Wednesday, December 21, 2011

አስኬማው የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን (የትዝታው ሳሙኤል ግሩፓች)



የሥርዓት አልበኞቹ ግሩፕ ቀንደኛ መሪዎች

(አንድ አድርገን ታህሳስ 11 ፤ 2004)፡- በዲላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ህገወጥነት እና ስርዓት አልበኝነት በፊት እነ በጋሻው ደሳለኝ እና ትዝታው ሳሙኤል ባስመረጧቸው የሰበካ ጉባኤ አባላት እየተከናወነ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን በስራ ላይ የሚገኝውን የሰበካ ጉባኤ እንዲበተን እና በምትኩ ህዝቡ ይሆኑኛል ፤ ቤተክርስትያኗን ለማተዳደር እውቀቱም ሆነ ብቃቱ አላቸው ያላቸውን ሰዎች እንዲመርጡ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተፃፈ ደብዳቤ ከሳምንት በፊት በእጃቸው ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፓትርያርኩም ሆነ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አያገባቸውም በሚል እሳቤ ሰውን ለሌላ ብጥብጥ ለማነሳሳት የቤተክርስትያ አስተዳዳሪው የኛ የሚሏቸውን ሰዎች  እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡

በፊት የነበረው ሰበካ ጉባኤ በእነ በጋሻው እና ትዝታ ሳሙኤል ገፋፊነት እነርሱ ያቀረቧቸውን ሰዎች ያስመረጡ ሲሆን ቀድሞም ቢሆን አካሄዱ ትክክል ስላልሆነ ተቃውሞ ገጥሞት ነበር፡፡ ለእነሱ አላማ የሚያስፈፅም ቃላቸውን የሚሰማ ፤ ተግባራቸውን የሚያደርጉ ሰዎችን ነበር ማስቀመጥ የቻሉት ፡፡ ለዘመናት ዲላ ሚካኤል ላይ አውደ ምህረቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲከለክል እነዚህ አባላት በመፍቀድ ሲያስፈነጩበት ከርመዋል፡፡ የህዳር የቅዱስ ሚካኤል ጉባኤ የመላእኩን ስም ሰውን አስረስተውት የትዝታው ጉባኤ እስከመባል ደርሶ ነበር ፡፡ አሁን ግን ስራቸው ተመዝኖና ፤ ግራ ቀኙ ታይቶ የቤተክርስያኑ ሰበካ ጉባኤ እንዲበተን እና አዲስ ሁሉ ምዕመን በተገኘበት የምርጫ ፕሮግራም እዲደረግ በደብዳቤ መልክ ከሀገረስብከቱ ቢደርሳቸውም ፤ ‹‹ቤተክርስትያኗ የምትተዳደረው በህዝቡ እንጂ በማንም አይደለም›› በማለት በግብር የሚመስሏቸውን ሰዎች ሰብስበው በመነጋገር የጋራ አቋም በማስቀመጥ ፤ እምቢተኛነታቸውን በቃለጉባኤ በማስደገፍ ተሰብስበው ተፈራርመዋል፡፡

በስብሰባ ላይ ከተገኙት ምግባርም ሆነ ስርአተ ቤተክርስያንን የማያውቁ ሰዎች ፤ ‹‹አስኬማው የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን›› ጳጳሱ የሚሠሩት እኛ የማንሰራው ምንም ነገር የለም ብለው ሲናገሩ አርፍደዋል፡፡ በሌላ በኩል እነዚህን ሰዎች የሚቃወሙ ስርአተ ቤተክርትያን ይከበር የሚሉ ሰዎች ፤ የሀገረ ስብከቱ ትዕዛዝ እንዲከበር አጥብቀው እየተሟገቱ ሲሆን ፤ ጉዳዬ መፍትሄ እንዲያገኝ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት መምጣቱን ለማወቅ ችለናል፡፡
 
እንደሚታወቀው ባለፈው የጥቅምት ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሕገወጦቹን ሰባኪያንና ዘማሪያን ቅዱስ ሲኖዶስ የማያዳግም መልስ ይስጥልን፣ ቤተክርስቲያናችንን አይክሉም የሚል ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት፥ እነዚሁ ሕገወጥ ሰባኪያንና ዘማሪያን በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ባቀረቡት አቤቱታ በበኩላቸው በሐዋሳ ከተማ ያለአግባብ ከቤተክርስቲያናችን ተገፍተናል፣ ተሰደናል በሚል ምክንያት ቅዱስ ፓትሪያሪኩን ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመንበረ ፓትሪያሪኩ የሆነ ቤተክርስቲያን እንዲተክሉላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ የተቀበሉት በሚያስመስል መልኩ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን ሊመለከቱት አይችሉም መባሉ በብዙ ታዛቢዎች ዘንድ ብዥታን የፈጠረው የፓትሪያሪኩ አካሄድ እንደገና ጥያቄ ውስጥ እንዲገቡ ሳያደርጋቸው የሚቀር አይመስልም። በሌላ በኩል አቡነ ፋኑኤል የሀረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት ቅዱስ ሲኖዶስ በ፳፻ ዓም ባስተላለፈው ውሳኔ ሰባኪያኑ እና ዘማሪያኑ ሁኔታዎች እስኪጣሩ በየትኛውም የቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ እንዳይሰብኩ እና እንዳይዘምሩ የተላለፈውን ውሳኔ፣ አቡነ ፋኑኤል በኔ ሀገረ ስብከት ዲሞክራሲ ሞልቷል በሚል ማንም ሊከለክላችሁ አይችልም በማለት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማናለብኝነት ሽረው ሰባኪያኑን እና ዘመሪያኑን የልብ ልብ ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ያደረጉ አባት መሆናቸው አይዘነጋም፥ በወቅቱም ከፓትሪያሪኩም ሆነ የቤተ ክህነቱ ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ አስተያየት ስላልቀረበላቸው በተመሳሳይ ማናለብኝነት ሥራቸው ይህው እስከ ዛሬ ቀጥለውበት ይገኛሉ።
አሁን ስራውን እንዲያቆም የተወሰነበት ሰበካ ጉባኤ የምርጫው ሂደት ላይ ራሳቸው ተመራጭ ፤ ራሳቸው ፔቲሽን ሰብሳቢ ፤ ራሳቸው ቆጣሪ ፤ ሆነው ነበር ምርጫውን ያከናወኑት፡፡ በቦታ ላይ ብዙ ተከታይ ያላቸው የእነ በጋሻው ግሩፕ የተቀነባበር የምርጫ ትርኢት ነበር፡፡ አሁን ግን በቃችሁ ሲባሉ ‹‹አይበቃንም ፤ ማንም ከህዝቡ ውጪ ስለቤተክርስትያኗ የሚያገባው የለም›› የሚል ፤ ከስርአተ ቤተክርስትያን ያፈነገጠ አካሄድ ይዘው የሚመጣውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡
ከአንድ አድርገን የተወሰደ
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

1 comment:

  1. ለሚመለከተው ሁሉ ….

    ይህንን ጩኸት ለዲሲ ምዕመናን እንድታደርሱልን እንማጸናለን፡፡


    ባለንበት ቤተክርስቲያን በተደጋጋሚ አውደ ምሕረቱን የራስን ዲስኩር ፤ ዝና ፤ ስድብ ፤ ፓለቲካ መናገሪያ ሳይሆን ወንጌል መስበኪያ፤ ቃለ እግዚአብሔር መማሪያ ይሁን ብለን ብንጮህ የሚሰማን ስላጣን ሕዝብ አንድ እንዲል ለማሳሰብ ነው፡፡ ሰባኪም ይሁን ካህን ወይም ጳጳስ ለሕዝቡ ሊያስተላልፍ የፈለገው አስተዳደሪያዊ መልዕክት ካለ ወንገል የሚሰብክ አስመስሎ ሕዝቡን የሚያሳዝን ወቀሳ አይሉት ስድብ የመሰለ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ወንጌል ከሆነ በአውደ ምሕረት ፤ የግል መልዕክት ወይም አስተዳደራዊ ጉዳይ ከሆነ ደግሞ ለይቶ በአዳራሽ ማድረግ ይገባል፡፡ ሁል ጊዜ ቦርዱና ክህናቱ የሚፈልጉትን ተናግረው ሕዝቡ እንዳይናገር ይገባሉ ሕዝቡ ግን በአውደ ምሕረት ላለመናገር እግዚአብሔር መፍራት ይዞት ዝም ይላል፡፡ ክርስቶስ ለዚህ ነው ቤተ የጸሎት ቤት ናት እንጂ የራስ ዲስር መደስኮሪያ፤ የግለሰብ ዝና ማውሪያ ፤ የነጋዴዎች መነገጂያ አይደለችም ብሎ በጅራፍ እየገረፈ ከቤቱ ያስወጣቸው፡፡

    በዲሲ ደብረ ምሕረት ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ለመምረጥ የሁለት ዓመት የፍርድ ቤት ውጣ ውረድ ከፈጀብን በኋላ በማን አለብኝነት በሕዝብ ተመርጠው የገቡት ተጨማሪ አስመራጮች ችግር አለ መፍትሔ ስጡን ብለው ከቦርዱ እና ከካህናትና ሰንበት ት/ቤቶች ጥምረት መፍትሔ እየተጠባበቅን ቦርዱ መርጦ ያስቀመጣቸው ጥቂት አስመራጮች ስራውን አጠናቀናል ብለው የማይፈልጉትን እጩ ሁሉ ከውድድሩ አስወጥተው ምርጫው ተጠናቀቀ፡፡ የሕዝቡን ድምጽ አፍነው በልተዋልና እግዚአብሔር ይፍረድባቸው ብለን ዝም ስንል አቡነ ፋኑኤል (የቀድሞው አባ መላኩ) በአደባባይ ምን ታመጣላችሁ አይነት ስድባቸውን ወንጌል ላስተምር ብለው ባሳለፍነው እሁድ ሲወርዱብን አረፈዱ፡፡ ወገን እስከመቼ ነው የምንታገስ … ማነው በቃችሁ የሚላቸው፡፡

    ለቦርዱ የተመረጡትን 8 ሰዎች (አብዛኛዎቹ ቦርዱ እና አጋሮቹ) ፤ 4 የካህናት ተወካዮች ቃል ለማስገባት ብለው መድረኩን የያዙት አብነ ፋኑኤል ድምሩ ዜሮ ለሚሆን ነገር ያለአግባብ ፍርድ ቤት ሔዳችሁ ብለው ፍትሕ ለተጠማ ወገናቸው የሚያጽናና የእግዚአብሔር ቃል እንደማቀበል የስድብ እሩምታ መግበውታል፡፡

    እኛማ አባት አለን ብለን ነጻ ምርጫ ይኑር ፤ በቤተክርስቲያኑ ተጠያቂነት ያለበት አሰራር ይፈጠር ፤ በአዳርሽ እየሰበሰባችሁ አወያዩን ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ ቦርዱ መልስ ነፍጎናል እና እርሶ መፍትሔ ይስጡን ብል ብንጠይቆ እኔ ቤተክርስቲያኑን አስረክቤያችሁ ሔጃለው እና አይመለከተኝም ነበር ያሉት የዛሬ አመት ገዳማ፡፡ ይህ ጵጵስና ማዕረግ ከደረሰ አባት አይደለም መሃከላችን ካሉ ሽማግሌዎች የማይጠበቅ ነው፡፡ ይህ ሳይጸጽቶት አሁን ደግሞ ለምን ፍርድ ቤት ሔዳችሁ ብለው መሳደቦ ቅሌት ነው፡፡ ፍትህ ፍለጋ የሚሰማን ብናጣ ወዴት እንሂድ … እድለኛ ብንሆንማ እርሶ መፍትሔ ይሰጡን ነበር፡፡ ነገር ግን ቦርዱ እርሶ እራሶ ባሉበት ሆነው ያንቀሳቅሱት ስለነበር መልሱ አንድ አይነት ሆነ፡፡ ፍትህ ፍለጋ ሰብስቡንና አወያዩን ፤ ሃሳባችንን እንግለጽ ፤ በአውደ ምህረት ወንጌል ብቻ ይሰበክ ፤ የአስተዳደር ጉዳይ በአዳራሽ እንወያይ ብንል እድል አይሰጠን ቢል ፤ አባት አለን ብለን ፍትህ እንዲሰጡን ብንጠየቅ… አይመለከተኝም ቢሉን ፍርድ ቤት ሔድን፡፡

    አይመለከተኝም ባሉበት ቤተክርስቲያ ግን የሃገረ ስብከቱ ጳጳስ ሆኜ መጥቻለውና ከሰራሁት ቤቴ ማንም አያስቀጣኝም ብለው ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ማስተማር ሲገባዎ ስለራስዎ አስተመሩን፡፡ ቤቱስ የእግዚአብሔር እጂ የማናችንም እንዳልሆነ ልብ ይበሉ፡፡

    ይህ አይበቃ ብሎት እኛን ከጠላችሁ ለምን ቤተክርስቲያን ትመታላችሁ እዛው በየቤታችሁ መቅረት ትችላላችሁ አሉን፡፡ ቤተክርስቲያን የምንመጣው እኮ እግዚአብሔርን ፍለጋ ነው እንጂ እናንተን አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰጣችሁ ክህነት የምትፈልጉትን ልትጠሩበት ሌላውን ደግሞ ቤታችሁ ቅሩ ሊሉበት ነውን፡፡ በጉንም ግለገሉንም ጠቦቱንም ጠብቅ አለ እንጂ አባሩ አላለም፡፡ ብዙ የተጋደሉ ሃዋሪያቱ እንካን እኛ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን አሉ እንጂ “ ብትፈነዱ እንደኛ ካህን ጳጳስ አትሆኑም ” ብለው በሕዝብ ላይ አይደለም በአሕዛብ ላይ አልተዘባበቱም፡፡ … ምን አይነት ዘምን መጣ ወገን … በአውደ ምህረቱ “እኔ ተምሬ ዶክተር ፕሮፌሰር መሆን እችላለሁ እናንተ ግን ካህን ጳጳስ መሆ አትችሉም” ብለው በሕዝቡ ላይ ሲቀልዱ እና ሲያሽማጥጡ ምነው ወንጌሉ ጠፋዎ፡፡ ምን አልባት ካህን ጳጳስ ብቻ ሳይሆን እንደ ተክልዮ ቅዱስ ጻድቅ የሚሆኑ ሕጻናትና ወጣቶች ልጆቻችን በመካከላችን እንዳሉ ዘንግተውት ነውን፡፡ ነገሩማ እንካን 20 ዓመት እና ከዛም በላይ ጠንክሮ መማር የሚጠይቅ ዶክተር ፕሮፌሰር መሆ አይደለም ተራ ሞያተኛ ለመሆንም የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሚያስፈልግ ዘነጉት፡፡



    “ስትወለዱም ስትሞቱም ያለእኛ አይሆንላችሁም የአህያ ሥጋ አደላችሁ አትጣሉም …” ይህንን ቃላት ከአንድ መነኩሴ መንጋውን እንዲጠብቅ አደራ ከተሰጠው ከኔ ቢጤ ወንበዴም አልጠብቅም ያውም ቤተክርስቲያን ውስጥ ወንጌል አትታበይ ትላለችና፡፡ ትህቢት የኃጢያት ሥር ናት ብላችሁ ያስተማራችሁን እናንተ ናችሁ፡፡ ለነገሩ ምን አለብዎ ቢታበዩ ይህ ለመንፈሳዊ ሰው ነው የሚገደው እንጂ አለማዊ ለሆነ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ የሆኑት አባቶቻችን መነኮሳትማ ደሞዛቸው ለተቸገሩ እየረዱ ለታረዘ እያለበሱ ሕይወታቸውን ሆሩ እንጂ ሁለት ሶስት የተንጣለለ ፓላስ ለራሳቸው ሰርተው አላከራዩም፡፡


    “እርሶ ብቻ ቤተክርስቲያኑን የሰሩ እርሶ ብቻ ሞርጌጅ እንደቀፈሉ ደጋግመው ሲናገሩት ያሳዝናል” እግራችን እስኪንቀጠቀጥ ቆመን ሰርተን ያመጣነውን ገንዘብ ሳያሳዝነን ለቤተክርስቲያን የሰጠን እኛ ምዕመናን እኮ ነን፡፡ የሚያሳዝነው እኛን በአንድ ቤተክርስቲያን የምንገኝ አብረነዎት የሰራን ልጆቾትን አንድ ማረግ ሳይችሉ እንዴት ነው ሰሜን አሜሪካን ሊመሩ የመጡት … ፡፡ “ማፈሪያ ማፈሪያዎች ናችሁ … ማፈሪያዎች” እያሉ ከዱርዮ እንካን የማይጠበቅ ቃላት ሲደጋግሙት እኛ በንዴት አንድ ቃል እንድንናገር እና በፓሊስ ለማባረር እንደሆነ ይገባናል፡፡ “እዛው በየቤታችሁ ቅሩ” ያሉንም ለዚሁ ነው፡፡ እኛ ግን ከእግዚአብሔር ቤት ወዴትም አንሄድም ይልቁንም ጳጳስ ነዎት ብለን የሸፋፈነውን ጉድ ማውጣት ካስፈለገ አውጥተን በህግ ሁላችሁንም እንፋረዳለን፡፡ የተዘረፈው ገንዘብ ፤ የደማው ልብ ሁሉ ይቅርታ ጠይቃችሁበት መፍትሔ እስካልሰጣችሁት ድረስ ሕግ እንዲገዛችሁ ያስፈልጋል፡፡

    አሁንም የእግዚአብሔር ቤት የጸሎት እና የእምነት ቤት ናትና የራሳችሁን ዲስኩር በአውደ ምሕረቱ ከመስበክ ተቆጠቡ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ አስተምሩን፡፡

    ከተቆርቋሪ አንዱ …

    ReplyDelete