በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ብዙ ነገሮች መርፈዳቸው ያስታውቃል። ዛሬ ስለ ሃይማኖት፣ መንግስት፣ ልማት፣ ወዘተ አዲስ ማብራርያ መስጠት በራሱ እንዲህ ብዪ ነበር ለማለት ያህል የተሰነዘረ
የቃላት ስብስብ ብቻ እየመሰሉኝ ከመጡ ከረምረም ብሏል ።
ዛሬ ላይ ሆነን የነገን ተስፋ ስናማትር
እንደትውልድ
እና ሀገር የማያስቀጥሉን ጋረጣዎች ከፊታችን ተቀምጠው በትክክል አፍጠው እየመጡ ነው። አላየንም ብሎ ችግሩን ላለመተው
ሰው መሆን ብቻውን አስገዳጅ መመዘኛ ይመስለኛል።
ድሮ ድሮ ቤተመንግሥቱ ሕዝብ ምን
እያለ እንደሆነ ለማወቅም ሆነ የተከፋበትን ጉዳይ ለመረዳት ነገሥታቱ ''እረኛ ምን አለ?'' ብለው ጉድለታቸውን ይለኩበት ነበር አሉ ። ዛሬ ደግሞ ምናልባት ''ፌስ ቡክ ምን አለ? ኢንተርኔት ምን አለ?'' ሳይሆን አይቀርም። የሚያሳዝነው ግን መፍትሄ
ለመስጠት ሳይሆን ማን ከነማን ጋር ቆመ? ለማለት መሆኑ ነው።
ሰሞኑን በሀገራችን በቤተ
እምነቱና ቤተ መንግሥቱ በሁለት ጎራ ሆነው ቤተ መንግስቱን እየሞገቱት ነው። አንድም የእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድሞቻችን ''መጅልሱ'' ይውረድ
ብለው ባቀረቡት ጥያቄ፣ ሌላም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን መነኮሳት አባቶችና ምእመናን ''የዋልድባ ገዳም
ይዞታ ይከበር'' ብለው።
ለሁለቱም ቤተመንግሥቱ መልሶችን ሰጥቷል ። መልሶቹ ግን አስገራሚ፣ አስደናቂ እና አሳዛኝም ናቸው። የሚመሩትን
ሀገር ባህልና አምነት በአግባቡ አለመረዳት ለካ ምን ያህል ትልቅ በሽታ ነው ጎበዝ!። የችግሩ ዋነኛ መነሻ ይሄው አትዮጵያን ለማወቅ
ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር አልያም ህብረተሰቡ ውስጥ እይተከባበሩ ማደግን የግድ ይላልና።
በሁለተኛው ዓለም ጦርነት መዳረሻ በ1928 ዓም ኢትዮጵያ በኢጣልያ ተወራ በነበረችበት ወቅት የኢትዮጵያ መወረር
ካንገበገባቸው ብርቅዬ የባህር ማዶ ሰዎች መሃከል አንግሊዝያዊትዋ ወ/ሮ ሲልቭያ ፓንክረስ ይጠቀሳሉ። አኚህ የ ኢትዮጵያ ታሪክ ምሁሩ የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስ እናት ከነፃነት በሁዋላ ኢትዮጵያ መኖራቸውና ቀብራቸውም አዲስ አበባ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ መሆኑ ይታወቃል። አሁን ግን ልነግራችሁ የፈለኩት ስለ ወ/ሮ ሲልቭያ ፓንክረስ የልጅ ልጅ አሉላ ፓንርክረስ ነው። አሉላ በኢትዮጵያ ታሪክ የተሳበ ወጣት ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤ በራሱ የሚማርከው ወጣት ነው። ባልሳሳት ከስድስት
ዓመት በፊት ይመስለኛል ከአዲስ አበባ ከ5oo
ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ የገጠር አንዲት ከተማ ከመስርያቤቴ ባልደረቦች ጋር ባንድነት ገዳም ለመሳለም
በሄድኩበት ጊዜ አዳፋ ጋቢ
ለብሶ በከተማዋ መንገድ ላይ ሲሄድ አየሁት። እኔና ጉአደኞቼ በሚቀጥለው ቀን ለሚኖረን ጉዞ ለመዘጋጀት በጊዜ እራት በልተን ለመተኛት እራት የሚገኝበትን ቤት እያሰስን
ነበር። ከእዚህ በፊት በቴሌቭዥን የማውቀው አሉላ ለምን እዚህ መጣ ? ደግሞስ
ለምን የአደፈ ጋቢ አርጎ ይሄዳል? እኔና ጓደኛዬ ግራ ተጋባን።በኃላ ግን ተጠግተን ሰላምታ ተለዋውጠን እራት አብረን
እንድንበላ ጠየቅነው አላቅማማም እሺታውን ገለፀልን። በእራት ሰዓታችን በተቀላጠፈ አማርኛው ሁሉን ተረከልን። ባጭሩ እርሱ የ ''ሶሻል ዎርክ''ትምርቱን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እያጠና መሆኑን፣ አሁን እዛች ከተማ ውስጥ ከመጣ አራት ወራት ማስቆጠሩን፣ለጥናቱ እንድረዳው ትንሽ ቤት ተከራይቶ
መንደር ውስጥ እንደሚኖር እና ይህም ለጥናቱ አስተዋጽዖ እንደሆነ ተረከልን። በነገራችን ላይ አሉላ ጥናቱን ሲሰራ ከህዝቡ ጋር አብሮ እየኖረ፣ ጠላ ቤት አብሮ እየሄደ፣ ጠጅ ቤት አብሮ እየጠጣ መሆኑን ሲነግረን። ህዝብን ማወቅ ሁሉን ነገሩን መሆን እንደሚገባ ትልቅ ተሞክሮ የሚያዝበት መሆኑን ያስተምረናል። ለእዚህ ነው
ኢትዮጵያን ለማወቅ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር አልያም ኅብረተሰቡ
ውስጥ እየተከባበሩ ማደግን የግድ የሚለው።
ሃይማኖት ናመንግሥት እስከ ደርጉ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ቤተመንግስት ከቤተ ክህነት ጋር ባብዛኛው እየተባበሩ አልያም ቤተ ክህነቱ ቤተመንግሥቱን
እየመከረ ቤተመንግሥቱም
እየተመከረ ኖረዋል። ይህ ሁኔታ በ1966ቱ አብዮት ድረስ ቀጥሎ ታይቷል። የአብዮቱ መምጣት ቤተ ክርስትያን የነበራትን የመሬት ምሪት (ምንም የቤተ ክርስትያን
ይዞታዋን በቀጥታ አላዘዘችበትም
የሚሉ ቢኖሩም) መወሰዱ በ ምመናን አስተዋፅዖና በአዲሱ የቤተክርስትያን መዋቅር '' የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ'' በሚል እራሷን ለመቻል ጥረት አደረገች። በዚህ
ብቻ ለምግፋት አለመቻሏን ያየ ደርግም በአካፋ ንብረቷን ወስዶ በማንክያ በዓመት የሁለት
ሚልዮን ብር ድጎማ ለቤተክርስትያን ይሰጥ እንደነበር በወቅቱ ጉዳዩን የሚያውቁ የሚናገሩት ነው። በዘመነ ደርግ ቤተክርስትያን እምነቷን ለማስፋፋት ከኮሚኒስታዊ አስተሳሰብና ፍልስፍና አንፃር ፊት ለፊት የተጋፈጠችበትቅ፣ ቅዱስ
ፓትርያርኩ ሰማዕትነት የተቀበሉባት፣ ብዙዎች አንደ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ጌጡ
(አሁን በስዊድን ስቶኮልም የሚገኙት) በባሌ ጎባ ከተማ እግዝያብሔር አለ ብለው ለሃይማኖታቸው በአደባባይ ተናግረው ለእስር የተዳረጉበት፣ ለደርግ ቅርበት ያላቸው የሶሻሊስት ርዕዮት አቀንቃኝ የነበሩት ልጆቻቸውን ክርስትና ለማስነሳት ፈርተው በድብቅ የምፈፅሙበት ቤተክርስትያንና ምዕመኖችዋ አሳዛኝ ወቅት ላይ የነበሩበት ጊዜ ነበር።
ይህ በእንዲህ እያለ ግን ደርግ የሃይማኖትን በህብረተስቡ ውስጥ ያለውን ሚና አልረሳውም። እንደ ወቅቱ አገላለጽ ኅብረተሰቡ
በኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ '' 'እስኪነቃ' ድረስ ሃይማኖትን አለማራቅ'' የሚል ''ራሽያዊ''
አስተሳሰብ ነበረው። ለዚህም ይመስላል የእስልምና አና የክርስትና ሃይማኖቶች መሪዎች በወቅቱ ''ብሔራዊ ሸንጎ'' ተብሎ በሚጠራው የመንግሥት ምክር ቤት ስብሰባ
እንዲገኙ የሚያደርገው። በነገራችን ላይ የወቅቱ ምክር ቤት የይስሙላ ምርጫ ''ኢሠፓ'' (የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ ) ያሸነፈው
ወንበርና ባለፈው ምርጫ ኢህአዴግ አሸነፍኩ ካለው የምክር ቤት ወንበር ብዛት
መካከል ያለው ልዩነት የደርግ ከአንድ ፐርሰንት በታች የሚበልጠው መሆኑ ነው። ይሄውም ደርግ መቶ ፐርሰንት ሲያሸንፍ አህአዴግ ግን ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ምናምን ፐርሰንት ማሸነፉ ነው።
ሃይማኖትና መንግስት በዘመነ ኢህአዴግ
ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በጣም የሚፈራቸው (ሊገቡት ስላልቻሉ ሊሆን ይችላል) ግን ሊፈራቸው የማይገባው የነበሩ ሁለት ነገሮች አሉ። እነርሱም- የመጀመርያው ''ምርጫ'' ሲሆን ሁለተኛው '' ሃይማኖት'' ነው።የምርጫው ይቆየንና ሃይማኖትን ግን ለምን ይፈራዋል? ብለን ስንጠይቅ ስለ ሁለት ምክንያቶች መሆኑ ይታዩኛል። እነርሱም
:-
፩- ኢህአዴግ በመዋቅሩ የሃይማኖት አስተምሮቱም ሆነ ትምህርቱ ያላቸው ሰዎች በአመራር ደረጃ አለመኖር።
ኢህአዴግ በከፍተኛ አመራሩ ደረጃ ያሉት አባሎቹ ማለ- ሊግ ፣ግምገማ ናየራስን እድል በራስ መወሰን፣ወዘተ በሚሉ ሃሳቦች አንጂ የ ሞራልም ሆነ
ሃይማኖታዊ መሰረቶች ቦታ የላቸውም። አዚህ ላይ ለማስረጃ ቢሆነን ባለፈው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ አና አቡነ ጳውሎስ መካከል በተነሳው ውዝግብ መንግስት ቢያንስ ቤተክርስቲያኒቱን
የሚያውቁ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የተመሰከረላቸው ባለሥልጣን ስላላገኘ ሊቃነ ጳጳሳቱ ፊት ጠረንዼዛ አየደበደበ
የሚያስፈራራ ሰው ልኮት አረፈው። አባቶችን አክብሮ ትህትና በተሞላ ማነጋገር ሃይማኖተኛነትን
ሳይሆን ኢትዮጵያነት ማስረጃ ነው። ሌላው ማሳያ
የቤተክርስቲያኒቱን
ጉዳይ በተመለከተ ሁሉ የሚያማክራቸው የ ''እኔ ናቸው '' ብሎ
የሚያስባቸውን የቤተክህነቱን ፊታውራሪዎች ብቻ አንጂ ከስር ምን ችግር አንዳለ ህዝቡ ምን እንደሚያስብ ያወቀ ቢመስለውም አንዳላወቀ ተግባሩ እና ለነገሮች የሚሰጠው ምላሽ ያሳብቅበታል።
፪-ሁለተኛው ሃይማኖትን
የሚፈራበት ዋነኛ ምክንያት የቤተክርስቲያን አደረጃጀትና አስተምሮ
ከኢህአዴግ ክልልን መሰረት ያደረገ አሰራር በሚከተል መልክ ቤተክርስቲያኒቱም እንድትቀኝ መመኘቱ ነው። ቤተክርስቲያን
ከሞያሌ እስከ ደብረዳሞ
ከሐረር እስከ
ኢሉባቦር
ድረስ ቅዳሴዋ፣ አስተምሮዋ ሁሉ ዘርና ቋንቋ ሳትለይ ለሁሉ እናት መሆኗ፣ የቀደመው የሀገሪቱ ታሪክ፣ትምህርት፣ ፍልስፍና፣ ነፃነት ሁሉ በአሻራነት መያዝዋ - ኢህአዴግ አዲስ ታሪክ ለመፍጠር ከሚሞክረው ሙከራ ጋር እየተጋጨ ብዙ ጊዜ ስላነጠረበት ቤተክርስትያንን በበጎ ዓይን ከማየት በሂደት ወደሚፈልገው አካሄድ እንድትሄድ በቤተክህነት፣ በአጥብያ አብያተክርስቲያናት
እና በመንፈሳዊ ማኅበራት ውስጥ ጭምር ካድረዎቹን እያስገባ ምዕመናንን ቁም ስቅል ማሳየት ተያይዞታል።
ለዚህም ማሳያው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተጠመቁ ካድሬዎች ቤተክህነቱን እንደፈለጉ ሲንፈላሰሱ፣ የሊቃነ ጳጳሳትን ማደሪያ በር እየሰበሩ ሲደበድቡና ሲያስፈራሩ ፣ የስልክ ዛቻ ሲፈፀም ሁሉ ጉዳዩን ለምርመራ አቅርቦ ለሕዝብ ከማሳየት ይልቅ እንደዋዛ ማለፍ የተጠቀመበት የአጉል ብልጣብልጥነት መንገድ ነበር።
''ኢትዮጵያ - የእግዚአብሔር የምስጢር ሃገር''
በኢትዮጵያ
ሁኔታ ሃይማኖት የእድገት ትልቅ መሳርያ የሚሆንበት ብዙ አይነት እድሎች ነበሩ።
የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን በመዋቅር ደረጃ ብንመለከት ከቤተመንግሥት
እስክ ገጠር መንደር ድረስ መዋቅር ያላት፣ በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ የያዘች፣ በያንዳንዱ ሰው ዘንድ የመሰማት እና ተፅእኖ የመፍጠር አቅም ያላት ፣ የሀገሪቱን የቱሪዝም
እንዱስትሪ ከሰማንያ በመቶ በላይ ድርሻ ያላትን ትልቅ ተቋም በፍርሃት ማየትና የልማት አጋር አለማድረግ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን በሚፈለገው መንገድ ለመቅረፅ የመሞከር አጅግ አስፈሪ ተግባር ነው። እርግጥ ነው ቤተክርስትያን የአስተዳደራዊ መዋቅር ችግሯ ሁሉ ከኢህአዴግ ችግር ብቻ የሚነሳ ነው ለማለት አይቻልም። ግን በነበረው ችግር ላይ ቤተክርስትያን መፍትሄ እንድትፈልግ እድል ከመስጠት ይልቅ
የባሰ ሌላ የቤት ሥራ መስጠት ምን የሚሉት ፈልጥ ይሆን?
''ኢትዮጵያ የአግዚአብሔር የምስጢር ሀገር'' ይህን የተናገሩት በ1982 ዓም በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ነበሩ ለዚህም ምክንያት ነበራቸው። ሀገራችን ከክርስቶስ
ልደት በፊት በሕገ - ልቦና (ሰዎች አምላካቸውን በልቦናቸው ያወቁበት)፣ በሕገ -
ኦሪት (በሙሴ አስርቱ ትዛዛት ሕግ ስር አክብራ የኖረች
መሆኗ) እና በሕገ -
ወንጌል አምልኮተ -
እግዚአብሔርን
ስትፈጽም
የነበረች አሁንም ያለች ሀገር ነችና አንዲሁም የሚወዱትንና የሚሳሱለትን ነገር
በሚስጥር ቦታ እንደሚሸሽጉት ታቦተ ፅዮንን ከእስራኤል አምጥቶ፣ ሃብተ ንግስናን ከዳዊት አምጥቶ፣ ሃብተ ትንቢትን ከነቢያት አምጥቶ፣ ሐዋርያነትን ከቅዱስ ፊልጶስ ዝማሬ መላዕክትን
በቅዱስ ያሬድ አምጥቶ ሸሽጎባታልና የሚስጥር ሃገሩ
ትባላለች። ይህ ብቻ አደለም ክርስትናን በዓለም ላይ ከምድረ እስራኤል ቀጥላ ጌታችን ገና ባረገ በዓመቱ በ34 ዓም የተቀበለች (በጃንደረባው አማካይነት)
ሀገርም ነችና የእግዚአብሔር የሚስጥር ሀገር ትባላለች።
ይህች ሀገር የራሷ የሆነ የአኗኗር፣ አመጋገብ፣ አለባበስ፣ አነጋገር፣ ሰላም አፈጣጠር፣ እራሷን የመከላከል ብልሃት ፣ ሀገርኛ የሆነ አሸመጋገልና የመንግሥት አስተዳደር ባህል ያላት ሀገር ነች። ኢትዮጵያን ለማወቅ መጀመርያ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መፈጠር አለበለዝያ ኅብረተሰቡ
ውስጥ እየተከባበሩ ማደግ የግድ የሚሉት ሁለቱ መስፈርቶች ናቸው። ከእዚህ ውጭ ግን ሁል ጊዜ ጉዳዩ ሁሉ ''ሾላ በድፍን'' እንደሆነ መቅረት ደግሞ ሌላው እድል
ሊሆን ይችላል።
ገዳማዊ አባት
''ስኳር አንፈልግም ብለን ገዳም ብንመጣ
ዛሬስ ከነ አካሉ ስኳር ታጥቆ መጣ '' የዋልድባ ገዳም አባቶች
ከላይ ከተውሱት ጉዳዮች አንፃር በዋልድባ ገዳም ጉዳይ የሰሞኑ የመንግሥትን ተግዳሮት ስንመለከተው የእስካሁኑ ተከታይ ግን ከወትሮው በበለጠ ድፍረትና ተጠያቂነት ያጣና ግራና ቀኙን ያላገናዘበ የይድረስ ይድረስ ሥራ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው ። ጉዳዩን እንደምናውቀው መንግስት የገዳሙን (ዋልድባ ገዳም) አንድኛውን ክፍል
በማይ ፀብሪ በኩል በነካ
መልኩ የስኳር ፋብሪካና የፖርክ ይዞታ አቋቁማለሁ ብሎ ለፋብሪካው የሚረዱ ስራዎችን እየሰራሁ ነው ማለቱና የገዳሙ አባቶች ደግሞ እንዲሁም በተለያየ ዓለም ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ''ቦታው የቃል ኪዳን ቦታ ነው ገዳሙ ሃጥያት የማይሻገርበት ፣ ዘር የማይዘራባት፣ እህል የማይበላባት ቦታ ነው'' ማለታቸው ይታወሳል። በገዳሙ አባቶች የተፈረመ ደብዳቤ እስክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮና ለቤተክህነቱ ድረስ መድረሱን እስካሁን ግን መንግሥት በቴሌቪዥን መነኮሳቱን በ''ፖለቲካ አስተሳሰብ የተወጠሩ'' ምዕመናኑን ደግሞ “ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት” በማለት ለአንድ የሃይማኖት አባቶች መስጠት የሚገባውን ክብር እረስቶ 'እንክያ ሰላምታ' ውስጥ መግባቱ ይታወቃል። ዓለማዊ ኑሮና ምግብ ይቅር ብለው በመነኑ የፈሩትን የዓለም ሁካታና፣ ሆይሆይታ
ለማምጣት ብሎም ከፋብሪካው ተከላ
ጋር ተያይዞ የሚመሰረተው ከተማ ገዳምሙን መጠጋት ለዋልድባ አባቶች ታሪካዊ ስህተት መሰራቱን ያሳየ ክስተት ነበር ።
ከዋልድባ ገዳም ንትርክ የኢህአዴግ
ፖለቲካዊ ትርፍና ኪሳራ ሲሰላ
ረቡዕ መጋቢት 12/2004 ከምሽቱ ሁለት
ሰዓት በአዲስ አበባ አቆጣጠር የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተለመደ ''ጆሮ የሚጠልዝ'' ዜና አሳየን። በሰሜን ጎንደር የተካሄደ አቶ አባይ
ፀሐዬ የመሩት በፊልሙ ላይ
አንደምታየው ወደ አራት ብቻ የሚጠጉ መነኮሳትና
ሌላ ጥቁር ለባሽ የተሰበሰቡበት ስብሰባ ታየ። ሁለት ሰዎች የስኳር ፋብሪካውን አንደደገፉ
ሲናገሩ ተሰማ። ''የማይመስል ነገር ለምንትስ አትንገር'' ይላሉ ይሄው ነው። በዚህ የመገናኛ አገልግሎት በተስፋፋበት ጊዜ የዚህ አይነት የዜና ልዩነት ማንበብ በራሱ ግራ መጋባት ነው። ቀጥሎ አባይ ፀሐዬ አርገውት የማያውቁትን የቴሌቭዥን ጣቢያ
ዜና አንባቢው ጎን
ተቀምጠው ማብራርያ ሰጡን '' ገዳሙ ውስጥ አልገባንም ከዳር ነው ያለነው . . .ወዘተ''።
ከዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር መንግሥት አንድ ስለ ገዳማት ያልተገነዘበው ነገር መኖሩን ነው። ይሄውም ገዳማት (የዋልድባን
ገዳም በልዩ ሁኔታ ቃል ኪዳን
ስላለበት አይዘራበትም፣ አይታረስም አንጂ) ሥራ የምንኩስና
ሕይወት አንዱ አካል ምሆኑና ''መፅሐፈ መነኮሳት'' የተሰኙት መፃህፍትም ስራን ወደ
ሃጥያት ላለማምራት አንዱ ተራጅ መንገድ መሆኑን ነው።
ዋልድባ ያለው አንዱ ጥያቄ በገዳሙ ክልል የመግባት አና አለመግባት ጉዳይ ብቻ አይደለም ከዚህ በዘለለ የገዳሙ መንፈሳዊ ሕይወት ከግንዛቤ መግባት ይገባው ነበር። ይህ ብቻ አይደለም በሰሞኑ የመንግሥት ንትርክ የሚከተሉት ነጥቦች ለመታወቃቸው ወይንም ግንዛቤ አለማግኘታቸው ያስገርማል። አነርሱም-
·
በአካባቢው ሸንኮራ
አደጋ መትከል አደለም ድምፅ ማሰማት የተከለከለ ነው።
·
ዶዘርና ትራክተር
ማርመስመስ አደለም ድምፅን ከፍ አርጎ ማውራት አይገባም።
የብዙዎች ስውራንና ግዑዛን ቅዱሳን አባቶች ባዕት (ሃይማኖት ባይኖረን እንኳን ከሞራል አንፃር ለማየት ቢሞከር) ለዓለም የሚጸልዩ፣ ለሕዝብ የሚጸልዩ፣ ለመሪዎች የሚጸልዩ ቅዱሳን አባቶችን ባዕታቸውን ማስከበር የሚኖሩበትን ፍጹም የጸሎት እና የልመና ቦታ እንዲሆን ማድረግ ሲገባ ለምን? የፀለምት ወረዳ አስተዳዳሪ በአሜሪካ ድምፅ አማርኛው ክፍልም አንዳረጋገጡትና ገዳማውያኑም አንደተናገሩት የቆዩ የቅዱሳን እና ምዕመናን ተረፈ አፅማቸው እየፈለሰ እና አየተፈነቀለ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወሩና ''ቤተሰብ ወደፈለገው ቅዱስ ቦታ ተወሰደ'' ብሎ መናገር ምን አይነት ሞራላዊ ንግግር ይሆን?
መንግሥታችን ከእዚህ
አይነት ሂደት
አንድን ነገር ድርቅ ብሎ ሃሳብን ባለመቀየር ወደፊት ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ አስተማሪ ይሆናል በሚል ግምት ትርፍ አገኛለሁ ብሎ ያስባል። ጉዳዮችን ሁሉ ''ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ''
ፍልስፍና አንፃር ብቻ ከታየ ያውም ለሺህ ዓመታት
የፀናን ሃይማኖት በመገዳደር አና መንግስትን ያህል ተቋም ከዋና ከተማ በብዙ መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ካለ ገዳም ጋር ቦታ መጋፋት ለቤተክርስቲያኒቱ
ሌሎች ይዞታዎች ሊተላለፍ የተፈለገው መልክት ከመንግስት በኩል መኖሩን የሚያሳይ
ይመስለኛል። ይሄ ድርጊት ግን ሕዝቡን ወደ አንድ የግዴታ ጥግ እየመራው ነው። ይህ ደግሞ ቀልድ አይደለም ያ ጥግ ምንድነው? ቢባል አሁን ላይታወቅ ይችላል። አንድ ሰው የራሱን ድመት በር ዘግቶ ባይገርፍ ይመረጣል።ብችል በሩን ገርበብ አርጎ መግረፍ ይሻላል።ድመትቱ ለተወሰነ ጊዜ የክፍሉን ዙርያ አየዞረች ለመሸሽ ትሞክራለች። ዱላው ሲበዛባት ግን የገራፊዋ ጉሮሮ ለመቆም ትገደዳለች። ዛሬ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
የማያዝንላት የለም። እናት ስትጎሳቆልና
ስትገፋ ማን የማያዝን አለ?
''አሳ ለገዳማውያኑ!?''
ለምን አያሳዝን?
የቤተክርስቲያን ከፍተኛው አካል ቅዱስ ሲኖዶስን የሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ነው። በቅዱስ መንፈስ የሚመራ ቅዱስ ሲኖዶስ (ባልፈው ሳምንት የመንግሥት ባለስልጣን በአሜሪካ ድምፅ ራድዮ እንደ ምክርቤት አባል
አጠራር 'ክቡር ሲኖዶስ' አያለ ሲናገር ነበር)
የሚያሳልፈው ውሳኔ ፖትርያሪኩ ሊሽረውም ሆነ ሊያሻሽለው አይችልም። ቅዱስ ሲኖዶስ በሃያ ቀን ይፍረስ ያለው የአቡነ ጳውሎስ ሃውልት ይሄው ሳይፈርስ ሁለት ዓመት ሊሞላው ሲሆን ማዘን ይነስ?
በቤተክህነቱ (በመንግስት ሹመኞች ጋር በተሞዳሞደ መልኩ) ከፍተኛ ሙስና ተስፋፍቶ ሙስናው ቅጥ አጥቶ የካህናት ምደባ በሙስና የተበላሸ ሲሆን ማዘን ይነሰን?
በቤተክርስቲያኒቱ አስተምሮ የተመሰከረላቸው ሊቃውንት በሙስና በተቀጠሩ ቅጥረኞች እየተሰደቡ፣እየታዘዙ ሙሰኞቹ ሲሻቸው ሲያስባርሯቸው
ቤቱን የወንበዴዎች ዋሻ ሲያደርጉት ማዘን ይነስ?
ነጋ ለፀሎት ሲመሽ ለፀሎት በሚተጉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ስብስባ ላይ ተሰብስበው በወሰኑት ውሳኔ ምሽት በራቸው እየተሰበረ፣ የማስፈራርያ ማስጠንቀቅያ እየተሰጠ '' ይሄ የተለመደ ሁኔታ ነው'' ተብሎ ካለ አንዳች ምርመራና ውጤት
ይሄው ሁለት ዓመት ሲሆን ማዘን ይነሰን?
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን እንደ ክፍል ውስጥ ተማሪ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኑን ልኮ ጠረንጴዛ እየደበደበ ሲያስፈራራ ሲውል ማዘን
ይነስ?
በአሰቦትና ዝቁላ ገዳም እሳት ተነስቶ ቤተክህነት ለምን በቶሎ አልደረሰም ሲባል ''እሳት የትም ይነሳል ምነው ቤተክርስትያን ሲሆን እንዲህ ይጋነናል?'' በአራዳ አነጋገር '' ለምን ታካብዳላችሁ?'' መሰል መልስ ሲሰጥ ምነው አያሳዝን?
የ ዋልድባ ገዳም መንግስት እሰራዋለሁ
በሚለው የስኳር ፋብሪካ ገዳማውያኑ 'ከቋርፍ ስር 'ሌላ እንደማይበሉ እየታወቀ ለፋብሪካው
በምንገድበው ግድብ ገዳማውያኑ አሳ በመብላት እንድጠቀሙ እናደርጋለን ተብሎ ሲሾፍባቸው አንዴት አያሳዝን? ''የዋልድባ ገዳም የአርምሞ፣ የጸሎት፣ የጸጥታና፣ የቃልኪዳን ቦታ ነው ሀጥያት የማይሻገርበት፣ ዘር የማይዘራበት ቅዱስ ቦታ ነው'' ብለው በተናገሩ በገዳሙ አቤሜኔት ተወክለው በመጡት አባት ላይ
''የፖለቲካ አላማ አላቸው፣ መንኩሴ አደሉም '' ብሎ መሳለቅ ሲፈፀም ለምን አናዝን?
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስትያን
ላይ የተሰራው ግፍና የማናጋት ሥራ እጅግ አደገኛ ብቻ ሳይሆን ነገ የተደገሰውንም አመላካች ሥራ ነው። በአጠቃላይ የዋልድባው
ጉዳይ የዋልድባን ችግር ብቻ የሚያሳይ አደለም። ይልቁንም የእያንዳንዱ አጥብያ
ቤተክርስትያን ይዞታ ጉዳይ ነው። አንድምታው ለሁሉም ነው። ዋልድባ የእፍታው ማሳያ ነው። እፍታው ከተገላለጠ በኋላ ዋናው ወጥ
ገና እየተሰራ ወይንም ተሰርቶ ሊወጣ መሆኑን አመላካች ነው። ጉዳዩንም እግዚአብሔርን አውቃለሁ የሚል በሙሉ ሊቃወመው ቢያንስ ገዳማውያኑ በዚህች ዓለም በአርምሞ፣ በዝምታ ከአምላክ ጋር ለመነጋገር ፀጥ ያለው ዋልድባ ውስጥ የመፀለይና የማልቀስ ሰብዓዊ መብታቸውን ባይነፈጉ
። እንደ ሰው ማሰብ ተጀመረ ማለት ነበር።
በዋልድባ ገዳም ላይ የአሜሪካ ራድዮ ያቀረባቸው ዘገባዎች ያዳምጡ
1. Waldibba Monastery Reportage by VOA Radio
http://www.youtube.com/watch?v=JLiJ2ADUh_k&feature=related
2. Waldibba Monastery Reportage by VOA Radio
http://www.dejeselam.org/2012/03/waldibba-monastery-3rd-reportage-by-voa.html
አበቃሁ
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment