የተወደዳችሁ ምእመናን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደዘመነ ማቴዎስ አሸጋገራችሁ!
እንዴት መኖር እንዳለባቸው ሲመክራቸው ደግሞ‹‹እንደጥበበኞች›› በጥበብ መመላለስ እንደሚገባቸው፤ ዳግመኛም‹‹በጥንቃቄ›› እና ‹‹በመጠበቅ›› እየኖሩ ዘመኑን እንዲዋጁአሳስቧቸዋል፡፡ (ኤፌ5.15-16) እነዚህ ቁም ነገሮች ለጊዜውበኤፌሶን ላሉ ምእመናን ቢጻፉም ለሁላችን ምክር እና እዝናትየሚሆኑ ናቸውና በየተራ እንመለከታቸዋለን!
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን ለሚገኙ ምእመናንመጪው ጊዜ ምን እንደሚመስል ከገለጠላቸው በኋላ አያይዞእንዴት መኖር እንዳለባቸው መክሮአቸዋል፡፡ ስለመጪው ጊዜሲነግራቸው ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና›› ብሏቸዋል፡፡
ዘመነ ሰላም ያድርግልን 2005 |
‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው›› ማለት ምን ማለት ነው? የቀንክፉ አለን? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ ክፋት አስቦናፈቅዶ በሚበድል በሰው ልጅ ዘንድ እንጂ በቀናት ዘንድ ክፋትየለም፡፡ ዕለታትን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስእንደሚነግረን ደግሞ ‹‹እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካምነው›› (1ጢሞ4.4) ስለዚህ ዕለታት በሙሉ በተፈጥሮ አንድናቸው፤ እንዲሁም ሁሉም መልካም ናቸው፡፡
የዕለታት መልካቸው የሰው ልጅ ምግባር ነው፡፡ የሰው ሥራ ክፉየሆነ እንደሆነ ዕለታትም ይከፋሉ፡፡ ሰው መልካም ሲሆን ዘመናቱመልካም ይሆኑለታል፡፡ ሐዋርያው በዕለት አንጻር የሰውን ክፉነትሲነግረን ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች›› ናቸው አለን፡፡ በጸሎተ ቤተክርስቲያን ‹‹እግዚኦ አድኅነነ እምዕለት እኪት ወባልሃነ እምኩሉመንሱት›› - ‹‹አቤቱ ከክፉ ቀን ከፈተናም ሁሉ ፈጽመህአድነን፡፡›› የሚል ኃይለ ቃል እናገኛለን፡፡ አበው ካህናት ሲያሳርጉ‹‹ከዕለት እኪት ከዘመን መንሡት ይሰውረን!›› የሚሉት እነዚህንየቅዱሳት መጻሕፍት ኃይለ ቃላት መሠረት አድርገው ነው፡፡ የሰውልጅ ምግባር ሲከፋ ዘመናቱ ክፉዎች የሚሆኑት ዕለታትየተፈጠሩት ለሰው ልጆች ጥቅም ስለሆነ ነው፡፡ ‹‹ሰንበት ስለ ሰውተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም›› እንዲል፡፡(ማር2.27) ሐዋርያውም ቀኖች ለሰው የተፈጠሩ መሆናቸውንበሚጠቁም ቃል ‹‹ቀኖቹ›› ማለቱን ልብ እንበል፡፡ ‹‹ቀኖቹ››ያለው የሰው ልጅ ቀኖች ለማለት ነውና፡፡ ስለዚህ ዕለታት ለሰውልጅ መጠቀሚያነት እስከተፈጠሩ ድረስ ሰው ሲያበላሻቸውይበላሻሉ ማለት ነው፡፡ ሰው ምግባሩን ሲያከፋ ዕለታት እየከፉየሚሄዱት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ሰው መልካም ሲሁንም‹‹ቀኖቹ›› መልካም ይሆኑለታል፡፡
መጪው ጊዜ
ነቢዩ ዳንኤል እንደተናገረው ዘመን እየገፋ በሄደ ቁጥርዕውቀት ይበዛል፡፡ ሥልጣኔም ይሰፋል፡፡ (ዳን12.4) ይሁን እንጂበሥነ ምግባር ደረጃ የሰው ልጆች ክፋት እየጨመረና በምድር ላይኃጢአት በምልዓት እየተፈጸመ ይመጣል፡፡ ስለዚህ ይህን እውነትበትንቢት መነጽር የተመለከተው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ቀኖቹ ክፉዎችናቸው›› ማለቱ የሚገባ ነው፡፡
አምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ከዚህ ሐሳብ ጋር የሚስማማ ነገርአስቀድሞ ተናግሯል፡፡ በመጨረሻዎቹ ዘመናት እምነት በሰው ልጅዘንድ ጎደሎ እንደሚሆን በተጠየቅ መንገድ ‹‹ነገር ግን የሰው ልጅበመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?›› ሲል ተናግሯል፡፡(ሉቃ18.8) እንዲሁም በሰው ልጆች መካከል ፍቅርእንደሚቀዘቅዝ ‹‹ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅርትቀዘቅዛለች፡፡›› በማለት ከነምክንያቱ አስቀምጦልናል፡፡(ማቴ24.12) ይህ በግልጥ የሚታይ እውነት ስለሆነ ምስክርምአያስፈልገውም፡፡ እንግዲህ በመጪዎቹ ዘመናት እምነትና ፍቅርበሰው መሃል ካልተገኙ የሰው ልጅ ለበጎ ምግባር ምን መነሻይኖረዋል? ከፍቅርስ የሚበልጥ ምን ምግባር ይኖረዋል? እንዲህስከሆነ ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው›› መባሉ ተገቢ አይደለምን?
ቀኖቹ ክፉዎች መሆናቸው እና የሰው ልጆች መንፈሳዊ ደረጃእየዘቀጠ የሚሄድ መሆኑን ከራሳችን የግል ሕይወት በመነሣትመረዳት የምንችለው ነው፡፡ አብዛኞቻችን ለመንፈሳዊ ነገር ያለንትጋት ስንጀምር እንዳነበረን አይሆንልንም፡፡ መንፈሳዊ ኑሮ ጀማሪክርስቲያን ከጳጳስ ይበልጣል እንደሚባለው እየሆነብን የምንቸገርብዙዎች ነን፡፡ ስንጀምር የነበረን ለጸሎት ማልዶ መነሣት፣ ዘወትርቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ በሱባኤ ወራት ወደገዳማት ሄዶ ደጅመጥናት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ፣ ቃለ እግዚአብሔርንበመመሰጥና በድስታ ማዳመጥ፣ ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንመጠንቀቅ፣ ንስሐ መግባት፣ ሥጋ ወደሙ መቀበል፣ ወይምከመንፈሳዎ ምሥጢራት ስለ መራቃችን መቆጨት ከውስጣችንሙጥጥ ብሎ ያለ ይመስላል፡፡ በምትኩ ተስፋ መቁረጥ፣ ድንዛዜስንፍና እና ልዩ ልዩ የኃጢአት ልምምዶች ልባችንን አጣበውታል፡፡ታዲያ በእኛ ውስጥ የምንመለከተው ይህ ሁኔታ በብዙ ሰዎች ዘንድመኖሩን በተደጋጋሚ ስንሰማ ዘመኑ እየከፋ መምጣቱንአይነግረንምን?
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው›› በማለት ብቻአላበቃም፡፡ በሌላ ክፍል ‹‹ነገር ግን በመጨረሻው ቀንየሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ ዕወቅ፡፡›› እያለ መጪው ጊዜምን እንደሚመስል ከነምክንያቱ ጽፏል፡፡ (2ጢሞ3.1) መጪውጊዜ አስጨናቂ የሚሆነው ሰዎች ‹‹ራሳቸውን የሚውዱ፣ ገንዘብንየሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸውየማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ቅደስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ዕርቅን የማይሰሙ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፣ ችኩሎች፣ በትዕቢትየተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ›› ሰለሚሆኑእንደሆነ አያይዞ ይናገራል፡፡ ሐዋርያው የቀኖቹን ክፉነት ብቻሳይሆን እኛ ከዚህ ሁሉ ለመዳን ምን ማድረግ እንዳለብንምጠቁሟልና ያንን ቀጥለን እንመለከታልን፡፡
1ኛ. ዘመኑን መዋጀት
ሐዋርያው ‹‹ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ›› ብሎናል፡፡ዘመንን መዋጀት ማለት ምን ማለት ነው ዘመኑን መዋጀት ማለትዘመኑን መግዛት፣ ድል ማድረግ፣ ማሸነፍ፣ የራስ ማድረግ፣ ዘመኑንመቅደም እንጂ በዘመን አለመቀደም… ወዘተ ማለት ነው፡፡ዘመንዘመናት የሚባሉት የሚመጡት አዳዲስ ዓመታት ብቻ አይደሉም፡፡ያለፈውም ጊዜ የዘመን አካል ነው፡፡ ስለዚህ ዘመንን መዋጀትስለሚመጣው ብቻ ሳይሆን ስላለፈውም መመርመር፣ ታሪክንበሚገባ ማወቅ፣ ካለፈው መማርና ለወደፊቱ መጠንቀቅ ነው፡፡ያለፈውን ዘመን ካልመረመርነው ዘመንን ዋጀን አይባልም፡፡የሚመጣውን ብንዋጅ ያለፈውን ዘመን ካልዋጀን ዘመኑን ዋጀንሊባል አይቻልም፡፡ በተጨማሪም ዘመኑን መዋጀት ማለት ዘመንያፈራውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማወቅና መጠቀም ማለት ብቻአይደለም፡፡ ከዚህም የሚሰፋ ሐሳብ ያለው ነው፡፡
ዘመኑን መዋጀት ማለት በእያንዳንዱ ቀን ፈተናዎችንእንደየአመጣጣቸው እየለዩ መመከት ማለት ነው፡፡ የሰው ልጆችጥንተ ጠላት ሰይጣን ዓለምን ማርኮ ለመግዛት ብዙ አሳሳችመንገዶችን ይጠቀማል፡፡ አዳምንና ሔዋንን የፈተነው አምላክነትንእንዲመኙና ዕፀ በለስን እንዲበሉ በማድረግ ነው፡፡ ኢዮብንየፈተነው ያለውን ሁሉ በማውደም እና በሽታ ላይ እንዲወድቅበማድረግ ነው፡፡ እስራኤልን የወርቅ ጥጃ እንዲያመልኩስቧቸዋል፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስምበዲያብሎስ ተፈትኗል፡፡ የፈተናው መንገድ ግን ከተዘረዘሩትበእጅጉ ይለያል፡፡ ስለዚህ ሰይጣን የሚፈትነን እንደዘመናችንስለሆነ ዘመኑን ካልዋጀን ፈተናውን ማለፍ አንችልም፡፡ስለዚህሐዋርያው እንደመከረን ‹‹መጠንቀቅና›› ራሳችንን ‹‹መጠበቅ››አለብን፡፡ ‹‹መጠንቀቅ›› ካላወቅነው፤ ነገር ግን ሊሆን ይችላልብለን ከምንገምተው ክፉ ነገር ሁሉ ራስን ለማዳን መሽቀዳደምሲሆን ‹‹መጠበቅ›› ደግሞ ክፉ መሆኑን ከተረዳነው ነገር ሁሉእንዳይጎዳን የምናደርገውን ጥረት ያመለክታል፡፡ (ኤፌ5፦5)
2ኛ. በጥበብ መመላለስ
ጥበብ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ተብሎ በሁለት ይመደባል፡፡ ወይምበቅዱስ ያዕቆብ ገለጻ መሠረት ሰማያዊ እና ምድራዊ ጥበብይባላል፡፡ (ያዕ3.15-17) የመንፈሳዊ ጥበብ መነሻው ሃይማኖትነው፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹የጥበብ መጀመሪያእግዚአብሔርን መፍራት ነው›› ይላልና፡፡(መዝ1)0፥0) እግዚአብሔርን መፍራት ደግሞ በሃይማኖትይተረጎማል፡፡ ምክንያቱም በዓይነ ሥጋ ያላዩትን እግዚአብሔርንኃጢአት ብሠራ ይፈርድብኛል ብሎ መፍራት ራሱ ሃይማኖትነውና፡፡ ስለዚህ የጥበብ መጀመሪያ ሃይማኖት መሆኑን በዚህእናውቃለን፡፡ እንዲህ ከሆነ በጥበብ መመላለስ ማለት ደግሞበሃይማኖት መመላለስ ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም በጥበብ መመላለስ ማለት በዚህች ዓለም ማታለልናክፉ አሠራር እንዳይያዙ በዘዴ፣ በዕውቀት፣ በማስተዋል፣በብልሃትና በፈሊጥ መመላለስ ማለት ነው፡፡
በሃይማኖት መመላለስ ከክፉ ሁሉ ይሰውራል፡፡ እውነተኛ የልብእምነት ክፉውን ሁሉ ይመክታል፡፡ ‹‹ዓለምንም የሚያሸንፈውእምነታችን ነው›› ተብሎ እንደተጻፈ ሃይማኖት ያለው ሰውበምንም በማንም አይሸነፍም፡፡ (1ዮሐ5፥4) ስለዚህ በዚህ ዘመንሃይማኖታችንን ጠበቅ አድርገን መያዛችን ለአሸናፊነታችን ዋስትናነው፡፡
3ኛ. ከክፉ መሸሽ
አብዛኞቻችን በጎ ዘመን ላይ ደርሰን በሰላምና በደስታለመኖር የምንጓጓውን ያህል ለዚህ የሚያበቃውን መስፈርት ግንለማሟላት ስንደክም አንገኝም፡፡ ወደፊት በመልካም ለመኖርየሚጠበቅብን ነገር አለ፡፡ ለዚህም ቅዱስ ዳዊት የተናገረውን ልብእንበል፡፡ አስቀድሞ ‹‹ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማነው? በጎንምዘመን ለማየት የሚወደድ?›› ሲል ይጠይቃል፡፡ መቼም ለዚህጥያቄ እኔ እፈልጋለው ብሎ መልስ የማይሰጥ አይኖርም፡፡ ቀጥሎማሟላት የሚገባን ነገር መኖሩን ‹‹አንደበትህን ከክፉ ከልክል፡፡ከንፈሮችህም ሽንገላን ሽንገላን እንዳይናገሩ ከክፉ ሽሽ መልካምንምአድርግ ሰላምን እሻ ተከተላትም›› ሲል ይጠቁመናል፡፡(መዝ33.12-14) ስለዚህ በአጭሩ ከክፉ መሸሽና መልካምማድረግ የወደፊት መንገዳችንን እና መጪውን ዘመን ብሩህያደርግልናል፡፡ መልካም አኗኗር ከውስጣችን የሚፈልቅ እንጂበግዢ የሚገኝ ቁስ አይደለምና፡፡ ደስተኛና ሰላማዊ ኑሮ መኖርከፈለግን ምግባራችንን እናስተካክል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹መልካምብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን?›› ብሎአልና፡፡ (ዘፍ4.7)መልካም ከሠራን ፊታችን ይበራል፡፡ ዘመኑም መልካምይሆንልናል፡፡ እንጂ መልካም አዲስ አመት ስለተባባልን ብቻ ዘመኑመልካም እንደማይሆንልን እንረዳ! በጎ መመኘታችን እንደተጠበቀሆኑ በጎ ለመሥራት አሁኑኑ እንነሣ!
ከዕለት እኪት ከዘመን መንሡት ይሰውረን!አሜን!
መልካም አዲስ ዓመት ያድርግልን!
በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment