Wednesday, February 8, 2012

ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል


"ታላቅ ምክር"

የብፁዕነትዎን ይቅርታ እየጠየቅሁ እንደ መንፈሳዊ ልጅነቴ በግሌ ላሳስብዎት የምሻውን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። እድሜ 30ዎቹ ሲሆን በውጭ ሃገር ተወልደው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነትን በባለቤትነትና በኩራት የሚከተሉ ሁለት ልጆችን እግዚአብሔር ሰጥቶኛል። ድሜቸው በአስራ ሲሆን በእምነታቸው ግን በጣም በመብሰላቸው ለዘመኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንትርክ ሳይወዱ ተካፋይ ሆነዋል። ለዚህም የዳረጋቸው በየአብያተ ክርቲያናቱ ዶግማና ቀኖና ርዓት ነው። ዝርዝሩን እዚህ ላይ ባላሰፍረውም የሁሉም የእምነቱ ተከታይ የሆኑት ምእመናን ቤት ጠንቅቆ ያውቀዋል።

ወደ ዋና ሃሳቤ ልመለስና፤ እንደዚህ ይነት የማን አለብኝነት መንፈሳዊ ሥራ ከማድረግዎ በፊት ማሰብና ማድረግ የሚገባዎ ብዙ ነገሮች ነበሩ። የተደረገው ድርጊት ትክክል እንዳልሆን የሚያብራሩ ሳቦቸን ከዚህ በታች አቀርባለሁ።
·         ቅዱስ ኖዶስ ወደ አሜሪካ ሲልክዎ ለየትኛው ወገን እንደሆነ አውቀው ተግባራዊ አለማድረግዎ (ለአቡነ አብርሃም ወይስለገለልተኛውወይስለተገንጣዩ አቡነ መርቆርዮስ”)
·         አሜሪካ እንደደረሱ ቅዱስ ሲኖዶስ ለላከዎት ወገን ቀርበው የሥራ አቋምዎን አለመግለጽዎ፤
·         መንፈሳዊ አባት ዛሬ እየከቸው ያሉትን ቀደም ለው የተዋቀሩትን የሃገረ ስብ አስተዳደር ክፍል ለማነጋገር አልሞክርም ብለው አገረ ስብከት እንደሌለ በቪኦኤ መግለጫ መስጠትዎ፤
·         ጋዊ ያልሆነ ነው እያሉ የሚነጅሉትን ክፍል ጋዊነቱን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አሜሪካ ክፍለ ሃገር ያስተዳደራዊ መብቱን ያስጠበቀ መሆኑን ለመገንዘብ አለመቻልዎ፤
·         መኖሩን አላውቅም ብለው የካዱት ሀገረ ስብከት የተመሠረተው በእርሶ መሆኑን አለማገናዘብዎ፤
·         እንደ ክርቲያናዊ አባትነትዎ እርቅን ከመሻት ይልቅ የበላይነትንና በቀልን ምርጫ ማድረግዎ፤
·         የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ አካል ሆነው ያገለገሉትን የአቡነ አብሃምን ሥራ ጅምር ተከታትሎ ከማስፈጸም ይልቅ አብያተ ክርቲያናትን የሚበታትንና የእርስዎን ተቀባይነት የሚያሳጣ ተግባር መፈጸምዎ፤
·         ንበት /ቤት ማደራጃ መምሪያን ሳያነጋግሩ በሩን የሚመራ አባል ምርጫ እንዲደረግ ማድረግዎ፤
·         መንበረ ጵጵስናዬ ነው ብለው የሚሉት ደብረ ምሕረት ቤተክርስቲያን በገለለተኛ አስተዳደር ይልቁንም በእርሶ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር ያለ መሆኑን ምዕናን ማወቃቸው፤
·         እንደ ክርቲያናዊ አባት መምከርና ማወያየት ሲገባዎ ለልጅዎ (ልጆችዎ) የማስፈራሪያና ዛቻ የተሞላበት ደብዳቤ መጻፍዎ፤ ለዚያውም የግል መብቱን በመንካት። ለመሆኑ በአሜሪካ የአንድ በመንፈሳዊ ድርጅት ውስጥ እየ ያለ ሰው የግል መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እያወቁ ይሆን ይህንን ደብዳቤ የጻፉት።
·         ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ዛዝ ሳይሰጠዎ በራስዎ ልጣን ይህንን ሹመትና ክስ ማቀናበርዎ፣ ምንም ቢሆን ጸሐፊዎ የለየለት ማናፍቅ መሆኑን ቀደብ ተብሎ የታወቀ በመሆኑ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የልማት ክፍል በሃይማኖቱ ህፀፅ መባረሩን አለመገንዘብዎ፤
·         እንደ አቡነ ዘካርያስ ያሉ አባት በቅርብ እያሉ ከእርሳቸው ጋር መመካከርና ሁሉንም ክፍል እንዲያነጋግሩና በመንፈሳዊ ሥራ እንዲረዱዎት ማድረግ ሲገባዎ ለዚህ ሁሉ ብጥብጥ እና ትርምስ እርሶ ብቸኛው መፍትሄ መሆኑን እያወቁ ሰላምን አለመፈለግዎ፣ ቤተክርስቲያንን የብጥብጥ መድረክ እንድትሆን መፍቀድዎት፤
·         ሥርዓቷን፣ ቀኖናዋን፣ ትውፊቷን ሽቶ የመጣውን በቅድስት ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የተሰባሰበውን የክርስቲያኖች አንድነት አላውቅም ማለት ምን ማለት ነው? እርሶም እኮ እንደሚሉት ስደተኛ፣ መፃተኛ፣ ገለልተኛ የሚል የለም ከእንግዲህ ነበር እኮ ያሉት፣ ታዲያ በእናት ቤተክርስቲያን አስተዳደር ስር ያሉትን ምን ይሏቸዋል? ሌላው ቀርቶ ከነዚህ አጥቢያዎች የብጹዕነትዎን ስም ሳይቀር በሥርዓተ ቅዳሴው የሚያነሱ እንዳሉ ይነገራል። ለምን ቀርበው ማነጋገር ወይም ማግባባት አልቻሉም?
·         እንደ ቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ከሆነ የመጡት ለሁለት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንደመጡ እናውቃለን እርሶም ተናግረዋል፣ ታዲያ ለምን ሁለቱንም ጨፍልቆ የነበረውን ስም አጠራሩን እንኳ ለማጥፋት ለምን አስፈለገ?
·         በዚህ በሰሜን አሜሪካ ይልቁንም በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ገለልተኛ የሚለውን ስሙን ሳይቀር ያመጡት የሠሩት እርሶ እንደሆኑ ሁላችንም እናውቃለን፣ አሁንም እርሶ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንደመሆንዎ ይህንን ለቤተክርስቲያን የማይስማማ ስም "ገለልተኛ" ከነ ስም አጠራሩ ለማጥፋት ለምን ጥረት አላደረጉም?
·         በዚህ በመጨረሻ በሹመትዎት ላይ ብዙ ጥያቄ ያለባቸውን ሰዎች ይልቁንም የተወገዙም እንዳሉ ይነገራል፣ ለምን እነርሱን ወደ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለማስረጽ ሞከሩ፣ ቀጥተኛ አላማዎት ምንድነው? ላከበረቾት፣ ለክብር ላበቃችዎት ቅድስት ቤተክርስቲያን ራዕዮ ምንድነው?
·         ከተሾሙት አንዳንድ ካህናት ውስጥ በእምነት ማጉደል፣ በሴሰኝነት፣ እንዲሁም በተለያየ የሥነ-ምግባር ችግር ያለባቸው ሰዎች ሹመዋቸዋል፥ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ከነ ችግራቸው ከነ ጥፋታቸው ንሰሐ ሳይገቡ፣ ቀኖና ሳይቀበሉ እንዴት ከክርስቲያኖች ጋር መሥራት ይችላሉ? እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ቀሲስ ሰብስቤ፣ አባ ኃይለሚካኤል፣
·         በአንዳንድ በሚቀርብዎት ሰዎች ከዚህ በኃላ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱ ይነገራል "እኛ የፈለግነው ሥልጣኑን ነበር የፈለግነው፣ ከዚህ በኃላ ምን ቀረን" የሚል አነጋገር ይሰማል እውነት "የገለልተኛው ጳጳስ" ሆነው መቅረት ነው የሚፈልጉት?
እነዚህና ሌሎችም ቀደም በለው የተደረጉት ምንኛ እርስዎን ሊጎዱዎት እንደሚችሉ አስቀድመው ማወቅ ይጠበቅበዎት ነበር።

ለምእመናን የሚሆን መልእክት።

ሀ. አቡነ ፋኑኤል የተላኩት በቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን ሁላችንም እንስማማለን። 
ለ. ቅዱስ ሲኖዶስም የላካቸው አቡነ አብርሃምን ለመተካት ነው። በዚህም እንስማማለን። 
ሐ. ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ በአቡነ አብርሃም አባታዊ መሪነት የተመሠረተ ሀገረ ስብከት እንዳለ ጠንቅቆ ያውቃል።
መ. ታዲያ ብፁዕነታቸው አቡነ ፋኑኤል ጽ/ቤቱን እንደመጡ መረከብ የለባቸውምን?
ሰ. ለምንድንስ አቡነ አብርሃምን በአካል ተገናኝተው ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ አላነጋገሩም?
ረ. እነዚህ አባቶች ሁለቱም የቅዱስ ሲኖዶስ አካል ሲሆኑ ስለምን ሲባል አንደኛው እጅ የሰራውን ሌላው ያፈርሰዋል፥ አንዱን አስተዳደር አንዱ ይበትናል። 

           እንደኔ አስተያት የችግሩ መንስኤም መፍትሔውም እርሶ ነዎት። ስለዚህ እባክዎትን ይንቁ፤ ችግሩ እርሶ ወይም መካሪዎችዎ እንደሚሉት ቀላል አይሆንም፥ ነገር ግን ለክብር ስላበቃችዎት ቤተክርስቲያን ሲሉ፣ ስለ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሲሉ ችግሩን ይረዱ በማስተዋልና በጸና እምነት ሆነው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነትን ይጠብቁ በጎችንም በመልካም መስክ ያሰማሩ። ንጽይት፣ ርትዕይት የሆነችውን ሃይማኖታችንን ዘመኑ ከፈጠራቸው ተረፈ አርያሳዊያን ይጠብቁት፣ ቅዳሴው ረዘመ፣ ጾም በዛብን፣ ስግደት በዛብን፣ እያሉ የፕሮቴስታንት እምነታቸውን በኦርቶዶክሳዊ እምነታችን ላይ የሚያመጡትን መንጥረው ያውጡዋቸው ነገ ትውልድ ሊወቅሶት እንደሚችል አይርሱ፥ በሌላ በኩል ደግሞ አንባቢው የአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነት ተከታዮች አባል ከሆኑ፤ ነቃ ይበሉ በከፍተኛ ማስተዋል በእምነትዎ ይጽኑና አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነትን ይጠብቁ። ጠላታችን የጥቅም ጥያቄ ነው (ውስ ተሃድሶ) እንጂ እነ ግራኝ መሃመድ ተመልሰው አልወረሩንም። እድሳት የማትሻ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነትን እንጠብቅ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር 

 

No comments:

Post a Comment