Wednesday, November 23, 2011

አባ ሰረቀብርሃን ወልደ ሳሙኤል በሎስ አንጀለስ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

አባ ሰረቀ ማን  ናቸው?
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ ለማለት ቢያስቸግርም የቤተክርስቲያናችን ሥርዓት፣ የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ አንቱ በማለቱ እቀጥላላልሁ ።
አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበት ሎሳንጀለስ ከተማ) ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈዋቸው ስለሄዱ አባ ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል ። አንዲ የቤተክርስቲያናችን አዛውንትማ ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው ነው የሚያንገሸግሻቸው።
ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ በሎሳንጀለስ እንደት ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦
አባ ሰረቀ ብርሃን በ1993 መስከረም ላይ ከኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ይህንን መረጃ የሰጡን አባት እንዲህ ያጫውቱናል።
አባ ሰረቅ ብርሃንን ለማስመጣት ሂደቱን የጀመእኩት እኔ ነኝ። በ1993 እ.ኤ.አ. የእህቴን  ባል እባክህ ጥሩ ካህን የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ሰው ፈልግልን ብየ ነገርኩት።
እርሱም ወዲያው አንድ በጣም የተማሩ ሰው አግኝቸልሃልሁ ብሎ አጫወተኝና (በኢትዮጵያብክረምት አካባቢነው)ደስ አለኝ። ደውየም እንዳነጋግራቸው አመቻቸልኝና  አባ ሰረቀን ድውየ አግኘኋቸው።  እርሳቸውም ለመምጣት እፈልጋለሁ ግን ለመጉዋጓዣ 2000 ዶላር ያስፈልገኛል ብለው ነገሩኝ። እኔም ቦርዱን አስፈቅጀ የመምጫቸውን ሁኔታ ጀመርን።2000 ዶላርም ተላክላቸው።
በኋላም ስለመምጫቸው ተነጋግረን ንዋያተ ቅዱሳት (ጽናጽልና መቋሚያ ) እንዲሁን ጽላትም ጭምር እንደሌለን ስነግራቸው፤ ሁሉንም ማግኘት እንደሚችሉ፤ ነገር ግን ተጨማሪ 1000 ዶላር እንደሚያስፈልግ ነገሩኝ። ያንንም ቦርዱን አስፈቅጀ ላኩላቸው።
መስከረም 1993  እ.ኤ.አ. 12 ጸናጽል፣ 12 መቋሚያ፣ ና ጽላት ይዘውልን ሎሳንጀለስ ገቡ። እኛም አባት ናፍቆን ስለነበረ ምንም እንኳን ያወጣነው ወጭ ብዙ ቢሆንም በደስታ ተቀበልናቸው። ስላሁሰንና ዌስት (between Slauson and West) ላይ አንድ የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ተከራይትን አገልግሎት ማግኘት ጀመርን።
ትንሽ ቆይቶም አባ ተከስተ የሚባሉ መነኩሴ (የዛሬው ብጹእ አቡነ ሣᎀኤል) ወደዚህ እነደሚመጡ ተነገረንና እኔው ተቀብዬ አብረው መኖር ጀመሩ። የሚገርመው ገን አባ ሰረቀ ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ስለማይፈልጉ፤ አባ ተከስተ ጋር አለመግባባት ፈጠሩና አባ ተክስተ ወደ ሌላ ስቲስት ሄዱ።
ከዚያም እርሳቸውም ብቻቸውን እንዳይሆኑ በማለት ሳንሆዜ የነበረ አንድ ይሥሐቅ የሚባል አገልጋይ ልናመጣልዎት ነበር ብንላቸው ያሉንን እስከ አሁን አስታውሰዋለሁ (እኔ ቤት አንድ ሰው አይገባም ነበር ያሉት።) ያን ጌዜ ነበር አባ ሰረቀ ላይ የነበረው እምነታችን እየተሸራረፈ የመጣው። እንደመንም አግባብተን ልጁን ብናመጣውም አሁንም እርሱም የአባ ተክስተ እጣ ደርሶት አባረሩትና ሄደብን።
መቼም የኛ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ነችና ከአሪዞና አባ ወልደ ሰንበት የሚባሉ አንድ መነኩሴ ደገሞ አስመጣንላቸው። ለካስ ሁለቱም መሰሪ ነበሩና የሚከተለውን ምእመናን የማይረሱትን አሳዛኝ ሥራ ሰሩ።
አንድ እሁድ ነው አስታውሳለሁ አባ ስረቀና አባ ወልደ ሰንንበት ቅዳሴ ቀድሰው ሲያበቁ አባ ሰረቀ ለእኔና ለጓደኞቸ  “አባ ወልደ ሰንበት ወንድሙ ስላረፈ ልናረዳው ነው ምን ትላላችሁ” አሉ። እኛም አዝነን አሁን ቅዳሴ ቀድሰው ከምንነግራቸው ለምን ሳምንት ወይንም ነገ አንነግራቸውም አልናቸው። እርሳቸውም እሽ ብለው እኛን ከላኩ በኋላ አረድተዋቸው ነበርና ወዲያው ደውለው አርድቻቸዋለሁና ኑ ተባልን በጣም ሁላችንም ተመልሰን መጣን ። እውነት መስሎን በጣም አዝነን አባ ወልደ ሰንበትንም አጽናንተን ተመለስን። ከዚያም ወደ ሀገራቸ መመልስ እንደሚፈልጉ አባ ሰረቀ ነገሩን እኛም አዝነን ያለንን አዋጥተን ላክናቸው። ትዝ የሚለኝ ለቤተሰቦቻቸውም አምነዋቸው ብር አድርሱልንም ያሉ ሰዎች ነበሩ። ግን አባ ወልደ ሰንበት ሳያደርሱላቸው ብራቸውን በልተው ቀርተዋል።
ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ የአባ ወለደ ሰንበትን እህት ወይዘሮ አብርኸትን የሚያውቅ አንድ የቤተ ክርስቲያናችነ አባል፤ አዲስ አበባ ሄዶ ወይዘሮ አብርኸትን ያገኝና እባክሽ የወንድማችሁን መሞት ሰምተን እኮ አባን አጽናናቸው ቢሏት የምን ሌላ ወንድም ነው የምታወራው ትለዋለች። ለካስ አባ ወልደ ሰንበት ወድማቸው ሞተ ትብሎ የተነገረው የውሸት ኑሯል። አባ ሰረቀና እርሳቸው የፈጠሩት ወሸት። ከዚያ በኋላ  ይኸው አባ ወልደ ሰንበት   ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እንደዘገበው በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ  ተደርሶባቸው መጀመርያ ወደ ጀርመን አሁን ደግሞ መቼም ጅብ በማያውቁት ሀገር እንደሚባለው በገለልትኞች ሲኖዶስ ጳጳስ ሆነው ካናዳ ይኖራሉ።

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና አባ ሰረቀ አባ ወልደ ሰንበትን እንዲህ አድርገው ከአጠገባቸው ካራቁ በኋላ ከቤተ ክርስቲያን አባልት ጋር መግባባት አልቻሉም። ከእለታት አንድ ቀን እንደውም ቤተክርስቲያን የለችም አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም በማለት ሲስብኩ አስታውሳለሁ። ይህ በእምነታችን የሌለ ኑፋቄ ነው። ከዚያም በኋላ ከቤተክርስቲያናችን ተለይቶ የአቡነ ጳውሎስ እንደራሴ ነኝ እኔ ማንንም መነኩሴ ጳጳስ እንዲሆን አስደርጋለሁ ከሚለው ና እዚሁ ሎሳንጀለስ ከሚኖረው ቄስ ጋር ገጠሙና ከእኛ ጋር መጣላት ጀመሩ።  ከዚያም አቡነ ማትያስ ለጥቅምት አቡነ አረጋዊ ሲመጡ ምእመናን ክስ አቀረቡ። ውይይቱ የተደረገው ከእነ አቶ ዕቁበ ጽዮን ቤት ነበር። ብጹእ አባታችንም ቢመክሩዋቸው አልሰማ አሉ። አባ ሰረቀንም ብጹእ አቡነ ማትያስ ምእመናኑ ምንም አልበደሉምና ተሳስባችሁ አብራችሁ ኑሩ ቢሉዋቸው አባ ሰረቀ ከአሁን በኋላ እዚህ አላገልግልም እንደውም ያሉት ቃል ትዝ ይለኛል። “ብርሌ ከነቃ…” አሏቸው።
ብጹእ አቡነ ማትያስም እንግዲያውስ እናንተም ሌላ ካህን ፈልጉ እርሳቸውንም መጉዋጉዋዣ ከፍላችሁ ላኳቸው እርሳቸውም ንዋያተ ቅዱሳቱን፤ ታቦቱን ጭምር ያስረክቧችሁ (ይህንንም በዚያን ጊዜ አባ ኢሳይያስ- የሳንዲያጎ ግብረኤል አስተዳዳሪ የነበሩ- የአሁኑ ብጹእ አቡነ ኢሳይያስ ያረካክቡዋችሁ ተባለ)።
እኛም አዝነን እሽ ብለን 700 ዶላር ከመመናን ሰበሰብንና ዶ/ር ኃይሉ ፤ አቶ ጥላሁንና አንድ ሌላ ሰው ወክለን አባ ኢሳይያስን ይዘው እንዲረከቡ ላክናቸው።
 ከዚያም  አባ ሰረቀ በለመዱት አንደበታቸው የተወከሉ ምእመናንን ታቦቱን ነው የያዝኩት ብለው ብሪፍ ኬዝ ይዘው መጡና ይህንን ለመነኩሴው ለአባ ኢሳይያስ ብቻ ነው የማስረክበው በማለት ወደውስጥ ሁለቱ ብቻ ገቡ። ብዙ ቆይተው ሲዎጡ አባ ኢሳይያስን የተወከሉት ሰዎች ታቦቱን ተረከቡ ወይ ሲሉዋቸው “ታቦት ተረከብኩም አልተረከብኩም አይባልም” አሉዋቸው።
ተወካዮችም ግራ ግብቷቸው ሲመለሱ አባ ኢሳይያስም ለብጹእ አቡነ ማትያስ ደውለው ታቦቱን እንዳልተረከቡ እንደውም ወደውስጥ ከገቡ በኋላ   አባ ሰረቀ ብሪፍ ኬዙን ሳይከፍቱ ይረከቡ ይሏቸዋል። አባ ኢሳይያስም ይክፈቱት እንጂ እንደት ዝምብየ ረከባለሁ ይሉና ተቀብለው ቢከፍቱት የተገኘው ታቦት ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ፤ ከዚያም አባ ሰረቀ እግራቸው ላይ ወድቀው እባከወ አልተቀበልኩም በለው ለተወካዮች አይንገሩብኝ፤ ታቦቱን ዲሲ ልኬዋለሁ እዚያ ሄጀ  ለአቡነ ማትያስ እሰጣለሁ ወይንም እልከዋለሁ ብለዋል ይሏቸዋል።
ይህንን ነገር አቡነ ማትያስ ሲሰሙ በጣም አዝነውና ተናድደው ነገሩን ምእመናን እንዲሰሙ ያደርጋሉ። ሁለቱም አባቶች (አቡነ ማትያስና አቡነ ኢሳይያስ በሕይዎት ስላሉ ህያው ምሥክር ናቸውና ስለ እውነትነቱ እነሱው ሊጠየቁ ይችላሉ።)
ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል። ምእመናንም በዚህ ተናድደን ያዋጣነውን ገንዝብ ሳንሰጣቸው ቀርተናል።
ከሁሉ የሚገርመኝ ሲሄዱ አንዲት ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሰንና ብርት ይስጡን ብለን ስንጠይቃቸው፤ መልሳ ወስዳዋለች አሉን። ይህ ሁሉ እንግዲህ በሎሳንጀለስ የነበራቸው ታሪክ ነው።
አንድ መነኩሴ ከሰረቀ፤ ከዋሸ፤ ከቤተክርስቲያን ይልቅ ስልጣን ገንዝብና ክብርን ከፈለገ እንዴት መነኩሴ ይሆናል። በአሁኑ ሰዓት የሚያደርጉት ብጥበጣ እኔ ከአባ ሰረቀ የማልጠብቀው አይደለም። እርሳቸው፤ ከሰው ጋር ተስማምተው የማይሰሩ፣ የሚዋሹና በሃሰት ማንኛውንም ኃጢያት ሁሉ ሊሰሩ የሚችሉ ሰው ናቸው። ለዚህ ደግሞ አቡነ ማትያስ በአሁኑ ሰዓት የኢየሩሳሌም ሊቀጳጳስ፣ አቡነ ሣᎀኤል፤ አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና እነሱን በመጠየቅ ወይንም ለእኔም በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኜት ይቻላል በለውናል።
በአጠቃላይ አባ ሰረቀ፡
1.      ለእነታቸው ሳይሆን ለሆዳቸውና ለገንዘብ የሚኖሩ
2.     ካለ ፍርኃት የሚዋሹ
3.     ካለ ሃፍረት የሚሰርቁ
4.     ከሰው ጋር ተባብረው ና ተግባብተው መኖርን የማያውቁ ሰው ናቸው።
እርሳቸው ከሄዱ  በኋላ ስድስት ወራት ሙሉ ካለ ካህን እሁድ እሁድ ምእመናን ብቻችንን ተሰብስበን አቶ እቁባይ መጽሐፍ ቅዱስ  እያነበቡልን እንበተን ነበር። በኋላ ይኼው እስከ አሁን ይሚያገለግሉንን ታላቅ አባቶች አግኝተን እንገለገላለን... እንደውም ባለፈው ዓመት ቤተ ክርስቲያን ገዝተን ገብተናል። በአሁኑ ሰዓትም ከልብ የሚያገለግሉ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ታላላቅ ም እመናን ያላት ቤት ክርስቲያን በማግኘታችን ደስትኞች ነን።
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት ነው።

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
 

1 comment:

  1. በጣም ያሳዝናል፡፡ ይህንን የሚያውቁ አባቶች ማጋለ
    ጥ አለባቸው የሚያስፈጽም ባይኖርም

    ReplyDelete