Wednesday, November 9, 2011

አባ ፋኑኤልን ለምን መቃወም አስፈለገ

የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ???

ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ
      
አባ ፋኑኤል
አባ ፋኑኤል
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደዘገብነው በሰሜን አሜሪካ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍል ዋናኛው ተዋናኝ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ነበሩ:: ብፁዕነታቸ የጵጵስና ማዕረግ ከማግኘታቸው በፊት “አባ መላኩ” በመባል ይጠሩ ነበረ:: በወቅቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ነበሩ:: የዛኔው አባ መላኩ ብፁዕ አቡነ ማትያስን አልቀበልም በማለት “ገለልተኛ” ቤተ ክርስቲያን አቋቋመው ነበረ:: ከሌሎች ከግባበሮቻቸው ጋር በመሆን አሁን የሚሰግዱላቸ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመቃወም “የገለልተኞች”የካህናት ማህበር አቋቁመው ነበረ:: አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የዚሁ “የገለልተኞቹ” ማህበረ ካህናት ከአባልነት በተጨማሪም በኃላፊነት ሰርተዋል::
እንግዲህ ሁለቱንም ማለትም የዛኔው “አባ መላኩ” የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እና አባ ሰረቀ ብርሃን የጵጵስና ማዕረግ እንደሚያስፈልጋቸው ወሰኑ፤ በዚህም ምክንያት የዋሽንገተን ዲሲው “የገለልተኞቹ” የካህናት ማህበርን በተመሳሳይ ግዜ ከዱ:: ለምን እንደከዱ ግን በወቅቱ ግልጽ አልነበረም:: ማህበረ ካህናትን መክዳታቸው ብቻ ሳይሆን ምዕመናንን ዋሽተዋል:: “ምንድ ነው የዋሹት”? ትሉ ይሆናል:: ውሸቱ እንዲህ ነው:: ሁለቱም የየራሳቸው በስማቸው ያቋቋሙት ቤተ ክርስቲያን አላቸው:: የጵጵስና ማዕረግ ፈልገው ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ግን ቤተ ክርስቲያናቸውን “ወደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስረከብን፣ የምንተዳደረውም በኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው” በማለት ተናገሩ:: በግዜው ምእመናኑ ተደናገሩ:: መደናገርም ብቻ ሳይሆን ለሁለት ተከፈሉ:: ውሳኔያቸውን የተቀበሉ አብረው ቆዩ፤ በውሳኔያቸው ያልተስማሙት ግን ተለይተው ወጡ:: 
ታዲያ የግል ንብረታቸው ነገር ግን ምዕመናን የሰሩትን ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መለስን ይበሉ እንጂ፤ እስከ አሁን ድረስ ግን የሁለቱም ስም በባለቤነት (articles of incorporation) ላይ እንደተመዘገበ አለ:: አጥቢያቸውም ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አላስቀየሩትም:: የሚገርመው ነገር እዚህ አሜሪካን  ምዕመናንን ብቻ ሳይሆን የዋሹት ኢትዮጵያ ሄደውም ቅዱስ ሲኖዶስ ጭምር ዋሹት:: በአሜሪካን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ሰርተን አስረከብን በማለት::
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንደ ግብር አባታቸው እንደ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በትልቁ ፎቶዋቸውን አሰርተው ከሥዕለ እግዚእ በላይ አሰቅለዋል:: ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች በሰፊው እንመለስበታለን::
እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችን አንድነት ይጠብቅልን!!!
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

No comments:

Post a Comment