Wednesday, October 3, 2012

የመስቀል በዓል “ግዙፍነት ከሌላቸው የዓለም መንፈሳውያን ሀብቶች” ተርታ ሊመዘገብ ይችላል



  • ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ቅርስ የመኾን ዕድሉን ካገኘ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጥበቃና ክብካቤ ይደረግለታል
  • የአ/ /ስብከት አንዳንድ ሓላፊዎች ለዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል የሰጡትትኩረት አከባበሩን በማዳከም የወቅቱን የቅ/ሲኖዶስ አመራር የማስነቀፍ ዓላማእንደነበረው ተጋልጧል
  • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ፖሊስ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራንና አባላትላይ ያካሄደው ፍተሻና በኅትመቶች ሽያጭ ላይ የተደረገው እገዳ ተቃውሞገጥሞታል፤ 
  • የአቶ መለስ ዜናዊ 40 ቀን ተዝካር በታላቁ ቤተ መንግሥትና በጠ//ክህነትይደረጋል፤ 
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- የመስቀል - ደመራ በዓልአከባበር በዓለም ግዙፍነት ከሌላቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ኾኖ እንዲመዘገብ ሲደረግ የቆየው ጥረትበመልካምና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ላይ እንደሚገኝ በመጪው ዓመት ኅዳር ወርምኢትዮጵያ ለዩኔስኮ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ተቀባይነት አግኝተው የመስቀል - ደመራ በዓልየመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ (World Intangible Heritage) ኾኖ እንደሚመዘገብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንአስታወቀ፡፡


የባለሥልጣኑን ኢንታንጀብል ሄሪቴጅስ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ገዛኽኝ ግርማን ጠቅሶ የፋና ብሮድካስትኮርፖሬት ዜና መጽሔት እንደዘገበው÷ ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት(UNESCO) ስድስት የቅርስ ማስመዝገቢያ መስፈርቶች ዋነኛ በኾነው አይ..ኤች - 02 የተሰኘ የጥያቄማቅረቢያ ቅጽ አማካይነት ስለ መስቀል በዓል ሰፊ መረጃ ተሰጥቷል፡፡ የጥያቄ ማቅረቢያ ቅጹ ከያዛቸው24 ያህል ጥያቄዎች መካከል÷ ስለ መስቀል በዓል ታሪካዊ አመጣጥና የአከባበር ሂደት፣ በዓሉለማኅበረሰቡ ስለሚያበረክተው ባህላዊና ማኅበራዊ ፋይዳ፣ ሕዝቡ ቅርሱን ጠብቆ ያቆየበት መንገድናየኅብረተሰቡ ተሳትፎ ምን እንደሚመስል፣ መንግሥት ቅርሱን ጠብቆ ለማቆየት እያደረገ ያለው ጥረትየመሳሰሉት ነጥቦች እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

ባለሥልጣኑ ስለ መስቀል - ደመራ በዓል ለዩኔስኮ በላከው መረጃ በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ደቡብክልሎች የተካሄዱት የመስክ ጥናቶች በጥንቃቄ የተተነተኑበት ሲኾን ይህም የበዓል አከባበሩን ገጽታበሚያሳዩ በርካታ ፎቶግራፎችና የዐሥር ደቂቃ ቪዲዮ ክሊፕ የተደገፈ መኾኑን ከፍተኛ ባለሙያውለዜና መጽሔቱ አስረድተዋል፡፡ ዩኔስኮ ሰነዶቹን ለማባዛትና ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ጥያቄ አቅርቦፈቃድ መሰጠቱን ያመለከቱት አቶ ገዛ÷ ከመጪው ታኅሣሥ እስከ ሰኔ ወር በመረጃዎቹ ላይየሚካሄደው ተጨማሪ ግምገማ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘት አለማግኘቱከታወቀ በኋላ በመጪው ዓመት ኅዳር ወር የመስቀል በዓል የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለምአቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ ኾኖ ይመዘገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

የመስቀል - ደመራ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ስለሚያስገኘው ፋይዳ የዘረዘሩት ከፍተኛባለሙያው ስለ መስቀል በዓል በዩኔስኮ ድረ ገጽ ላይ መለቀቁ፣ ዩኔስኮ የመስቀል በዓል ዓለም አቀፍጥበቃና ክብካቤ እንዲያገኝ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉ ለአገራችን ከፍተኛ የቱሪስት መስሕብነትናኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደሚያስገኝላት አመልክተዋል፡፡

የቀድሞው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተከበረው የመስቀልደመራ በዓል ላይ የመስቀል በዓል ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ሀብት ኾኖ እንዲመዘገብ ጥሪ ሲያደርጉመቆየታቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከዚያም በመነሣት ባለሥልጣኑ ሲያደርግ በቆየው ጥረትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሐዶ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደኾነች ዜና መጽሔቱ ዘገባ ላይተመልክቷል፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን ከመስከረም 16 – 24 ያለው አንድ ሳምንት የመስቀል በዓል የሚከበርበት ወቅትነው፤ በርካታ ቱሪስቶች ወደ አገራችን በሚጎርፉበት በዚሁ ሰሞን አብሮ የሚከበረው የዓለም ቱሪዝምቀን በዓሉ ባለፈው የበጀት ዓመት እስከ አራት ቢልዮን ብር ማስገኘት ለጀመረው ለአገራችን የቱሪዝምገቢ ያለውን የጎላ ሚና የሚያጠይቅ ነው፡፡ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በመስቀል ደመራ በዓል መልእክታቸው እንደተናገሩት አዲስ አበባን ጨምሮ በጎንደር፣ በአኵስም፣ በቅዱስ ላሊበላና በመላው ኢትዮጵያ በድምቀት የሚከበረውን የመስቀል በዓል ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ አገር ጎብኚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አጋጣሚው የአገራችንን መልካም ገጽታ ለቀሪው ዓለም የምናስተዋውቅበት ነጻ መድረክ በመኾኑ በአግባብ ልንጠቀምበት እንደሚገባ ብፁዕነታቸው መክረዋል፡፡ “የመስቀል በዓል የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ በዓል ቢኾንም ብሔራዊ በዓልና ዓለም አቀፍ ዕውቅና እያገኘ የመጣ ታላቅ ክዋኔ ነው” ያሉት ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ÷ አገራችን ይበልጥ እንድትጠቀም በዓሉ በዩኔስኮ ዕውቅና ተሰጥቶት በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አማካይነት የተጀመረው ጥረት ከግብ ይደርስ ዘንድ የሚመለከታቸው የመንግሥትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ነገር ግን÷ መንግሥትና የዓለሙ ድርጅት ይህን ያህል ትኩረት የሰጡት የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርበብሔራዊ ደረጃ በሚከበርበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከተለመደው ሰዓት ቀደም ብሎበመጀመር በድምቀት የተከበረ ቢኾንም ቅሬታና ስጋት ያሳደሩ ጉዳዮች አልነበሩም ለማለት አይቻልም፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ ለበዓሉ አከባበር የሚያስፈልገውን ከብር ሦስት መቶ ሺሕ በላይ በጀት በወቅቱ ፈቅዶየነበረ ቢኾንም በሀገረ ስብከቱ በኩል በጀቱን በወቅቱ ወጪ አድርጎ ጥቅም ላይ በማዋል በኩል የታየውዳተኝነት በአምስት የሀገረ ስብከቱ ክፍለ ከተሞች የተከፋፈሉት የሰንበት /ቤቶች አንድነትበሚያደርጉት የበዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ ጫና ፈጥሮ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ለአብነት ያህል 18 አጥቢያዎችንና 490 ያህል መዘምራን የያዘው የሰሜን ክፍለ ከተማ ላቀረበውየሆሄያት መጠበቅ ዐውደ ትርኢት የአስፈላጊ ማቴሪያሎች ግዥ ገንዘብ የተፈቀደው ከደመራው በዓልአንድ ቀን ቀደም ብሎ በነበረው ዕለት ከቀትር በኋላ ሲኾን ጥቂት ፊደሎችም ተሠርተው የደረሱትከዐውደ ትርኢቱ ማቅረቢያ ሁለት ሰዓት በፊት መኾኑ፣ ይህም በዐውደ ትርኢቱ አስተባባሪዎች ላይየፈጠረው ብስጭት ዐይነተኛ አስረጅ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ ተጠንተው ዝግጅት ከተደረገባቸው የዐውደትርኢቱ ክፍሎች ውስጥ በማቴሪያልና የጊዜ እጥረት ሳይቀርቡ የቀሩ እንዳሉ ተገልጿል፡፡ ቀደም ሲልየመስቀል ደመራ በዓል ቅድመ ዝግጅት ዋነኛ አካል ለኾነው የክፍለ ከተሞች መስቀል ጥናት ከፍተኛክትትል የሚያደርገው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱና የሀገረ ስብከቱ የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያለዘንድሮው የክብረ በዓሉ ቅድመ ዝግጅት የሰጠው ትኩረት እዚህ ግባ የሚባል እንዳልነበር ሂደቱንለመገምገም ባሳየው አናሳ ተነሣሽነት መጋለጡ ተነግሯል፡፡

የተፈቀደን በጀት በወቅቱ ወጪ አድርጎ በመጠቀም፣ ለቅድመ ዝግጅቱ ሊሰጥ የሚገባውን የተለመደትኩረት በመንፈግና በክብረ በዓሉ የመርሐ ግብር አመራር ወቅት አንዳንድ ትዕይንቶች ጉልሕ እይታእንዳያገኙ በማድረግ የተገለጸው የዘንድሮውን በዓል አከባበር የተዳከመ ገጽታ የመስጠት ተንኮል(sabotageክብረ በዓሉን በበላይነት በሚያስተባብረው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት/ቤት ሓላፊዎች የቅርብ ክትትል የተመከተ ቢኾንም የተንኮሉ መነሻ ከፓትርያርኩ ሞት በኋላሥራ የለም በማሰኘት የወቅቱን የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ለማሳጣት የታለመ መኾኑ በቀጣይነትበሚካሄዱ ሌሎች የተቋማዊ ለውጥና የአሠራር ማሻሻያ ጥረቶች ላይም ያለውን አደገኝነትየሚያመላክት ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በተጨማሪ ስምንት ብፁዓን አባቶች እንዲጠናከር የተደረገው ቋሚሲኖዶስ በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ከሚመራው የበዓል አከባበር ኮሚቴ በሚቀርበለት ሪፖርትመሠረት የበዓሉን አከባበር በመገምገም ርምጃ እንደሚወስድ ተጠቁሟል፡፡

በዚሁ የበዓል አከባበር ከፍተኛ ቅሬታ ካሳደሩ ሌሎች ተግባራት አንዱ ከቤተ ክርስቲያን በሚወጡናለሃይማኖታዊ ክብረ በዓል በተዘጋጁ የክፍለ ከተሞች አንድነት መዘምራንና ሌሎች አገልጋዮች ላይበፖሊስ የተደረገውና ለማድረግ የታሰበው ፍተሻ ነው፡፡ ፍተሻው ባለፈው ዓመት ሲካሄድ ተቃውሞተሰምቶበት የነበረ ቢኾንም በዘንድሮውም ዓመት ለምሳሌ የምዕራብ ክፍለ ከተማ አንድነት መዘምራንወደ መስቀል አደባባይ ጉዞ ለመጀመር በተዘጋጁበትና በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ባሉበት ኹኔታ ላይለማካሄድ በመታሰቡ ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ቆይቶ የክፍለ ከተማው አንድነት አስተባባሪዎችለማንኛውም ችግር ሓላፊነት እንዲወስዱ በማድረግ ፍተሻው እንዲቀር ተደርጓል፡፡

ከዚህ በተለየ አኳኋን በመስቀል ደመራው ዕለት ከቀኑ 700 ጀምሮ ወደ መስቀል አደባባይ ለማምራትበተዘጋጁ የማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን ላይ በዋናው /ቤት የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ባሰማራቸውከደርዘን በሚልቁ ኀይሎች የተደረገው ፍተሻ ግን በዕለቱ በተጠቀሰው ሰዓት ወደ /ቤቱ የሚገቡትንናየሚወጡትን ሠራተኞችና ባለጉዳዮች ጭምር ያልማረ ነበር፡፡ ነገሩ በዚህ ብቻ ሳያበቃ በየዓመቱ እንደተለመደው ማኅበሩ በክብረ በዓሉ ለሽያጭ አሽጎ ያዘጋጃቸው የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፣ ሐመርመጽሔትና ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ በጥናትና ምርምር ማእከሉ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት (ጆርናል) እንዳይሰራጭ መከልከል ብቻ ሳይሆን እሽጎቹ በፖሊስ የጥበቃ አጀብ ወደማከማቻቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

የማኅበሩ /ቤት ሓላፊዎች ስለፍተሻውና በኅትመቶቹ ሽያጭ ላይ ስለተደረገው ክልከላ ከሚመለከተው የፖሊስ አካል ማብራሪያ መጠየቃቸው ተነግሯል፤ የተሰጠውም ምላሽ “ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ጋራ በመነጋገር የተደረገ ስለመኾኑና በአዎንታዊነት እንዲታይ የሚያሳስብ” እንደነበር ተመልክቷል፡፡ ስለጉዳይ ለማጣራት በተደረገው ጥረት የፍተሻው መንሥኤ አንድ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎግ የአዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮቴስታንታዊነት በመጥቀስ ማኅበረ ቅዱሳን ሹመታቸውን እንደሚቃወም ካወጣው መሠረተ ቢስ ዘገባ ጋራ በተያያዘ “ማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዳትቀበሉ የሚል በራሪ ጽሑፍ ለመበተን አዘጋጅቷል” በሚል የተነዛው አሉባልታ መኾኑ የርምጃውን ቅንነት አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ ክብረ በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከሚነሣ ፍላጎትናአጋጣሚውን ከበዓሉ ጋራ ምንም ግንኙነት ለሌለው ዓላማ ለመጠቀም የሚያስቡ ወገኖች የሚፈጥሩትንሁከት (ካለ?) አስቀድሞ ለመከላከል የሚደረገውን የጸጥታ አጠባበቅ እንደሚደግፉ የተናገሩት አስተያየትሰጭዎችም ይህንኑ ስሜት የሚጋሩ ናቸው፡፡

የማኅበሩ አመራሮች ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋራ ባደረጉት ውይይት መንግሥት አክራሪነትንና ሌሎች የጸጥታ ስጋቶችን በተመለከተ በማኅበሩ ላይ የሚወስዳቸው አቋሞች በትክክለኛ የመረጃ ምንጭና በተገቢ የመረጃ ትንታኔ የተመሠረቱ እንዳልነበሩ ማብራራታቸውን ያስታወሱት አስተያየት ሰጪዎቹ÷ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጅ ብሎጎች ላይ የሚነዙ አሉባልታዎችን መነሻ ያደረገው የአሁኑ ፍተሻ የመንግሥትን የደኅንነት ስጋት በመጠቀም ለድብቅ ዓላማቸው መሳካት ማኅበሩን ማጥቃት የሚሹ በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናት ስለመኖራቸው በውይይቱ ወቅት የተሰጠውን ገለጻ እንደሚያጠናክር አስረድተዋል፡፡

ይህ ዐይነቱ ውንጀላ ከውይይቱም በኋላ አንዳችም እርማት ሳይደረግበት ሰሞኑን የሃይማኖት አክራሪነትን በተመለከተ ለክልሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሠራተኞች በተጀመረውና ከመስከረም 23 ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባና በአዳማ በሚቀጥለው ውይይት እየተንጸባረቀ እንደኾነ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የአክራሪነትን አስተሳሰብና ተግባር በመኰነን ማኅበሩ የሃይማኖት አጥባቂነት እንጂ የአክራሪነት ትእምርት እንዳልኾነ የሚገልጹ ጽሑፎችን በማውጣት ላይ እንደኾነ ተገልጧል፡፡

በሌላ በኩል ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትና በጸሎት እየታሰቡ የቆዩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (ስመ ጥምቀቱ ገብረ ማርያም) 40 ቀን መታሰቢያ (ተዝካር) መስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋድ ላይ በታላቁ ቤተ መንግሥት እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚደረግና በርካታ ነዳያን እንደሚመገቡበት ተዘግቧል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment