እሄዳለሁ”

"የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አከብራለሁ፣ የተመደብኩበት ቦታ እሄዳለሁ” ብፁዕ አቡነ አብረሃም
READ IN PDF
ብፁዕ አቡነ አብረሃም

ዛሬ በሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላድ ኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር የተገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ መደባቸ ሀገረ ስብከት እንደሚሄዱ ገለጹ:: ብፁዕነታቸው የተመደቡበት ቦታ የሚገልጽ ደብዳቤ ህዳር 1፣ 2004 ዓ/ም እንደደረሳቸው ገልጸው፤ ነገር ግን ለዚህ ሀገረ ስብከት ስለተመደበ አባት ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል:: ብፁዕነታቸው አንዳንድ ጅምር ሥራዎች ሥላሉዋቸው እስከ ታህሣሥ ወር አጋማሽ ድረስ ለመቆየት ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ መጻፋቸውም ጭምር ገልጸዋል:: በዕለቱም ትምህርታቸው “እኔ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ቀኖና ይከበር ብዬ እያስተማርኩ፤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የምጥስበት ምክንያንት ምንም የለኝም” በማለተ ተናግረዋል:: አንዳንድ ሰዎች “ዛሬ ለምን የቅዳሴ ቤቱን አከበርክ”? ብለው ይጠይቁ ይሆናል፤ ነገር ግን ዛሬ የተገኘሁበት ምክንያት አስቀድሞ የተያዘ መርሀ ግብር በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ ከሀገረ ስብከቱ መነሳቴ እንደ እናተው ዜና ከማንበብ ውጪ ሌላ ምንም የደረሰኝ መልዕክት ስላልነበረ ነው::  ሥለዚህ በዛሬው እለት የቅዳሴ ቤት ማክበሬ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን የወጣ አይደለም ብለዋል::

ሦስት መቶ ሺህ ተሽጦ ሰባ ሺህ ጉርሻ ያስገኘ…..

          ተካ ፍሬሰንበት ከራጉኤል መርካቶ 
የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር የሚያደርጉት ግብግብ ተሳክቶ ፍሬ እያስገኘ ነው፡፡ ምዕመኑም “ከልጆቻችን ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን የቀረበ የለም የምንሰማው እነሱን ነው” ብሎ እየተከተላቸው ነው፡፡ ይኽ በእውነት ትልቅ ለውጥ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት በአዳራሽ ተወስኖ መቅረት የለበትም፡፡ በቅድሚያ እያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት በየአጥቢያው የስብከተ ወንጌሌ አገልግሎት በኮሚቴ ከመሳተፍ ጀምሮ በመማር ማስተማሩ ሒደት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ከጥሎ በአቀማመጥ ቅርብ ለቅርብ የሆኑት ደግሞ ተጋግዘው ቦታቸውን ከአጉራ ዘለል ሰባኪያን ለማጽዳት አንድ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በቅርቡ መናፍቁ አሰግድ በአንድ አጥቢያ ተጋብዟል መባልን የሰሙ ሰ/ተማሪዎች ከሩቅ ቦታ በቶዮታ ቲካፕ መኪና ተጭነው ቀድመው ቦታውን ለማስከበር ሲደርሱ ስለተደወለለት ይመስላል አሰግድ ግን ሳይመጣ ቀርቷል፡፡
    ሌላው ሰ/ተማሪዎችና ጉዳዩ የሚያንገበግበን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ልንሰራው የሚገባንን የቤት ሥራ ላቅርብና ተወያዩበት ያላችሁንም መረጃ በሰንበት ት/ቤቶች ኅብረቱ በኩል ሰብስቡት እላለሁ፡፡እነሆ ፍሬ ነገሩ፦

Wednesday, November 9, 2011

ጠ/ቤተ ክህነቱ በሹመትና በሽረት እየታመሰ ነው፤ አባ ሰረቀ ም/ሥራ አስኪያጅነቱን አጥተዋል

by Deje Selam on Wednesday, November 9, 2011 at 4:36pm
 • የጠ/ቤ/ክህነቱ የሹመትና ዝውውር ውዝግብ በሽምግልና ተይዞ ቀጥሏል 
 • ንቡረ ድ ኤልያስ ኣብርሃ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅነትን ቀድሞ ከነበሩበት የጠ/ቤ/ክህነቱ የመንፈሳዊ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ጋራ ደርበው እንዲይዙ፤
 • ንቡረ ድ አባ ገ/ማርያም ገ/ሥላሴየገዳማት መምሪያ ዋና ሓላፊ እንዲሆኑ፤
 • አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊእንዲሆኑ ሐሳብ ቀርቧል 
 • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ዋና ሓላፊ የሆኑትን ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬን ከትንት በስቲያ አባ ሰረቀን በሕገ ወጥ መንገድ ለሾሙበትየመንፈሳዊ ጉዳዮች ዘርፍ ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን መርጠዋቸው የነበረ ቢሆንም የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን ስምምነት አላገኙም 
 • ቤተ ክህነቱ ሙስና የሚያፍርበት ሳይሆን የሚያሾምበት ይነተኛ ተቋም ሆኗል

የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋ

የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋ

 ከቀሲስ ወንድምስሻ አየለ ፌስ ቡክ የተወሰደ:: READ IN PDF
ቁማር ከመዝናናት ሌላ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚጫወቱት ሕጋዊና ሕገወጥ ጫወታ መሆኑና ማንኛውንም ጫወታ በቁማርነትም ሆነ በመዝናኛነት ለይቶ የመጫወቱ ድርሻ የተጫዋቹ መሆኑ ግልጥ ነው፤ ካርታን ለመዝናኛነትም፣ ሲያስፈልግ ደግሞ በሕገወጡ ቁማርነትም መጫወት እንደሚቻል። ይህም መንፈሳዊውን ሥልጣን በያዘው ሰው ዘንድ መነገሩ እጅግ የሚያሳስብና የሚያሳዝን ነው። «አባት»ን ቁማርተኛ ብሎ ለሚናገረውም ሁለት ጊዜ ብቻ ሳይሆን አሥር ጊዜ አስቦ ዓላማንም ለይቶ የሚጸናውን ከያዙ ላያሳፍር ብሎም ሊጠቅም ይችላል። ተሳድቦና ዘልፎ ለመርካት ወይም ብስጭትን ለመወጣት ሊረዳ ቢችልም ከኅሊና ዕዳ ነፃ ለመሆን ግን እውነተኛ መረጃ ይፈልጋል፤ እንደነ በጋሻውም በአደባባይ ለመገላበጥ አይገደድም። እኛምይህን ታሳቢ አድርገን እንቀጥል።

ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ

ከዳንኤል ክብረት እይታዎች የተወሰደ:

አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን ከመቶ ዓመታት በፊት የሞራል እና የሥነ ምግባር ልዕልናን ከእምነት ተቋሞቻቸው ነጥቀዋል፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በእምነት ተቋማቱ ውስጥ እና በእምነት መሪዎቹ ዘንድ የሚፈጸሙት ጥፋቶች፣ ኃጢአቶች እና
ወንጀሎች የእምነቱ ተከታዮች ከሚሠሯቸው ይልቅ እየባሱ መምጣታቸው ነው፡፡

ሴትዮዋ ጉድጓድ ውስጥ ትወድቅና ትጮኻለች፡፡ አንድ ሰው ይሰማትና ይመጣል፡፡ እጅሺን አምጭ ብሎ እጇን ጎትቶ ሊያወጣት ሲሞክር እጇን ይገነጥለዋል፡፡ ሴትዮዋ ጉድጓድ ከመግባቷ ይልቅ የእጇ መገንጠል ይብስባታል፡፡ እናም «አውጣኝ ብለው ገነጠለኝ» አለቺ ይባላል፡፡ አውጭው ከጉድጓዱ ባሰባት፡፡
 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለተዋህዶ ቤተሰቦች በሙሉ

  ወቅታዊ ወሬ
           የእነ አቡነ ፋኑኤልና  የአባ ሰረቀ  ግብረ ሃይል በቅድስት ሀገራችን ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ጠንካራ አቋምና በቆራጥ ምዕመናን ትግል ክንዳቸው ለጊዜው ተመቷል። ነገር ግን  ለረጅም ጊዜ ዕቅድ በዘረጉባት  ምድረ አሜሪካ ግን የተሳካላቸው ይመስላል። በአቡነ ጳውሎስ አዝማችነት ታምነው የሚንቀሳቀሱ አቡነ ፋኑኤል፥ አባ ሰረቀ፥  ዲ/ን ኃይለ ጊዮርጊስ እና ሌሎችም ኢትዮጵያ ባይሳካላቸውም የግብር ሃገራቸው በሆነው አሜሪካ ግን እንደዛቱት ተሳክቶላቸዋል። አቡነ ፋኑኤል ቀድሞ ከቤተክርስቲያን ተገልለው በከፈቱት የግል ቤተክርስቲያናቸ  መኖራቸው የታወቀ ቢሆንም አሁን ደግሞ ለአላማቸው ሥልጣንን ከአቡነ ጳውሎስ በአድልዎ ተቀብለው ተመልሰው በአሜሪካ የፈለጉትን ለማድረግ ተመደቡ።

አባ ፋኑኤልን ለምን መቃወም አስፈለገ

የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ???

ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ
      
አባ ፋኑኤል
አባ ፋኑኤል
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደዘገብነው በሰሜን አሜሪካ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍል ዋናኛው ተዋናኝ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ነበሩ:: ብፁዕነታቸ የጵጵስና ማዕረግ ከማግኘታቸው በፊት “አባ መላኩ” በመባል ይጠሩ ነበረ:: በወቅቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ነበሩ:: የዛኔው አባ መላኩ ብፁዕ አቡነ ማትያስን አልቀበልም በማለት “ገለልተኛ” ቤተ ክርስቲያን አቋቋመው ነበረ:: ከሌሎች ከግባበሮቻቸው ጋር በመሆን አሁን የሚሰግዱላቸ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመቃወም “የገለልተኞች”የካህናት ማህበር አቋቁመው ነበረ:: አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የዚሁ “የገለልተኞቹ” ማህበረ ካህናት ከአባልነት በተጨማሪም በኃላፊነት ሰርተዋል::

Tuesday, November 8, 2011

አቡነ ጳውሎስ አባ ሰረቀን የጠ/ቤ/ክ/ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾሙ

 • ሹመቱን የተቃወሙት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ከሓላፊነታቸው እንደሚለቁ አሳውቀዋል:: 
 • የሹመቱ ደብዳቤ ፓትርያኩ በሚቆጣጠሩት ጽ/ቤት በኩል የወጣ ነው::
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 27/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 7/2011/ PDF)፦ ባለባቸው ከፍተኛ የአቅም ማነስ እና በተጠረጠሩበት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ሤራ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊነት ተወግደው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በሚገኙበት የሊቃውንት ጉባኤ ምርመራ እንዲካሄድባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተወሰነባቸው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ዛሬ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ በፓትርያሪኩ ማኅተም እና ፓትርያሪኩ በብቸኝነት በሚቆጣጠሩት ልዩ ጽ/ቤት በኩል ደርሷቸዋል፤ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሹመቱን በአድራሻ ለ‹አባ› ሰረቀ በደረሳቸው ደብዳቤ ግልባጭ እንዲያውቁት መደረጉ ተዘግቧል፡፡

የዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት አብያተ ክርስቲያናት እና ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔውን እንዲያጤን ጠየቁ


ጥቅምት 22/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 2/2011/ )፦ የቅዱስ ሲዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 21/2004 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ለዲሲ እና ለካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት የተመደቡትን የአቡነ ፋኑኤል ሹመት የቀሰቀሰውን የምዕመናንን ቁጣ ተከትሎ በሀ/ስብከቱ  ሥር የሚገኙ  11 አብያተ ክርስቲያናትም አስቸኳይ ስብሰባ አድርገው ድምጻቸውን አሰምተዋል፤ ለቅዱስ ሲኖዶስም ባለ 5 ገጽ መልእክት አስተላልፈዋል። “በሰሜን አሜሪካ አሁን የሚታየው ችግር ተወሳስቦ ተወሳስቦ አሁን ያለበት ደረጃ የደረሰው ከመጀመሪያው ጀምሮ  የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የማስጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ ባለመሰራቱና በወቅቱ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚገቡ  አስተዳደራዊ ችግሮች ሳይፈቱ በመቅረታቸው ነው” ያለው መግለጫው
ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ  ግን የተሻለ  የአህጉረ ስብከት አደረጃጀት እየታየ በመምጣቱና የቤተክርስቲያን አንድነት እንደሚያስፈልግ በመረዳት  በሀገረ ስብከት ሥር የሚካተቱ አብያተ ክርስቲያናትም ቁጥር” እየጨመረ መምጣቱን አስታውሶ “በየትኛውም መልኩ ቢሆን  በአሜሪካ ደረጃ የቤተክርስቲያንን መዋቅር ባልጠበቀ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ ቤተክርስቲያንን የመለያየት እና ለተለያዩ ከቤተክርስቲያን ውጭ ለሆኑ አመለካከቶችና አጀንዳዎች  ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሚሰጥና የቤተክርስቲያንን ክብር” የሚቀንስ መሆኑን አውስቷል።