- ይድረስ ለብጹ ቅዱስ አቡነ ፋኑኤል
ካህናትን ለማስፈራራት ተንሳስተው የጻፉትን ደብዳቤ ቁጥር ሀ\ስ\24\04 በተለያዩ ድረ ገጾች አይች ሕዝብ እንዲያውቀው ለእርስዎ ጥያቄ ላቀርብ ክርስቲያናዊ በሆነ መንፈሳዊ ግዴታ ተገደድኩ።
አይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቁንጮዎች፤ ምነው ቤተክርስቲያኒቱን ካለችበት ፈተና ለማውጣት ብትጥሩ። አሁን ይህ ድርጊት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይጠቅማታል? ምእመናን አባትን በማክበርና በሀዋሳ ልይ የሆንውን ግብግብ ችግር ላለመድገም ብለን ዝም ብንል ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል
እንደተባለው ጳጳሱ እየጮሁ አላስቀምጥ አሉን። ከእንግዲህስ ወዲያ ዝምታው እየከበደን ነው።
ብጹእነትዎ እስኪ የሚከተሉት ጥያቄወች የእርስዎን መምጣት በጉጉት እየጠበቅን ላለነው ለምእመናን ይመልሱልን።
፩. ዛሬ እርስዎ ስልጣንዎን በመጠቀም እያስፈራሩአቸውና እየወነጅሉአቸው ያሉት ካህናት በጥያቄ ቁጥር ፬ ላይ በተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የእርስዎን መምጣት
በጉጉት እየጠበቅን ያለነወችን ምእመናን አሰባስብው ቀደም ብሎ በብጹእ አቡነ አብረሃም የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በተመሰረተው ሃገረ ስብከት
ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና በመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር በመሆን ምእመናን እንዳይበተኑና ቤተ ክርስቲያ
እንዳትበደል በማገልገል ላይ ያሉ መሆናቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉን?
እርስዎን ሊጠቅም የማይችል ድርጊት በእነዚህ አባቶች ላይ ባይፈጽሙ መልካም ነው።
፪. ለመሆኑ ይህንን ውሳኔ ሲወስኑ ከየትኛው መንበር ላይ ቁጭ ብለው ነው ???
፫. በብጹእ አቡነ አብረሃም መልካም አባታዊ መሪነት የተገዛውንና በቅዱስ ሴኖዶስ የሚታወቀውን የሃገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ለምን አልተረከቡም?
፬. በቅዱስ ሴኖዶስ የታወቁትንና ሊቀ ጳጳስ ተመድቦላቸው በብጹእ አቡነ አብረሃም ይተዳድሩ የነበሩትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አብያተ ክርስቲያናት ለምን አልተረከቡም?
፩ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ባልቲሞር
፪ ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሌክሳንደሪያ
፫ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ሉዊቪል
፭ አንቀጸ ምህረት በዓታ ለማርያም ሻርለት
፮ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አትላንታ
፯ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ አረጋዊ
፰ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ታምፓ
፱ ደብረ ዕንቁ ቅድስት ማርያም ሜምፊስ
፲ ደብረ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ካንሳስ ሲቲ
፲፩ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኦክላሆማ ሲቲ
፲፪ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ
፲፫ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ ቢች
፭. ለምንስ በቪ.ኦ.ኤ በሰጡት መግለጫ "አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት መተዳደሪያ ደንብ የላቸውም፣ ሃገረ ስብከት የለም" አሉ?
ከላይ የተጠቀሱት አብያተክርስቲያናት በሙሉ የምንጠቀመው መተዳደሪያ ደንብ ቃለ አዋዲ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከቃለ አዋዲ የተለየ እርስዎ የሚያውቁት መተዳደሪያ ደንብ አውጥታለች?
፮. እርስዎ ከመምጣትዎ በፊት የሃገረ ስብከቱ አስተዳዳሪ የነበሩትን ብጹእ አቡነ አብረሃምን ለምን ሸሹ ለምን የርክክብ ስርአት አልተደረገም?
፯ በግንቦቱ የቅዱስ ሴኖዶስ ምላተ
ጉባኤ ላይ ከብጹእ አቡነ አብረሃም ጋር በግንባር ለመወያየት ፈቃደኛ ነወት?
፰ በአሁኑ ሰዓት እርስዎ እየመራኋቸ ነው የሚሏቸውን አብያተ ክርስቲያናት ስምና ቦታ በዝርዝር ለምእመናን ቢያስረዱን?
፱ በግ፣ ፍየል እና ተኩላ አንድ ላይ ደባልቄ ካልመራሁ ብለው ከሆነ እረኛ ሁነው ከፊት ሲመሩ በጎችን ተኩላ እንድሚጨርሳቸው ያውቃሉን ተኩላዎችን ለመመገብ አስበው ከሆነ ፍየሎች ያጋልጡወታል
ቅዱስ እግዚአብሔር መልካም እረኛ የሚያደርግና መልካሙን መንገዱን እንዲገልጽልዎ እየጸለይኩ መልስዎን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ያቅርቡልኝ ስል በጥህትና እጠይቃለሁ።
ግልባጭ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቁንጮ ለሆነው ቅዱስ ሴኖዶስ::
ይድረስ ለብፁዕነትዎ! ብፁዕ መባሉ የማይመጥንዎትና ለተግባርዎት የማይስማማ የቅድስናና ክብር ማእረግ ቢሆንም ቅሉ ግን ይህን እውነተኛ ቅድስና ወይም ብፅዕና የሌለውን መጠሪያዎትን ለቤተክርስትያኔ ስርአት ወይም ለስልጣነ ክህነት ካለኝ ክብር አንጻር እነደተባሉት ብፁዕ ልልወት ተገድጃለሁ። ወደ ደብዳቤዬ ዋና ጉዳይ ስገባ ልልወት የምፈልገው በዝቶብኝ ከየት እንደምጀምር ግራ በመጋባት እንደሆነ ሊረዱልኝ ይገባል። የአጻጻፌንም ስልትና ይዞታ ከዚህ አንጻር እንዲያነቡልኝ አሳስባለሁ። በቅድሚያ ላደንቅልዎት የምወደው ለጵጵስና ደረጃ በቅተው ዛሬ የዲሲና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ የመሆን ጥረትዎና ስኬትዎን ሲሆን ሌሎች የምጠላብዎትንና ዋናውን የዚህን ጽሁፍ አላማ ግን በዝርዝር ላቀርብልዎ እወዳለሁ። መቼስ እኔም፤ ቤተክርስትያንም ትሁን ሌሎች ምእመናን የምናውቅልዎት ብዙ የተቀደሱ ተግባራት ስለሌሉዎት ብዙ ለማድነቅና ለማወደስ አልቻልኩም። ይህን ስልዎት ግን ከይቅርታ ጋር ነው።
ለመሆኑ የኢትዮጵያ ቤተክርትያንና ስልጣነ ክህነቷ ለእርስዎ ምንድን ነው?
በውኑ ከእርስዎ እስከ ሾሙዎት አባት ጭምር ቤተክርስትያንን ያውቋታልን ? በምን መልኩ? ብፁዕ ወይም አባ አባ መባልዎ እኮ በዚች ቤት በመሆንዎ እንጅ መች እንዲህ ያለውን ክብር ካህን ወይም የቤተክርትያኗ አባል ባይሆኑ ኖሮ ያገኙት ነበር! ከዚህ ስልጣን ውጭ እስኪ ራስዎን እንደተራ ሰው ያስቡት! ምን ተሰማዎት? መቼስ መጽሃፉን የእኔን ያህል ሳያውቁት አይቀሩም። መጽሃፍት እንዳላጣቅስ መጽሃፉ ከሊቃውንት ፊት አትጥቀስ ይላልና ተውኩት። ለቤተክርስትያን እንዴት አይነት ልጅ ፤ አገልጋይ ወይም ሊቀ ጳጳስ መሆን እንደሚገባዎና ቤተክርስትያንዎ ማን እንደሆነች፤ ስልጣነ ክህነትም ምን እንደሆነ በደንብ ጠንቅቀው ቢያውቁት ጥቅሙ የጋራችን ይሆን ነበርና እባክዎትን መንፈሳዊነትን፤ ክህነትንና ቤተክርስትያንን በደንብ ይወቋትና ይጠቀሙባት። እውነተኞች ልጆቿን ለማየት አንገትዎትን ና አይንዎትን ወደሁዋላ መለስ አድርገው በርስዎ ማእረግና በዚች ቤት ያለፉትን መልካም እረኞችና ህይወታችውን ያስቡ። ክህነት ተከብሮ ባይወርድ ባይዋረድ ኖሮ እርስዎ ዘመን ደርሶ እርስዎ ሊቀ ጳጳስ ባልተባሉ/ባልሆኑ ነበር። ስለዚህ የስርአተ ቤተክርስትያን መከበር የያዙት ሹመት ውበትም ህልውናም ነውና ስርአቷን በሚገባ ጠንቅቀው አውቀው በጥንቃቄ ቢኖሩ ከዚህም በላይ ያለ እርስዎ ፈቃድና አስተዋዋቂነት ብዙ ባልንልዎት ፤በቁሙዎ ሀውልት ባቆምንልዎት ፤ ሳይጋደሉ ገድል በጻፍንልዎ ነበር። አሁንም ቢሆን ግን እድሜ/ስልጣን ጸሃይዎ ሳትጠልቅ ይሄኔ በብርሃን ይመላለሱ ዘንድ እኔም በመሃየም/በማይም ቃሌ፤ በእውነተኞቹ አባቶቼ ስልጣን እውነተኛ የሀይማኖት አባት ይሆኑ ዘንድ አውግዤዎታለሁ። ምናልባት በቤተ ክርስትያን ላይ በውስጥዎ የሚመላለስ የጥርጣሬ ወይም ክህደት መንፈስ ካለም ‘’አለማመኔን እርዳው’’ እያሉ በጸሎት ይበርቱ። ጸሎቱም እምቢ ካልዎት ለጸሎቱም ይጸልዩ። ይህን ሁሉ ያናገረኝ መንፈስቅዱስ ነው እንዳልል እራሴን ላጸድቅ ሆነ እንጅ እርስዎና መሰል አባቶችዎ በቤተክርስትያን ላይ እየፈጠሩት ያሉት ችግሮች የሚያስቀባጥረኝና፤ በቤተክርስትያን ሀዘን ልቤ የቆሰለና የታመመ የሞት አፋፍ ላይ ያለሁ በሽተኛ ልጅዎት ነኝ። ይቅርታ መቼም እኔንም እንዳያወግዙኝ። ቢያስቡም የሚወገዝ ስልጣን የለኝም። ምናልባት ለማውገዝ እንዲያመችዎት እንደርስዎ ካላሾሙኝ/ካልሾሙኝ በስተቀር።
ይቆየኝ>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም