Monday, April 30, 2012

ሦስት መቶ ሺህ ተሽጦ ሰባ ሺህ ጉርሻ ያስገኘ…..

ተካ ፍሬሰንበት ከራጉኤል መርካቶ

"የፈራ ይመለስ" ከምን??
የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር የሚያደርጉት ግብግብ ተሳክቶ ፍሬ እያስገኘ ነው፡፡ ምዕመኑም “ከልጆቻችን ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን የቀረበ የለም የምንሰማው እነሱን ነው” ብሎ እየተከተላቸው ነው፡፡ ይኽ በእውነት ትልቅ ለውጥ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት በአዳራሽ ተወስኖ መቅረት የለበትም፡፡ በቅድሚያ እያንዳንዱ ሰንበት ት/ቤት በየአጥቢያው የስብከተ ወንጌሌ አገልግሎት በኮሚቴ ከመሳተፍ ጀምሮ በመማር ማስተማሩ ሒደት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ከጥሎ በአቀማመጥ ቅርብ ለቅርብ የሆኑት ደግሞ ተጋግዘው ቦታቸውን ከአጉራ ዘለል ሰባኪያን ለማጽዳት አንድ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በቅርቡ መናፍቁ አሰግድ በአንድ አጥቢያ ተጋብዟል መባልን የሰሙ ሰ/ተማሪዎች ከሩቅ ቦታ በቶዮታ ቲካፕ መኪና ተጭነው ቀድመው ቦታውን ለማስከበር ሲደርሱ ስለተደወለለት ይመስላል አሰግድ ግን ሳይመጣ ቀርቷል፡፡
ሌላው ሰ/ተማሪዎችና ጉዳዩ የሚያንገበግበን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ልንሰራው የሚገባንን የቤት ሥራ ላቅርብና ተወያዩበት ያላችሁንም መረጃ በሰንበት ት/ቤቶች ኅብረቱ በኩል ሰብስቡት እላለሁ፡፡እነሆ ፍሬ ነገሩ፦

                     

መዝሙርና አሳታሚዎቹ
እስክንድር የተባለ ንጉሥ በጦር ሜዳ እያዋጋ ሳለ አንድ ወታደር ሲሸሽ ያይና አስጠርቶ ቢያየው የእሱው ወታደር ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ስሙን ሲጠይቀውም እስክንድር መባሉን ይረዳል ይኼኔ ንጉሡ ወታደሩን “ወይ እንደኔ ተዋጋ ወይ ስሜን መልስ” አለው ይባላል፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ስንት መዝሙር አታሚና አከፋፋይ እንዳለ ያውቃሉ? እነዚህ መዝሙር ቤቶችስ ከቢዝነስ እውቀት ያለፈ የቤተ ከርስቲያን እውቀት አላቸው? ሥራቸው ገብያ ተኮር ነው ወይስ እምነት ተኮር?እንዲያውም ተሐድሶዋውያኑ ያስቀመጡአቸው የቤት ሥራዎቻችን ቢሆኑስ? ምን አገባህ ካሉኝ መልሴ “ወይ እንደኛ ተዋጉ ወይ ስማችንን መልሱ ነው፡፡” የባሰባቸውን ለመጥቀስ፦ አብ፣ቢታንያ፣አንፆኪያ፣ቬሮኒካ፣ራጉኤል መንፈሳዊ መዝሙር ቤቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህ መዝሙር ቤቶች በእስካሁኑ ስራዎቻቸው ለቤተ ክርስቲያን ጉዞ እንቅፋት ከመሆን ባለፈ ያደረጉት በጎ አስተዋጽኦ የለም፡፡ ርግጥ ነው አስተዋጽዖ ከተባለ ለራሳቸው በቂ ሀብት አከማችተዋል፣ራሳቸው ግጥምና ዜማ ገዢ ሆነዋል፣ (ስለዚህም የአንድ ግጥም ዋጋ አንድ ሺህ ብር የዜማውም እንደዛው ሲሆን ለስቱዲዮ ቀረጻ አምስት ሺህ ብር ሲከፈል አንድ ሙሉ ካሴት አራት መቶ ሺህ ይሸጥ ጀምሯል) ለገዙት ግጥምና ዜማ እንደ እግር ኳስ አሰልጣኝ ድምፃዊ በመፈለግ እያዘመሩ ቸብቸዋል፣ሕፃናቱን ሳይቀር በመመልመል ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ በሕፃንነት የልጅ እናት እንዲሆኑና በተንሻፈፈ መስመር እንዲሰለፉም አድርገዋል፡፡ ለአብነትም ዘማሪት ሕፃን ዮርዳኖስና ጽጌረዳን(በሕፃንነት ከወለዱት) ሕፃን ዘማሪ እዝራና ዘማሪ ሐዋዝ ደግሞ ገንዘብ ጥሟቸው ትምህርታቸውን አቋርጠው በተሐድሶ ጎራ ተሰልፈው ከሚገኙት ውስጥ ናቸው፡፡


"ዘማሪ" ተዝታው ሳሙኤል
ትዝታው ሳሙኤል
በቅርቡ “ዘማሪ” ትዝታው ሳሙኤል ያወጣውንና ከየት እንደምንመለስ ግልጽ ባይሆንም “የፈራ ይመለስ” ብሎ ርዕስ የሰጠውን ዘፈን አይሉት አሽሙር፤ (ለነገሩ እነሱ ካቀጣጠሉ የተሐድሶ ዘመቻ ማለት መሆኑ ያፈጠጠ እውነት ነው )ሙሉ ግጥምና ዜማ ራሱ ሠርቶ አራት መቶ ሺህ ብር ለመሸጥ ሲስማማ መዝሙር ቤቶቹ ተጠቃቅሰው ሦስት መቶ ሺህ ብር ይገምቱለትና ይሸጠዋል፡፡ ይኽ መዝሙር ቁጥር አራት ሲሆን በውስጡ አሥራ ሦስት መዝሙሮችን ይዟል፡፡ ከነዚህ ውስጥ “ሙሉ ሰው” የሚል ርዕስ የተሰጠው የመዝሙር ግጥም ይኼ ነው፦

                       ሙሉ ሰው
ስመሰክር ዓይኔን እንዳበራ፤ከለከሉኝ ስሙን እንዳልጠራ
ሙሉ ሰው ነኝ መቼም ዝም አልልም፤ለኔ ኢየሱስ ነው ለዘልዓለም፡፡
በራሳቸው ፈቃድ ጠይቀው መዳኔን፤ማመን ተስኗቸው የበራውን ዐይኔን
ማዳኑን አውጄ ከሙክራብ ሲያስወጡኝ፤የማይጥለው ንጉሥ ኢየሱስ አቀፈኝ፡፡
ኃጢአተኛ ቢሉት በክፉ ልባቸው፤ክብሩን ባይቀበል ጎዶሎ እምነታቸው
ለእኔ ግን አምላክ ነው የሞት መድኃኒት፤ጨለማን የረታው የሌሊት መብራት፡፡
የዋህ ወላጆቼን ከቶ አታስጨንቁ፤ሙሉ ሰው ነኝና እኔኑ ጠይቁ
ለመሆን ካሻቹ ደቀመዛሙረቱ፤የልባችሁን ደጅ ለጌታ ክፈቱ፡፡
ይጣፍጣል መኖር ከክርስቶስ ጋራ፤መፍትሄ ስላለው ላዘን ለመከራ፡፡
ሞትም ጥቅም ሆኗል በጌታ ከሆነ፤ሁለተኛ አይሞትም አንዴ እርሱን ያመነ፡፡
 
“ዘማሪ” ትዝታው ይኽንን ካሴት ሦስት መቶ ሺህ ብር በሸጠው ማግስት አዲስ አበባ ላይ በአንድ የእራት ግብዣ ላይ አንዲት በብሯ የምታስብ ወይዘሪት “ትዜ በዚህ መዝሙርህ ጌታን በሚገባ ስለገለጥክልኝ ይኽቺን ተቀበለኝ” ብላ 70ሺህ ብር ሰጥታዋለች፡፡
በቅርቡ በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ መናፍቃን ሰልፍ ላይ የተገኘው ትዝታው የአዲስ አበባን ሰ/ት/ቤት “እናንት የማኅበረ ቅዱሳን ቡችሎች” ብሎ በመሳደቡ በፖሊስ የከሸፈ መጠነኛ ጉሸማ ከደረሰበት በኋላ በሰጠው ኢንትርቪው “የክርሰቶስ ልብ አለኝ…..የተደበደብኩት…….”እያለ በመፎከሩ ደግሞ ስንት ተሸልሞ ይሆን? ሰንበት ተማሪዎቹ ግን የደበደብነውም ያስደበደብነውም እኛ ሆነን ሳለን ምክንያቱንም እያወቀው ሌላ ነገር መዘባረቁ አሳዝኖናል ይላሉ፡፡ በጣም የሚገርመው ግን እሱንና በጋሻውን፣ናትናኤልንና አሰግድን፣ተረፈንና ሌሎቹንም ብለው ተቀስቅሰው የመጡትን መናፍቃን ሰንበት ተማሪዎቹ ጠርተው አስደብድበውኛል ማለቱ ነው፡፡ ለማንኛውም “ከለከሉኝ ስሙን እንዳልጠራ” ብለህ 70 ሺህ ጉርሻ ከመናፍቃኑ ሲሰጥህ ከሰንበት ተማሪዎች ግን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሰይፍ ባይሆንም ቡጢ የተሰጠህ ለምን እንደሆነ የገባህ አይመስለኝም፡፡ እነሱ (የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹ)እያሉህ ያሉት “በእኛ ዓውደ ምህረት የፕሮቴስታንቱን፣አማላጁን….ኢየሱስ መስበክ አትችልም” ነው፡፡ ገባህ? ለማን እየሰራህ እንዳለህ እኮ አንተው እራስህ እየነገርከን ነው፡፡ እነሱ(መናፍቃኑ) ሸለሙህ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ግን የኑፋቄ አፍህን እንዳታላቅቅ ከለከሉህ፡፡ ውድ ገብርኄራውያን ለማለት የፈለኩትን ብዬ ልሰናበት በዚህ ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ዘመቻ የመዝሙር አሳታሚዎች ጉዳይም ይታሰብበት፡፡አበቃሁ፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

2 comments:

  1. አንድ እውነት፡ብቻ፡አረጋገጥኩኝ፡ማህበሩ፡ለዱርዬ፡ብር፡እየከፈለ፡ለማህበሩ፡ጥሩ፡አመለካከት፡የሌለውን፡ግለሰብ፡ማስደብደብ......... አሁን አረጋገጣችሁልን...እግዚአብሄር፡ልብ፡ይስጣችሁ።

    ReplyDelete
  2. If you are Christians Please stop igniting war on Gods servants!

    ReplyDelete