የውይይት መድረክ ዋልድባን ለመታደግ በሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ኮሜቴ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በAug. 12, 2012
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ኮሚቴ ይህንን ማስተዋቂያ ልከውልናል እኛም መልዕክቱን በማድረስ ግዴታችንን ለመወጣት እንደሚከተለው አቅርበንዋል መልካም ንባብ።
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
“. . . በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ . . .” ሉቃስ ፲፫ ፥ ፳፬
በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ለምትኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን በሙሉ፥
ጉዳዩ: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ እየተከሰተ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ለመነጋገር እና ለመወያየት፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ታሪክ ማኅበራዊና ሥነ- ጥበብ እድገት ያበረከተችው አስተዋጽዖ ከኢትዮጵያ አልፎ በመላው ዓለም የሚታወቅ አውነታ ነው ። ቤተ ክርስቲያናችን ባላት ታሪክና መንፈሳዊ ሀብት ለበርካታ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ትልቁን ድርሻ የምትይዝ ሲሆን በዚህም መንግሥትንና የተለያዩ ተቋማትን ተጠቃሚ እያደረገች ስትገኝ ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶችም በዋነኛነት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥንታዊያን ገዳማት አድባራት እና እንደ ጥምቀት መስቀል/ደመራ/ እና ልደት የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት መንፈሳዊ አከባበርን ለመመልከት እንደመጡ ዘወትር የሚመሰክሩት ነው ። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ ጥበብ እድገት ያበረከተችውን አስተዋጽዖ በየትኛውም ዘመን የነበረ እና ወደፊትም የሚኖር እንደሆነ ማንም ኢትዮጵያዊ የሚመሰክረው እውነታ ነው።
እንደሚታወቀው ቅድስት ቤተክርስቲያን በበርካታ ችግሮች ከውስጥና ከውጪ እየተፈተነች ትገኛለች፥ በችግሮቹ ዙሪያ ለመወያየት እና ዘላቂ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመፈለግ እና ለመወያየት በዋሽንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር ከ4:00 PM. ጀምሮ በሚከተለው አድራሻ ተገናኝተን እንድንወያይ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እያቀረብን፥ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ችግር ተነጋግሮ መፍትሄ መሻት የሁላችንንም ተሳትፎ ይጠይቃልና። እርስዎም የበሉልዎን አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። በዚህ ጉባኤ ላይ ሊቃውንት ቤተክርስቲያን፣ መምህራን፣ ዘማሪያን እንዲሁም ምሁራን ተጋብዘዋል፥ ኑና የበኩልዎን ያበርክቱ።
ቀንና ሰዓት
ነሐሴ ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. (August 12, 2012) ከ 4:00 PM. ጀምሮ
አድራሻ:
St. George Church Ballroom
4335 16th Street NW.
Washington, DC 20011
savewaldba@gmail.com
የበለጠ መረጃ ቢያስፈልግዎ
571-224-2869 ወይም 571-299-0975 ይደውሉ
PO Box 56145 Washington, DC 20040
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment