Wednesday, October 31, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ ሐሳቦች


 • READ THIS NEWS IN PDF.
 • የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ “ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ እያለ ራሱን የሚጠራው” የሚለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ተ.ቁ (2) “እኛንም አላስደሰተንም፤ እንዲስተካከል እናደርጋለን”ሲሉ ሌላው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ደግሞ እንዲህ ያለው ቃል ከጋዜጠኞች በፊት ምልአተ ጉባኤው በተናበበው የመግለጫው ክፍል ላይ እንዳልነበረ ተናግረዋል
 • “ስድስተኛውን ፓትርያርክ በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ እየተዘጋጀን ነው ያለነው፤ ሕጉን ካጸደቅን በኋላ ወደ ምርጫው ነው የምንገባው፤ በውጭም ያሉት ተቀብለውን፣ በውስጥም ያለነው ተቀብለናቸው ከእኛው ጋራ ምርጫውን እንዲያካሂዱ ፈቃደኞች ነን፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
 • “ጳጳስ ንብረት የለውም - ጎመን የሚዘራበት፣ ሽንኵርት የሚተክልበት፤ ንብረቶቹ ምእመናን ናቸው፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄ የመለሱት/

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ መግለጫም በማውጣት ተጠናቀቀ • ምልአተ ጉባኤው የዕርቀ ሰላሙንአምስት የመነጋገሪያ ነጥቦች ለይቷል፤
 • ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባን፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትን ይመራሉ፤
 • “የመነኰሳት መተዳደሪያ ደንብ” ይወጣል፤ የገዳማት ተወካዮች በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉና ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤
 • ለአኵስም ጽዮን ማርያም አዲስ ንቡረእድ ይሾማል፤
 • ለካህናት ማሠልጠኛ፣ ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች (ብር 10 ሚልዮን+) እና ለሌሎችም የልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ከብር 128 ሚልዮን በላይ በጀት ተመድቧል፤

Monday, October 29, 2012

የቅ/ሲኖዶስ የቅዳሜ ውሎና ውሳኔዎች፤ ስብሰባው አልተጠናቀቀም • READ THIS NEWS IN PDF.
 • ቤተ ክህነታችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአጭር እና የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅድያዘጋጃል፤
 • ለአዳሪ እና አብነት ት/ቤቶች ማጠናከርያ 10 ሚልዮን ብር በጀት ተመድቧል፤
 • የካህናት ማሠልጠኛዎች በየክልሉ ይቋቋማሉ፤ በየቋንቋዎቹ የመጽሔቶችና ጋዜጦች ኅትመት ይጀመራል፤
 • የሥርዐተ ምንኵስና አፈጻጸም በየገዳማቱ ሕግ መሠረት ጠብቆ “ልማት እንዲጠናከርባቸው” ይደረጋል፤
 • የጋዜጠኛ መ/ር ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር “ብፁዓን እነማን ናቸው?” መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብበት ተወስኗል፤
 • የአቡነ ጳውሎስ “ንብረት” ተሰብስቦ ወደ ሙዝየም እንዲገባ ተወስኗል፡፡ ሐውልታቸውስ?
 • ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል  የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ጸሐፊ የኾኑትን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን ከሥልጣነ ክህነት በማገድ የወሰዱት ርምጃ “በግል ጥላቻ የተገፋ ነው”ያለው ምልአተ ጉባኤው ካህኑም ሊቀ ጳጳሱም ለዕርቀ ሰላሙ በሚያመሩት ብፁዓን አባቶች አቀራራቢነት ተነጋግረው መፍትሔ እንዲሹ ትእዛዝ ሰጠ
 • በሕገ ወጡ የዋሽግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ላይ አስቀድሞ የተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ “የጽ/ቤቱ ባለሙሉ ሥልጣን” በሚል በአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ተሹሞ የነበረው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከተሰጠው ሓላፊነት ተወግዶ በቃለ ዐዋዲው መሠረት አዲስ ሥራ አስኪያጅ እንዲሾም ተወስኗል
 • የአቡነ መቃርዮስ የኤርትራ ጉብኝት እንደማይወክላቸው በስደት የሚገኙት አባቶች ገለጹ፤
 • በድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የሀ/ስብከቱን የአስተዳደር ችግር የሚያጠራው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ልኡክ ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡

Saturday, October 27, 2012

የቅ/ሲኖዶስ የሰሞኑ ውሎ ሪፖርታዥ • በግብጹ የፓትርያርክ ምርጫ ቤተ ክርስቲያናችን በአምስት ብፁዓን አባቶች ትወከላለች
 • የጠ/ቤ/ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያ እንዲጠና ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ሰጠ::
 • የውጭ ግንኙነት መምሪያ በክፍለ አህጉር ዴስኮች ይደራጃል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚዳስስ መጽሔት በእንግሊዝኛ ቋንቋ  ይጀምራል::
 • “አዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት መከፈሉ አስተዳደራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ይቀርፋል፡፡” /የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/
 • ሢመተ ፓትርያርክ በምርጫ ወይስ በዕጣ? ከግብጽ ምን እንማራለን?

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 16/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 26/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 25 ቀን 2005 (እ.አ.አ ኖምበር 4 ቀን 2012) በሚካሄደው የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 118 ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚገኙ አምስት ብፁዓን አባቶችን በልኡክነት መሠየሙን የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ አስታወቀ፡፡

የፓትርያርክ ምርጫ ሕግን በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶሱ በኅዳር ወር መጨረሻ ልዩ ስብሰባ ይጠራል


አርእስተ ጉዳይ፡- 
 • READ THIS ARTICLE IN PDF
 • የግብጹ ፓትርያርክ ምርጫ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደ ካይሮ ያመራል፤ በምርጫው ይሳተፋል፤
 • የጠ/ቤ/ክህነቱ ‹የጨለማ ቡድን› የተቋማዊ ለውጡን አመራር ለመቀልበስ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ፤
 • በወኅኒ ቤት የሚገኙ መነኰሳት ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ኾኗል፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው ከ70 ያላነሱ ‹መነኰሳት› ይገኛሉ፤
 • ገዳማት የመነኮሳታቸውን ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎቻቸውን ለአህጉረ ስብከትያሳውቃሉ፤ መነኰሳት መታወቂያ እንዲኖራቸውና ከቦታ ወደ ቦታም ያለደብዳቤ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል፤
 • ከአብነት ት/ቤቶች ጋራ የተያያዘው የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት ክትትል ይካሄድበታል፤ የአብነት ትምህርት መለኪያ ተበጅቶለትና በየቋንቋው መምህራን ተመድበው መምህራን በየጊዜው የሚስመርቋቸው ደቀ መዛሙርት በምደባ በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዲመደቡ ይደረጋል፤
 • ምልአተ ጉባኤው በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያጣራው ልኡክ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲያመራ አዘዘ፤ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ስም በማጥፋት የኮሚቴውን ተልእኮ የሚያደናቅፉ ሕገ ወጥ ቡድኖችን እያደራጁ ነው፤
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤

Wednesday, October 24, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባጸደቃቸው በ20 አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው


 • ዕርቀ ሰላሙ የምልአተ ጉባኤው ግንባር ቀደም አጀንዳ ነው::
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ላይ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል::
 • ንቡረእድ ኤልያስ ኣብርሃ ከሓላፊነታቸው ሊነሡ ይችላሉ::
 • በአቡነ ጳውሎስ ዕረፍት የታሸገው መንበረ ፓትርያርክ ጉዳይ ውሳኔ ያገኛል::

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 24/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት የተጀመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ 20 የመወያያ አጀንዳዎችን በማጽደቅ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡


መግባባት በተመላበት መንፈስ እየተካሄደ የሚገኘውና በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ይኸው የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በሁለቱ ቀናት ውሎው ከአምስት በላይ አጀንዳዎች የተመለከተ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ የስብሰባው ምንጮች እንደተናገሩት “ሰላምን በተመለከተ” እና “ሕገጋትን በተመለከተ” በሚል የዕርቀ ሰላሙን ሂደት፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማሻሻልና የቃለ ዐዋዲው የማሻሻያ ሂደት የሚገመግምበት ኹኔታ በመነጋገሪያነት ከተቀረጹት አጀንዳዎች ዋነኞቹ ሲኾኑ “የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ማውጣት” በሚል ቀጣዩን ፓትርያርክ ስለመምረጥ የተመለከተው አጀንዳ ደግሞ በመጨረሻው ተራ ቁጥር ገደማ ከተያዙት ጉዳዮች መካከል ይገኝበታል፡፡ ከእኒህም ጋራ “የዐቃቤ መንበሩን መተዳደርያ ሕግ ማውጣት” በሚል የተያዘ አጀንዳ መኖሩን ለመረዳት ተችሏል፡፡

Tuesday, October 23, 2012

ለሚያያቸው ተዋህዶዋዊ ፤ ውስጣቸው ግን የተሐድሶ ኑፋቄ የሚዘሩ መጻህፍት(አንድ አድርገን ጥቅምት 13 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው ዓመት በወርሀ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አንድ ወሳኝ ውሳኔ መወሰኑን ይታወቃል ፤ በውሳኔውም በርካቶች የተወገዙበት ቀሪዎቹ ደግሞ መዝገባቸው በይደር እንደቆየ የምናስታውሰው ነው ፤ በጊዜው  በፕሮቴስታንቶች እየተደገፉ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በኅቡእና በገሃድ ተደራጅተው ለማፍረስና ለማፋለስ እየተንቀሳቀሱ  ድርጅቶች ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች በመለየት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ የመሰሉት ሰዎችና ላያቸው ማር የተቀቡ ውስጣቸው ግን ነጣቂ የሆኑ ተቋማት ተለይተው መለየታቸው ይታወቃል፡፡

Monday, October 22, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጀመረ


 • የሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው የቀብር ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ:: 

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የ2005 ዓ.ም ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ትናንት ተሲዓት በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ አምስተኛው አንቀጽ ቁጥር 164 በታዘዘው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም የሚጀምረው ምልአተ ጉባኤው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሥራ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት የዕርቀ ሰላሙ ሂደት አስቸኳይ ፍጻሜ ስለሚያገኝበት ኹኔታ፣ በፓትርያርክ አመራረጥ ሕግ ረቂቅ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ካለፈው ምልአተ ጉባኤ በተላለፉ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

Friday, October 19, 2012

31ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው


 • ብፁዓን አባቶችን በጎጥ በመከፋፈል ቀጣዩን ፓትርያርክ በብሔር ማንነት ለማስመረጥ በየሆቴሉ፣ በየመናፈሻው እና በየግለሰቡ ቤት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የሚገደዱበት አቋም እንዲወሰድ ለአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ ቀርቧል
 • በሪፖርት የተካተተው የዋልድባ ጉዳይ በንባብ መዘለሉ ጥያቄ አሥነስቷል
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 7/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 31ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ትናንት፣ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋድ ላይ በመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅትከአራረ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ አመራር በሚሰጣቸው የተሐድሶ መናፍቃን ግንባር ቀደም መሪዎች የተደራጁ ጥቅመኛ ቡድኖች የሽግግር ወቅት አጋጣሚውን ተጠቅመው ብፁዓን አባቶችን በጎጥ በመከፋፈል ቀጣዩን ፓትርያርክ በብሔር ማንነት ለማስመረጥ በየሆቴሉ፣ በየመናፈሻው እና በየግለሰቡ ቤት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የሚገደዱበት አቋም እንዲወሰድ ለአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ ቀርቧል፡፡

ዋልድባና የመንግሥት ተግዳሮቶች


በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ብዙ ነገሮች መርፈዳቸው ያስታውቃል። ዛሬ ስለ ሃይማኖት፣ መንግስት፣ ልማት፣ ወዘተ አዲስ ማብራርያ መስጠት  በራሱ እንዲህ ብዪ ነበር ለማለት  ያህል የተሰነዘረ የቃላት ስብስብ ብቻ እየመሰሉኝ ከመጡ ከረምረም ብሏል
ዛሬ ላይ ሆነን የነገን ተስፋ ስናማትር  እንደትውልድ እና ሀገር የማያስቀጥሉን ጋረጣዎች ከፊታችን ተቀምጠው በትክክል አፍጠው እየመጡ ነው። አላየንም ብሎ  ችግሩን ላለመተው ሰው መሆን ብቻውን አስገዳጅ  መመዘኛ ይመስለኛል። ድሮ ድሮ ቤተመንግሥቱ ሕዝብ ምን እያለ እንደሆነ ለማወቅም ሆነ የተከፋበትን ጉዳይ ለመረዳት ነገሥታቱ ''እረኛ ምን አለ?'' ብለው ጉድለታቸውን ይለኩበት ነበር አሉ ዛሬ ደግሞ ምናልባት ''ፌስ ቡክ ምን አለ? ኢንተርኔት ምን አለ?'' ሳይሆን አይቀርም። የሚያሳዝነው  ግን መፍትሄ ለመስጠት ሳይሆን ማን ከነማን ጋር ቆመ? ለማለት መሆኑ ነው።
ሰሞኑን ሀገራችን በቤተ እምነቱና ቤተ መንግሥቱ በሁለት ጎራ ሆነው ቤተ መንግስቱን እየሞገቱት ነው። አንድም እስልምና እምነት ተከታዮች ወንድሞቻችን  ''መጅልሱ'' ይውረድ ብለው ባቀረቡት ጥያቄ፣ ሌላም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን መነኮሳት አባቶችና ምእመናን  ''የዋልድባ ገዳም ይዞታ  ይከበር'' ብለው። ለሁለቱም ቤተመንግሥቱ መልሶችን ሰጥቷል መልሶቹ ግን አስገራሚ፣ አስደናቂ እና አሳዛኝም  ናቸው። የሚመሩትን ሀገር ባህልና አምነት በአግባቡ አለመረዳት ለካ ምን ያህል ትልቅ በሽታ ነው ጎበዝ!። የችግሩ ዋነኛ መነሻ ይሄው  አትዮጵያን ለማወቅ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር አልያም ህብረተሰቡ ውስጥ እይተከባበሩ ማደግን የግድ ይላልና።

የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስለ እርቀ ሰላሙ ያወጣው መግለጫ


                                                                                                                        
                                                                 ጥቅምት 7/2005 ዓ.ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

የአባቶቻችንን ትእዛዝ መፈጸም እና ለተጀመረው እርቀ ሰላም መሳካት የልጅነት ድርሻችንን መወጣት መንፈሳዊ ግዴታችን ነው!
በሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ
ቤተክርስቲያናችን የሰላም እና የአንድነት መሠረት ነች። ሰላም እና አንድነት ከቤተክርስቲያን ተለይተው የሚነገሩም ሆነ የሚሰበኩ አይደሉም። ሆኖም ተክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ የተፈራረቁባት ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ህልውናዋን ሲጋፉ ፣ሰላም እና አንድነቷን ሲፈታተኑ ቢኖሩም በጌታችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለተመሰረተች እና የክርስቶስን አርአያ በተከተሉ ጽኑአን አባቶች ሰማእትነት ተጠብቃ ስለቆየች ሳትጠፋ እኛ ዘመን ላደርሳለች። ነገር ግን የዘመኑን የቤተክርስቲያን ፈተና ለየት የሚያደርገው ፈተናው የልጆችዋ መለያየት መሆኑ ነው። ይህም ልጆችዋ በአንድ የአስተዳደር ጥላ ውስጥ ሆነን ሥርዓተ አምልኮአችንን እንዳንፈጽም እና ለመጪው ትውልድ መተላለፍ ያለበትን ትውፊት እና የተቀናጀ የቤተክርስቲያን አስተዳደር እንዳናቆይ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል።

Tuesday, October 16, 2012

የየራሳቸውን “ፓትርያርክ ለመሾም” ሙከራ የሚያደርጉ …


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 6/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 16/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አንድነት አስፈላጊነት ከምንም በላይ በሁሉም ዘንድ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ነው። በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም “አንድነት፣ እርቅ” የሚሉት ቃላት ተደጋግመው በመሰማት ላይ ናቸው። የቀጣዩ ፓትርያርኩ ጉዳይ ከእርቅ እና ከአንድነት በኋላ እንጂ በችኮላ አሁን መሆን እንደሌለበት አጽንዖት እየተሰጠው ባለው በአሁኑ ወቅት የየራሳቸውን ወገን “ፓትርያርክ” አድርገው ለማስሾም ፍላጎት አላቸው የተለያዩ አካላት፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና ስብስቦች በይፋ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ከመንግሥት እንጀምር።

አቡነ ጎርጎርዮስ

መንግሥት
መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን አስመልክቶ ያለውን የቆየ እና መሠረት የያዘ አቋም በተመለከተ ከዚህ ቀድሞ ሰፊ ሐተታ ማቅረባችን ይታወሳል። ያላነበበ ካለ ከዚህ (LINK) ያገኘዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመንግሥትን አቋም አስመልክቶ ወይም በመንግሥት ስም ስለ ዕርቀ ሰላሙ ሂደትና በቀጣዩ ፓትርያርክ መመረጥ ዙሪያ የሚሰማው መረጃ የተቀላቀለ ነው። (የሚባለውን በርግጥ የሚያደርገው ከሆነ ከሕገ መንግሥቱ ጋራ የሚጋጭ ነው፡፡) የአራተኛውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ አገር ቤት የመመለስ ፍላጎት “በራሱ መንገድ አረጋግጧል” የተባለው መንግሥት÷ ቅዱስነታቸው ወደ አገር ቤት ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት በአዎንታዊነት ተቀብሎ ሲያበቃ የቅዱስነታቸው ፍላጎት ምንም ይኹን በአባትነታቸው በመንበሩ ተቀምጠው ማየት እንደማይሻና ዕርቀ ሰላሙ ይህን ሳይጨምር ሊፈጸም እንደሚችል አቋም ይዟል መባሉ ግን አሳሳቢ ኾኗል፡፡ ከዚህ ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ቀጣዩን ወይም ስድስተኛውን የፓትርያርክ ምርጫ እንድታከናወን፣ እንድታከናወን ብቻ ሳይሆን በዚሁ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወቅት ቀን ቆርጣ በፍጥነት እንድታከናወን እንደሚሻ ነው የሚነገረው፡፡

Monday, October 15, 2012

ዐቃቤ መንበሩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት አደረጉ(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 5/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 15/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ የውይይት መሥመሩን ያመቻቸው በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል ዕርቀ ሰላም ወርዶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት ይጠበቅ ዘንድ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው “የሰላምና አንድነት ጉባኤ” ነው፡፡ በሁለቱ አባቶች የስልክ ውይይት÷ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ጋራ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፤ ከአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አብረው መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡

Friday, October 12, 2012

ቅ/ሲኖዶስ የድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የሚያጣራ ኮሚቴ አቋቋመ

የድሬዳዋ ሳባ ደ/ኀ/ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን


 •    በቅ/ሲኖዶሱ አቋም የተደሰቱት የደብሩ ካህናት፣ ምእመናንና የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አባላት አጣሪ ኮሚቴውን ለማገዝ ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል።
 •    ኮሚቴው ማጣራቱን እስኪያጠናቅቅ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ሥ/አስኪያጅ እና የደብሩ አስተዳዳሪ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ታግደው እንዲቆዩ ተወስኗል።
 •      ጉድለቱ ከብር 1.8 ሚልዮን አሁን ከብር 5.6 ሚልዮን በላይ ደርሷል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 1/2004 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 11/2012/ READ IN PDF)፦ ከቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያዎች፣ በዕርቀ ሰላም እና በቀጣዩ ፓትርያርክ ሹመት የቅድመ ዝግጅት ምዕራፎች ላይ አበክሮ እየሠራ የሚገኘው ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው ፀረ - ሙስና አቋም ያላቸውን አገልጋዮች ለበለጠ ተጋድሎ የሚያነሣሣ፣ ምእመኑም በአመራሩ ላይ ያለው እምነት ይጠናከር ዘንድ ታላቅ ተስፋ የሚሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

Thursday, October 11, 2012

ፓትርያርክ ምርጫ እስከ ሚከናወን ድረስ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር አብረው የሚሠሩት አባላት በእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ተወያዩ
ከጥቅምት 6-11 ቀን 2005 . ጀምሮ ሠላሳ አንደኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ይካሔዳል፡፡
የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋናው ስባሰባ ደግሞ ጥቅምት 12  እንደሚጀመር እየተጠበቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት እንዱና አንገብጋቢው አጀንዳ የፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች እንደሚሆን እየተጠበቀ ነው ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከውጪው ሲኖዶስ ጋር ያለውን እርቀ ሰላም በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ከአቡነ መልከፄዴቅ ጋር ብቻ ውይይት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ሰሞኑን የዋናው ፓትርያርክ ምርጫ እስከ ሚከናወን ድረስ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር አብረው የሚሠሩት ሰባቱ አባላት    ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ወይይት ማድረጋቸው ተነግሯል ፡፡

በውይይቱም አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ በፊት እንደሚገመተው ሁሉ በገዳም መኖርን እንደሚመርጡና አንድ  ጊዜ የተጣሰው ስርዓት እሳቸው በህይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ እንዲመረጥ እንደማይፈቅዱና እሳችው እስኪያርፉ አሁን እንዳለው ቤተ ክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርክ እየተመራች እንድትቆይ እንደሚሹ ማስታወቃቸውን ምንጮቻችን ዘግበውልናል፡፡
ልዑል እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅልን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤  አሜን፡፡

Monday, October 8, 2012

“መሰናዘሪያ” የተባለ ጋዜጣ “አቡነ መርቆሬዎስ ኤርትራን ጎበኙ” ሲል መዘገቡ ለዕርቁ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላል ተባለ

“አቡነ መቃርዮስ”


(ደጀ ሰላም መስከረም 28/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 8/2012; READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሜላቢን ፕሮሞሽን ሓላ/የተ/የግ ማኅበር የሚታተመው “መሰናዘሪያ” የተሰኘ ሳምንታዊ ጋዜጣ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም “አቡነ መርቆሬዎስ ኤርትራን ጎበኙ” ሲል በዜና ገጹ ላይ የተሣሣተ ዘገባ ማውጣቱ ለተጀመረው ዕርቅ እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ ጋዜጣው በስደት ላይ የሚገኙት አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ኤርትራ አምርተው ለቀናት ጉብኝት እንዳደረጉ፣ ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋራ አብረው እንደሚሠሩና ጉብኝታቸው ከዚሁ ጋራ የተያያዘ መኾኑን በመጥቀስ ያቀረበው ዘገባ “ትግራይ ኦንላይን” የተባለውን ድረ ገጽ በምንጭነት በመጥቀስ ነው። ድረ ገጹ “Why was Abune Mekariossent to Eritrea by Ginbot-7 after Prime Minister Meles died? በሚል ርእስ ሴምቴፐር 27/ 2012 ባወጣው ዘገባው ኤርትራን ጎበኙ ሲል የጠቀሳቸው “አቡነ መቃርዮስ”ን ነው፡፡

Wednesday, October 3, 2012

የመስቀል በዓል “ግዙፍነት ከሌላቸው የዓለም መንፈሳውያን ሀብቶች” ተርታ ሊመዘገብ ይችላል • ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ቅርስ የመኾን ዕድሉን ካገኘ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጥበቃና ክብካቤ ይደረግለታል
 • የአ/ /ስብከት አንዳንድ ሓላፊዎች ለዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል የሰጡትትኩረት አከባበሩን በማዳከም የወቅቱን የቅ/ሲኖዶስ አመራር የማስነቀፍ ዓላማእንደነበረው ተጋልጧል
 • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ፖሊስ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራንና አባላትላይ ያካሄደው ፍተሻና በኅትመቶች ሽያጭ ላይ የተደረገው እገዳ ተቃውሞገጥሞታል፤ 
 • የአቶ መለስ ዜናዊ 40 ቀን ተዝካር በታላቁ ቤተ መንግሥትና በጠ//ክህነትይደረጋል፤ 
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- የመስቀል - ደመራ በዓልአከባበር በዓለም ግዙፍነት ከሌላቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ኾኖ እንዲመዘገብ ሲደረግ የቆየው ጥረትበመልካምና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ላይ እንደሚገኝ በመጪው ዓመት ኅዳር ወርምኢትዮጵያ ለዩኔስኮ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ተቀባይነት አግኝተው የመስቀል - ደመራ በዓልየመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ (World Intangible Heritage) ኾኖ እንደሚመዘገብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንአስታወቀ፡፡